ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

الذهاب إلى القناة على Telegram

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 935
المشتركون
-224 ساعات
+507 أيام
+18430 أيام
أرشيف المشاركات
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲 "ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ።ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን #ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።"         አቡነ ሺኖዳ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

photo content

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ጥቅምት ፭ (5) ❖ ✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ" እና "ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +"+ አቡነ ገብረ ሕይወት +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው:: +የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን? +አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና ነውና): ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና): ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት: ሃገራችንን አስምረው: አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል:: +ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም: ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብጸ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል:: +ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና:: +የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቀር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቁዋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው:: +ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል:: +ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ:: "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል:: +የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው:: +"+ ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ +"+ =>ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ: ሽምግልናውም ያማረ ነው:: ብዙዎቻችን የምናውቀው በበዓለ መስቀል ስሙ ተደጋግሞ ሲጠራ ነው:: ግን ይህ ታላቅ ሰው ለቅድስት እሌኒ መካነ መስቀሉን አሳያት ከሚል አረፍተ ነገር የዘለለ ታሪኩ ሲነገርለት ብዙ ጊዜ አንሰማምና እስኪ በዕለተ ዕረፍቱ ስለ ቅዱሱ ጥቂት እንበል:: +ቅዱስ ኪራኮስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን እናቱ ቅድስት ሐና ትባላለች:: በእጅጉ የተባረከች ሴት ናት:: ምንም በነገዳቸው አይሁድ ቢሆኑም የዘመኑ የአይሁድ ክፋት አልገዛቸውም:: የተባረከች እናቱ ታሪክ እያስጠናች ከማሳደጉዋ ባለፈ አስቀድማ ኦሪቱን: ነቢያቱን እንዲያውቅ አደረገች:: +አስከትላም ሕገ ክርስትናን እንዲረዳ አደረገችው:: የታሪክና የመጻሕፍት ምሑሩ ቅዱስ ኪራኮስ ከእናቱ ጋር ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ: ክርስቶስን እያመለከ ቆየ:: በዚህ ጊዜ ግን እድሜው እየገፋ ነበር:: +ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) ጉባኤያቸውን ከፈጸሙ በሁዋላ ቅድስት እሌኒም መስቀሉን ፍለጋ ስትወጣ ትልቁ ፈተናዋ የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ አለመቻሏ ነበር:: እንዲያውም አማራጭ ስታጣ በአካባቢው የነበሩ አይሁድን ምሥጢር እንዲያወጡ ቀጥታቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ኪራኮስ ስለሚባል ደግ ታሪክ አዋቂ ሰው ሰምታ ተገናኙ:: +ቅዱስ ኪራኮስም አባቶቹ አይሁድ ናቸውና አካባቢውን ያውቀው ነበር:: ችግሩ ቆሻሻው ተራራ በመሆኑ ከ3ቱ የትኛው እንደ ሆነ አለመታወቁ ነበር:: ቅዱሱ ግን ለዚህም መፍትሔ ነበረውና "ደመራ ደምረሽ: በእሳት አቃጥለሽ: እጣን ጨምሪበትና ይገለጥልሻል" አላት:: +ቅድስት እሌኒም የተባለችውን በትክክል ፈጽማ የመድኅን ክርስቶስን ቅዱስ ዕጸ መስቀል አገኘች:: ቅድስት እሌኒ ወደ ሃገሯ ከተመለሰች በሁዋላም ቅዱስ ኪራኮስ በኢየሩሳሌም አካባቢ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: +አረጋዊው ቅዱስ የሚገርም እረኛ ነውና የባዘኑትን ሲፈልግ: በቤቱ ያሉትንም ሲያጸና ብዙ ደከመ:: በቅርቡ ያሉትን በአፉ: የራቁትን ደግሞ በጦማር (በመልእክት) አስተማረ:: በወቅቱ በአካባቢው ኤልያኖስ የሚሉት ከሃዲ ንጉሥ ነበርና በቅዱስ ኪራኮስ ላይ ተቆጣ:: +ወደ እርሱ አስጠርቶ በአደባባይ: ቅዱስ ቃሉን ይጽፍበት የነበረው ቀኝ እጁን አስቆረጠው:: ቅዱስ ኪራኮስ ግን እጁ መሬት ላይ ወድቃ: ደሙ እየተንጠፈጠፈ ተናገረ:- "አንተ ልብ የሌለህ ንጉሥ! እጄን ቆርጠህ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው:: +በዚህ የተበሳጨ ንጉሡ እሳት አስነድዶ: አልጋውን አግሎ ቅዱሱን ጠበሰው:: ኪራኮስ ግን በእሳቱ ላይ ሳለ ወደ እሥራኤል ፈጣሪ በእብራይስጥኛ ጸለየ:: በማግስቱ እናቱን ቅድስት ሐናን አምጥተው የነደደ እሳት ውስጥ ጣሏት:: +ለ3 ሰዓት ያህል በእሳት ውስጥ ስትጸልይ ቆይታ በጦር ወግተው ገደሏት:: ቅዱስ ኪራኮስንም ለአራዊት ሰጡት:: አራዊቱ ሰገዱለት:: በሌሎች ዓይነት ስቃዮችም ፈተኑት: ግን እንቢ አላቸው:: በመጨረሻው በዚህ ቀን ገድለውት የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል:: =>አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን:: =>ጥቅምት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ 2.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ (ዻዻስ ወሰማዕት) 3.ቅድስት ሐና ሰማዕት (እናቱ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ (ከ12ቱ ሐዋርያት) 5.አባ ዻውሎስ ሰማዕት (አርዮሳውያን አንቀው የገደሉት አባት) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም 3.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ 4.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ 5.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) =>+"+ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ:: በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና:: +"+ (ገላ. 6:14) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Dm and call 0922255259 for order
Dm and call 0922255259 for order

ምድሪቱን ባርከው ወተት ያፈለቁት ጻድቅ! አባታችን በርተሎሜዎስ የጎንደር አውራጃ ምድረ እንፍራንዝን ተሻግሮ ምጽራሓ በሚሏት ደሴት ውስጥ አደረ፡፡ በዚያም የአባ አኖርዮስን ልጅ ቅዱስ አባ ጌርሎስን አገኘው፡፡ ከእርሱ ጋራም ብዙዎች ቀናትን ኖረ፡፡ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡለት፡፡ አንዱ ተአምርም አባ ያፍቅረነ እግዚእና አባ በርተሎሜዎስ በአንድነት ቆመው ሳለ መንፈሳዊ አባታችን ጻድቅ በርተሎሜዎስ በቆመበት በኩል ከምድር ወተት መነጨ፡፡ አባ ያፍቅረነ እግዚእ በቆመበት ሥፍራም ውኃ መነጨ፡፡ አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንበት ‹‹ሰይጣን ወተትን ከምድር በማመንጨት ለማሳት እንደዚኽ ይፈታተነኝን!›› ብሎ እያሰበ ስለዚኽ ነገር እጅግ አዘነ፡፡ አባ ያፍቅረነ እግዚእም በመንፈስ ቅዱስ ዐውቆ ‹‹ይኼ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከሰይጣን ስላልኾነ ስለምን ታዝናለህ? እግዚአብሔር እኮ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ አድርጎ መርጦሃል›› አለው፡፡ አባታችን አባ በርተሎሜዎስ በከንቱ ምስጋና በሰው ዘንድ ተወድሶ እንዳይኾንበት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተጋድሎውን ለማንም ቢኾን ሊገልጥ አልወደደም ነበር፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን ቃልኪዳን ሲሰጣቸው ‹‹አንተ ከወንድሞች መካከል ለአንዱም ስንኳ ገድልህን ሳትነግር በምሥጢር ሠውረህ ነበር፤ እኔ ግን የገድልህን ክብር በዓለም ዳርቻዎች ኹሉ ገልጬ በዐሥራ አምስቱ አህጉራተ ገነት በአምስቱ አህጉራተ መንግሥተ ሰማያትም እሾምሃለሁ፡፡›› ዘመኑም ወደ ቅድስት ደብረ ዘመዳ ከገባ መቶ ዘጠና ዓመት ከዘጠኝ ወራት ኖረ፡፡ ንዑድ ክቡር አባታችን አባ በርተሎሜዎስ ታቦቷን ወደ ዋሻው ቤተ መቅደስ ውስጥ በአገባበት ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአደረገችለት ተኣምር ይኽ ነው፡- መቆሚያውን በዋሻው በር እጅግ በደረቀች ዐለት ላይ አደረገ፡፡ በአንዲት ዕለትም ቆሞ ሳለ ጣዕሙ ወተት የሆነ ነጭ ውኃን ከእግሩ በታች አፈለቀችለት፡፡ ወንድሞቼ ሆይ! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለወዳጆቿ የምታደርገው ዕፁብ ድንቅ ነው! ለዚኽ ተኣምርም አንክሮና ምስጋና ይገባዋል፡፡ ንዑድ ክቡር አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ጣዕሙም እንደ ወተት የኾነ ነጭ ውኃ በአየ ጊዜ ይኽን ተኣምር አደነቀ፡፡ ጻድቅ አባታችን አባ በርተሎሜዎስም ይኽንን አይቶ ለእመቤቱ ለድንግል ማርያም ‹‹ቀድሞ ለሌሎች ቅዱሳን ያልተደረገን ለእኔ ከአደረግሽልኝስ እለምንሻለሁ፤ እሺ በይኝና ከእግሬ በታች ያመነጨሽውን ይኽንን መልኩን ለውጠሸ ጣዕሙም በልክ እንዲኾን አድርጊልኝ፡፡ ይኽ ዛሬ የመነጨ ውኃማ ለዘወትር ከኾነ የሀገሩ ሰዎችና መኳንንቱ ለራሳቸው መሻት ይቀሟቸዋል እንጂ ለልጆቼ ገዳማውያን አይጠቅማቸውምና ጣዕሙ በልክ ይኹን፡፡ ለገዳማውያን ልጆቼ ተስፋ ይኾናቸው ዘንድ ግን ሀብተ ረድኤትሽ አይለየን›› ብሎ ለመናት፡፡ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም ልመናውን ኹሉ የምትቀበል ናትና ወተትነቱን ወደ ውኃ ለወጠችው፡፡ የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎቷና በረከቷ፤ የጻድቁ አባታችን የአባ በርተሎሜዎስም ቃል ኪዳን ኹላችንን ከድንገተኛ ሞት ያድነን፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርጉልን። ✞ ✞ ✞

photo content

photo content

በዕረፍታቸው ዕለት ጥቅምት 4 ቀን በዋዜማው የቤተ መቅደሱ ምሰሶ ማርና ወተት ያፈልቅ የነበረው ጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ፍልፍል ቤተ መቅደስ! በአገራችን 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያሠሩ ሲሆን 44ቱ ፍልፍል ናቸው፡፡በተለይም ገርዓልታ ያለው ቀመር ዐርባዕቱ እንስሳ ፍልፍል ቤተ መቅደስ በሩ በራሱ ጊዜ ይከፈታል ይዘጋል እንጂ ሰው አይከፍተውም አይዘጋውም፡፡ በዚህ በፎቶው ላይ የሚታየው ጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ፍልፍል የቤተ መቅደሱ ምሰሶ በዕረፍታቸው ዕለት ጥቅምት 4 ቀን በዋዜማው ማርና ወተት ያፈስ ነበር፡፡በእነርሱም ዘመን አማናዊው ጥምቀትና ቍርባን ለመጀመሪያ ጊዜ መጣልን፡፡ ቅዱሳን ነገሥታቱ የአድባራት ሁሉ የበላይ የምትሆን የአክሱም ቅድስት ጽዮንን ቤተ ክርስቲያን በወርቅና በዕንቊ ሠሯትና አባ ሰላማ ባርከው ቀደሷት፡፡ ታቦተ ጽዮንም ከድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ተገኘች፡፡የከበሩ ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሓ እግዚአብሔርንም ሰውንም አገልግለው ለአገራችንም ብርሃን አብርተውላት ነው ያለፉት፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአብርሃ ወአጽብሓን ተገልጦላቸው ‹‹በዚህች ቦታ ላይ ቤተ መቅደሴን አንጹልኝ›› ብሎ ያዘዛቸው እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት በሞት ያረፉት በሰማዕትነት ነው፡፡ሰይጣን በደቡብ አንድ ኢአማኒ በማስነሣት ጦርነት ከፍቶ ሰውን ሁሉ እየገደለ በክርስቲያኖች ላይ ክፉ በደል እየፈጸመ መሆኑን አብርሃ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት ዐወቀ፡፡ በዚኽም ጊዜ በመረረ ኀዘን ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አቀረበ፡፡ እርሱም በሰማዕትነት ያርፍ ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ በሰማዕትነት እንደሚሞት ነግሮት በክብር ዐረገ፡፡ ከዚኽም በኋላ ቅዱስ አብርሃ ወደ ጦርነቱ ገባ፡፡ ዐላማው ሰማዕትነትን ለመቀበል ስለነበር በእጁ ጋሻ ጦር አልያዘም፣ሰይፍም በወገቡ አልታጠቀም፡፡ ያንጊዜም አንድ አላዊ ግንባሩን በጦር ወጋውና ንጉሥ አብርሃ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ አላዊውም አንገቱን በሰይፍ በቆረጠው ጊዜ ደም ውኃ ወተትና ማር ከአንገቱ ፈለቀ፡፡ አብርሃ በሰማዕትነት ቢያርፍም ጦርነቱ ቀጠለና ክርስቲያኖች ድል አደረጉ፡፡ ንጉሥ አብርሃን የገደለውን ዐላዊ ወንድሙ አጽብሓ ፊት ባቀረቡት ጊዜ ወንድሙ አብርሃ አስቀድሞ ነግሮት ነበርና በቍጣ ሳይሆን በፍቅር ተመለከተው፡፡ ሃይማኖትንም አስተምሮ አሳምኖት አጠመቀው፡፡ የወንድምን ገዳይ በፍቅር ተቀብሎ አስተምሮ ማጥመቅ እንዴት ያለ ፍቅርና ሐዋርያነት ነው በእውነት!!!ንጉሥ አጽብሓም እንደ ወንድሙ አብርሃ ሕይወቱን በድንግልና ለማሳለፍ ዐላማው ነበር፡፡ ነገር ግን ዘር ይተካ ዘንድ እግዚአብሔር ስላዘዘው በ53 ዓመቱ ቅዱስ ጋብቻ ፈጽሞ ሚስቱ ወዲያው ፀነሰች፡፡ ወንድ ልጅም ወለደችና ስሙን አስፋህ ብለው ሰየሙት፡፡ ከ12 ዓመት በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ለአጽብሓ ተገልጦለት ቃልኪዳን ገባለትና እርሱም እንደወንድሙ በሰማዕትነት እንደሚያርፍ ነገረው፡፡ ንጉሥ አጽብሓ ስለቀናች ተዋህዶ ሃይማኖቱ ክብር ሲል በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ሰማዕት የሆነውም በሀገረ ጅማ አብያተ ክርስቲያናትን እያጠፋ ይመዘብር ክርስቲያኖች ይገድል የፈጣሪን ስም ይሳደብ ከነበረ አንድ ከሃዲ ጋር በተደረገ ጦርነት ነው፡፡ በዚህም ጦርነት ቅዱስ አጽብሓ ሰማዕት ቢሆንም ክርስቲያኖች ግን ዳግመኛ ድል ማድረግ ችለዋል፡፡ በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ያረፉ የቅዱሳኑ ነገሥታት የአብርሃ ወአጽብሓ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

Dm and call for order 0922255259