Sinksar tube(ስንክሳር)
Kanalga Telegram’da o‘tish
እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
2 981
Obunachilar
-224 soatlar
+507 kun
+18430 kun
Postlar arxiv
2 988
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ገዳማዊ "ቅዱስ አባ ባውላ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ አባ ባውላ መስተጋድል +"+
=>ቅዱሱን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::
+ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን (ኃጣውዕን) ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::
+በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: ታላቁ አባ ባውላ ገዳማዊ ጻድቅ እንደ መሆኑ ትግሉ የነበረው ከአጋንንት ጋር ነው:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::
+ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ (ቀዝቃዛ) በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::
+ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::
+ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታ "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" (ማቴ. 16:24) እንዳለው: ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::
+ታላቁ አባ ባውላ የተወለደው በላይኛው ግብጽ አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከክርስቲያን ወላጆቹ መንፈሳዊ ነገሮችን ተምሮ በወጣትነቱ መንኗል:: ያ ዘመን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን የነበሩበት ነውና ወደ ጠመው አካባቢ ሔዶ ምናኔን ተምሯል::
+ሥርዓተ ገዳምን ማለትም:- አገልግሎትን: ፍቅርን: ተጋድሎንና የመሳሰሉትን ከተማረ በሁዋላም ደቀ መዝሙሩን አባ ሕዝቅኤልን አስከትሎ ለዋናው የተጋድሎ ሕይወት ወደ በርሃ ወጣ:: አባ ባውላ ዘወትር በፍቅረ ክርስቶስ ይመሰጥ ነበርና የተጋድሎ ምርጫው ልዩ ሆነ::
+አንድ ቀንም እንዲህ ሲል አሰበ:- "ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ለኃጥአን ኃፍረተ መስቀልን ታግሠህ: ሞትን ከሞትክልን እኛ ደግሞ ስለ ንጹሑ አምላክ ስንል እልፍ ሞትን መታገስ አለብን::"
+ይህንን ብሎ ከወትሮው በተለየ መንገድ ሊጋደል ጀመረ:: በዚህ እጅግ የጸና ተጋድሎው ምክንያትም 7 ጊዜ ሙቶ 7 ጊዜ ተነሳ::
1.እግሩን ከረዥም ዛፍ ላይ አስሮ: ወደ ታች ተዘቅዝቆ ይጸልይ ጀመረ:: እህልም: እንቅልፍም: ዕረፍትም አልነበረውምና ደሙ በአፍ: በአፍንጫው ፈሶ አለቀ:: እንዲህ በሆነ በ40ኛው ቀንም ሞተ:: መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ ከሞት አስነሳው::
2.ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ እንዳስለመደ ይጸልይ ጀመረ:: ከባሕሩ ሳይወጣ: ከቆመ ሳያርፍ: ከዘረጋም ሳያጥፍ ለ40 ቀናት ጸለየ:: በዚያው ሳለም ለ2ኛ ጊዜ ሞተ:: ቅዱስ መልአክ መጥቶ ከሞት አስነሳው::
3.እርሱ በሚኖርበት ጠመው አካባቢ ረዥም ተራራ ነበርና ወደዚያ ወጣ:: ከተራራው ጫፍ ሆኖ ወደ ታች ተመለከተ:: የተጠራረቡ ድንጋዮች በየመንገዱ ተሰልፈው ነበር:: በዚያች ቅጽበት የጌታ ኅማማት ከፊቱ ቢደቀንበት ከላይ ወደ ታች ተወርውሮ ሔደ::
በየመንገዱ ያሉት ጥርብ ድንጋዮች ቢቀበሉት አካሉ እየተነተፈና እየተቆራረጠ በየመንገዱ ቀረ:: በዚህም ሞተ:: አሁንም ፈጣሪው ከሞት አስነሳው::
4.አንድ ቀን ደግሞ (ዕለቱ ዓርብ ነበር) የጌታን ኅማማት እያሰበ የሚያደርገው ጠፋው:: ከቆመበት አካባቢ ትልቅ ዛፍ ነበርና ወደዚያ ወጥቶ ሲመለከት ከመሬት ላይ የተነጠፈ ትልቅ ድንጋይ አየ:: ከላይ ወደ ታች ሲወድቅና ድንጋዩ ላይ ሲያርፍ ለሁለት ተከፍሎ ሞተ:: አሁንም በፈጣሪ ትዕዛዝ ተነሳ::
5.በሌላ ቀን ደግሞ በዕለተ ዓርብ ጭንቅላቱን ከእግሩ ጋር አሥሮ ይጸልይ ገባ:: ያለ ምንም እህል: ውሃና እንቅልፍ ለ40 ቀናት ቆይቶ ሞተ:: እንደገናም ተነሳ::
6.እጅግ ሊመለከቱት እንኩዋ በሚከብድ የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ገብቶ ለ40 ቀናት እጆቹን ዘርግቶ ቢጸልይ ከጭንቁ ብዛት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች::
7.አንድ ቀንም እንደዚሁ የጌታን ሕማማት እያሰበ ወደ ጽኑ ቆላ ወረደ:: በአካባቢው ከአሸዋ በቀር ምንም አልነበረምና ቆሞ ሲጸልይ አሸዋው ውጦ ደፈነውና ለ7ኛ ጊዜ ሞተ:: በዚህ ጊዜ ግን ሊያስነሳው የመጣው እንደ ወትሮው ቅዱስ መልአክ ሳይሆን ራሱ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ ነበር::
+ጌታችን አባ ባውላን ከሞተበት አስነስቶ:- "ወዳጄ ባውላ! ስለ እኔ ፍቅር እጅግ ተሰቃየህ" አለው:: ቅዱሱ ግን "ጌታየ ሆይ! የእኔ መከራ በአንተ መከራ ሲታሰብ ኢምንት ነውና እባክህ ስለ ስምህ ሌሎች መከራዎችን እንድቀበል ፍቀድልኝ? ገና ሕማምህን አስቤ አልረካሁምና" አለው::
+ጌታ ግን "የለም! መከራው ይበቃሃል:: መጥቼ እስክወስድህ ድረስ ከአባ ብሶይ ጋር ቆይ" ብሎት: ባርኮት ዐረገ:: አባ ባውላም እንደ ታዘዘው በአባ ብሶይ ገዳም ከቅዱስ ብሶይ ጋር ቆይቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::
+ይህቺውም ዕረፍቱ ለ8ኛ ጊዜ ሆና ተቆጥራለች:: የቅዱሱን ዜና የጻፈው ደቀ መዝሙሩ አባ ሕዝቅኤል ሲሆን ያሰፈረው እንባው እንደ ዥረት እየወረደ ነው:: አባቶቻችን ሊቃውንትስ ታላቁን ጻድቅ ሲያመሰግኑት እንዲህ አይደለምን!
"ውስተ ገድል ጽኑዕ ዘአልቦ ምምዐ:
ወደቀ ስብአ: ወተንሳእከ ስብአ::"
=>አምላከ አባ ባውላ በጻድቁ ላይ ያሳደረውን ፍቅሩን ያሳድርብን:: ከበረከቱም ያድለን::
=>ጥቅምት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ባውላ መስተጋድል
2.አባ ሕዝቅኤል ጻድቅ
3.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ሐናሲ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ: ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? +"+ (ማቴ. 16:24)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2 988
Repost from Sinksar tube(ስንክሳር ቲዩብ)
3.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ (ዕን. ከ1 - 3 ያንብቡ)
4.ቅድስት ሐና ነቢይት (የሳሙኤል እናት - 1ሳሙ. ከ1 - 2ን ያንብቡ)
5.ቅዱሳን ኡሲፎርና ኡርያኖስ (ሰማዕታት)
6.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮዽያዊ (ፍልሠቱ)
7.ቅዱስ ሄኖስ ነቢይ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና
እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
=>+"+ ምንም እንኩዋ በለስም ባታፈራ:
በወይን ሐረግም ፍሬ ባይገኝ:
የወይራ ሥራ ቢጐድል:
እርሾችም መብልን ባይሰጡ:
በጐች ከበረቱ ቢጠፉ:
ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ:
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል:: በመድኃኒቴ
አምላክ ሐሴት አደርጋለሁ:: +"+ (ዕን. 3:17)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2 988
Repost from Sinksar tube(ስንክሳር ቲዩብ)
🌻✝✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ጥቅምት ፮ (6) ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ" ወአባ "ዸንጠሌዎን" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ ሊቅ +"+
=>በዘመነ ሐዋርያት ከነበሩና አስደናቂ ታሪክ ከነበራቸው
ቅዱሳን አንዱ ይህ አባት ነው:: ቅዱስ ዲዮናስዮስ
በትውልዱ አረሚ (ግሪካዊ) የሆነ ፈላስፋ: ከነ አሪስቶትል
ሲያያዝ የመጣውን ፍልስፍና ጨርሶ በማጥናቱ ርዕሰ
ሊቃውንት (የፈላስፎች አለቃ) የሚል ስም ተሰጥቶት
ነበር::
+በግሪክ አቴና (ATHENS) ለነበሩ ፈላስፎችም ሁሉ
የበላይ ሲሆን በአርዮስፋጐስ (ሐዋ. 17) ታላቁ ሰው
እርሱ ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እድሜው ገና ወጣት
ነበር:: ቅዱስ ዲዮናስዮስ ፈላስፋ ስለ ሆነ ቅሉ
ይመራመር ነበር::
+ይልቁኑ ስለ እውነተኛው አምላክ ያስብ ነበር:: በግሪክ
ምድር ከሚመለኩ 250 አማልክት መካከል ቁም ነገር
አልተገኘምና:: ነገር ግን አንድ ቀን ዓለም በተፈጠረች
በ5,534 ዓመት: መጋቢት 27 ቀን: በዕለተ ዓርብ: 6
ሰዓት ላይ ምድር ተናወጠች:: ፀሐይ ጨለመች: ጨረቃ
ደም ሆነች: ከዋክብትም ረገፉ::
+በዚህ የተደናገጡ የአቴና (ATHENS) ነዋሪዎችና
ፈላስፎች ወደ ዲዮናስዮስ ተሰብስበው "መምሕራችን
የተፈጠረውን ነገር መርምረህ አስረዳን" አሉት::
+ዲዮናስዮስም ባለው ጥበብ ባሕሩን: የብሱን: ፀሐይ:
ጨረቃን: ከዋክብትን መረመራቸው:: "ወረከቦሙ
ኅዱዓነ" እንዲል በቀደመ ቦታቸው አገኛቸው:: ግራ
ቢገባው እንቅልፍ ከዐይኑ ተከለከለ::
+ከዚያም ወደ ቤተ መዛግብቱ ገብቶ መጻሕፍትን
ሲያገላብጥ "አርስጣላባ" የሚባል ግዙፍ መጽሐፍ
አግኝቶ ቢገልጠው "እልመክኑን" የሚል ጽሑፍ አገኘ::
ወደ ውጪ ወጥቶ በሕዝቡና ጠቢባኑ ፊት ልብሱን ቀድዶ
አለቀሰ::
+እነርሱም ደንግጠው "ምነው መምሕራችን? ምን
ሆንህ?" ቢሉት "የማይታየው አምላክ ቢወርድ
በምቀኝነት ገደሉት የሚል ጽሑፍ አገኘሁ" አላቸው::
"እልመክኑን" ማለት "የማይታይ አምላክ" ማለት ነውና::
"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ:
እሳት በላኢ አምላክነ" እንዲል::
+ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዛሙርቱን (ተማሮቹን) ጠርቶ
(ኡሲፎስና ኡርያኖስ ይባላሉ) "እልመክኑን" የሚለውን
ስም "ከቤተ ጣዖቱ በር ላይ ለጥፉት" ብሏቸው
ለጠፉት:: በእንዲህ ያለ መንገድ 14 ዓመታት አልፈው
ቅዱስ ዻውሎስ ወንጌልን እየሰበከ አቴና ደረሰ:: ዘመኑም
በ48 ዓ/ም ነበር::
+ወደ ከተማዋ ሲገባ በጣዖት ቤቱ በር ላይ
የተለጠፈውን ጽሑፍ ተመለከተና ያስተምራቸው ያዘ::
ትምሕርቱን የሰሙ ጠቢባኑና ሕዝቡ ሐዋርያውን ይዘው
ወደ ዲዮናስዮስ ፊት አቀረቡት:: "ምንድን ነው በደሉ?"
ቢላቸው "አዲስ አምላክን ሲያስተምር አግኝተነዋል"
አሉት::
+ቅዱስ ዻውሎስም "እኔ አዲስ አምላክን
የምሰብክላችሁ አይደለሁም:: ይልቁኑ ከቀድሞም
የፈጠራችሁ: ቀጥሎም የሞተላችሁ: እናንተም
"እልመክኑን" ብላችሁ ሳታውቁት ታመልኩት የነበረውን
ጌታ እንጂ:: እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አላቸው::
+ዲዮናስዮስም ቅዱስ ዻውሎስን "ለዚህ ምን ምልክት
አለህ?" ቢለው "የዛሬ 14 ዓመት: መጋቢት 27 ቀን:
በዕለተ ዓርብ 6 ሰዓት ላይ ታላላቅ ተአምራት የተደረጉ
አይደለምን! እነዚህ ሁሉ የተደረጉት በስቅለቱ ጊዜ ነው"
ሲል መለሰለት::
+ዲዮናስዮስም ፈጥኖ በክርስቶስ አመነ:: የአካባቢው
ጠቢባንና ሕዝቡም አምነው ከመሪያቸው ጋር ተጠመቁ::
ቅዱስ ዻውሎስም ቅዱስ ዲዮናስዮስን አስተምሮ የአቴና
የመጀመሪያው ዻዻስ አደረገው:: ቅዱሱም ክርስቲያኖችን
ያበዛ: መንጋውንም ያጸና ዘንድ ብዙ ተጋ::
+በተለይ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ታዋቂ
ደራስያን አንዱ ሆነ:: በርካታ ድርሰቶችንም በመንፈስ
ቅዱስ ደረሰ:: ዛሬ ድረስ እንኩዋ ሃይማኖተ አበው
ውስጥ የሚገኘው ድርሰቱ (ዘዲዮናስዮስ) ጣዕሙ ልዩ
ነው:: ቅዱሱ ለብዙ ዘመናት ለወንጌል አገልግሎት
ተግቶ: በዚህች ቀን የአካባቢው አገረ ገዥ አንገቱን
አስቆርጦት ሰማዕት ሆኗል::
+የሚገርመው ግን ሲገድሉት በቦታው ሰው ስላልነበረ
ቅዱሱ ተነስቶ: ተቆርጣ የወደቀች ራሱን አነሳት:: በጐኑ
አቅፎም ደቀ መዛሙርቱ እስካሉበት ሒዶ በፊታቸው
ዘንበል አለ:: ምዕመናንም እያለቀሱና እየዘመሩ
ከአርድእቱ ኡሲፎስና ኡርያኖስ ጋር ቀብረውታል::
እነርሱም አብረውት ተሰይፈዋልና::
+"+ አባ ዸንጠሌዎን ዘጾማዕት +"+
=>ታላቁ ጻድቅ: ሰባኬ ወንጌልና ገዳማዊ አባ
ዸንጠሌዎን የተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መሪ (አባት)
ናቸው:: ጻድቁ ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ቢሆንም
ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ነው::
+ወላጆቻቸው በሮም ቤተ መንግስት የቀኝ መንበር
ያላቸው ክቡራን ቢሆኑም ልጃቸውን ይማር ብለው ወደ
ገዳም ከተቷቸው:: በገዳም ትምሕርቱን ከጠነቀቁ
በሁዋላ በዚያው ጠፍተው ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያም
መነኮሱ::
+እድሜአቸው እየገፋ ሲሔድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት
8ቱን ቅዱሳን ሰብስበው: በአቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
መሪነት ወደ ሃገራችን መጡ:: በ470ዎቹ አካባቢ
የነበረው ንጉሥ አልዓሜዳም በክብር ተቀብሎ አክሱም
ውስጥ "ቤተ - ቀጢን" የሚባል ቦታን ሰጣቸው::
+ዘጠኙ ቅዱሳን በአንድነት: ቀን ቀን ወንጌልን
ሲያስተምሩ ውለው ሌሊት ሲጸልዩና መጻሕፍትን
ሲተረጉሙ ያድሩ ነበር:: ነገር ግን ለየብቻቸው
መኖራቸውን መንፈስ ቅዱስ ስለ ወደደ ሁሉም
በየራሳቸው ገዳማትን መሠረቱ::
+አባ ዸንጠሌዎንም ከአክሱም ከተማ በላይ ከደብረ
ቆናጽል ጐን ወደ ሚገኝና 'ጾማዕት' ወደ ሚባል ረዥም
ተራራ ወጡ:: ቦታው ዛሬ "እንዳባ ዸንጠሌዎን" ይባላል::
በዚያም አስቀድመው ለወንጌል አገልግሎት እየተጉ
ድውያንን ፈወሱ::
+ሙታንን አስነሱ: አጋንንትን አሳደዱ:: ብዙ ተአምራትንም
አደረጉ:: እንዲያውም አንድ ቀን ወይራውን በጧት
ተክለው: በሠርክ ትልቅ ዛፍ ሆነላቸው:: ከዚያ ዘንጥፈው
እሳቱን በቀሚሳቸው ላይ አፍመው ማዕጠንት
አሳርገዋል::
+የሚገርመው ያ ዛፍ ዛሬም ድረስ ለምስክርነት ቁሟል::
እኛም ሳይገባን ሔደን በዓይናችን አይተነዋል:: አምላከ
ቅዱሳን ግሩም ነው !!! በመጨረሻ ዘመናቸው ግን ጻድቁ
5 ክንድ ርዝመት ባላት ጾማዕት (በዓት) ውስጥ ገብተው
ቆሙ:: ለ45 ዓመታት ሳይቀመጡና ሳይተኙ በእንባ
ቢጸልዩ ቅንድባቸው ተላጠ:: አካላቸውም በአጥንቱ ብቻ
ቀረ::
+በ6ኛው ክ/ዘመንም በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት
መድኃኔ ዓለም መጥቶ "ወዳጄ! ስምህን የጠራ:
መታሰቢያህን በእምነት ያደረገውንም ሁሉ እምርልሃለሁ"
አላቸው:: ያን ጊዜ አጥንቶቻቸው ተወዛወዙና ነፍሳቸው
በክብር ዐረገች:: ከዚህ አስቀድሞም ንጉሡን አፄ
ካሌብን አባት ሆነው ያመነኮሱት እርሳቸው ናቸው::
=>አምላከ አበው የወጡ ወገኖቻችንን ሁሉ በሰላም
ይመልስልን:: ከክብረ ቅዱሳንም አይለየን::
=>ጥቅምት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ
2.አባ ዸንጠሌዎን ዘጾማዕት
2 988
3.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ (ዕን. ከ1 - 3 ያንብቡ)
4.ቅድስት ሐና ነቢይት (የሳሙኤል እናት - 1ሳሙ. ከ1 - 2ን ያንብቡ)
5.ቅዱሳን ኡሲፎርና ኡርያኖስ (ሰማዕታት)
6.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮዽያዊ (ፍልሠቱ)
7.ቅዱስ ሄኖስ ነቢይ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና
እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል
=>+"+ ምንም እንኩዋ በለስም ባታፈራ:
በወይን ሐረግም ፍሬ ባይገኝ:
የወይራ ሥራ ቢጐድል:
እርሾችም መብልን ባይሰጡ:
በጐች ከበረቱ ቢጠፉ:
ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ:
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል:: በመድኃኒቴ
አምላክ ሐሴት አደርጋለሁ:: +"+ (ዕን. 3:17)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2 988
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
"ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ።ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን #ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።"
አቡነ ሺኖዳ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2 988
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ጥቅምት ፭ (5) ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ" እና "ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ አቡነ ገብረ ሕይወት +"+
=>ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን
አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን
ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ:
ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::
+የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት
ይኖራል?
እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል?
ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው
ይሆን?
+አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች
ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና
ነውና): ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን
ነበርና): ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ
ነፍሳትን ያዳኑ አባት: ሃገራችንን አስምረው: አስራት
እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ
አርፈዋል::
+ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም: ገብረ ሕይወትም
ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት
ከምድረ ግብጸ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል::
በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት
ምክንያት ሆነዋል::
+ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን
ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው
ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ
ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር
ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::
+የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ
ፍቀር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100
ዓመታት በደብረ ዝቁዋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው
ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::
+ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም
ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት
አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው::
ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን
መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::
+ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል
የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ:
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ:
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ:
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ:
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::
+የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ
መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ
(ቅያሪ) ሆኖ ነው::
+"+ ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ +"+
=>ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ:
ሽምግልናውም ያማረ ነው:: ብዙዎቻችን የምናውቀው
በበዓለ መስቀል ስሙ ተደጋግሞ ሲጠራ ነው:: ግን ይህ
ታላቅ ሰው ለቅድስት እሌኒ መካነ መስቀሉን አሳያት
ከሚል አረፍተ ነገር የዘለለ ታሪኩ ሲነገርለት ብዙ ጊዜ
አንሰማምና እስኪ በዕለተ ዕረፍቱ ስለ ቅዱሱ ጥቂት
እንበል::
+ቅዱስ ኪራኮስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን
ሲሆን እናቱ ቅድስት ሐና ትባላለች:: በእጅጉ የተባረከች
ሴት ናት:: ምንም በነገዳቸው አይሁድ ቢሆኑም የዘመኑ
የአይሁድ ክፋት አልገዛቸውም:: የተባረከች እናቱ ታሪክ
እያስጠናች ከማሳደጉዋ ባለፈ አስቀድማ ኦሪቱን:
ነቢያቱን እንዲያውቅ አደረገች::
+አስከትላም ሕገ ክርስትናን እንዲረዳ አደረገችው::
የታሪክና የመጻሕፍት ምሑሩ ቅዱስ ኪራኮስ ከእናቱ ጋር
ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ: ክርስቶስን እያመለከ
ቆየ:: በዚህ ጊዜ ግን እድሜው እየገፋ ነበር::
+ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) ጉባኤያቸውን
ከፈጸሙ በሁዋላ ቅድስት እሌኒም መስቀሉን ፍለጋ
ስትወጣ ትልቁ ፈተናዋ የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ
አለመቻሏ ነበር:: እንዲያውም አማራጭ ስታጣ
በአካባቢው የነበሩ አይሁድን ምሥጢር እንዲያወጡ
ቀጥታቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ኪራኮስ ስለሚባል ደግ
ታሪክ አዋቂ ሰው ሰምታ ተገናኙ::
+ቅዱስ ኪራኮስም አባቶቹ አይሁድ ናቸውና አካባቢውን
ያውቀው ነበር:: ችግሩ ቆሻሻው ተራራ በመሆኑ ከ3ቱ
የትኛው እንደ ሆነ አለመታወቁ ነበር:: ቅዱሱ ግን
ለዚህም መፍትሔ ነበረውና "ደመራ ደምረሽ: በእሳት
አቃጥለሽ: እጣን ጨምሪበትና ይገለጥልሻል" አላት::
+ቅድስት እሌኒም የተባለችውን በትክክል ፈጽማ
የመድኅን ክርስቶስን ቅዱስ ዕጸ መስቀል አገኘች::
ቅድስት እሌኒ ወደ ሃገሯ ከተመለሰች በሁዋላም ቅዱስ
ኪራኮስ በኢየሩሳሌም አካባቢ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ::
+አረጋዊው ቅዱስ የሚገርም እረኛ ነውና የባዘኑትን
ሲፈልግ: በቤቱ ያሉትንም ሲያጸና ብዙ ደከመ:: በቅርቡ
ያሉትን በአፉ: የራቁትን ደግሞ በጦማር (በመልእክት)
አስተማረ:: በወቅቱ በአካባቢው ኤልያኖስ የሚሉት ከሃዲ
ንጉሥ ነበርና በቅዱስ ኪራኮስ ላይ ተቆጣ::
+ወደ እርሱ አስጠርቶ በአደባባይ: ቅዱስ ቃሉን ይጽፍበት
የነበረው ቀኝ እጁን አስቆረጠው:: ቅዱስ ኪራኮስ ግን
እጁ መሬት ላይ ወድቃ: ደሙ እየተንጠፈጠፈ ተናገረ:-
"አንተ ልብ የሌለህ ንጉሥ! እጄን ቆርጠህ ከክርስቶስ
ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው::
+በዚህ የተበሳጨ ንጉሡ እሳት አስነድዶ: አልጋውን
አግሎ ቅዱሱን ጠበሰው:: ኪራኮስ ግን በእሳቱ ላይ ሳለ
ወደ እሥራኤል ፈጣሪ በእብራይስጥኛ ጸለየ:: በማግስቱ
እናቱን ቅድስት ሐናን አምጥተው የነደደ እሳት ውስጥ
ጣሏት::
+ለ3 ሰዓት ያህል በእሳት ውስጥ ስትጸልይ ቆይታ በጦር
ወግተው ገደሏት:: ቅዱስ ኪራኮስንም ለአራዊት ሰጡት::
አራዊቱ ሰገዱለት:: በሌሎች ዓይነት ስቃዮችም ፈተኑት:
ግን እንቢ አላቸው:: በመጨረሻው በዚህ ቀን ገድለውት
የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::
=>አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም
ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን::
ክብራቸውንም አያጉድልብን::
=>ጥቅምት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
2.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ (ዻዻስ ወሰማዕት)
3.ቅድስት ሐና ሰማዕት (እናቱ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
5.አባ ዻውሎስ ሰማዕት (አርዮሳውያን አንቀው የገደሉት አባት)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
4.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
5.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
=>+"+ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም
ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ:: በክርስቶስ
ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ
ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና:: +"+ (ገላ. 6:14)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2 988
2 988
⛪️ ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል
🔐ከስር ክፈት የሚለውን
በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
................💚💛❤️...............
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
...............💚💛❤️................
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት
2 988
2 988
2 988
ምድሪቱን ባርከው ወተት ያፈለቁት ጻድቅ!
አባታችን በርተሎሜዎስ የጎንደር አውራጃ ምድረ እንፍራንዝን ተሻግሮ ምጽራሓ በሚሏት ደሴት ውስጥ አደረ፡፡ በዚያም የአባ አኖርዮስን ልጅ ቅዱስ አባ ጌርሎስን አገኘው፡፡ ከእርሱ ጋራም ብዙዎች ቀናትን ኖረ፡፡ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡለት፡፡ አንዱ ተአምርም አባ ያፍቅረነ እግዚእና አባ በርተሎሜዎስ በአንድነት ቆመው ሳለ መንፈሳዊ አባታችን ጻድቅ በርተሎሜዎስ በቆመበት በኩል ከምድር ወተት መነጨ፡፡ አባ ያፍቅረነ እግዚእ በቆመበት ሥፍራም ውኃ መነጨ፡፡ አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንበት ‹‹ሰይጣን ወተትን ከምድር በማመንጨት ለማሳት እንደዚኽ ይፈታተነኝን!›› ብሎ እያሰበ ስለዚኽ ነገር እጅግ አዘነ፡፡ አባ ያፍቅረነ እግዚእም በመንፈስ ቅዱስ ዐውቆ ‹‹ይኼ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከሰይጣን ስላልኾነ ስለምን ታዝናለህ? እግዚአብሔር እኮ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ አድርጎ መርጦሃል›› አለው፡፡
አባታችን አባ በርተሎሜዎስ በከንቱ ምስጋና በሰው ዘንድ ተወድሶ እንዳይኾንበት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተጋድሎውን ለማንም ቢኾን ሊገልጥ አልወደደም ነበር፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን ቃልኪዳን ሲሰጣቸው ‹‹አንተ ከወንድሞች መካከል ለአንዱም ስንኳ ገድልህን ሳትነግር በምሥጢር ሠውረህ ነበር፤ እኔ ግን የገድልህን ክብር በዓለም ዳርቻዎች ኹሉ ገልጬ በዐሥራ አምስቱ አህጉራተ ገነት በአምስቱ አህጉራተ መንግሥተ ሰማያትም እሾምሃለሁ፡፡›› ዘመኑም ወደ ቅድስት ደብረ ዘመዳ ከገባ መቶ ዘጠና ዓመት ከዘጠኝ ወራት ኖረ፡፡
ንዑድ ክቡር አባታችን አባ በርተሎሜዎስ ታቦቷን ወደ ዋሻው ቤተ መቅደስ ውስጥ በአገባበት ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአደረገችለት ተኣምር ይኽ ነው፡- መቆሚያውን በዋሻው በር እጅግ በደረቀች ዐለት ላይ አደረገ፡፡ በአንዲት ዕለትም ቆሞ ሳለ ጣዕሙ ወተት የሆነ ነጭ ውኃን ከእግሩ በታች አፈለቀችለት፡፡ ወንድሞቼ ሆይ! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለወዳጆቿ የምታደርገው ዕፁብ ድንቅ ነው! ለዚኽ ተኣምርም አንክሮና ምስጋና ይገባዋል፡፡ ንዑድ ክቡር አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ጣዕሙም እንደ ወተት የኾነ ነጭ ውኃ በአየ ጊዜ ይኽን ተኣምር አደነቀ፡፡
ጻድቅ አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ይኽንን አይቶ ለእመቤቱ ለድንግል ማርያም ‹‹ቀድሞ ለሌሎች ቅዱሳን ያልተደረገን ለእኔ ከአደረግሽልኝስ እለምንሻለሁ፤ እሺ በይኝና ከእግሬ በታች ያመነጨሽውን ይኽንን መልኩን ለውጠሸ ጣዕሙም በልክ እንዲኾን አድርጊልኝ፡፡ ይኽ ዛሬ የመነጨ ውኃማ ለዘወትር ከኾነ የሀገሩ ሰዎችና መኳንንቱ ለራሳቸው መሻት ይቀሟቸዋል እንጂ ለልጆቼ ገዳማውያን አይጠቅማቸውምና ጣዕሙ በልክ ይኹን፡፡ ለገዳማውያን ልጆቼ ተስፋ ይኾናቸው ዘንድ ግን ሀብተ ረድኤትሽ አይለየን›› ብሎ ለመናት፡፡
እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም ልመናውን ኹሉ የምትቀበል ናትና ወተትነቱን ወደ ውኃ ለወጠችው፡፡ የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎቷና በረከቷ፤ የጻድቁ አባታችን የአባ በርተሎሜዎስም ቃል ኪዳን ኹላችንን ከድንገተኛ ሞት ያድነን፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርጉልን።
✞ ✞ ✞
