ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 061
Підписники
+224 години
+4287 днів
+1 25730 днів
Архів дописів
#የሜጀር_ጀኔራል_ዉባንተ_አባተ_የአብራክ_ክፋይ ተመስገን ዉባንተ እና ደረበ መኮነን
በላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦር አዛዥ ተመስገን ዉባንተ እና የሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮነን
የአገዛዙ አሸርጋጅ ቡጅሌ እና ሰራዊቱ ክፉኛ ሽንፈትን አስተናገዱ!!!
በትናንትናው እለት ጥር15 /2018 የጠላት ሀይል መነሻውን ማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ አፀደማርያም ከተማ በማድረግ ወደ ችማ ለምበዝ ቀበሌ ሚኒሻ እና ፋሽስታዊው የአገዛዙ ሰራዊት በመሆን የአርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታትና ለመዝረፍ አቅደው ወደ ቀጠናው መግባት ቢችሉም ከአድዋ ክ/ጦ አሀድ ተመርጠው ወደ ቀጠናው በተላኩ የፋኖ ሀይሎች ቀድሞ መረጃውን በመከታተል ሚኒሻው ወደ አርሶአደሩ ቤት ፍተሻ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ስአት ከፊት ለፊት መከላከያውን በመግጠም እና ቆራጭ ሀይል በማስገባት ለመዝረፍ የገባውን ሚኒሻ እቅዱን ከማክሸፍ ባሻገር ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እግሬ አውጭኝን ፈርጥጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። ይሄን ስምሪት በማስተባበር ላይ የነበረው ዋሴ የተባለው ጅብ የስርአቱ ተላላኪ ቤተክርስትያን ገብቶ የካህናትን አልባሳት ለብሶ እንዳመለጠ የውስጥ መረጃዎቻችን አድርሰውናል።
በዚህ መብረቃዊ ጥቃት ጠላት የደረሰበት ኪሳራ:
7 እስከ ወዲያኛው የተሰናበተ
3 ከባድ ቁስለኛ
ቀኑን በሙሉ ከባድ መሳሪያ በመተኮስና በቁጥር በርካታ ሀይል በማስገባት ሙት እና ቁስለኛውን ይዞ ወደ መጣበት ጉድጓድ ተመልሶ ገብቷል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የስርአቱ አስፈፃሚ አመራሮች እና ጥምር ሰራዊቱ በህዝባችን ላይ ፀያፍ ተግባራትንና ጀኖሳይድን ከመፈፀም ባሻገር በአርሶ አደሩ ላብ ለመክበርና የስጋ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ውድድር ላይ ስለሚገኙ የአማራ ህዝብ እና ሰው የሆነ ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አንዲታገላቸው መልእክታችን ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
ጥር 15/2018 ዓ.ም
፩ አላማ፤ ፩ ድርጅት፤ ፩ ዓምሐራ🔑✊
እኛ ዓምሐሮች ለትግላችን እሥከጠቀመን ድረሥ ከምንፈልገው አካል ጋር ተገናኝቶ ለመሥራት የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ለትግላችን እሥከጠቀመን ድረሥ ከሰይጣንም ጋር እናብራለን። በእኛ ላይ ከልካይውም ሆነ ፈቃጁ እኛው ራሳችን የዓምሐራ ፋኖዎች ነን። ነጻነት ይጠየቃል እንጅ አይለመንም ነውና የዓምሐራ ብሒሉ❗
ዓምሐራ ምርጫው አንድ መሆን ነው። ይህ ማለት ከአጥፊ ቁማር የፀዳ ዓምሐራዊ አንድነት ያሥፈልጋል ማለት ነው። የትኛውም አካል ከትግላችን በታች እንደሆነ የሚያምን አንዳዊ የዓምሐራ ትግልን ማራመድ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው።
በአንድ አላማ፤ በአንድ መዋቅር
ጎጠኛን ማሽቀንጠር
ፀረ ዓምሐራን መመንጠር
አንድ ያልሆነ አንድነትን ማባረር
ውሉደ ፋፍን ወደ እንጦሮጦሥ መወርወር
በዓምሐራነት ማማር🔑
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑
ዘረ ውባንተ አባተ[ፈለገ ውባንተ አባተ] ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ ዘ ብሔረ ዓምሐራ
N.B ልዩ ማሥታወሻ፦
✔ጥቁር ጣልያናዊነት፣ ወዶ ገብነት፣ ባሪያነት፣ ባንዳነት እና ፀረ ዓምሐራነት ማንን ይመሥላል ቢሉ የዳውንት ቁጥቋጦ ሥር ቁማርተኛ ተደራዳሪዎችን ይመሥላል ነው መልሱ።
✔የዳውንት ቁጥቋጦ ሥር ቁማርተኞች የገቡት ብቻ ሳይሆን ያልገቡትም የአማራ ሕዝብን ትግል ወደኋላ የጎተቱና የጫካው ብአዴን ጭምብል አጥላቂ የእንግዴ ልጆች ናቸውና ምሽግ ሰርቶ መደበቅ ከወንጀለኞቹ በላይ ወንጀለኛ መሆን ነው። ለፋሕፍዴን ጥብቅና የሚቆም ቁ #1 ፋሕፍዴን ነውና እርሱ ከእኛ ዘንድ አይደለም። መሥዋዕትነትን በከፈለ አንገተ ቅጥል ወንድሞቻችን ደም የምትቀልዱ ሁሉ አድቡ።
✔ለትግል ጠላፊውና ተቋም አፍራሹ ቅጥ-እረኛ ኃብታሙ አያሌውና መሰሎቻቸው ዓምሐሮች ቦታ የላቸውም፤ የፈለከውን ያህል አሽላላ፣አሽቃብጥ፣ ሳሙና ሁንም ምን ማንም አይሰማህም። ፈጣሪ በአካል ቢወርድ ሜ/ጀ ውባንተ አባተን ባዋከባችኹት በአንተና በመሰሎችህ ምንም ዓይነት የይቅርታ ልብ የለንም።
ቋሚ ምሥል፦ ከዕውነትና ፍትሕ ውጭ የትኛውንም ጎጠኛ፣ ቁማርተኛ፣ የሥልጣን ጥመኛ፣ የአፍ አማራ የልብ ጎጠኛና በአጠቃላይ ማሥመሰልን ሕይወታቸው ያደረጉ የእንግዴ ልጆችን አምርሮ የሚጠላው እንዲሁም ዕውነተኛ ትግልን ከብርጋዴር ጀነራል አሣምነው ፅጌ፣ ከአርበኛ ባዬ ቀናው፣ ከአርበኛ አራጋው እንዳለ፣ ከአርበኛ አሥቻለው ደሤ፣ ከሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ፣ ከአርበኛ አሰግድ መኮንን እና ከፕሮፌሰር አሥራት ወልደየሥ የተማረው የትግሉ ባለቤት ዘረ ውባንተው/ፈለገ ውባንተው ፋኖ ኃቅ-ዓለው ዘ ብሔረ ዓምሐራ
+1
ሶስት የአገዛዙ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ::
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በጊራና መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል::
የ35ኛ ክፍለ ጦር እንደጉም ተበትና አልቃለች። ከተለያዩ አሀዶች አውጣቶ ኮማንዶዎች ቢያመጣም ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ብለው ሶስት የሰራዊቱ አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ጋር በሰላም ተገናኝተዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 15/2018 ዓ.ም
ልባዊ ጥምረት፣ ወንድማዊ አንድነት!...የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ‼️
በላይ ዘለቀ ዕዝ እና ሚኒልክ ዕዝ በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፉ።
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ እና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስደዉበታል።
ሬሽን ለመቀበል መነሻዉን ከላሊበላ ጋሸና - ከጋሸና ላሊበላ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ የነበረዉ የአገዛዙ ሰራዊት በዛሬዉ ዕለት ማለትም በ ቀን 15/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 1:00 -10:00 ሲቀጠቀጥ የዋለ ሲሆን ከወደ ጋሻና የመጣዉን ግትልትል ሰራዊት በነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ በተለምዶ እንኳይ በር ላይ ሲያረግፉት የዋሉ ሲሆን ከወደ ላሊበላ የመጣዉን የአገዛዙ ሰራዊትን ደግሞ የዉባንተ አባተ ግስላወች በተለምዶ ቆጋ ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ጠቁር አስፖልቱን ግጥም አድርገዉ ዘግተዉ ሲወቁት ዉለዋል።
በዚህም ዉጊያ ላይ ብዛት ያለዉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ የሆነ ሲሆን ብዛት ያላቸዉ መሳሪያዎች እና ተተኳሾችም ተማርከዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
15/ዐ5/2018 ዓ.ም
+1
ስምንት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ::
የአማራ ህዝብ መሪ ድርጅት "አፋብን" መመስረትን ተከትሎ ስምንት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
የፋኖን አንድ መሆንና የመሪ ድርጅቱ አፋብን መመስረትን ተከትሎ የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በሰፊው ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን ስምንት አባላቶቹ ሰባት ክላሽ፣ 1400 ተተኳሽ፣ ሰባት የወገብ ትጥቅና ስድስት F1 ቦምብ ይዘው ካላኮርማ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 15/2018 ዓ.ም
+1
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር ከፍተኛ አመራር ኮሎኔል ገዳሙን አጃቢ ጨምሮ አራት አባላቶች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቀሉ::
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 203ኛ ኮር አመራር የሆነው ኮሎኔል ገዳሙ አጃቢ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ በመያዝ እና 83ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ የሆነው ሌላኛው አባል እንዲሁም ሌሎች ሁለት ሶስት ክላሽ በመያዝ ባጠቃላይ አራት የአገዛዙ ወታደሮች ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ
ጥር 15/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር በወሰደው ስምሪት የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች በአዲሱ ሪፎርም መሰረት ሻለቆችን ወደ ቀደመ ቁመናቸው መመለስ ተችሏል።
በዚህ መሰረት በአንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው የተወያየን ሲሆን
1.አባላትን ስለመጠርነፍና ለግድጅ ዝግጁ ስለማድረግ፣
2.በህገ ወጥ መንገድ የማህበረሰብ በደል የሚያደርሱና የሚዘርፉ አካላት ላይ እርምጃ ስለመውሰድ፣
3.አዲሱን ድርጅታዊ መዋቅር ስለመቀበልና ስለማስፈጸም፣
4.ጊዚያዊ መንግቱ በአስቸኳይ ወደ ስራ የሚገባበትንና ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚሆንበትን በሰፊው ተወያይተን የስራ አቅጣጫ አስቀምጠናል።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!!!
አንድ አማራ እስከ ምጽዓት አማራ!!!
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ!!!
©Dawit Shiferaw Takele
+1
60 የሚሊሻ አባላት 2ብሬንና 45 ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ።
አንድነቱ በተበሰረ ማግስት በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እየፈራረሱ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቀጠናዎች #ብልፅግና ሲያሳድዳቸዉ የነበሩ ኃይሎች ታጥቀዉ ራሳቸውን ከአረመኔዉ መንግስት ጥቃት ሲከላከሉ የቆዩ፣ በመተከል አዉራጃ ዳንጉር ወረዳ በሻለቃ #ሲሳይ ገነት ሲመሩ የነበሩ 60 የአገዉ ተወላጅ ወንድሞቻችን አባላትና መሪዉ ሻለቃ ሲሳይ ገነት በቀን 14/05/2018 ዓ.ም #2 ብሬን እና ከ45 በላይ ክላሽንኮቭ በመያዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦርን በመቀላቀል አረመኔዉን የአብይ አህመድ መንግስት ስርዓት በማዉገዝ እስከመጨረሻው ለማስወገድ ቃል መግባታቸውንም አስታዉቀዋል።
+4
"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ"
ጥር 15/ 2018 ዓ.ም
========================
፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው መዝገቡ ፣ ፲ አለቃ ሸጋየ ተሸገር፣ ፲ አለቃ መኳንት አዱኛ የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ ጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረባቸው ደስታ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዘው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አብራጅት ሻለቃን ተቀላቅለዋል።
የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሁነን በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፋና በደል ተመልክተናል ያሉት የጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ስርዓቱን ለቀው ትግሉን ለመቀላቀል እንቅፋት እንደሆነባቸው የተናገሩ ሲሆን ጥር ዘጠኝ የተሰማውን የአንድነት ብስራት ተከትሎ በግንባር ቀደምነት ድርጅቱን ለመቀላቀል ረጅም መንገድ በእግራችን ተጉዞን ጎጃም ገብተናል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት አላማ በተቃራኒው በራሱ ህዝብ ላይ በመዝመት ፀረ -አማራ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ የአብይ አህመድን የጭካኔ ተልዕኮ የተቀበሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ወደ ህዝባቸው መተኮሱን አቁመው የፋኖን ትግል እንዲቀላቀሉ አዛዦች ጥሪ አቅርበዋል።
የአረመኔውን ስርዓት በተቀናጀ መልኩ እያፈረሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር 61ኛ ክላሽ ከጠላት የተቀበለ ሲሆን የሰራዊት አባላትን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
"የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ 4 (ጋንታ) አዛዦች 206ኛ ኮርን ተቀላቀሉ"
ጥር 15/ 2018 ዓ.ም
========================
፲ አለቃ ደርብ ምስጌ፣ ፲ አለቃ አትርሳው መዝገቡ ፣ ፲ አለቃ ሸጋየ ተሸገር፣ ፲ አለቃ መኳንት አዱኛ የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ ጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ በፈጠረባቸው ደስታ ከኦሮሚያ ክልል በመነሳት ቀናትን የወሰደ ጉዞ ተጉዘው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር አብራጅት ሻለቃን ተቀላቅለዋል።
የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሁነን በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፋና በደል ተመልክተናል ያሉት የጋንታ አዛዦች የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ስርዓቱን ለቀው ትግሉን ለመቀላቀል እንቅፋት እንደሆነባቸው የተናገሩ ሲሆን ጥር ዘጠኝ የተሰማውን የአንድነት ብስራት ተከትሎ በግንባር ቀደምነት ድርጅቱን ለመቀላቀል ረጅም መንገድ በእግራችን ተጉዞን ጎጃም ገብተናል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ከተቋቋመለት አላማ በተቃራኒው በራሱ ህዝብ ላይ በመዝመት ፀረ -አማራ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ የአብይ አህመድን የጭካኔ ተልዕኮ የተቀበሉ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ወደ ህዝባቸው መተኮሱን አቁመው የፋኖን ትግል እንዲቀላቀሉ አዛዦች ጥሪ አቅርበዋል።
የአረመኔውን ስርዓት በተቀናጀ መልኩ እያፈረሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር 61ኛ ክላሽ ከጠላት የተቀበለ ሲሆን የሰራዊት አባላትን የተሀድሶ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ባየ ደስታ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ ነው። ማንኛውንም የድርጅቱን ኦፊሻል መረጃወች ለማግኘት ገፁን እንድትከተሉ ይሁን።
https://www.facebook.com/profile.php?id=61586791120575
+1
የተቋም እህል ሊዘረፍ የመጣው ሰራዊት በጀግኖቹ የሽፈራው ልጆች ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል!!
ጥር 15/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ የዕዱውኃ እና አካባቢው ጎይ ቀበሌ የተቋም እህል ሊዘርፍ ከመጣው የአገዛዙ ሰራዊት ጋር በተደረገ ውጊያ ከአራት በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሙት እና ቁሰለኛ ሆነዋል።
በየዕዱኃ እና አካባቢው ጎይ ቀበሌ የተቋም እህል ለመዝረፍ የመጣው ዘራፊ ሀይል አቶ አንለይ እውነቱ የተባለ ንፁሀን እረሽኖ ወደ መጣበት ቦታ ሄዶል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ!!
ጥር 15/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
በሦስት ተሽከርካሪዎች ተሳፍረው ከመርሣ አባ ጌትየ ወደ ደሴ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች የላውንቸር ጥቃት ተፈፅሞባቸው በርካቶች ተገደሉ!
በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ስምና ማዕረጋቸው ለጊዜው ያልታወቀ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እንደሚገኙበት ታውቋል።
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለ ሽርጡ ክ/ጦር ፋኖዎች፡ ትናንት ጥር 14/2018 ዓ/ም በአንድ ተሳቢና አንድ ሲኖትራክ እንዲሁም በአንድ ፓትሮ ተሳፍረው ከመርሳ አባ ጌትየ ወደ ደሴ እየተጓዙ በነበሩ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ኢላማውን የጠበቀ ላውንቸር ጥቃት በመፈፀም ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ከመርሳ አባ ጌትየ ደሴ ባለው ጥቁር አስፓልት ልዩ ስሙ ሊብሶ ኤላ እየተባለ በሚጠራ አከባቢ ላይ ሲሆን፡ በዚህም በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በከባድ ሁኔታ ቆስለው በአስር ተሽከርካሪ ወደ መርሳ ሆስፒታል ተወስደዋል፡
በዚህ ጥቃት ከተደመሰሱት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል ስምና ማዕረጋቸው ለጊዜው ያልታወቀ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እንደሚገኙበት የተነገረ ሲሆን፡በጥቃቱ ወታደሮቹ ተሳፍረውባቸው የነበሩት ተሽከርካሪዎችም ወድመዋል።
ፋኖ የአንድነቱን ችቦ ከለኮሰ በኋላ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ እየወሰደው የሚገኘው እርምጃ እጅግ እየጠነከረ መምጣቱ ነው የተነገረው።
"የአቅጣጫ መሳት" ትርክት እና የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስትና ደጋፊዎቹ "ትግሉ አቅጣጫውን ስቷል" የሚል ተደጋጋሚ ፕሮፓጋንዳ በስፋት ሲያሰራጩ ይስተዋላል። ይህ ትርክት በተለይም በገንዘብና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ተደልለው እጃቸውን ለሰጡ ጥቂት የቀድሞ የፋኖ አባላት እንደ ስክሪፕት ተሰጥቷቸው በየመንግስት ሚዲያው እንዲደጋገም እየተደረገ ነው። ይሁን እንጂ ይህ "ትግሉ አቅጣጫ ስቷል" የሚለው የፌዘኝነት ንግግር፣ የአማራ ህዝብ ላለፉት ዓመታት ሲያሳልፍ የቆየውን መከራና የደረሰበትን የህልውና አደጋ ሆን ብሎ የሚዘነጋ ነው።
መንግስት ትግሉ አቅጣጫ መሳቱን ከመናገሩ በፊት፣ የአማራ ህዝብ በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልልና በተለያዩ አካባቢዎች በማንነቱ ምክንያት በጅምላ ሲጨፈጨፍ ለምን ዝምታን መረጠ? የሚለው ጥያቄ የትግሉን መሰረት ያረጋግጣል። መንግስት በወለጋ፣ በቤኒሻንጉልና በሌሎችም ስፍራዎች ለተፈጸሙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ተገቢውን ጥበቃ ሳያደርግና ለተጎዱትም ፍትህ ሳይሰጥ መቆየቱ፣ ህዝቡ በራሱ ክንድ ለመከላከል እንዲገደድ አድርጎታል። በመሆኑም ትግሉ "የአቅጣጫ መሳት" ሳይሆን፣ መንግስት ህዝቡን የመጠበቅ ሃላፊነቱን መወጣት ባለመቻሉ የመጣ የህልውና ግዴታ ነው።
ከጦር ግንባር ውጪ ያለው መንግስታዊና መዋቅራዊ ጫናም የዚህ ተጋድሎ ሌላኛው ምክንያት ነው። በአዲስ አበባ ከተማ "የኮሪደር ልማት" በሚል ስም የሚከናወነው ሰፊ የማፈናቀል ስራ፣ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ምሁራንንና ጋዜጠኞችን ያለምንም ምክንያት ማሰር፣ እንዲሁም ወደ ዋና ከተማዋ እንዳይገቡ የሚደረገው መዋቅራዊ መገለል ህዝቡ በገዛ ሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንዲቆጠር ማድረጉ ግልጽ ነው። ይህ ስልታዊ ማገለልና ጥቃት ደግሞ ትግሉ ግልጽ የሆነ "የመኖር መብት" ጥያቄ እንጂ አቅጣጫ የሳተ አመጽ አለመሆኑን ያረጋግጣል።
መንግስት በጥቂት "ተስፋ የቆረጡ" ግለሰቦች አማካኝነት ትግሉ እየፈረሰ እንደሆነ ለማሳየት ቢሞክርም፣ በቅርቡ በጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም (January 17, 2026) የታወጀው የፋኖ ሃይሎች ውህደት ሌላ እውነታን ይነግረናል። የጎጃም፣ የጎንደር፣ የወሎ እና የሸዋ ፋኖዎች በጋራ "የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ" (አፋብን) በሚል መደራጀታቸው፣ ትግሉ ካለበት የመከላከል ደረጃ ወደ ተደራጀ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ተቋም መሸጋገሩን ያሳያል። ይህ አንድነት ደግሞ በመንግስት በኩል የሚቀርበውን "የመበታተን" ወሬ ውድቅ የሚያደርግ ታሪካዊ ምላሽ ነው።
ባጠቃላይ፣ የአማራ ህዝብ ተጋድሎ የመነጨው መንግስት በህዝብ ደም ላይ ካሳየው ዝምታና በመዋቅር ከዘረጋው መገለል ነው። ትግሉ አቅጣጫውን የሳተው ሳይሆን፣ ህዝቡ በገዛ ሀገሩ በክብር ለመኖርና ከጥፋት ለመዳን የያዘው ብቸኛ የህልውና መስመር ነው። መንግስት ለገደላቸውና ለተገደሉበት ህዝቦች ፍትህ መስጠትና መዋቅራዊ ጥቃቱን ማቆም ሲገባው፣ በትግሉ መሪዎች ላይ የሚያካሂደው የባህርይ ማጠልሸት ዘመቻ የህዝቡን ቁጭት ከማባባስ ውጪ የሚያመጣው ሰላም አይኖርም።
በጋምቤላ ክልል ከዋና ከተማዋ በስተቀር አብዛኻኛው የክልሉ አከባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የጋምቤላ ታጣቂ ኃይል ጥምረት በሀገራዊ ጉዳይ ከፋኖ ጋር አብሬ መስራት እፈልጋለሁ አለ!
ታጣቂ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ፡ ከሰሞኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ለሃገራዊ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ነው አብሮ መስራት እንደሚፈልግ የገለፀው።
ፋኖ ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በዚህ ፀረ ሕዝብ ኦህዴድ መር የብልፅግና ቡድን ጭቆና የደረሰባቸው ብሔር ብሔረሰቦች ጭምር ተስፋ አድርገውታል።
የፋኖን እንቅስቃሴ በተስፋና በጉጉት እየጠበቁት የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የምስራቅ አፍሪቃና የቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን የሚሹ ኃይሎች ሁሉ አይናቸውን ፋኖ ላይ ተክለዋል።
