uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 136
Підписники
+224 години
+4237 днів
+1 19130 днів
Архів дописів
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለክፍለ ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባሎች ፖለቲካዊ ስልጠናዎችን ሰጠ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ለተከታታይ ሶስት ቀናት አጠቃላይ ለክፍለጦር፣ለሻለሻለቃ አመራሮችና አጠቃላይ ለሰራዊቱ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ወሮበላው የኦሮምማው ስብስብ አማራን ለማጥፋት በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከአማራ ግዛቶች ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት እያደርገ መሆኑን አለም የሚያቀው ሀቅ ነው። ሆኖም ይህን የብልፅግና ፋሽስታዊ ስርዐት የአማራ ልጆች በነበልባል ክንዳቸው እየተፋለሙትና እየመከቱ የበላይነታቸው እየወሰዱ ይገኛል። ስለሆነም የአሳምነው አናብስቶች ከትግሉ ጎን ለጎን በተለያዩ ለሰራዊት ፖለቲካዊ ስልጠና ማለትም፦ *የሰራዊት ስነምግባር እና ስነስረዓት መወሰኛ ደንብ *ጓዳዊ ዝምደና *ባህል እና ጨዋነት *ድርጅትና የድርጅት ምንነት *የአማራ ህዝብ ምንነት እና *የገጠሙት ፈተናወች እና ያደረጋቸው ተጋድሎወች *ፋኖነት እና መገለጫ ባህሪያት በሚሉ አርዕስቶች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ ኢያሱ ሙሉጌታ ፣የአሳምነው ዕዝ ህግ ክፍል ሀላፊ አርበኛ ተስፋዬ ገስጥ እና የአሳምነው ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ ለማ በመሆን ከትምህርት እና ስልጠና መምሪያ  በተሰጠው ዕቅድ መሰረት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር  የሻለቃ አመራሮች እና ለሰራዊት አባላት  በበቂ ሁኔታ ስልጠና በመስጠት አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በስልጠናውም የተገኙት የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራር አባላት በስልጠናው የአማራን የሞኖር ነፃነት በቅርቡ እንዲሚያበስሩ እርግጠኛ እየሆኑ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሚሰጣቸውን ማነኛውምንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው ታህሳስ 23/04/2018 ዓ.ም

ልደት 🎂🍰🧁 ክሪስ * ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለው * በአሁን ስአት በህመም ለሚሰቃየው * እንዲሁም ያለ ፍርድ በእስር ቤት የሚማቅቀው * ለያዘለት ዓላም እና ላመነበት ነገር የሚታ
ልደት 🎂🍰🧁 ክሪስ * ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለው * በአሁን ስአት በህመም ለሚሰቃየው * እንዲሁም ያለ ፍርድ በእስር ቤት የሚማቅቀው * ለያዘለት ዓላም እና ላመነበት ነገር የሚታገለው የታላቁ የክርስቲያን ታደለ (ክሪስ) ልደት ነው:: እንኳን ተወለድክ.....ገብርዬ ... መልካም ልደት

ይህ ምስል ሺህ ቃላት የሚተካ መራራ እውነትን ይናገራል። በአስከሬን ላይ መፎከር ጀግንነት ሳይሆን፣ የሥነ-ልቦና ስብራት እና የታሪክ ውርደት መሆኑን የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው በዚህ ዘግናኝ ምስል ላይ የምናየው ትዕይንት የብልጽግና ሰራዊት፣ የሞራል ዝቅጠትና የአውሬነት ማረጋገጫ ነው። ነፍስ በሌለው እና ደሙ በፈሰሰ ንጹሕ ሰው አስከሬን ላይ ጠመንጃ ደቅኖ ለፎቶግራፍ መመቻቸት፣ ከጦርነት ሕግም ሆነ ከሰውነት ተራ መውጣትን ያበስራል። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እውነተኛ ጀግና ጠላቱን በክብር ያሸንፋል፤ የሞተን ሰው ደግሞ በክብር ይሸኛል። በአስከሬን ላይ መሳለቅ ግን በውጊያ ሜዳ ድል ለራቀው፣ በውስጡ ፍርሃት ላነገሰ እና ሰብዓዊነቱን ላራገፈ ኃይል የሚሰጥ የሽንፈት ማስታገሻ ነው። ጀግና ፊት ለፊት ካለው ኃይል ጋር ይገጥማል እንጂ፣ መሬት ላይ በወደቀ አስከሬን ላይ የጥይት አፈሙዝ አያሳይም። ይህ ጀግንነት ሳይሆን "የሞራል ኪሳራ" ነው። ዛሬ እነዚህ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂብም ወታደሮች በአስከሬን ላይ ቆመው የሚነሱት ፎቶ ለፕሮፓጋንዳና ለጊዜያዊ መዝናኛ ሊሆናቸው ይችላል። ነገር ግን ታሪክ አይረሳም፤ ቴክኖሎጂም አይደመስሰውም። እያንዳንዱ እንዲህ ያለ ምስል ነገ በፍትሕ አደባባይ የገዛ ወንጀላቸውን የሚያረጋግጥባቸው ዋነኛ የክስ ሰነድ ይሆናል። ፋሽስት ጣሊያንና የናዚ ኃይሎች እንዲህ ያሉ የጭካኔ ድርጊቶችን በመፈጸም ሕዝብን ለማንበርከክ ሞክረው ነበር። ውጤቱ ግን ተገላቢጦሽ ሆነ፤ ጭካኔው የሕዝብን የነፃነት ወኔ አቀጣጠለው። ዛሬም በዚህ ምስል ላይ የሚታየው ግፍ የሕዝብን እንባ ወደ ቁጣ፣ ቁጣውንም ወደ ነፃነት ትግል ይለውጠዋል እንጂ አያሸንፈውም። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሆይ፤ ይህ ምስል ብቻውን የጦር ወንጀል (War Crime) መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ህያው ማስረጃ ነው። ዝምታ ለገዳዮች እውቅና መስጠት ነው። በአስከሬን ላይ የሚሳለቅ፣ ንብረት የሚያቃጥልና ንጹሐንን የሚያድን ሰራዊት የሀገር መከታ ሊባል አይችልም። ዓለም ይህንን ግልጽ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊያወግዘውና ገዳዮችን ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል። ንጹሐን ይሞታሉ፣ ቤቶች ይቃጠላሉ፣ አስከሬኖች ይረገጣሉ፤ ነገር ግን የእውነት ብርሃንና የነፃነት መንፈስ ፈጽሞ አይሞቱም። በአስከሬን ላይ ቆሞ የሚፎክር ሥርዓት የውድቀቱ ዋዜማ ላይ መሆኑን ይህ ምስል ምስክር ነው። ፍትሕ ለተገደሉ ንጹሐን! ውርደት በአስከሬን ላይ ለሚፎክሩ ጨካኞች! ከኤልያስ በላቸው ገፅ የተወሰደ @highlight:-👉 Estibel Alemu Zerihun

ደራሲ፣ አርበኛ እና ታዋቂው የፋኖ መሪ የነበሩት ኮማንደር አሰግድ መኮነን በአገዛዙ ተሰውረው እስከ-አሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደ-ማይታወቅ እና ፍርድ/ቤት እንዳልቀረቡ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ጭምር
ደራሲ፣ አርበኛ እና ታዋቂው የፋኖ መሪ የነበሩት ኮማንደር አሰግድ መኮነን በአገዛዙ ተሰውረው እስከ-አሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደ-ማይታወቅ እና ፍርድ/ቤት እንዳልቀረቡ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ጭምር የአገዛዙን ወንጃል እያጋለጡ ይገኛሉ። ### ሁላችንም ያለማቋረጥ እንጠይቅ.. ጋሽ አሰግድ የት ናቸው? ብለን ልንጠይቅ ይገባል። ጀግናውን የረሳ ማንነቱን እና ታሪኩን እንደረሳ ይቆጠራል! ጀግናውን የረሳ ብቻውን ቢሮጥ እንኳ አያሸንፍም! አሁንም እጠይቃለን where is he? የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/MerebMedia24

🔜ሰበር መረጃ ከግንባር:-👉👉👉 ፋኖ ወደ ጠላት ምሽግ ተስቦ በመግባት በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በምሽጉ ውስጥ የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮችን ሙሉ በሙሉ መደ-ም-ሰ-ሱን አስታወቀ! ፍጥነትን፣ ጀግንነ
🔜ሰበር መረጃ ከግንባር:-👉👉👉 ፋኖ ወደ ጠላት ምሽግ ተስቦ በመግባት በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በምሽጉ ውስጥ የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮችን ሙሉ በሙሉ መደ-ም-ሰ-ሱን አስታወቀ! ፍጥነትን፣ ጀግንነትና ኃያልነት እንዲሁም ጥልቅ የሽምቅ ሳይንስ እውቀትን ያጣመረ ነው በተባለው በዚህ ኦፕሬሽን፡ ምሽጉ በቦ-ም-ብ ብትንትኑ የወጣበትና በምሽጉ ውስጥ የነበሩ የጠ-ላ-ት ወታደሮችም የእ-ሳ-ት እራት ሆነው የቀሩበት ድል መመዝገቡ ታውቋል:: በዝርዝር እንመለስበታለን።

ሠሞኑን በመላው አማራ ክልል -ህዝቡን እየሰበሰቡ '' ደውሉላቸው ፣ መቶ ሺ ብር እንሰጣችኋለን በሏቸው ፣ በሬ እንገዛላችኃለን ኑ ግቡ በሏቸው ፣ መንግስት መሬት ይሰጣችኃል በሏቸው ፣ ...'' እያሉ ማስገደድ ተጀምሯል! በጣም ያሳፍራል! ይህ ትውልድ የሚታገልለትና የሚሞትለት ኮዝ እንዳለው እንኳ እስካሁን አልተረዱም። ወይ ደግሞ ለመረዳት አይፈልጉም። ዛሬም ይሄን ትንታግ ትውልድ ለገንዘብና ለጥቅም ጫካ እንደገባ አድርገው ነው የሚያስቡት! ታዲያ በዚህ እሳቤ ላይ ካለ ሀይል ጋር በምንስ አይነት መልኩ በጥቂቱ እንኳ ልትግባባ ይቻልሃል? ትናንት በአምባሰል ውጫሌ ከተማ በነበረው ስብሰባ ለህዝቡ ተመሳሳይ ሀሳብ አቅርቀው ሲነተርኩት '' አልናገርም '' በማለቱ በነዋሪዎች ላይ የጅምላ አፈሳው ተጠናክሮ መቀጠሉን ለማረጋገጥ ችያለሁ! ስህተትን በስህተት ለማረም የሚደክሙ ከንቱ ፍጡራን!😥

በ54ኛ ክ/ጦር ባሉ ሻለቃዎች በወትሮ ዝግጁነትና በወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ተደርጓል ። ➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠ ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም የሻለቃዎችን ወትሮ ዝግጁነት በመፈተሽ የ54ኛ ክ/ጦር የሻለቆችን የአደረጃጀት ስራዎች በመዋቅሩ ለአባሉ በዓላማቸው ላይ በስርፅት በመንገር ህዝባችን እና ድርጅታችን የመጠበቅ እና የማዳን ተግባር በመተባበር በአንድነት መስራት የጋራ ሀላፊነታችን መወጣት እንዳለብን አስተውሎት እንዲኖራቸው ተደርጓል። ከአባሉ ጋር በጥልቀት በመወያየት ችግሮችን በጥልቀት በመለየት በመፍታት መግባባትና የትግሉን ዕድገት በተሻለ ግለት ማስቀጠል እንዲሁም በቀጠናው የተሻለ ከወትሮው በበለጠ በስነምግባር በማነፅ የወጣንለትን አላማ በማስገንዘብ በጥምረት ኦፕሬሽን መደረግ እንዳለበት የመግባባት ስራ ተስርቷል። ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

"ወ/ሮ አየሁ አበባየሁ እና ወ/ሮ አታላይ አንቴ በጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ትዕዛዝ ተገደሉ" 206ኛ ኮር ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም ወ/ሮ አየሁ አበባየሁ እና ወ/ሮ አታላይ አንቴ የ57 እና የ55 ዕድሜ ላይ ያሉ እናቶች ሲሆኑ ትዳር ቀልሰው ልጆችን ወልደው ባሳደጉበት ቂየ ጥቅጥቅ ባለው ጨለማ በ6ኛ ዕዝ አዛዥ ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ትዕዛዝ በአረመኔው ሰራዊት ተገድለዋል። ወ/ሮ አየሁ አበባየሁ በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ በነብር ገደል ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ የአረመኔው ሰራዊት ከሌሊቱ 5:00 ሰዓት ቤታቸውን በኃይል ገንጥሎ በልጆቻቸው እና በባለቤታቸው በአቶ ግዛቸው ወንዴ ፊት  በጭካኔ ተረሽነዋል። የአማራን ህዝብ ስነልቦና ለማድቀቅ በጭካኔ እናቶችን እየገደለ የሚገኘው የአረመኔው ሰራዊት የ6ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ብርሀኑ ጥላሁን ባስተላለፈው ትዕዛዝ እናቶችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀመ ነው። ይህ የጭካኔ ተግባር በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋባል ወረዳ የረብረብ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት የ55 ዓመቷ ወ/ሮ አታላይ አንቴ በአረመኔው ሰራዊት ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት  በቤታቸው ሳሎን ከልጇቸው ፊት ለፊት ተንበርክከው ልጅችን አጥብጠው ባሰደጉባቸው ጡቶች የጥይት በረዶ ዘንቦባቸዋል። አስገድዶ መድፈር እና ንፁሀንን በጭካኔ መግደል እንደ ትልቅ የጦርነት ስልት በመጠቀም የአማራን ህዝብ ለማንበርከክ ግልፅ ትዕዛዝ ያስተላለፉት ጀነራሎች በጭካኔ በሚገድሉት ህዝብ መሀል የሰላም አምባሳደር ሁነው መቅረባቸው በህዝቡ ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል። ማይክ ጨብጠው ከሰንበቴ አፍሰው አዳራሽ ባስገቡት ህዝብ ፊት የሰላም መናንያን ሁነው የተገኙት እነ ብርሀኑ ጥላሁን ሰራዊታቸውን ልከው እናቶችን መጨፍጨፋቸውን ሊያቆሙት ግን አልቻሉም። የአማራ ህዝብ ይህን ትግል እንደ አራስ ልጁ አቅፎ ይዞታል የሚታለል የሚሸወድ ለአረመኔዎች የሚገዛ የድሮው ህዝብ ዛሬ የለም አዲሱ ትውልድ በአዲስ የትግል ስልት ስርዓቱን ነቅሎ ነፃነቱን ይተክል ዘንድ አምርሮ መታገሉን አጠናክሮ ይቀጥላል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በምዕራባዊ ቤተ ዐማራ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር እንደ ንስር ታድሶ እየመጣ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ከደ
+1
በምዕራባዊ ቤተ ዐማራ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር እንደ ንስር ታድሶ እየመጣ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ በሚገኙ 11 ወረዳዎች የሚያካልል ሰፊ ቀጠና የሚሸፍን ነው። አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የንስሮች ስብስብ ነው ስንል ያለ ምክንያት አይደለም!! ዓላማችን ተባብረን መዳን ነው!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

ብአዴናውያን ወደው የገቡበት ቁማር ይሄ ነው። በአብይና ሽመልስ የሚመራው ኦሮሙማ መዳረሻ ግቡ በየቢሯቸውና በሀብላቸው አጫዋች ሁሉ አንጠልጥለውት የሚዞሩት ከስር የሚታየውን ካርታ ነው። መላላክን የፖለ
ብአዴናውያን ወደው የገቡበት ቁማር ይሄ ነው። በአብይና ሽመልስ የሚመራው ኦሮሙማ መዳረሻ ግቡ በየቢሯቸውና በሀብላቸው አጫዋች ሁሉ አንጠልጥለውት የሚዞሩት ከስር የሚታየውን ካርታ ነው። መላላክን የፖለቲካ ጠቢብነት አድርጎ የሚመለከቱት ብአዴናውያን በኢትዮጵያ ስም እየማሉ ጠብ እርግፍ እያሉ የሚላላኩት ይህን የኦሮሙማ ፕሮጀክት ለማስፈፀም ነው።ነገር ግን የትኛውንም የደም እዳም የሚከፍሉት፡ራሳቸው ብአዴናውያን እንደሆኑም ታሪክ መዝግቦ ይዞታል። አሁን የአማራ ጠላት ሁሉ ህልማቸው በሰሜንም በደቡብም የአማራን ርስት ነጥቆ እና ህዝቡን ጨፍጭፎ የራሱን ሃገር ከኢትዮጵያ ይዞ መውጣት ነው። አማራ እነዚህን ነው እየታገለ ያለው!! ቢያስቡም ቢፍጨረጨሩም እንደማይሳካላቸው ሀገር ያወቀው ሀቅ ነው ግን ለጊዜው የንፁሀንን ንበረትና ህይወት እየቀጠፉ ስለሆነ ማንኛውም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከጎናችን መሰለፍ አለበት ብለን እናምናለን!!

"ከአማረነቱ_ይልቅ_ሆዱ_የበለጠበት_የቢቸና_ከተማ_ቀንደኛ_ባ*ን*ዳ_ሚሊሻ_ገበና_ሲጋለጥ" ሰሞኑን በ64 ከፍለ ጦር ቀጠና እነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ በነበረው የብአዴን/ብልፅግና ስብሰባ የአካባቢው ማህበረሰብ በመምሰል #ጋቢ_በመልበስ  በቢቸና ከተማ የፋኖን ስም በሐሰት በመወንጀል #በtiktok_facebook አገዛዙ በአዘጋጃቸው ሚዲያዎች የፋኖን ስም በሐሰት የሚያጠለሹ ግለሰቦች የአገዛዙ #ገሚሱ_ብአዴን #ሚሊሻ መሆናቸውን ህዝባችን እና የትግሉ ደጋፊ እውቅና እንዲኖራቹህ በትህትና እናሳውቃለን። የመድረክ ተናጋሪዎች በእነማይ ወረዳ የትመን፣ ዘብች ፣ ሁለት አንባ ዳቢሳ ፣ወይራ ጠልማ፣ ማህበረብረሃን ቀበሌ እና ቢቸና ከተማ የሚገኙ ንፁሀን ማህበረሰብ ሀብት ንብረት በዝረፊያ ስራ ላይ የተሰማሩ የብአዴን #ገሚሶቹ_ሚሊሻ እና የአማራን ህዝብ በመክዳተሰ የአገዛዙ ቅጥረኛ መረጃ ሰጭ የካድሬ ቤተሰቦች መሆናቸውን ላረጋግጥላቹህ እወዳለሁ። የፋኖን የትጥቅ ትግል #ጋቢ_በመልበስ አርሶ አደር በመምሰል የሐሰት ፕሮፖጋንታ በመንፋት የረከሰ ፖለቲካውን በማህበራዊ ሚዲያው ተቀባይነትን ለማምጣት የሚሞክረው #ብአዴን_ብልግና ከወደቀበት አዙሪት ለመነሳት መሞከር ከንቱነት ወይም ቅዥት ብቻ ነው። በውሸት የረከሰ ፖለቲካ እና ፕሮፖጋንዳ የአማራ ህዝብ አይደናገርም ትግሉም አይንኮላሽም! ሰሞኑን በአሚኮ የሚዲያ ድረገፅ በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ በነበረው መድረክ የሚናገሩ ግለሰቦች የአማራን ህዝብ በመካድ በቢቸና ከተማ የሚገኘውን አገዛዝ በመደገፋ #ጋቢ_ለብሰው አርሶ አደር በመምሰል የፋኖን ትጥቅ ለማንኮላሸት የውሸት ንግግር ከአደረጉት ውስጥ በፎቶ የምታዮቸው ጥቂቶቹ ናቸው። ‎1ኛ. ሚሊሻ ይርጋ ብዙአለም ሁለት አምባ ዲቢሳ ሊቀ መንበር የነበረ ‎2ኛ. ሚሊሻ ሰይድ ጫኔ የቢቸና ከተማ ቀንደኛ ሚሊሻ  ‎3ኛ. ሚሊሻ አደገ ታዱ ጎተራ ሊቀመንበር የነበረ ‎4ኛ. ሚሊሻ ጤናው አብተው ብቸና ደብር ሊቀመንበር የነበረ ‎5ኛ. ፲ አለቃ አዳነ ተሾመ እና ሌሎቹ የመከላከያ ምልስ ሚኒሻ ሲሆኑ ሰሞኑን #በtiktok_facebook እና መሰል የአገዛዙ ሚዲያዎች ለፋኖ የሀሰት ስም በመስጠት የተስተዋሉ ቢቸና ከተማ #ቀንደኛ_ባንዳ መሆናቸውን እናረጋግጣለን። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !!            ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም

@@ስቦ ማስከዳቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው@@ ታህሳስ 23/2018ዓ.ም ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የአገዛዙ
+2
@@ስቦ ማስከዳቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው@@ ታህሳስ 23/2018ዓ.ም ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የአገዛዙ ሰራዊት በገፍ እየፈረሰ የፋኖ ኃይሎችን እየተቀላቀለ ይገኛል:: በዛሬው ዕለትም ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም አገዛዙ እንደ ቀንድ አውጣ በአንድ ኪሎሜትር ራዲየስ ጭንቅላቱን ቀብሮ ከሚገኝባት ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ ከ52ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት ወ/ር ጌታነህ ፈንታዬ የተባለ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ወታደር የደባይ ጮቄ ሻለቃን ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል። ከአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ አረመኔ ሰራዊት ከ52ኛ ክ/ጦር በዚህ ወር ብቻ ከ 18 በላይ የሚሆኑት የደባይ ጮቄ ሻለቃን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን በክብር ለተቀላቀሉት ትልቅ ክብር በመስጠት አሁን አብዛኞቹ ከደባይ ጮቄ ሻለቃ ጋ በሐቀላቀል አማራዊ ኃላፊነታቸውን አመት የተኸጡ ይገኛሉ!!!!   አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!!   Hailemariam Kiber Temesgen   አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል

የህዝቡን አንድነት በማፅናት አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስታወቀ። ታህሳስ 23/ 2018  ዓ.ም   በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመልሶ ማደራጀት ትግበራው የህዝብን አስተዳደር የፀጥታና የፍትህ ጥያቄዎችን በመመለስ አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነትን   እንዲያረጋግጥ ታስቦ በአዲስ የተዋቀረው ጊዚያዊ መንግስት በ206ኛ ኮር ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች አገልግሎት በመጀመር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ከጠላት ነፃ በወጡ ሁሉም ቀበሌዎች የአስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የፍትህና ህግ አገልግሎት፣ ፀጥታ፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በፍጥነት ምላሽ በመስጠት አመርቂ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን የወረዳው ጊዚያዊ መንግስት ገልጿል። የህዝብን አስተማማኝ ደጀንነት በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ጊዚያዊ መንግስቱ የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በማረጋገጥ እንደቻሉ በማውሳት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ድርጅታዊ ግዳጅ ከመደበኛ ሰራዊቱ ጎን ተሰልፈው እንደሚወጡም አረጋግጧል። በመልሶ ማደራጀት ትግበራው ባንዳዎችን በማፅዳት የሰራዊቱን የህዝቡንና የትግሉን ደህንነት በማስጠበቅ የጠላትን እረጅም እጅ እየቆረጠ የሚገኘው 206ኛ ኮር ለደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች፣ በህግና እና ስነ-ስርዓት  እንዲሁም በጊዚአዊ መንግስት መመሪያዎች ላይ ከ14ኛ ክ/ጦር አመራሮች ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጧል። የድርጅቱን ህግ እና ደንብ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የፀደቁ መመሪያዎች ላይ ስልጠና የተሰጣቸው የወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች ህዝቡን ለማስተዳደርና የድርጅታችንን ህግና ደንብ ለማስፈፀም በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ተናግረዋል ። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ፣ ዶ/ር ካሻ ተሻገር ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያምንና ሌሎች ፖለቲከኞች ጋዜጠኞችና የግፍ እስረኞችን በተመለከተ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው። እነ ክርስቲያን ታደለ ይቅርታ ጠይቀው ሊፈቱ ነው፣ ፓርላማውንም ይቅርታ ሊጠይቁ ነው ወዘተ የሚለው መረጃ ብልፅግና በአማራ ክልል ከሰሞኑ በተለያዩ ከተሞች እያደረገ ላለው የፖለቲካ ቅስቀሳ ማጀቢያ እንዲሆን ታልሞ እየተሰራ ያለ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ አንደሆነ ተረጋግጧል። ብልፅገና እሰኞች ክርስቲያን ታደለን ከዳኸን ብለው ደበደቡት የሚልም ሀሰተኛ መረጃ ተሰራጭቷል። ምናልባት የታሰሩት ጋሻው መርሻና በለጠ ሞላ ቢሆኑ ይሄ መረጃ ይታመን ነበር። ቅሉ ግን የታሰሩት ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቧያለውና መሰል የቃል ሰዎች ናቸው። በተለይም አቶ ክርስቲያን ታደለ አቶ ዮሐንስ ቧያለውና ዶክተር ካሳ ተሻገርን ና ሌሎችን በተመለከተ በህዝቡ ዘንድ የሚነሱ ግልፅ የሆኑ ተወካዮቻቸን ታሰሩብን ፣ ሰላማዊ ፖለቲካ ብልፅግና አይወድም ፣ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ይደረግ የምትሉት ውሸት ነው የሚሉ መሰል ጥያቄዎችን በየ አዳራሹ ለማፈን አልሞ አገዛዙ የሚያሰራጨው ይህ ስም ማጥፋት ብሎም ተሸናፊ ናቸው ማለትን ያካተተ የደንቆሮ ፕሮፖጋንዳ ነው። ሌላው እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ ይቅርታ ጠይቀው ሊፈቱ ነው በማለት ጥፋት እንዳጠፉና ወንጀለኛ እንደሆኑ በማስመሰል ነገር ግን ይቅርታ ጠይቀው ሊወጡ ስለሆነ የፋኖ አባላትም ይቅርታ እየጠየቃችሁ ግቡ የሚልን ማጭበርበሪያም የያዘ ነው። አፈና የተፈፀመባቸው እነዚህ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞችና የአማራ ሙህራን ላለፉት ሶስስተ አመታት ምን አይነት የረባ መስረጃ አቅርቦ ወንጀለኛ መሆናቸውን ማረጋገጥና ማስመስከር ያቀተው ብልፅግና በህግ ውሳኔ ሊፈታተው ባለመቻሉ ይቅርታ ይጠይቁ የሚል ቅስቀሳ ውስጥ ገብቷል። ከመጋረጃ ጀርባ ጭምር ተከልለው የቀረቡ ምስክሮች የረባ ማስረጃና ወንጀለኛ የሚያስብል ምስክርነት ሊያስመዘግቡ ለመቻላቸው አሁን ላይ በነፃ መለቀቀቅ ያለባቸውን የግፍ እስረኞች ይቅርታ ጠይቀው ሊፈቱ ነው በማለት ልዩ የማደናገር ዘመቻ ጀመረዋል። ዘመቻው በአማራ ህዝብ እንዲሁ በፋኖና በእስረኞች መካከል መጠራጠር እንዲፈጠር ያለመ ሲሆን በዋናነት ግን በፖለቲከኛነታቸው ፣ በአመለካክታቸውና በማንንታቸው የታሰሩትን አማራዎች አቅመ ቢስና ተሸናፊ ሆነው ይቅርታ ጠይቀው ሊወጡ ነው በማለት በምስር ከተለወጡ ጓዶቻቸው ጋር ለማስተካከል የተደረገ ጥረት ነው። በዋናነት አገዛዙ እነዚህን የግፍ እስረኞች ይቅርታ ጠይቆ መፍታት አለበት። ይቅርታ ጠይቆ ባይፈታ እንኳን ፖለቲካዊ ውሳኔ በማሳለፍ በምህረት አዋጅ መሰረት "ምህረት" አደረግሁ ብሎ መፍታት ግዴታው ነው። በሁሉም መንገድ ስንመለከተው ብልፅግና ብልጥ ሆኖ ጨዋታ ቢጀምርም ተሸናፊና ከሳሪው ግን እሱ ነው። © ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው