uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 061
Підписники
+224 години
+4287 днів
+1 25730 днів
Архів дописів
አንዳንድ ነገሮች ላይ እንዲህም እናውራ መሰለኝ! 1. ወታደራዊ አመራር አይዋሽም። ሲናገር በአሀዝ፣ ሁኔታና ተጨባጭነት ያቀርባል። ለፕሮፓጋንዳ የምናወራው ውሸት ሳይሆን ለሀቅ የምንናገረው እውነት ቢኖ
አንዳንድ ነገሮች ላይ እንዲህም እናውራ መሰለኝ! 1. ወታደራዊ አመራር አይዋሽም። ሲናገር በአሀዝ፣ ሁኔታና ተጨባጭነት ያቀርባል። ለፕሮፓጋንዳ የምናወራው ውሸት ሳይሆን ለሀቅ የምንናገረው እውነት ቢኖር ትግሉ ሶስት ወሳኝ የትግል ምዕራፍ የእድገት ደረጃዎችን አልፏል። በስትራቴጂካል ድል ይጠብቁን። 2. ባህርዳር ላይ የመሸገው የአብይ አገዛዝ ሀይል በምናውቃቸው አብሮ አደግ ወጣቶች በኩል የህዝብ በደል ትብብርን እያገኘ ነው። በመሆኑም ከንፁሀን እገታ ጀርባ የአገዛዙን ይሁንታ ያገኙ በርካታ ወጣቶች እጃቸው እንዳለበት ዝርዝር ማስረጃ አለን። የድምፅ ቅጅ፣ ባንክ ትራንዛክሽንና የውሎ ትስስር ማስረጃዎች ቀስ እያሉ ሂደቱን ጠብቀው ይገለፃሉ። እነዚህ አካላት ጋር በማንኛውም ሰዓት ልንፈራረድበት የምንችልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። እነዚህ አካላት የእገታ ሰነዳቸው የሚያነፃፅረው ደግሞ ፍፁም ንፁህ፣ ሰርቶ አደር ነጋዴ፣ ህክምና ባለሙያ፣ ቅቡልነት ያላቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ትኩረት ያደረገ የደም ንግድ ሲሆን ከአረፈደ አራዳ ሚሊሻ እስከ ብርጋዴል ጀኔራል የገበያው ትስስር ፈጣሪ ናቸው። ለሆድ አምላካቸው ማለት የምንፈልገው ነገር “አንተዛዘብ እረፍት አድርጉ” ብቻ ነው። 3. የትግሉ አጋር መሆን የምትፈልጉ አካላት ፋኖ በየትኛውም ቀጠና ውስጥ ይዘትና ቅርፁን ቀይሮ ከጎንህ ስላለ ነካ አድርገህ ጠይቅና ተቀላቀል፤ አግዘው። ከጎንህ ግራና ቀኝ ወይም ከፊትና ኋላ ሲራመድ የምታያቸው አራት ሰዎች ካሉ ሶስቱ የፋኖ አባል ነው። ሳትፈራራ ተነጋገር። አይቀሬ ለሆነው የድል ብስራት የራስህን ሚጢጢዬ አሻራ አሳርፍ። አካላችን መሆን ለምትፈልጉ ሁሉ በራችን ክፍት ነው። Manchilot Esun

የአገዛዙ ተቋሙ እየተናደ ነው‼️ ጥር16/2018 ዓ.ም ስቦ ማስከዳት:➔ ከአንድነቱ ምስረታ ጋር ተያይዞ በዛሬው እለት ሁለት የመከላከያ አባላት 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺➺➺
+3
የአገዛዙ ተቋሙ እየተናደ ነው‼️ ጥር16/2018 ዓ.ም ስቦ ማስከዳት:➔ ከአንድነቱ  ምስረታ ጋር ተያይዞ በዛሬው እለት ሁለት የመከላከያ አባላት 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ 1.ልንገረው ዘዉድ....25ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት 2.አሸናፊ አሰፋ......25ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት  ሰዴ ወረዳ  መሽጎ ከነበረው ካምፕ በመውጣት በዛሬው እለት54ኛ ክፍ ለጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

🔥#ወታደራዊ_አፈሳ‼️ በምዕራብ አማራ ቀጠና (ጎጃም ላይ) ከሰሞኑን ከፍተኛ ወታደራዊ አፈሳ እየተደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በደንበጫ ፣ በጅጋ፣ በቡሬ ፣በፍኖተሰላም ፣በቢቸ
🔥#ወታደራዊ_አፈሳ‼️ በምዕራብ አማራ ቀጠና (ጎጃም ላይ) ከሰሞኑን ከፍተኛ ወታደራዊ አፈሳ እየተደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በደንበጫ ፣ በጅጋ፣ በቡሬ ፣በፍኖተሰላም ፣በቢቸና ፣በደባይ ጥላት ግን፣ በባህርዳር እና ደብረማርቆስ  በርካታ ወጣቶችን በማፈን ላይ ይገኛሉ። በዚህ አፈና የ10 አመት ህፃናት ሁሉ መታፈሳቸውን የአይን እማኞች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️ ስለሆነም ከአሸባሪው ወታደራዊ አፈሳ ራስን ለመጠበቅ እንቅስቃሴን መገደብ ወይንም አናብስቱ ወደተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች መሄድ ይጠበቃል‼️

#33ኛን #ክፍለ-ጦር #እንደ_ንሥር_ያደሰ_ትምህርታዊ_ግምገማ_ተካሄደ ══════════🕊❁✿❁🕊══════════ (ጥር 16/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት) የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐፋብን) 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር በውስጡ የነበሩ ችግሮችን አርሞ ወደ ተሟላ አቅሙ ተመለሰ። ከድርጅት አመራር እስከ ሬጅመንት አመራርና አባላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ምክክር በክፍለ-ጦሩ የነበሩ ችግሮች በጥልቀት ተነስተዋል። በየደረጃው ለተነሱ ችግሮችም በሚመለከታቸው የድርጅቱ እና የኮሩ አመራሮች ጥልቅ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ መግባባት ተችሏል። የማስተካከያ ሀሳብ እና ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎችም ከሚመለከታቸው የድርጅቱ አመራሮች መፍትሔ ተቀምጧል። ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዐፋብን አመራሮች የአባላትን መብትና ደኅንነት ለማስጠበቅ በአግባቡ ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠይቋል። በተያያዘም በሕዝቡ እና በድርጅቱ ሕልውና ላይ ችግር ለሚፈጥሩ ማንኛውም አይነት አዝማሚያዎችና ድርጊቶች ያለ ምሕረት ሊሠራ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የክፍለ-ጦሩን ቁመና በተፈተሸበት በዚህ ምክክር፤ ድርጅቱ የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ማስመለስ የሚችሉ ጥራት ያላቸው መሪዎችን እና አባላትን ለማፍራት አልሞ መሥራት እንዳለበትም በተሳታፊዎች ተነስቷል። በባህል እና በአኗኗር ታሪካዊ አንድነት የነበራቸው የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ እና የአርበኛ ዮሐንስ ዓለማየሁ ልጆች በነበራቸው ምክክር አስቸጋሪ የተባሉ የአሠራር ክፍተቶችን በጋራ አርመው ጠላትን ለመደምሰስ የሚያስችል ቁመና ይዘው ወጥተዋል። የ102ኛ ኮሩ 33ኛ ክፍለ-ጦር የጋራ ችግሮችን በግምገማ በመፍታት ለሚሰጡ አዳዲስ ግዳጆች በተሟላ አቅም ላይ መኾኑ ተረጋግጧል። በመጨረሻም 102ኛ ኮር ባልተሟሉ የሬጅመንት አመራሮችም አመራር የመተካት ሥራ ሠርቶ የቀጣይ አቅጣጫወችን በማስቀመጥ እና ለአመራሩ እና ለአባላት የሥራ ስምሪት በመስጠት ምክክሩ ተቋጭቷል። የድርጅቱ ልዩ ዘመቻ ም/አዛዥ ፶ አለቃ መኰንን ይፍሩ፣ የ102ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ዘውዳለም አዱኛ፣ የ102ኛ ኮር ጊዜያዊ መንግሥት ሰብሳቢ አርበኛ ይፍረድ ውዴ፣ የ102ኛ ኮር ጦር አዛዥ ፻ አለቃ ይንገሥ ብርሃኔ፣ የ102ኛ ኮር ም/ጦር አዛዥ ፶ አለቃ መኳንንት አበጀ፣ የ102ኛ ኮር ጦር አዛዥ ፻ አለቃ ሥራው ወ/እግዚአብሔር፣ የ102ኛ ኮር የፖለቲካ ዘርፍ አርበኛ ማንችሎት ጥላሁን፣ የ102ኛ ኮር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አርበኛ ትዕዛዙ በቀለ፣ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ አርበኛ ታደሠ አስማረ፣ የ102ኛ ኮር ኦርዲናንስ ፻ አለቃ አዳሙ እንዳለው፣ የ102ኛ ኮር ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር አርበኛ ፀጋየ ፈንታሁን እና የ33ኛ ክፍለ ጦር ሙሉ አመራሮች፣ የ33ኛ ክፍለ ጦር ሬጅመንት መሪዎች፣ እንዲሁም የ33ኛ ክፍለ ጦር የጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች በውይይቱ ተገኝተዋል። ነፃነታችን በክንዳችን ይረጋገጣል‼

ግርም የሚለኝ ነገር እጅ ሰጡ የሚባሉት ሃይሎች እጅ የሚሰጡት ለማነው ለብልፅግና/ለጨፍላቂው ስርዓት መጀመሪያ ወደ ትግል ስንገባ አላማ ኖሮን ሊሆን ይገባል አላማ የሌው ታጋይ እንሰሳ ነው ህዝቤ እየተ
+5
ግርም የሚለኝ ነገር እጅ ሰጡ የሚባሉት ሃይሎች እጅ የሚሰጡት ለማነው ለብልፅግና/ለጨፍላቂው ስርዓት መጀመሪያ ወደ ትግል ስንገባ አላማ ኖሮን ሊሆን ይገባል አላማ የሌው ታጋይ እንሰሳ ነው ህዝቤ እየተሰቃየ በማንነቱ ተለይቶ እየተገደለ ባለበት ስዓት እጅ መስጠት አላማቢስነት ነው ለእኔ ይህን ህዝብ ታግለን ነፃ እንደምናወጣው እርግጠኛ ነኝ የብላኝላቸው በሆዳቸው የህዝብን ትግል አሳልፈው ለሸጡት ባንዳዎች! የእኛ ትግል በግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን ድርጅታዊ አሰራርን የሚከተል በመርህ እና በአሰራር የሚያምን የህዝብን ጥያቄ ለማስመለስ የሚታገል እንጂ ማንም ባንዳ እንደ ፈለገ የሚያሽከረክረው ትግል አልጀመርንም ዛሬም ነገም አሸናፊዎች እኛው ፋኖዎች ነን ምክንያቱም ማሰልጠን ማደራጀት ማሰታጠቅ የዘወትር ስራችን ስለሆነ አፋብንን ይዘን ወደ ፊት። ጀግኖች በስራ ላይ ናቸው ለማለት ነው።

ማስጠንቀቂያ ለከተማ ወጣቶች በምዕራብ አማራ ቀጠና ጥምቀትን ሲያከብሩ የፋኖን ስም ጠርተው ጨፍረዋል በማለት የብልፅግና ሰራዊት እያፈነ ይገኛል። እስካሁን በቡሬ ፣በፍኖተሰላም ፣በቢቸና ፣በደባይ ጥላት
+1
ማስጠንቀቂያ ለከተማ ወጣቶች በምዕራብ አማራ ቀጠና ጥምቀትን ሲያከብሩ የፋኖን ስም ጠርተው ጨፍረዋል በማለት የብልፅግና ሰራዊት  እያፈነ ይገኛል።   እስካሁን በቡሬ ፣በፍኖተሰላም ፣በቢቸና ፣በደባይ ጥላት ግን፣ በባህርዳር እና ደብረማርቆስ  በርካታ ወጣቶችን በማፈን ላይ ይገኛሉ። በቢቸና ከተማ ያፈኗቸውን ሁለት ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሏቸው ሲሆን ሌሎችን ወደአልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸው አረጋግጠናል።     በመሆኑም ከተማ ላይ ከብልፅግና ጉጇ ስር የምትገኙ የአማራ የቁርጥ ቀን ወጣቶች ራሳችሁን ጠብቁ ።ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ ወንዶች ቦታ ተቀላቀሉ ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር በጊዜያዊ አመራሮች የተሰጠ የአደረጃጀት መግለጫ፡- የአደረጃጀታችን መነሻው መሰዋትነት፣ ፅናት፣ ሃቀኝነት፣ ታማኝነት፤ አገር ሰሪነት፣ ለአማራነታቸው መሰዋዕት ለሆኑ ጀግኖች መታመን፣ ከፍያለው ደሴን በሕይወት ሳለ ብቻ ሳይሆን ተሰውቶም የምኮራበትና የምንመካበት እንስፍስፍ ልጆቹ አለን። ''ከማይመስልህ ጋር አትጠመድ'' እንደሚባለው፤ ከማይመስሉን ጋር ጎን ለጎን እየተጠራጠሩ ከመኖር፤ መመንጠሩ የተሻለ በመሆኑ ፤ የብብት መዥገሮችን አራግፈን እንደ ንስር ታድሰን፣ እንደ ዝሆን ገዝፈን፣ እንደ ነብር ተቆጥተን፣ የምንነሳ የከፍያለው ልጆች እንጂ፤ የንዋይ ፍቅር አሳብዶን፤ የከተማ ቦታ አማሎን እርካሽ የብልፅግና ስልጣን ፈልገን ጫካ አልወጣንም። የአባቶቻችን እና የወንድሞቻችን እርም የምንበላ ከዳተኞችም አይደለንም። ክህደት ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፤ እንዲህ ዓይን ያወጣ እና ያገጠጠ ሳይጣናዊ ክህደት ግን አይተንም ሰምተንም አናውቅም፡፡ ዛሬ በአደባባይ ክህደታቸውንና ነውራቸውን ያሳዩን፤ የውስልትና ፓለቲካቸውን የጀመሩት፤ በታላቁ አርበኛ በአባታችን ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው ደሴ መስዋዕት፤ ያዘኑ መስለው ውስጥ ውስጡን ግን፤ ‹‹እንደሳር ውስጥ እባብ እና የጭቃ ውስጥ እሾህ›› በለስላሳ ባህሪ አታለው ነው ኢያጎአዊ ድርጊታቸውን የጀመሩት፡፡ ከዳተኞቹ ከስራዓቱ ጋር የጀመሩትን ውስልትና ቀደም አድርገው እንደጀመሩት መረጃዎች ቢጠቁሙም፤ አሊቧልታ ነው በማለት ነገሩን በትዕግስት ይዘነው ቆይተናል። ከሳይጣናዊ ምክክራቸው ከታቀብን እና ከተገለልን የቡድን መሳሪያ ሳይቀር በወገን ጥይት ናዳ እየወረደብን በውስጥ ታጋዮች እየተፈትነን ዘጠኝ የጨለማ ወራትን አሳልፈናል። ዛሬን በእሳት የተፈተን ነገን በተስፋ እስከ ቀራኒዮ የምንፋለም እንጂ፤ በድብብቆሽ ፓለቲካ እጃችንን አንከርፍፈን ለጨፍጫፊ ኦሮሙማ ስርዓት እጅ የምንሰጥ የሚሊሻ ልጆች አይደለንም። ስለሆነም የገብርዬ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበረው ግለሰብ አዲሱ ደባልቄ እና የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ የነበረው አዳነ ተስፋ ወደ ገዳያችን ብልጽግና ሲገቡ፤ በተቋማችን ላይ በመጠኑም ቢሆን የትጥቅ እና የስንቅ ጉድለት ቢያደርሱም፤ ትናንትም ህዝባችን ነገም ህዝባችን የትግላችን መሠረት በመሆኑ፤ አንገታችንን ቀና አድርገን የምንሄድ የዳግማዊ ገብርዬ ልጆች ነን። በመሆኑም ''በህይወት ኖሮ ከመቆሸሽ ሞቶ መወደስን'' የምንመረጥ የስመኘው መብራቱ (ጋሼ) የቃል ዕዳ ያለብን አቡነ ጴጥሮሶች ነን፡፡ ፈንገሶችን አራግፈን በንፁህ ህሊና የምናስብ በጤነኛ ሳምባ የምንተነፍስ ዮቶራዊያን ነን። በዚህ መሠረት አንዳንድ ነገሮችን ለድርጅታችን አፋብን፤ ለተከበረው ሰራዊታችን፤ ለመላው ህዝባችን፤ ለመላው በሃገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የትግላችን ደጋፊዎች ማሳሳብ የምንፈልገው ነገር፤ ቢኖር እንደሚከተለው ነው። 1ኛ, መላ የአማራ ህዝብ በተለይም በቀጠናችን ለሚገኘው ለራስ-ጋይንት ህዝብ፡- የብአዴን ማደጎ-ቤት ልጆች በሰሩት የጠራራ ፀሃይ ክህደት ብንበሳጭም፤ የእውነት ልጆቻችሁ ከጎናችሁ መሆናችንን፡፡ 2ኛ. ለድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፡- ከደረሰብን ድንገታዊ የውስጥ ጥቃት የሚታደግ የሃሳብ፣ የገንዘብ እንዲሁም የአደረጃጀት ድጋፍ እንዲደረግልን ስንል ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 3ኛ. ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ደጋፊዎች፡- ጥቅመኞች ትግላችንን በአደባባይ ሲሸጡት ሞራላችሁ ቢሰበርም፤ ታማኝ ወንድምና እህቶቻችሁ እንዲሁም ልጆቻችሁ ክንዳችንን ሳንንተራስ፤ ትከሻችን ዝሎ የአማራን ህዝብ ለጨፍጫፊ ስርዓት አሳልፈን አንሰጥም፤ 4. ለመላ ሠራዊታችን፡- እንደምታውቁት የትግላችን የጥቅም ወንድማማቾች እንጂ ሃቀኛ ታጋይ እንዳልሄደ ጠንቅቃችሁ ብታውቁም፤ የፍርሃትም ሆነ የመረበሽ ነገር እንዳልገጠማችሁ በትናንቱ የውስጥ ከሃዲዎችን እና የጠላትን የጋራ ውጊያ ሰብራችሁ መኪና እና ዲሽቃ የተቀባላችሁ፤ ዘረ-ከፍያለዋዊያን መሆናችሁን በተግባር አሳይታችኋል፡፡ ወደፊትም በጀግንነት እና በታማኝነት እንድትቀጥሉ እናሳስባለን። 5ኛ በዓመታዊ የፋኖ ድጋፍ ሰበብ ሕብረሰባችን መቀነት የፈቱ ሠራዊታችን የበተኑ አመራር ነን ተብዬወች፤ በአማራ ትግል ስም የሸቀጡ መሆናቸውን የአማራ ህዝብ በጥቁር የታርክ መዝገብ እንዲያስቀምጥልን የአማራ የህልውና ትግል ህዝብና ደጋፊ አደራውን እንሰጣለን። በመሆኑም እኝህና መሠል ጉዳዮችን ለማስተካከል ወቅታዊ ፈተናዎችን ለመወጣት የሰራዊታችን እና የሕዝባችን ሞራል ለመካስ እንደ ገብርዬ ክፍለ ጦር ጊዜያዊ አደረጃጀት የሠራን መሆኑን እየገለጽን፤ ቀጣይ ድርጅቱ (አፋብን) በሚያወረደው መመሪያ መሠረት አደረጃጀቱ እንደገና እንደሚዋቀር ለመግለጽ እንፈልጋለን፡፡ በዚህም መሠረት የጊዜያዊ አደረጃጀቱ መሪዎችን ሰይመናል። 1. አርበኛ ኢ/ር ደመወዝ ግዳፍ -----ጊዜያዊ ሰብሳቢ 2. አርበኛ ክንድሰው ከፍያለው ----- ምክትል ሰብሳቢ 3. አርበኛ ያለው ጥላሁን -----ወታደራዊ አዛዥ 4. አርበኛ አንዷለም አዳሙ ----ዘመቻ መምሪያ 5. አርበኛ አማረ ጌታው ------ምክትል ዘመቻ 6. አርበኛ ሲሳይ ------- ልዩ ዘመቻ (ልዩ ኦፕሬሽን) 7. አርበኛ ብርሃን ጌታው ------ፓለቲካ ዘርፍ 8. አርበኛ ዘላለም በላይነው -----ፋይናስ ክፍል 9. አርበኛ ልየው ተካልኝ -------ሕዝብ ግንኙት በማድረግ አደራጅተን፤ እንዲሁም በአራት ብርጌድ አመራር እና በሶስት ወረዳ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ የተጠረነፈ ሠራዊት ይዘን ወደ ስራ የገባን መሆኑን እንገልፃለን። ማሳሰቢያ፡- ለረጅም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የአማራ ፋኖ አንድነትን በሙሉ ድምጽ የተቀብልን እና በድርጅታችን አፋብን እንዲሁም ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮቻችን በሚሰጡን አቅጣጫ የምንመራ መሆኑን እየገለጽን፤ አስፈላጊውን የገንዘብም ሆነ የሃሳብ ድጋፍ እንዲደረግልን በታጋያችን እና በተገፋው ሕዝባችን ስም እንጠይቃለን። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር፦ አርበኛ ኢንጂነር ደመወዝ ግዳፍ ጊዜያዊ ሰብሳቢ፤

የወረኢሉ ከተማ ከንቲባ የግል አጃቢ ለጥምቀት በዓል ባንዲራ ሰቅለሃል ያለውን አቶ ጥላየ ሃይሉ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ግለሰብ በግፍ ረሸነ:: በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ ከንቲባ የግል አጃቢ የ
የወረኢሉ ከተማ ከንቲባ የግል አጃቢ ለጥምቀት በዓል ባንዲራ ሰቅለሃል ያለውን አቶ ጥላየ ሃይሉ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ግለሰብ በግፍ ረሸነ:: በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ ከንቲባ የግል አጃቢ የሆነ ታጣቂ ጥር 14/2018 ዓ.ም ምሽት 1:45 ገደማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ኮከብ የሌለው ባንዲራ ለጥምቀት በዓል ከተማዋ ላይ ስትሰቅል ነበር በሚል ሰበብ አቶ ጥላየ ሃይሉ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ግለሰብ ላይ ነፃ እርምጃ በመውሰድ በግፍ ረሽኖታል::  ነፃ እርምጃ የተወሰደበት እድሜው 35 አመት የሆነ የወረኢሉ ከተማ ነዋሪ ግለሰብ አቶ ጥላየ ሃይሉ ጦር መሳሪያ ያልታጠቀና በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረ ነው:: በሌላ በኩል በጃማ ከተማ እና ሚዳ/መራኛ መካከል ልዩ ስሙ ካራ ምሽግ የተባለ ቦታ ላይ አንድ ሾፌር በአገዛዙ ታጣቂዎች በግፍ የተገደለና አስከሬኑ ሜዳ ላይ ወድቆ የተገኘ ሲሆን የብልፅግና ታጣቂዎች ግለሰቡን በግፍ የገደሉት የያዘውን 70000 (ሰባ ሽ) ብር ለመውሰድ መሆኑንና ግፈኛ ታጣቂዎቹም እንደሚታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 16/2018 ዓ.ም

እጅ ስለሰጡት ሳይሆን ጠላትን ስለምንበቀልበት የክብር ትግል ላይ ነን!! የአንበሳው ጋይት ክፍለ ጦር ክንዳለም ሻለቃ ዋና ፊታውራሪ የአባቱ ምትክ የሆነው ክንደ ነበልባሉ አንደበት ክንዳለም ጋይንት ላ
እጅ ስለሰጡት ሳይሆን ጠላትን ስለምንበቀልበት የክብር ትግል ላይ ነን!! የአንበሳው ጋይት ክፍለ ጦር ክንዳለም ሻለቃ ዋና ፊታውራሪ የአባቱ ምትክ የሆነው ክንደ ነበልባሉ አንደበት ክንዳለም ጋይንት ላይ የማን ልጅ እንደሆነ በእጅ ሰጭዎችና በታጋዬች መካከል ያለውን ልዩነት ጠላትን ማርኮ አሳይቷል። ቃል የእምነት እዳ ነው። ትናት በደም በአጥንታቸው ውዱን ዋጋ ከፍለው የማረኩትን ዲሽቃ መልሰው ለጠላቶቻችን ሲያስረክቡ የአባቱ ልጅ ጠላትን አራግፎ የያዘውን ትጥቅ ተቀብሎታል። ትናንት ጥር 15/2018 ዓ.ምን ከቀኑ 7:00 ጀምሮ እስከ 9:00 ሰዓት ከጥጥራ እስከ ዳሞት በእንቅስቃሴ ላይ የነበረን የጠላት በኃይል፦ ## 9 ሙት ## 15 ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሲያደርገው ## 6 የክላሽ ትጥቅ ከጠላት ተረክቧቸዋል። በሌላኛው አውደ ውጊያ ከክምር ድንጋይ ወደ አጃ ሬሽን ጭኖ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረ የብልጽግናው ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ፣መከላከያና ፖሊስ በተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር አናብስቶች ውቅሮ መድሃኒያለም ላይ ከፍተኛ ሙትና ቁኛ አድርገውታል። ዛሬም ጀግና እማያልቅበት ምድር አንገቱን ከፍ እሚያደርግባቸው ልጆቹ እንዳሉ ምስክር ነው። ሌላው ደግሞ በጀግኖቹ ሲምልና ሲገዘት የሚዉለው የትግል ሾተላይ መሰሪው ቡድን እጁን አንከርፍፎ ጀግና የማረከውን ዲሽቃና እስናፐር ሲያስረክብ እንዲህ ያባቶቹን አደራ የማይበላ እንቁ አማራ ሜዳው ላይ አለ። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አላፊ አርበኛ

የፋኖን አንድነት ተከትሎ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት ፋኖን የሚቀላቀሉ ወታደሮች ቁጥር ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ! ወታደሮቹ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት መበሰሩን ተከትሎ፡
የፋኖን አንድነት ተከትሎ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት ፋኖን የሚቀላቀሉ ወታደሮች ቁጥር ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ! ወታደሮቹ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት መበሰሩን ተከትሎ፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከቡድን መሣሪያ ብሬንና ስናይፐር ጀምሮ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ፋኖን በገፍ እየተቀላቀሉ መሆኑን መረብ ሚዲያ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ ችሏል። ይህ ጉዳይም በአገዛዙ ቤት ከባድ ሽብርና ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤታቸው ዝናሽ ታያቸውን በአንድ ግንባር፡ የስድብ አማካሪው አቶ ዳንኤል ክብረትን በሌላኛው ግንባር፡ እንዲሁም ሌሎች ምንጣፍ ጎታቾቻቸውን በቀሪው ግንባር አሰልፈው ይዋጉ ካልሆነ በስተቀር ወታደሩስ "ማን ሞቶ የማን ስልጣን ሊቀጥል" በሚል ልክ እንደ እምቧይ ካብ እየተናደ አልቋል።

ጥር 15/ 2018 ዓ.ም ከእኔ ከፋኖ ትልቅአለም አሳብ ለአቶ ዋለ አባተ ለምስራቅ ጎጃም ምክትል አስተዳዳሪ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ። በቀደሙ ጥቂት ቀናት በፊት አስጨነቅ ታደለ ጀግኖች ተናንቀው ጀብድ ሰርተው መስዋትነት በከፈሉበት ባሶሊበን፣ ሰራዊታችን ሲፋለሙባቸው የነበሩ ዲሽቃዎችን ይዞ በመጥፋት እርምጃ ሊወሰድበት ሲል ለጠላት እጅ ሰጦ የአማራ ህዝብንና ህይወታቸውን ገብረው ይህን ትግል አደራ የሰጡ ጓዶችን መክዳቱ እንዳበሳጨኝ የማልደብቀው ሀቅ ነው። በሴት ተደልሎ 14 ንፁህ ታጋዮችን በተኙበት አስከብቦ በጉያችሁ የወደቀው ባንዳ አስክሮህ ለእኔ ለፋኖ ትልቅአለም በwhatsapp ቁጥሬ የአማራን ህዝብ ብሎም በየ በረሀው ተንከራትቸ ያደራጀውትን ሰራዊት በአማራ ምድር ሁሉ በዚህ የህልውና ትግል የተሰው ወንድሞቸን ደም እረግጨ እጅ እንድሰጥ የላክልኝ መልዕክት እንድበቀልህ የሚያነሳሳኝ እንጂ ንፁሀንን ስታስጨፈጭፍ ለነበረው ለአንተ፣ እናቶችን ፣ ሴቶችንና ህፃናትን በጅምላ የሚደፍረውን ሰራዊት አሰማርተህ በወገኖቸ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን በደል ለፈፀምከው ለአንተ፣ አረመኔ የሆነ ሰራዊት በራስህ ህዝብ ላይ አዝምተህ ምድሪቱን በደም ለአጨቀየህው ለአንተ፣ ለጌታህ ለአብይ አህመድ ታምነህ የራስህን ወንድም ሰውነቱን ቆራርጠህ ተማኝነትህን ላረጋገጥ ጨካኝ። ሺዎችን በማጎሪያ አሰቃይተህ ገላቸው በድን እስኪሆን ላሰቃየሀቸው ባንዳ፣ ህፃናት በሚቦርቁበት መንደር ፣ ቀሳውስት በሚቀድሱበት ደብር፣ ገበሬዎች በእርሻ መሬታቸው፣ እናቶች በጓዳቸው በድሮን ለአስጨፈጨፋካቸው ጥቁር ሂትለር፣ ህፃናትን ያለ ወላጅ ሴቶችን ያለ ባል አስቀርተህ ጎዳና ለአነጠፍካቸው መርዝ በጥባጭ እጀን አንከርፍፌ ወንድነቴን አጥቸ እጅ የምሰጥ የበላይ ልጅ አይደለሁም። ምናልባት አንተ አታውቀኝ ይሆናልና ብትደፍረኝ አይገርመኝም ማነህ ቢሉህ እኔ የማትለው ዋለ አባተ ሆይ! እኔ ትልቅ እባላለሁ ስለኔ አጠገብህ ያለውን ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን አሊያም ሶፊያ መሐመድን ጠይቅ ወይንም ኮማደር ግርማንም ማነው ብለህ ጠይቀው ። ክንዴንም አፈሙዜንም እነሱ በደንብ ያውቁታል በየ ጁቤ ምድር በባሶሊበን አፈር ስንት ሰራዊታቸውን ቀብረዋል ስንቶችን አንገቱን ቀልተን ለሞራ ቀለብ አድርገናቸዋል። ታጠቅነውን ብሬን ያነገብነው ስናይፐር ከመንጋጋቸው ፈልቅቀን የማረክነው ነው እኛ ነን። ምነው ዘነጋሀው ዉሎ አዳርህን እይ ስትፍረከረክ የምትውል በታክም በመድፍም ተከበህ የምትቃዥ እኛኑ ፈርተህ መግቢያ መውጫ አጠህ መሆኑንም አስታውስ። በሁለት ሚኒሽር የጀመርነው ትግል ዛሬ ሚሊዮኖቹን አፍርቷል! ጉዳዮ የአላማ ነው። አላማችንን ነፍስና ስግችን አድርገን መስዋትነት የምንከፍለው የአማራን ህዝብ ከጋረጣችሁበት የህልውና አደጋ አውጥተን ወደነበረበት ክብሩ ከፍ ለማድረግ እንጅ ኩሽና ተደብቆ ለሚውል ካድሪ እጅ ሰጠን ትውልድ የሚስቅብን ፈሪዎች ለመሆን አይደለም። እኛ መከራ ያልበገረን፣ በሞት ጥላ ውስጥ እያለፍን ለህዝባችንና ለተቀበልነው አደራ ታምነን የምንታገል የበላይ ዘለቀ ልጆች እንጅ እንደ ይሁዳ በሽልንግ የምንሸጠው ትግል የተሰው ጓዶች አደራ የለም። አቶ ዋለ አባተ ለአንተ በመጨረሻ ይህንን እወቅ ፣ ከእኛ ጥይት አታመልጥም ተደብቀህ የምታሳልፈው ማዕበልም የለም ወደ መቀመቁ ይዘንህ እንወርዳለን የሚመጣውን እልቂት አንተ ከአለፍከው እኛ ባንወለድ እንመርጣለን እመነኝ እንገልሀለን ሰራዊትህም ካድሪህም አይኖርም። እኔም ለአላማየ የምታገል ለአማራነቴና ለክብሬ የምሰዋ ግንባር ቀደም ታጋይ ነኝ ብወድቅ ወደኋላ ሳይመለስ ጉሮሮህን የሚያንቅ ሰራዊት ይየ ከፊት እቆማለሁ ቀናትን ብቻ ጠብቀኝ። ለመላ ሰራዊታችን እና ለባሶሊበን ወረዳ ለመላው የአማራ ህዝብ ፣ በተፈፀመብን ክህደት ፈፅሞም ከአላማችን ፈቀቅ እንደማንል እያረጋገጥኩ በባንዳዎችና በዳካማ ጠላታችን ላይ ለምናደርገው ትንቅንቅ በቁጭትና በወኔ ጠላትን ድባቅ ለመምታት እንድትረባረቡ አሳስባለሁ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ አርበኛ ትልቅ አለም ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ባሶሊበን

#የሜጀር_ጀኔራል_ዉባንተ_አባተ_የአብራክ_ክፋይ ተመስገን ዉባንተ እና ደረበ መኮነን በላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦር አዛዥ ተመስገን ዉባንተ እና የሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬ
#የሜጀር_ጀኔራል_ዉባንተ_አባተ_የአብራክ_ክፋይ ተመስገን ዉባንተ እና ደረበ መኮነን በላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦር አዛዥ ተመስገን ዉባንተ እና የሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮነን

የአገዛዙ አሸርጋጅ ቡጅሌ እና ሰራዊቱ ክፉኛ ሽንፈትን አስተናገዱ!!! በትናንትናው እለት ጥር15 /2018 የጠላት ሀይል መነሻውን ማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ አፀደማርያም ከተማ በማድረግ ወደ ችማ ለምበዝ ቀበሌ ሚኒሻ እና ፋሽስታዊው የአገዛዙ ሰራዊት በመሆን የአርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታትና ለመዝረፍ አቅደው ወደ ቀጠናው መግባት ቢችሉም ከአድዋ ክ/ጦ አሀድ ተመርጠው ወደ ቀጠናው በተላኩ የፋኖ ሀይሎች  ቀድሞ መረጃውን በመከታተል ሚኒሻው ወደ አርሶአደሩ ቤት ፍተሻ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ከፊት ለፊት መከላከያውን በመግጠም  እና ቆራጭ ሀይል  በማስገባት ለመዝረፍ  የገባውን ሚኒሻ  እቅዱን ከማክሸፍ ባሻገር ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እግሬ አውጭኝን ፈርጥጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይሄን ስምሪት በማስተባበር ላይ የነበረው ዋሴ የተባለው ጅብ የስርአቱ ተላላኪ ቤተክርስትያን ገብቶ የካህናትን አልባሳት ለብሶ እንዳመለጠ የውስጥ መረጃዎቻችን አድርሰውናል። በዚህ መብረቃዊ ጥቃት ጠላት የደረሰበት ኪሳራ:        7 እስከ ወዲያኛው የተሰናበተ       3 ከባድ ቁስለኛ ቀኑን በሙሉ ከባድ መሳሪያ በመተኮስና በቁጥር በርካታ ሀይል በማስገባት ሙት እና ቁስለኛውን ይዞ ወደ መጣበት ጉድጓድ ተመልሶ ገብቷል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የስርአቱ አስፈፃሚ አመራሮች እና ጥምር ሰራዊቱ በህዝባችን ላይ  ፀያፍ ተግባራትንና ጀኖሳይድን ከመፈፀም ባሻገር  በአርሶ አደሩ ላብ ለመክበርና የስጋ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ውድድር ላይ ስለሚገኙ የአማራ ህዝብ እና ሰው የሆነ ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አንዲታገላቸው መልእክታችን ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ   ጥር 15/2018 ዓ.ም

፩ አላማ፤ ፩ ድርጅት፤ ፩ ዓምሐራ🔑✊ እኛ ዓምሐሮች ለትግላችን እሥከጠቀመን ድረሥ ከምንፈልገው አካል ጋር ተገናኝቶ ለመሥራት የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ለትግላችን እሥከጠቀመን ድረሥ ከሰይጣንም ጋር እናብራለን። በእኛ ላይ ከልካይውም ሆነ ፈቃጁ እኛው ራሳችን የዓምሐራ ፋኖዎች ነን። ነጻነት ይጠየቃል እንጅ አይለመንም ነውና የዓምሐራ ብሒሉ❗ ዓምሐራ ምርጫው አንድ መሆን ነው። ይህ ማለት ከአጥፊ ቁማር የፀዳ ዓምሐራዊ አንድነት ያሥፈልጋል ማለት ነው። የትኛውም አካል ከትግላችን በታች እንደሆነ የሚያምን አንዳዊ የዓምሐራ ትግልን ማራመድ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው። በአንድ አላማ፤ በአንድ መዋቅር ጎጠኛን ማሽቀንጠር ፀረ ዓምሐራን መመንጠር አንድ ያልሆነ አንድነትን ማባረር ውሉደ ፋፍን ወደ እንጦሮጦሥ መወርወር በዓምሐራነት ማማር🔑 ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑 ዘረ ውባንተ አባተ[ፈለገ ውባንተ አባተ] ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ ዘ ብሔረ ዓምሐራ N.B ልዩ ማሥታወሻ፦ ✔ጥቁር ጣልያናዊነት፣ ወዶ ገብነት፣ ባሪያነት፣ ባንዳነት እና ፀረ ዓምሐራነት ማንን ይመሥላል ቢሉ የዳውንት ቁጥቋጦ ሥር ቁማርተኛ ተደራዳሪዎችን ይመሥላል ነው መልሱ። ✔የዳውንት ቁጥቋጦ ሥር ቁማርተኞች የገቡት ብቻ ሳይሆን ያልገቡትም የአማራ ሕዝብን ትግል ወደኋላ የጎተቱና የጫካው ብአዴን ጭምብል አጥላቂ የእንግዴ ልጆች ናቸውና ምሽግ ሰርቶ መደበቅ ከወንጀለኞቹ በላይ ወንጀለኛ መሆን ነው። ለፋሕፍዴን ጥብቅና የሚቆም ቁ #1 ፋሕፍዴን ነውና እርሱ ከእኛ ዘንድ አይደለም። መሥዋዕትነትን በከፈለ አንገተ ቅጥል ወንድሞቻችን ደም የምትቀልዱ ሁሉ አድቡ። ✔ለትግል ጠላፊውና ተቋም አፍራሹ ቅጥ-እረኛ ኃብታሙ አያሌውና መሰሎቻቸው ዓምሐሮች ቦታ የላቸውም፤ የፈለከውን ያህል አሽላላ፣አሽቃብጥ፣ ሳሙና ሁንም ምን ማንም አይሰማህም። ፈጣሪ በአካል ቢወርድ ሜ/ጀ ውባንተ አባተን ባዋከባችኹት በአንተና በመሰሎችህ ምንም ዓይነት የይቅርታ ልብ የለንም። ቋሚ ምሥል፦ ከዕውነትና ፍትሕ ውጭ የትኛውንም ጎጠኛ፣ ቁማርተኛ፣ የሥልጣን ጥመኛ፣ የአፍ አማራ የልብ ጎጠኛና በአጠቃላይ ማሥመሰልን ሕይወታቸው ያደረጉ የእንግዴ ልጆችን አምርሮ የሚጠላው እንዲሁም ዕውነተኛ ትግልን ከብርጋዴር ጀነራል አሣምነው ፅጌ፣ ከአርበኛ ባዬ ቀናው፣ ከአርበኛ አራጋው እንዳለ፣ ከአርበኛ አሥቻለው ደሤ፣ ከሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ፣ ከአርበኛ አሰግድ መኮንን እና ከፕሮፌሰር አሥራት ወልደየሥ የተማረው የትግሉ ባለቤት ዘረ ውባንተው/ፈለገ ውባንተው ፋኖ ኃቅ-ዓለው ዘ ብሔረ ዓምሐራ

ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በጊራና መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::
+1
ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ:: በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በጊራና መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል:: የ35ኛ ክፍለ ጦር እንደጉም ተበትና አልቃለች። ከተለያዩ አሀዶች አውጣቶ ኮማንዶዎች ቢያመጣም ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ብለው ሶስት የሰራዊቱ አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተገናኝተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 15/2018 ዓ.ም

ልባዊ ጥምረት፣ ወንድማዊ አንድነት!...የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ‼️ በላይ ዘለቀ ዕዝ እና ሚኒልክ ዕዝ በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፉ። አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ እና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስደዉበታል። ሬሽን ለመቀበል መነሻዉን ከላሊበላ ጋሸና - ከጋሸና ላሊበላ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ የነበረዉ የአገዛዙ ሰራዊት በዛሬዉ ዕለት ማለትም በ ቀን 15/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 1:00 -10:00 ሲቀጠቀጥ የዋለ ሲሆን ከወደ ጋሻና የመጣዉን ግትልትል ሰራዊት በነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ በተለምዶ እንኳይ በር ላይ ሲያረግፉት የዋሉ ሲሆን ከወደ ላሊበላ የመጣዉን የአገዛዙ ሰራዊትን ደግሞ የዉባንተ አባተ ግስላወች በተለምዶ ቆጋ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ጠቁር አስፖልቱን ግጥም አድርገዉ ዘግተዉ ሲወቁት ዉለዋል። በዚህም ዉጊያ ላይ ብዛት ያለዉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን ብዛት ያላቸዉ መሳሪያዎች እና ተተኳሾችም ተማርከዋል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 15/ዐ5/2018 ዓ.ም