Abdulhakim Nasir
Відкрити в Telegram
መኖር ጀመርን....... ልንሞት ነው.... ኖረን እስክናልፍ እንቅስቃሴአችን የሚደበቀው በቆሻሻ ከተሞላው ጆንያ ብቻ ነው.... እንሰብካለን እንፅፋለን
Показати більше319
Підписники
+124 години
+47 днів
+2230 днів
Архів дописів
+2
መዲና እንደመድረስ
ኑር እንደመጠጋት፣
ብርሃን ተጠልሎ
አንቱን እንደ ማውጋት፣ እያንሾካሾኩ
በበርዎ እንደ ማለፍ፣
ምላሽዎን ለማድመጥ
ናፍቆ እንደመወንጨፍ፣
ከጀነቱ አፀድ
ከረውዷ እንደማረፍ፣
ደግሞም...
እየተንጠራሩ አሻግሮ እንደማየት እያንጎራጎሩ “ሰይዲ” እንደማለት፣ ሚንበርዎን እያዩ
ናፍቆ እንደመቃተት...
ለሸፈዓ ምልጃ
አማና እንደማለት፣
ዋስ እንደመጠየቅ፣
ነፍስ እንደማለቅለቅ...
ምን አላት ዱንያ…?
ምንስ አላት ዓለም
፣ ሲገኝ የሚያስቦርቅ
ሲቀር የሚያስነድም፣
ምንም
ምንም
ምንም!!
ሲመስለኝ ማወቅ እዳ ነው!
ያኔ ጅብሪል ሳያገኛቸው በፊት አንብብ ብሎ ሳይጨምቃቸው ማህበረሰባችው የተከናነበውን ድንቁርና በማወቃቸው ይጨንቃቸው ነበር ለዛም ይመስለኛል ከመካ ከ4 ኪሎ ሜትር በላት የሆነ ርቀት ላይ የሚገኘው ጀበለ ኑር የሚወጡት። ኧረ እንደው እዛ ቀጥ ያለ ተራራ ላይ ማን አሳውቋቸው ነው ጋሩ ሂራ እንዳለ ? ታዲያ እነዛ የጭንቅ ግዜዎች የፈጠሩት መሀይምነትን መረዳታቸው ይመስለኛል።
አንዳንድ ኹነቶች ላይ ሰዎች አለማወቅ ከንደዚህ አይነት ጭንቀት ስለሚገላግላቸው ኧረ እንኳን አላወኩት ሲሉ አስተውላለሁ እና ምን ይሰማኛል መሰላችሁ።
ምናልባትም ወደ ጋሩ ሂራ ወተው እነዛን የመመሰጥ ቀናት ባያሳልፉ ኖሮ አለም ምናልባትም ከዚህ የከፋ ጨለማ ውስጥ በገባች ነበር። ምናልባትም በየቀኑ የምንዋደቅለትን አሏህን ባላወቅን እና የ እንስሳት ህይወት በኖርን ነበር።
በዚህ ዘመንም ተመሳሳይ ነገር ይስተዋላል። ጭለማውን የተረዱት ያንን የ ኢስላም ብርሀን እንዴት የበላይ እንዲሆን እንታገል በሚል እንቅልፍ ያጣሉ።
ጭለማ ውስጥ የተዘፈቁት ደግሞ የውስጥ ሰላም ማጣት ፣ ብቸኝነት እና ከቢል ወደ ቢል የሆነ ኑሮ እረፍት ነስቷቸው እንመለከታለን። በአንፃሩ መሀይምነትን የተረዱ እና ወደ ጀባሩ የተጠጉ ባሮች ውስጣቸው ሰላም እንቅልፋቸው ጣፋጭ ሆኖ እንመለከተዋለን።
ኧረ እንደውም መሀይምነት ሰቆቃ ነው
أَفْضَلُ الصَّلَاةِ وَأَتَمُّ التَّسْلِيمِ عَلَى سَيِّدِنَا وَمَوْلَانَا مُحَمَّدٍ، الْمُصْطَفَى الْمُخْتَارِ، وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ
ይህንን ጭለማ ለገፈፉት ነብይ ምድር ላይ ባሉ ፍጡራን ልክ ሰላም ይውረድ
አሚን
ሴትየዋ ካንተ ተንኮል ተጠበቅ እንዳለቻቸው የገባት ግዜ አዘነች እኚያ ሰው ላይ እየተቀጠፈ እንደሆነ ለመረዳት የተሸከሙላትን ቅጠል መመልከት በቂዋ ነበር!
እንዴት ዐለም ላይ የተሻለ ስልጣን ያለው ሰው ደሀ ይመለከታል ያውም በእድሜ የገፉ ደሀ…..ለራሳቸው መከላከል የማይችሉ አሮጊት …… እነሱ የሚያውቁት የራሳቸውን ሹማምንት እንጂ የከውኑን አይነታ አልነበረማ!
የምድርን ታሪክ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ የለወጡት ነብይ ሰዐወ ከአደም ጀምሮ እስከ ቂያም ቀን ከሚመጣ ፍጡር የተላቁት ነብይ ዝቅ ብለው ለአንዲት መንገደኛ አሮጊት ቅጠል ተሸክሞ ነበር። ሴትየዋ ምርቃታቸው አንድ ሙሐመድ የሚባል ሰው መቶብናል ከሱ ተንኮል ተጠንቀቅ ነበር።
አይነታው ነቢ ያ ሰው እኔ ብሆንስ ነበር መልሳቸው። አእምሮአችሁ ውስጥ ካለ የትኛውም መሪ ይህንን መልስ ማግኘት እሩቅ ነው። አሀ አንተ ከሆንክማ እኔም ባንተ አምናለሁ ያመጣኸውን መልዕክትም እኖረዋለሁ ነበር መልሷ።
أَفْضَلُ الصَّلَاةِ وَأَتَمُّ التَّسْلِيمِ عَلَى سَيِّدِنَا وَمَوْلَانَا مُحَمَّدٍ، الْمُصْطَفَى الْمُخْتَارِ، وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ.
ስሙኝማ ረቢእም አይደል የአይነታውን ነብይ ታሪክ ብናነብ ምን ይመስላቹኃል እ
በየቀኑ አንዳንድ ፅሁፎችን እና ሀሳቦችን ከዚህ መፅሐፍ ረውደቱል አንዋር እናነሳሳ ምን ታስባላችሁ።
መፅሐፍ፦ ረውደቱል አንዋር
ገፅ ብዛት ፦ 300
ዛሬ 4 ነው ስነዚህ በቀሩን 26 ቀናት 300/26=11.538 በቀን 12 ገፅ ካነበብን መጨረስ ቀላል ነው
ምን ትላላችሁ
ከሚያስደንቁኝ መሀል
፦ ከመስጂድ ቸኪዬ በወጣሁበት ቅፅበት ምንም አሳክቼ አላውቅም
በተመሳሳይ ረጋ ብዬ አዝካር እና ሱና ሰላት ባስከተልኩባቸው ወቅቶች ያጣሁት ምንም ነገር የለም! በአንፃሩ ውስጣዊ ሰላም አገኝበታለሁ
@whenever11
አይኔን ከነሱ ዘወር አድርጌ ደግሞ ሌሎች ሰዎች መመልከት ጀመርኩ መስጂዱ ውስጥ ያሉት ሰዎች ቁጥር ቀንሶ ማን ማን እንዳለ ለመለየት የሚያስችል ያህል ቁጥር ደርሷል። በስተቀኝ በኩል አንድ ወጣት በተመስጦ ዱዐ ያደርጋል። ስለ ምን እየጠየቀ ይሆን የሚል እና ምን ያህል አላህን ያምነው ይሆን የሚሉ ሁለት ጥያቄዎች አዕምሮዬን ያዙት። እኔስ ምን ያህል አዕምሮዬን አምነው ይሆን?
ዛሬ ጁመዐ አራብሳ ነበር የሰገድኩት እናም ከሰላት በኃላ ዝም ብዬ ሰዉን መቃኘት ጀመርኩ።
ምናልባትም ከተወሰኑ ብሔረሰቦች በቀር ሁሉም ተወክሏል! …… ከመስጂዱ ውጪ የነበሩ ሰጋጆች ምናልባት በፀሀዩ ፣ በረሀብ ፣ በስራ ወይም በነበረባቸው ሀጃ እየተጣደፉ ወጡ…… ግማሽ ያህሉ ለሱና ሰላት ቆሙ እንደኔው ዝም ብለው ቆዝመዋል
አንድ የቃጥባሬ ኮፍያ ያደረጉ አባት ተነስተው አወል ሰፍ ላይ ያሉትን ይዘይሩ ጀመር ሁሉም ላይ እውነተኛ ፈገግታ ይታያል። ምናልባትም እዚሁ መስጂድ ውስጥ ለተከታታይ በርካታ አመታት በየሳምንቱ እንዲህ አይነት በፍቅር የተሞላ በስስት የታጀበ ሰላምታን ሲለዋወጡ ከርመዋል።
ምን አልባትም በዚህች እዚህ ግባ በማይባል ስራ እርስ በርሳቸው ያላቸው ውዴታ ጨምሯል። ምን አልባትም በመዘያየራቸው ብቻ ወንጀላቸው ተምሮ ይሆናል። ይሄኔ በፈገግታቸው ምክንያት የአላህንም ውዴታ አግኝተውበት ይሆናል። ምን ይታወቃል የቂያማ ቀን ምንም መጠለያ በሌለበት የአርሽ ጥላ ስር ለመጠለል ሰበብ ይሆናቸው ይሆናል።
❤️❤️ሐሙስ ሐሙስ ማታ💛💛
ሰላምታዬን ለእርስዎ፣ሰርክ ምሰድልዎ
በአካል ባላይዎም፣ወንድም ነኝ ያልኩዎ
ሳያዩኝ ያወሱኝ፣ከነጓደኞችዎ
ያበሻ ቡለሃ ፍቅርሆ የዋጠኝ ነኝ
ሰላምታዬ ብቻ ደርሶኛል ይበሉኝ
በሳምንት አንድ ቀን ሰላምታ እልካለሁ
ነሻጣ ሲቀርበኝ ሁሌ ነጋ ጠባ እርሶን አወሳለሁ
እንደው ልጠይቆ ይደርሳል ሰላሜ?
የልበ ደረቁ የከንቱው ሠው የኔ?
ሰላምታዬ ይደርሳል?እርሶስ መልሰዋል?
መልሱን አለማወቅ እጅጉን ይጨንቃል
ሳወራ ማይደክመኝ ስለርሶ ጧት ማታ
ሰው እስኪሰለቸኝ ጮኬም በእርጋታ
አንደኛ ነበርኩኝ
ሳልለከፍ በፊት
ሠውን እያየሁኝ በንፅፅር ሳልሰንፍ
አንቱን ያሳወቁኝ ዑስታዞቼ ጠፍተው ሌሎቹ ተተኩ
----------
እንዲያው ግን ለስሙ ሰርካዊ ሰላምታ
አብዝቼ ምሰደው ሐሙስ ሐሙስ ማታ
ይደርሳል ወይ ነቢ ልቤ ሸከከብኝ
ይከነክነኛል የራቁኝ መሠለኝ።
✍️ ሑሴን ኸድር
@whenever11
ድህነት ግን ሲያስጠላ
''የልጅነት ፍቅሬን ላጣ ነው እኮ'' አለኝ። ፊቱን ሳይ አሳዘነኝ 11ኛ ክፍል እያሉ ነበር አንዳቸው ለሌላኛቸው ፍቅር ያደረባቸው። እሷ ''ኒካህ እንሰር እና እንቆይ አሁን ላይ አንድ ላይ መኖር ግዴታ አይደለም'' ብላ ብታስቸግረውም እሱ ፈቃደኛ አልነበረም። ግዴታ የሌለው መብት አያስደስተውም ነፃነት ከተጠያቂነት ጋር አብሮ ነው መምጣት ያለበት ብሎ ያምናል። ከኒካው የሚገኘውን ጥቅማጥቅም ያለበትን ግዴታ ሳይወጣ መጠቀም የ'ግር እሳት ሆኖበታል። አስታውሳለሁ ያኔ ሲያማክረኝ ''አረ ባክህ'' ነበር መልሴ ''በዚህ ግዜ? ደፋር ናት'' አልኩት። በግዜው አስረው ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር ከነበራቸው ፍቅር አንፃር ነው የኔ ምኞት።
በሱ ቦታ ሆነን ስንመለከተው ግን እሱ ልክ ነው ኒካህ በማሰራቸው ምክንያት እሷ ሀላል ትሆንለታለች። እቤቱ ይዟት ስላልገባ ደግሞ ኃላፊነቶች ይቀንሱለታል ወይም ከባዱ የማስተዳደር ኃላፊነት ይነሳለታል። ህይወትን ከሚያጣፍጡ ቅመሞች መሀል በዋነኛነት ኃላፊነት ነው። አስቡት አሁን ላይ ያላችሁ እሴት ባይኖር መኖር ምን ያጓጓል? ብትሞቱ ምድር ላይ ምንም የማይቀንስ ወይ የማይቀነስባችሁ ባይሆን የምቶዱዋቸው ሰዎች ባይኖሩ አልያም የምትሞቱለት አላማ ባይኖራችሁ ምን ያህል ጨለማ ይሆን ነበር ህይወታችሁ።
እርግጥ ነው አሁን ያለንበት አለም ነፃነን ሲጠይቅ ከተጠያቂነት ለይቶ ነው። መብትንም ከግዴታ ለይቶ ያ ግን አያዛልቅም ሰዎች ነፃ ብቻ ቢሆኑ ህግ አይኖርም ህግ ከሌለ ደግሞ ውጥንቅጡ የወጣ አለም ይሆናል። በርግጥ አሁንም አለማችን ውጥንቅጡ ወቷል። ህግ ለአውጪው ስለማይሰራ። እንደዛም ሆኖ ግን ቢያንስ የሆነ ያህል ተጠያቂነት የሆነ ያህል ግዴታ መኖሩ አለማዊ ስርዐት እንዲቆይ ያስችላል። እናም ጓደኛዬ ከዛ አንፃር የአእምሮ ሰላሙን ለመጠበቅ ሲል መብትን ካለ ግዴታ አልቀበልም አለ።
ታዲያ ሁለቱም የኮሌጅ ትምህርታቸውን አጠናቀው ህይወት የተባለ እውነታ ፊት ቀረቡ። እሷን እድሜ ያቻኩላታል እሱ ደግሞ ህይወት። እውነታን መጋፈጥ ከባድ ነው። በተለይ ደግሞ ለድሀ ልጅ! ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ሰው በየሚዲያው ቸገረኝ ሲል የሚያለቅሰው ህዝብ ቁጥር ያስቀኛል። ለምን መሰላችሁ የሚያለቅሰው ለራሡ ችግር ይሆን እንዴ ብዬ ስለማስብ ነው። እንደ ሀገር ደሀ የሆነ ችግር ውስጥ እስከ አናቱ የተዘፈቀ ህዝብ ስለ ምን ብሎ ነው ለሌሎች የሚያለቅሰው? ሰበብ እየፈለገ ለራሱ ያልቅስ እንጂ።
ሴቶች ግደሞ ታናድዱኛላችሁ የወንድን አርፋጅነት እያወቃችሁ ትቸኩላላችሁ እኛ የናንተ መሄድ ለቤተሰብ አለመድረስ ተደምሮ ናላችን ይዞራል። ከዛ ደግሞ ተፈጥሮን እታዘባለሁ እርስ በርስ መፈላለጋችን እየታወቀ አንዳችንን አርፋህ ሌላኛችንን ችኩል የተደረገበት ጥበብ ምን ይሆን ስል አስባለሁ! ለወንድ ሲሆን እድሜ ቁጥር ነው ሲባል ሰውዬውን ለማሞገስ ነው ልክ ሮናልዶ በ41 ሜሲ በ39 አመት እድሜያቸው እንደሚያሳዩን አይነት ተዐምር ለማደናነቅ....... ለሴት ሲሆንስ ማነው እድሜን ከቁጥር ያዘለለው ተፈጥሮ አይደለምን? ታዲያ ማነው መወቀስ ያለበት ተፈጥሮ? ወይንስ ተፈጥሮን ያልተረዱት ተፈጣሪዎች?
የሚቀጥል......ልብ ወለድ ........።
