የክብሩ ነፀብራቅ✨
Kanalga Telegram’da o‘tish
ልጁም የእግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅና የአምላካዊ ባሕርዩ አምሳያ ነው፡፡ ወልድ አምላክ በመሆኑም ይህን ዓለም በሥልጣኑ ኃይል ይቆጣጠረዋል ፤ በሥርዓት እንዲመራም ያደርገዋል ። እኛን ከኃጢአት ለማንጻትና የተመዘገበብንን የበደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ከሞተ በኋላ ፥ አሁን በአባቱ ጎን ባለው ከፍተኛ ሰማያዊ የክብር ቦታ ተቀምጧል ። [ሕያው ቃል ዕብራውያን 1:3]
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
358
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+127 kun
+9330 kun
Postlar arxiv
358
✍Unconditional
“God’s love is unconditional” ስንል፣ ፍቅሩ በውድቀታችን አይቀንስም ማለት ብቻ አይደለም......ነገርግን በመልካም ሥራችንም አይጨምርም ማለት ነው!!ምክንያቱም እኛ ከምንሰራው በፊት እርሱ ወድዶናል....የማይገባንን በፊትም ያልሆነ ከዚ በኋላም ሊሆን በማይችል በክርስቶስ ፍቅር በመስቀል ወዶናል...ደግሞም ያንን ፍቅር በቃል ብቻ ሳይሆን በሕይወቱ አሳይቷል!!...Jesus is not waiting for a better version of me to love me more....የእርሱ ፍቅር እኔ በምሠራው መልካም ነገር የሚጨምር ወይም በምወድቅበት ጊዜ የሚቀንስ conditionally based ያረገ መውደድ አይደለም!!
ስለዚህ እኔ መልካም ስለሆንኩ እርሱ የበለጠ አይወደኝም፤ ስወድቅም የበለጠ አይጠላኝም። My obedience doesn’t purchase His love, and my failure doesn’t cancel it!!!መልካም ሥራዬ የሚያሳየው እኔ እንደምወደው ነው እንጂ እርሱ እንዲወደኝ የምገዛበት ዋጋ አይደለም!!ይህን ስረዳ፣ እግዚአብሔርን የማገለግለው ፍቅሩን ለማግኘት ሳይሆን በማይነጥፍ ፍቅር እንደተወደድኩ ለማሳየት ነው!
“እኛ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ።” ሮሜ 5:8
358
ቤተሰብ....ትናንት እና ዛሬ ቀኔን ሙሉ የተቆጣጠረ መዝሙር ተጋበዙልኝ፡ በእርጋታ ስሟት ብቻ.... ልብን ርስርስ የምያደርግ መዝሙር 🙌 🎶. እንደዚህ አይነት ድንቅ እህቶቼ ይብዙልን🥰
https://youtu.be/WBbY7on0ZrI?si=EMrhwQ1K0wFz6fFi
358
+5
የእድሜዬ በኩሩ ጠሉ ዘሩ ኢየሱስ
የሽበቴ ወጉ ሙሉ ክብሩ ኢየሱስ
የሞቴ ማረጉ ልኩ ጥጉ ኢየሱስ
ያ'ሳቤ መክብቡ
መኃሉ እስክትሆነኝ
አስተምረኝ ስላንተ ማውራት አስተምረኝ ኢየሱስ ማለትJoin 👇 @ShekinnahKBR
358
Repost from Good Christian Books Shelf
እህቶች ለትዳራችሁ the best possible ወንድ..... ወንዶችም እንዲሁ the best possible ሴት በመፈለግ ተጋደሉ🥰
አብራችሁ በአንድ ቀንበር የምትጣመሩ፥ አንዱን ተስፋ የምትወርሱ፥ አንድ መንገድ የምትሄዱ፥ ለአንድ ህልም የምትኖሩ፥ በአንድ መንፈስ እምትመላለሱ፥ በአንድ የእምነት ታዛ ስር ምትጠለሉ፥ አብራችሁ ምትጸልዩ፥ ምትንበረከኩ፥ ምትጦሙ፥ ምታመልኩ፥ የልግስና እጃችሁን ለሌሎች እምትዘረጉ፥ በመከራ፣ በደስታ ጊዜ እርስ በእርስ እምትቀባበሉ፥ በአደባባይ እምትመሰጋገኑ፥ መከባበርና መፈራራት ገንዘባችሁ የሆነ፥ ኢየሱስ የሚደሰትባችሁ ባለትዳሮች ለመሆን ዘወትር ተጋደሉ…. የጠርጡሊያን ምክር ነው ደግሞ😊
358
ቋሚ ነገር በለለባት ዓለም፡ በማትረጋጋው፡ የማይቀየረውን የእግዚአብሔርን መልካምነት ማወቅ ልብን ከጭንቀት ነጥቆ እርፍ የምያደርግ እውነት ነው።
እግዚብሔርን መልካም ነው!@Kbr111
358
እምቢ የዓለምን ጥሪ
እምቢ የዓለምን ግብዣ
እምቢ ከቶ አንገናኝም
እምቢ እስከመጨረሻ
እምቢ እግዚአብሔርን መፍራት
እምቢ ያዋጣኛልና
እጅ አልሰጥም ለዓለም ሞት አለበትና።
358
Repost from Anti World
ለሰው አላወራም ምን ትርፍ አገኛለሁ
ሃዘኔን ብሶቴን ላንተው እነግራለሁ
ደጃፌን ዘግቼ አጫውትሃለሁ
አምናለሁ ካንተ ዘንድ ምላሽ አገኛለሁ (፪x)
አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፪x)
የኤርትራን ባህር ታሻግረኛለህ
ከሰማያት መናን ታወርድልኛለህ
ሃሳብህም ከቶ አይከለከልም
ሁሉ ይቻልሃል ምንም አይከብድህም (፪x)
የነገሩህንም የማትረሳ ነህ
አንዱም አይጠፋህም ታስታውሰዋለህ
ሕመሜን በሙሉ አንተ ታውቀዋለህ
መድኃኒቴ አንተ ነህ ትፈውሰኛለህ (፪x)
አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፪x)
የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፫x
358
ሰው እንኳን የሚያልፈውን ይሄ አለኝ ይላል
አንድ ሁለት ሶስት ብሎ ለሚያይ ያስቆጥራል
የማታልፍ የማታልቅ የማትደክም ትምክህቴየማልቀይርህ መዝሙር እስካለሁ በህይወቴ ለልጅ ልጅ ትምህርት ርስትም ያለኸኝ ለሚያዩኝ ሁሉ እዩልኝ የሚያስብለኝ እዩልኝ... ደግነቱን እዩልኝ 🥰
358
ና እና እየው ወዴት እንዳኖርኩት በልቤ ጓዳ ሽሽጌ ያኖርኩት እኔ እና አንተ ብቻ በምናውቀው ጉዳይ መልስ እጠብለው ከስማይ ኢየሱስ ለንተ ብቻ በወጋሁህ ጉዳይ መልስ እጠብቃለው ከስማይ
358
ና እና እየው ወዴት እንዳኖርኩት
በልቤ ጓዳ ሽሽጌ ያኖርኩት
እኔ እና አንተ ብቻ በምናውቀው ጉዳይ
መልስ እጠብቃለው ከሰማይ
ኢየሱስ ለንተ ብቻ በወጋሁህ ጉዳይ መልስ እጠብቃለው ከስማይ
እየጠበኩህ ነው ከትለንት ዛሬ
አደምጣለሁኝ ኮቴህን ከበሬ
እጠብቅሀለሁ በመጠበቂያዬ
አላሳንስህም በአንደበቴ ዝዬ
ኮሽ በለ ቁጥር አልደናበርም
እየጠርጠርኩህ እምነቴን አልጥም
አንተ ላይ ነው አቅሜ የጩኸቴ ብርታት
አቤቱ አቤቱ አቤት የምልበት
ና እና እየው ወዴት እንዳኖርኩት
በልቤ ጓዳ ሽሽጌ ያኖርኩት
እኔ እና አንተ ብቻ በምናውቀው ጉዳይ በልስ እጠብለው ከስማይ
ኢየሱስ ለንተ ብቻ በወጋሁህ ጉዳይ
መልስ እጠብቃለው ከስማይ
ደጅህን ብጠና እንደው ብመላለስ
ፈትህን አትቀጭምም ከበር እንድመለስ
ኮቴዬን ስትስማ አይዝህም ዝለት
የልቤን ተማጥኖ ቸል የምትልበት
በተስፍ ለሚሹህ ለሚጠባበቁህ
ታጠግባቸለህ ከመልካምነትህ
ቢጠብቅ እስሩ ቢሽት መቃብሩ
ባንተ ጊዜ ሲሆን ይሰማሀል ሁሉ
አንተ ምታስበው ደግ ደጉን ብቻ
መልካሙን ስለእኔ
ብትነሳኝ ደሞ ብትከለክለኝ
ብለህ ለጥቅሜ
ብቻ ዝም አትበል አንድ ነገር በለኝ
ትሁነኝ ፈቃድህ ያልከው ይከተለኝ
አይድጠኝም አፌ ለከንቱ ልስለፍ
ጸጋህ ይበቃኛል ባንተ ምክር ልረፍ
358
የምትሸፍን እውነት ሆይ!ማጥፋት ስትችል ያዳንከን ሆድህ የማይጠናው ፣ ጉስቁልናን የምትለውጠው የድሆች ቀን ፣ ጎኑ ባዶ ለሆነው ጽኑ ረዳት ፣ በራሱ የሞተ ባንተ የሚድንብህ ፣ እልልታ ከቤቱ ለራቀው ዝማሬው ፣ የሚሸፍን እውነት ያለህ ከባቴ አበሳ ፣ ሸክም ለተጫነው ቅለቱና ዕረፍቱ ፣ ማዕበል ላስጨነቀው ወደቡ ፣ ያልፈለገህን በመፈለግ የከበርህ ፣ ትልቅነትህ ኩራት የሌለበት ፣ ፈቃድህ ሁሉን የሚገዛ ፣ የኑሮ ጩኸት ሲያስጨንቅ ፀጥታችን ፣ ለተመረዘች ነፍሳችን መድኃኒት ፣ የፈረሱ ቅጥሮችን የሠራህ ፣ የሄደውን ወዳጅ የመለስህ ወዳጅ ፣ ካሰቡልን ይልቅ የምታስብልን የዘመድ አውራ ፣ ምሕረትህ ቀና የሚያደርግ ቀዩ ካባ ፣ የፈለጉትን እስረኞች የምትፈታ የመኰንኖች መኰንን ፣ መቼ ነው የማርፈው ለሚሉህ የደስታ አገራቸው ፣ የሁልጊዜ ቅዱስ የማትሳሳት ፣ በማዳንህ የተደነቅህ ፣ ፈውስ ጉዳት የሌለበት ፤ በሟችና በገዳይ መካከል የምትገባ የእሳቱ ውኃ ፣ የታመኑብህን የምትክስ የፍቅር ዳርቻ ፣ አረማመድህ የማይታወቅ ጎምላላ ፣ ደጁን የምታንኳኳ ጠባቂ ፣ ጥፋት ሲመጣ አንቂ ፤ ዋጋ ለሌላቸው ዋጋቸው ፣ ውሉ ለጠፋቸው ብልሃታቸው ፤ የሚፈሱ እንባዎች የሚገደቡልህ ፣ ባለ ችንካር እጁ ፤ ሰውን ሰው የምታደርገው የመራራው ጣዕም ፣ ጥያቄን የማትፈራው የሕይወት መምህር ፣ የሐኪሙ ሐኪም ፣ የድካም ቀንን የምታውቅ ፤ የሚፈሩህን የምታከብረው ፣ ሲወዱህ የማትኮራው ፤ ለንጉሥ ንጉሥ መባልን የሰጠኸው ፣ ስላለፈው የሚጠይቁህ ብሉየ መዋዕል /ዘመን ጠገቡ፣ ስለ ነገ የሚያምኑህ ፣ የመንገድ ስንቁ … አንተ እግዚአብሔር የእኔ አምላክ ነህ ! ተመስገን ! ሲቻል በቃል ፣ ሳይቻል በዝምታ ተደነቅ ፤ እባክህ ከምስጋና ማማዬ አልውረድ ፤ ለዘላለሙ አሜን! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
358
The power of እግዚአብሔር ያውቃል...... besemaaam!.😭..አንዳንድ ጊዜ ምንም መፍትሔ እንዳልቀረ ይሰማናል፤ ምን እንደምናደርግም ግራ ይገባናል.... But maybe faith is not always having an answer....it is knowing Who already has one! ሁሉን መረዳት ሳይኖርብኝ፣ ሁሉን በሚያውቀው እጅ መተውን መርጫለሁ...እኔ አላውቅም፤ እርሱ ያውቃል። እኔ አላየሁም፤ እርሱ ግን እያየ ነው...ስለዚህ ነፍሴ እንዲህ ትላለች..."እግዚአብሔር ያውቃል!”
358
Excuses ✍️.....
ይኸውላቹ ሰዎችዬ ሀጢያት stage በቀየረ ቁጥር ከልምድነትና ከባህሪ አልፎ ህይወት ነው የሚሆነው...ምክንያት በጨመራቹለትና በሸፋፈናችሁት ቁጥር ደግሞ መሪ ይሆንባቹዋል....መሪ ሆኖ አለቃ ከሆነባችሁ ደግሞ መሄጃም መመለሻም ቀዳዳ ያሳጣችዃልና....እባካችሁ don't give excuses for ur ሀጢያት!!
እናስታውስ የለ የኔ ሰዎች.....ሳኦል የወደቀው በአንድ ቀን ብቻ አይደለም መውደቁ የጀመረው ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የራሱን ፈቃድ ማስቀደም ሲጀምርና ለሀጢያቱ ምክንያት ሲደረድር ነው!!..... እግዚአብሔር ግልጽ ትእዛዝ ሰጥቶት ሳለ ሳኦል ግን በሙሉ አልታዘዘም...ነገር ግን ሲጠየቅ ኃጢአቱን በቀጥታ ከመቀበል ይልቅ ሕዝቡን ወቀሰ እሱ ብቻ አይደለም ምክንያትም አቀረበ.....እንዲያውም አለመታዘዙን እንደ አምልኮ ለማሳየት ሞከረ.....እንዲህም ሲል ተናገረ...“እነዚህን ለእግዚአብሔር ለመሥዋዕት አስቀርተናል” አለ...ለሀጢያቱ የሰጠው ምክንያት ያላሳመነው ሳሙኤል እንዲህ ሲል ተናገረው......"እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ መስማትም ከአውራ በግ ስብ ይሻላል!(1 ሳሙኤል 15፥22)".....ችግሩ ሳኦል ኃጢአት መሥራቱ ብቻ አልነበረም፤ ኃጢአቱን ከመናዘዝ ይልቅ ለማስረዳትና ራሱን ለማጽደቅ መሞከሩ ነበር!!!...ሰበብ ልብን ከንስሐ ያርቃል፤ ሰው እውነቱን እስካልተቀበለ ድረስ ፈውስን መፈለግ አይጀምርም!!!
ስለዚህ ሰዎችዬ፣ ከኃጢአት በኋላ የሚያድነን ሰበብ ሳይሆን እውነተኛ ንስሐ እና ትሕትና ነዉ‼️
ከTikTok መንደር ✍️ምፅላል❤️🩹
@Kbr111
358
በእግዚአብሔር ፍቅር ያልተሞላ ሰዉ ለሚያገኘዉ ሁሉ ተሸናፊ ነው።ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
358
አቤቱ ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ለራስህ ክብርና ዓላማ ሰርተሄናልና ዛሬም አንተን እንፈልግሃለን፥ ለፈቃድህ መንገድ ህያው አድርገን: በሰው ፍጥረት በዕድሜው ማለዳ የህይወት እስትንፋስን እፍ ያልክብን ፈጣሪያችን ሆይ : ዛሬም በመንፈስህ ለራስህ ለክብርህ እና ለክቡር ዓላማ አንቃን ::
@Kbr111
