uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 478
Підписники
+824 години
+657 днів
+91030 днів
Архів дописів
🔥#ጄትና_ድሮን_ከወሎ_ሰማይ_ስር‼️ የብልፅግና ጦር ሚግና ድሮንን ጨምሮ ሙሉ አየር ኃይሉን አሰልፏል።የፋኖ ኃይል ደግሞ አንዳች ምድራዊ ኃይል የሚያስቆመኝ የለም ብሏል። #ዘመቻው_አባ_ናደው_ነው። ናድ፣ ድቅቅ፣ ድምስስስስስስ💪 በምድር ታንክ በሰማይ ጄት ቢደባለቅ አንዴ ገጥመን መስሎኝ ወዴት ልንላቀቅ💪 #ወይ_ንቅንቅ💪 ህዝባችን ወደቤትህ ግባ ጀግኖቻችን ደግሞ በጥንቃቄ ተንቀሳቀሱ‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 16/ዐ1/2018 ዓ.ም

የአርበኛ ሀብቴ ወልዴ መልዕክት... የፋሽስቱ ብልጽግና ጀንበር እየጠለቀች ነው፤ የአማራ ፋኖ የድል ፀሐይ በመሀል አራት ኪሎ እያበራች ነው፡፡ የድል ፀሐያችን ለአማራ እያበራች፤ ለጠላቶች ደግሞ እያቃጠለች ነው!! ውድ የድርጅታችን አፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አመራሮች፣ የደቡብ፣ ምዕራብና ምስራቅ አማራ ቀጠናዊ ዕዞች፣ በየደረጃው ያላችሁ የዕዝ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የኮርና ከዛ በታች ያሉ ኃይል መሪዎች በሙሉ ይህ መልዕክት ከሰሜን አማራ፣ አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ከጎንደር ሰማይ ስር ለታጋዩ ሰራዊታችንና ለመላው ሕዝባችን የተላለፈ የትግል መልዕክት ነው!! በወሎ ቤተ አምሐራ ሰማይ ስር እየተደረገ ያለው የዘመቻ አርበኛ አደም አሊ ውጊያ፦ የሁለት ዓመት የትጥቅ ትግል ጉዟችን በተለይም የአፋብኃ ድርጅታዊ የትግል መስመራችን ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ያሳየ ነው፡፡ በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) እየተዘመገቡ ያሉ ወታደራዊ ድሎች ትርጉማቸው ዘርፈ ብዙ ነው። ከብዙ በጥቂቱ  ይህ ውጊያ ቀጥታ አራት ኪሎ ላይ ያነጣጠረ፣ የአራት ኪሎን የእብሪት ጉዞ በፍርሃት ያራደ ፣ የፋኖን የትግል ግብ ወደ መጨረሻው እያደረሰ ያለ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የአገዛዙን ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት፣ የኢንሳ ተቋማትን ያፈራረሰ ያለ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ ብልፅግና የሚመካበትን  ሠራዊት ፍርስርሱን ያወጣ መልሶ በሠው ኃይልም በሥነ-ልቦናም ለመገንባት እንዳይችል ያደረገ እግረኛ ሠራዊቱን በመናድ፣ በማፍረስና በመበተን ወደነፃነት ተፋላሚው እንዲቀላቀል በማድረግ ላይ ያለ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የብልፅግና ካድሬን የፍርሃት ውቂያኖስ ውስጥ የከተተ በካድሬው መካከል ቀውስን የዘራ የሞራል ድምሰሳን ያስከተለ ተዓምራዊ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የአገዛዙን የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ያፈራረሰ፣ የአገዛዙ አፎችን የለጎመ፤ ቅጥረኛ አፈ ቀላጤዎችን ፕሮፖጋንዳ ራቁቱን ያስቀረ የአማራ ልጆች በደማቸው ታሪክ እየሰሩ ያለበት ማርሽ ቀያሪ ውጊያ ነው!  ይህ ውጊያ የትግሉ ደጋፊዎችን ሁሉ የትግል ወኔ ያስታጠቀ፤ የፋኖ  ትጥቅ የደረሰበትን የወታደራዊ፣ የመረጃና ደህንነት፣ የውጊያ ምህንድስናና ዕቅድ፤ የዘመቻ አፈጻጸም የማድረግ አቅም ያመላከተ አዲስ የውጊያ ምዕራፍ ነው። የአማራ ፋኖ ትግል ደጋፊዎች በተለይም የድርጅታችን አፋብኃ ደጋፊዎች በያላችሁት መድረክ የህልውና ትግሉ አካል ሆናችሁ መዳረሻውን ድልና ነጻነት ያደረገውን ትግላችን በፅናት እንድትደግፉ የትግል ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታይ ወገኖች እንኳን ፤ለብርሃነ መስቀሉ በዓል አደረሳችሁ! የክርስቶስ መስቀል ተስፋ ባለመቁረጥ ፍለጋ ከተደበቀበት እንደተገኘው ሁሉ፣ የአማራ ሕዝብ የነጻነት ትግልም በልጆቹ ቆራጥ መስዋዕትነት ድልና ነጻነቱ ይገኛል፡፡ ኀልውናውንም በተባበረ ክንዱ ይረጋገጣል፡፡ ድል ለአፋብኃ! ድል ለአማራ ሕዝብ!! አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የሰሜን አማራ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ ህልውናችን በተባበረ ክንዳች የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ‎       ‎መስከረም 16/2018 ዓ.ም ‎16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ኮማንዶ ፍቅሩ አሁን በፋኖ እጅ ለሚገኙ ምርኮኞች የተናገረው !

‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በጠላት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል። ‎ ‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ እና አፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር በፈረድ ውሃ እና ሸበቶ በተባለ ቦታ ከባድ ውጊያ አካሄደዋል:: ‎የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክ/ ጦር ቃኝወች እና ደመላሽ ሻለቃ አንድ ሻምበል በቅንጅት በፈረድ ውሀ ቀበሌ በወሰዱት ኦፕሬሽን ጥምር የአብይ አህመድ ሰራዊት ዱቄት ሁኗል ። ‎ ‎ይህንን ኦፕሬሽን የወሰዱት ነበልባሎቹ የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ቃኚዎች እና የደመላሽ ሻለቃ ጠላት ቀጠና ድረስ ዘልቀው በመግባት ነው:: ‎በዚህም አውደ ውጊያ ጠላት የደረሰበትን ምት መቋቋም አቅቶት አስከሬኑን እያንጠበጠበ ጥሎ ወደ አጣዬ ከተማ ወጥቷል:: ‎ ‎በተመሳሳይ የአፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር ብሩኬ ደምሴ ብርጌድ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ ሸበቶ ቀበሌ በወሰደው ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት አንድ መቶ አለቃን ጨምሮ በርካታ የስርዓቱ ሰራዊት ተደምስሷል:: ‎ ‎የብሩኬ ደምሴ ብርጌድ ከግሸ ራቤል ወረዳ ተነስቶ ወደ አንጾኪያ ገምዛ ወረዳ በተንቀሳቀሰው  ራሱን 105ኛ ኮምንዶ ብሎ በሰየመው ጠላት ላይ በተወሰደ እርምጃ ኃይል መሪውን ከነ አባሉ አስደምስሶ ሸሽቷል። ‎ ‎ ህልውናችን በተባበረ ክንዳች የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ‎       ‎መስከረም 16/2018 ዓ.ም ‎16/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ኮማንዶ ፍቅሩ አሁን በፋኖ እጅ ለሚገኙ ምርኮኞች የተናገረው ! "እንደ አብይ አህመድ ቢሆን ቆፍረን ብንቀብራችሁ ደስ ይለን ነበር! ነገር ግን እኛ አማራዎች ነን የወደቀ ግንድ ላይ መጥረቢያ አናበዛም
ኮማንዶ ፍቅሩ አሁን በፋኖ እጅ ለሚገኙ ምርኮኞች የተናገረው ! "እንደ አብይ አህመድ ቢሆን ቆፍረን ብንቀብራችሁ ደስ ይለን ነበር! ነገር ግን እኛ አማራዎች ነን የወደቀ ግንድ ላይ መጥረቢያ አናበዛም እናታችሁ ትመርቀናለች ወደ ቤተሰቦቻችሁ እንልካቹሀለን። ደግሜ ገብቼ እዋጋለሁ ብለህ ካገኘነህ ግን እኛን አያርገን ምህረት የለንም! አሁን ለምታለቅሰው እናትህ ሰንል እና አለማቀፍ ህግንን አክበረን የምንዋጋ ዘመናዊ ሰራዊት ስለሆንን ወደቤትህ እንሰድሀለን!"

ቀን 16 /2018 ዓ.ም                       ቁጥር መ/ክ/ጦ 01/01/2018 ዓ.ም                  #የሐዘን_መግለጫ🕯️ በትላንትናው እለት መስከረም 15 /2018 ዓ.ም በሊቦ ከምከም ወረዳ ፎከራ ልዩ ስሙ ላምየ ከተባለው ቦታ በግዳጅ ላይ እያለ ብልጽግና ስርዓት ተልእኮ በሰጣቸው ከሃዲ ፋኖዎች ጓዳችን መንድማችን አርበኛ ሙቀት ጥሩነህን ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ገደማ ነጥቀውናል።        አርበኛ ሙቀት ጥሩነህ የፋኖ ትግል ከተጀመረ አንስቶ በመብረቅ ክ/ጦር ተጠርንፎ ሲታገልና ሲያታግል የነበረ ጀግና ጓዳችን ነበር።     አርበኛ ሙቀት ጥሩነህ መብረቅ ክ/ጦር ከጠላት ጋር በተዋጋችበትና ጠላትን ድል በነሳችበት በሁሉም ግንባሮች ከትግል ጓዶቹ ጋር ግንባር ቀደም ሆኖ በመሰለፍ ተወዳዳሪ የሌለው ጓዳችን ነበር። በዚህ የትግል አስተዋጽኦውና የትግል ተሞክሮው መብረቅ ክ/ጦር የአመራር ሽግሽግ በምታደርግበት ወቅት አርበኛ ሙቀት ጥሩነህ የክ/ጦሯ ም/ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ እንዲመራና እንዲታገል በተሰጠው ኃላፊነት እየታገለና እያታገለ ባለበት በዚህ ሰዓት ነው በከሃዲ ፋኖዎች የተገደለው።     የጓዳችን አርበኛ ሙቀት ጥሩነህ አስከሬንም በመላው የትግል አጋሮቹ፣ በወዳጅ ዘመዶቹ በሚካኤል ደብርና አካባቢው ህዝብ ታጅቦ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቀድመውት በጀግንነት ከተሰውት ጓዶቹ አጠገብ የቀብር ስነ ስርዓቱ ተፈጽሟል።      ጓዳችን አርበኛ ሙቀት ጥሩነህ የሞተለትን እንቁ ዓላማ ከግቡ ለማድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል እንደምንሰራ አበክረን እንገልፃለን።    ለቤተሰቦቹ ፣ ለትግል ጓዶቹ ፣ ለመላው የትግል አጋራችንና ወዳጆቻችን መጽናናትን እንመኛለን።    የጓዳችንን ነብስ በአጸደ ገነት ያኑርልን ።          ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!       © አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር መብረቅ ክ/ጦር ስራ አስፈፃሚ             መስከረም 16 / 2018 ዓ.ም 16/ዐ1/2018 ዓ.ም

በወልድያ ከተማ ጀነቶ ተብሎ የሚጠራው አከባቢ(ዩኒቨርስቲው) በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቷል። ከመኃል መቻሬ(ስታዲየም) በቅርብ ርቀት ጎላ መቻሬ፣ አማየሚጫ፣ ውድመን፣ ገብሬ አምባው የተባሉ ቀበሌዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል። ከተማዋ ዙሪያ የሚደረገው ትንቅንቅ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።

#አስታጥቄ💪 ኧረ አጨብጭብ ወገን የሚኒሊክ እስትንፋሾች💪 16/ዐ1/2018 ዓ.ም
+2
#አስታጥቄ💪 ኧረ አጨብጭብ ወገን የሚኒሊክ እስትንፋሾች💪 16/ዐ1/2018 ዓ.ም

መርሣ ከተማን ጨምሮ ብዙ የወረዳ ከተሞች በፋኖ ቁጥጥር ስር ሆነዋል‼ ስሪንቃ፣ መርሳ፣ ውርጌሳ፣ ገንፎ ጨፌ፣ መሀል አምባ፣ ሊብሶ፣ ውጫሌና ከሐይቅ በቅርብ ርቀት እስከሚገኘው ጃሪ በፋኖ ቁጥጥር ስር
መርሣ ከተማን ጨምሮ ብዙ የወረዳ ከተሞች በፋኖ ቁጥጥር ስር ሆነዋል‼ ስሪንቃ፣ መርሳ፣ ውርጌሳ፣ ገንፎ ጨፌ፣ መሀል አምባ፣ ሊብሶ፣ ውጫሌና ከሐይቅ በቅርብ ርቀት እስከሚገኘው ጃሪ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል። ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም ያልቻሉት የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛቸውን ሳያነሱ ወደ ሐይቅና ደሴ ከተሞች እየሸሹ ነው። #ዘመቻ አባናደው#

“ቃል በተግባር ፤ለአንድነት ሲባል የምናስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ የለም” ታሪካዊ ጠላቶቻችን አማራ የሚባል ጠላት በምናባቸው ፈጥረው እና ልብወለድ ፅፈው ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት አማራን ሲገድሉት ኖረዋል፡፡ተረኛው ገዳይ ቡድን ብልፅገና ላለፉት 8 ዓመታት አማራ ላይ የሞት አዋጅ አውጆ  ወገናችን ተጨፍጭፏል፡፡ ከጭፍጨፋው የተረፈው ለቀጣይ 40 ዓመታት እንኳን እንዳያገግም ሁሉን አቀፍ ውድመት ደርሶበታል፡፡ በተለይ በወለጋ ክፍለ ሃገር የሚኖረው አማራ ላይ ደረሰው ግፍ እንኳንስ በገሃዱ ዓለም ፣በልብወለድ መፅሐፍ ላይ ለመፃፍ እንኳን ፀሐፊው እጁ ሊታዘዝለት የማይችለው ከአዕምሮ በላይ የሆነ የበደል ጥግ ደርሶበታል፡፡እንኳን ለሰውና ለዱር እንስሳት እና ለእፅዋት ህልውና ጥብቅና እንቆማለን የሚሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ባሉበት ዓለም ላይ አማራ ላይ የደረሰውን ስቃይ ሰበር ዜና ብለው መሞታችንን ከማረጋገጥ ባለፈ ምንም አለማድረጋቸውን ስናይ ለአማራ ሞት ይቺ ዓለም ተባባሪ ናት አስብሎናል፡፡ አማራ ከፈጣሪ በታች መዳኛው ክንዱ በቻ መሆኑን ባሳለፍናቸው 5 ዓመታት እራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን በመጠቀሙ ልምድ አግኝቶበታል፡፡ ቀጥሎ በወለጋ ክፍለ ሃገር የሚኖረውን አማራ ከፈፅሞ መጥፋት ለመታደግ የወለጋ ክፍለ ሃገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) አደራጅቶ ዱር ቤቴ ካለ ሰነባብቷል፡፡ የወለጋ ክፍለ ሃገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) የአማራ ህልውና የሚረጋገጠው ሁሉም ታጋይ በአንድ አታጋይ አማራዊ ድርጅት ስር ሁኖ ሲታገል እንደሆነ በፅኑ ስለሚያምን፣ በተለያዬ ጊዜ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድ አማራዊ ድርጅት ለመምጣት ባደረጉት ሙከራ ሁሉ የወለጋ ክፍለ ሃገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) ተሳታፊ በመሆን የበኩሉን አስተዋፅኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ ግንቦት 1/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲመሰረትም ከመስራቾች ውስጥ አንዱ በመሆን የቆመለትን ዓላማ ለማሳካት አንድ እርምጃ ወደ ፊት ተራምዷል፡፡ለዚሁም የአማራን የመከራ፣የሰቆቃ እና የግፍ ዘመን ለማሳጠር እንዲሁም ቀጣዩን የአማራን ህዝብ ዕጣ ፋንታ ታሳቢ ያደረገ ትግል ምዕራፍ ውስጥ ለመገባት ሲባል ስንታገልበት የነበረውን ድርጅታችንን የወለጋ ክፍለ ሃገር ፋኖ ዕዝ (ቢዛሞ) የስም ስያሜውን ወደ አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ የቀየርን መሆኑን እያሳወቅን፣ አፋብኃ ለቢዛሞ ዕዝ በላከልን ደብዳቤ መሰረት የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ትግል ውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርጅቱ በሚፈልገው መስመር ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናችንን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በመሆኑም በመላው ዓለም የምትገኙ የአማራ ፋኖ ታጋዮች እና ደጋፊዎች የ 70 ሚሊዮን አማራን ህልውና ለማረጋገጥ የተመሰረተው የጋራ ቤታችን አፋብኃ ሌላኛው የቤቱ ግርግዳ  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ መሆኑን በደስታ ልናበስራችህ እንወዳለን፡፡ ከእንግዲህ ‹አማራ ለአማራ ከአማራ በአማራ› የመጣ የሄደው የሚገደለው ባለጊዜ እንዳይኖር ዛሬ ላይ ሁነን ነገን እንሰራለን፡፡ በመጨረሻም ይህ የአዲሱ ትውልድ ህልውና ትግል የአማራን ህዝብ የስቃይ ጊዜያትን በማሳጠር ትንሳዔውን በቅርብ ለማድረግ የሚደረግ ነውና ከሁሉም በፊት የአማራን ህልውና ማረጋገጥ ይቅደም እንላለን፡፡                                         ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ

በቀን 16/01/2018 ዓ.ም የአረመኔው መንግስት አሽከር መረጃ ክፍል ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ተመስጌን ካሴ እና ሌሎች ሁለት ምሊሻዎች ከየጁቤ በመውጣት የአፋብኃ ምዕ/አ/ቀ/ቴ/ዕዝ የሐዲስ ዓለማየ
+1
በቀን 16/01/2018 ዓ.ም የአረመኔው መንግስት አሽከር መረጃ ክፍል ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ተመስጌን ካሴ እና ሌሎች ሁለት ምሊሻዎች ከየጁቤ በመውጣት የአፋብኃ ምዕ/አ/ቀ/ቴ/ዕዝ የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር አብራጂት ብርጌድን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅሏል።

ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ በሶስት ግንባር ተጋድሎ በማድረግ ድል ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ታቦር ተራራ ብርጌድ መስከረም 12/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በሶስት ግንባር በጓሜዳ ከተማ፣ መለስ ሳንቃ በር፣ እና እዋ ከተማ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: ተጋድሎው በተደረገበት ሶስት ግንባር በጓሜዳ ወንድም መልኬነው ሻለቃ፣ ያምረው አለሙ ሻለቃ አንድ ሻምበል፣ እና የብርጌድ ቃኝ በጥምረት አንድ ፓትሮል የጠላት ሃይል ሲደመስሱ ከዚህ በተጨማሪም 15 ሚሊሻ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም ሶስት ክላሽ በመማረክ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል:: በሌላኛው እዋ ከተማ ግንባር ሳተናው ሻለቃ እና ነብሮ ሻለቃ በጥምረት ከተማው ላይ መሽጎ የነበረ አድማ ብተናና ሚሊሻ ጋር ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ በርካታ ሆድ አደር በመደምሰስና ቀሪውን በመበታተን ከተማዋን ተቆጣጥረዋል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ጠላት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን እስካሁን አስከሬኑን በማንሳት ላይ ይገኛል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 13/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በወንዳች በር፣ሙጃ፣ኩልመስክ፣ ዴንሳ በነበረው ቀጠና መስከረም 15/2018 ዓ.ም በተደረገው አውደ ውጊያ የተማረከ መሳሪያና ምርኮኛ።

ሰበር መረጃ❗️ ወልድያ የሚገኘው የብልፅግና አመራር ተሰልፎ እጁን ለፋኖ እያስረከበ ይገኛል። ቻው ብልፅግና❗️
ሰበር መረጃ❗️ ወልድያ የሚገኘው የብልፅግና አመራር ተሰልፎ  እጁን ለፋኖ እያስረከበ ይገኛል። ቻው ብልፅግና❗️

ሰበር ከወልድያ! ሚሊሻው ካድሬዎችን አገደ! በከተማዋ፡ ጀነቶ በርና መኃል መቻሬን ጨምሮ በዙሪያዋ በሚገኙ አከባቢዎች ከባድ ውጊያ መቀስቀሱን ተከትሎ፡ በከተማዋ የቀሩ የከተማ አስተዳደሩና የዞን አመራሮች ወደ ሐራ ሊሸሹ ሲሞክሩ በሚሊሻ አባላቱ መታገዳቸው ተሰምቷል። "ማን ሞቶ ማን ሊተርፍ ነው፡ ካለቅን ሁላችንም እዚሁ እንለቅ" በሚል የሚሊሻ አባላቱ ካድሬዎቹ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ማገዳቸውን የመረብ ሚዲያ ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል። በዚህም ካድሬ አሳፍረው የነበሩ ከ30 በላይ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ፒያሳ ዳቦ ቤቱ ላይ ታግደው ቆመዋል። በተመሣሣይ፡ ከትናንት ጀምሮ ቀድመው በመውጣት ሐራ የነበሩ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በባለሽርጡ ክ/ጦር ተቆርጠናል በሚል ወደ ሌሎች የአፋር አከባቢዎች ለመሸሽ እየተጋፉ ቢሆንም ነገር ግን የሚያጅባቸው ወታደር አጥተው ከባድ ጭንቀትና ሽብር ላይ መውደቃቸው ታውቋል። የሐራና የአከባቢው ወጣቶችም "ከተማችን የባንዳ መደበቂያ መሆን የለባትም" በሚል እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ቻለው! ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎