ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 632
Підписники
+124 години
+3977 днів
+1 06030 днів
Архів дописів
የድል ዜና !!
የኮሮቹ ጥምረት በደማቅ ድል እንደቀጠለ ነው ።
የካቲት 24/2018 ዓ/ም
የቴዎድሮስ ዕዝ ሶስት ኮሮች በመጣመር ፋግታ ለኮማ ወረዳ ላይ ብዛት ያለውን የጠላት ሀይል በመደምሰስ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል።
የዛሬ 130 አመት ወደ ኋላ አባቶቻችን በደማቸዉ ታሪክ በመፃፍ ለጥቁር ዘር ሁሉ ክብር፣ ለኢትዮጵያውያን የጀግንነት መገለጫ ኩራት የሆነ ድል ባስመዘገቡበት በወርሀ የካቲት የቴዎድሮስ ዕዝ ጀግኖች ከመተከል ጃዊ ጉምብር እስከ ጎጃም አገዉ ምድር የአባቶቻቸዉ ልጆች መሆናቸዉን ያስመሰኩሩበትን ታላቅ ድል አስመዝግበዋል።
የቴዎድሮስ ዕዝ ሶስቱ ኮር 105ኛ,109ኛ እና 201ኛ ኮር በጥምረት ከቀኑ 6:00 ስዓት እስከ 9:00 ስዓት በተደረገ ትንቅንቅ ጠላትን ድባቅ በመምታት ብዛት ያለው አሸባሪ የመከላከያ ሃይል ሲገደል ሙትና ቁስለኛውን ማንሳት እንዳይችል ተደርጓል።
#በዚህም ተጋድሎ፦
1/ ከ36 ጥቁር ክላሽ
2/ ከ20 ሺ በላይ ተተኳሽ
3/ ብዛት ያለው ቦምብና ወታደራዊ ቁሳቁስ ተማርኳል።
ዙፋን አስጠባቂው ሀይል ያለ የሌለ ሀይሉን በመያዝ ከድሮን እስከ ዙ_23 ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም ለመከላከል የሞከረ ቢሆንም በነበልባሎቹ ኮሮች ከመማረክና ከመደምሰስ አላዳነውም።
ድል ለጀግናው ፋኖ !!
#ዘመቻ_አርበኛ_ማንዴላ_እያዩ‼️
ጠላትን በመረፍረፍ አኩሪ ገድል ፈፁሞ ክቡር መስዋትነት በከፈለው የመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ማንዴላ ስም በተሰየመው "#ዘመቻ_አርበኛ_ማንዴላ_እያዩ " ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር #ደጎማ ላይ አኩሪና አስደማሚ ጀብድ ፈፅሟል በምርኮ ተምበሽብሿል ሲሉ ለንስር አማራ አረጋግጠዋል‼️
ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን የምንመለስበት ይሆናል‼️
#ክብርና_ሞገስ_ለትግሉ_ሰማዕታት‼️
24/ዐ6/2018 ዓ.ም
አስቼኳይ የጥንቃቄ መረጃ‼
ምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ ዋጃና አካባቢዋን ለማቃጠል የአገዛዙ ጥምር ጦር በፋንድቃ በኩል መጠጋቱን ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ምንጮች አረጋግጠውልናልና ህዝባችን በተጠንቀቅ እንዲቆም እናሳስባለን።
ገዳ ኮማንዶ፣ሚኒሻና መከላከያ በጥምረት በአሁኑ ስዓት አሰፍስፈው መቅረባቸውን የአይን እማኞች ለፍኖተ-አማራ ሚዲያ ገልጸዋል።
የካቲት 24/2018ዓ.ም
በእነማይ ወረዳ እና ሸበል በረታ ንፁሃን በጥይት ተገደሉ!!
የካቲት 22/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:10 ላይ "ወጣት ንጉስ ገዜ" የወይራ ቀበሌ ተወላጅ የኤሌክትሮኒክስ ሞባይል ጥገና ሰራተኛ እና "ወጣት ዘላለም አስማማው" የባጃጅ ሹፊር እድሜ 22 ብቸና ደብር ተወላጅ የካቲት 9/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ስዓት በእነማይ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ ሲገደሉ አድራሻቸውን ማወቅ ያልቻልናቸው ግለሰቦች መቁሰላቸውን አረጋግጠናል።
በእነማይ ወረዳ እና ሸበል በረንታ የሚገኙ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚኒሻ አካላት በሐይማኖት አባቶች ሳይቀር በማሰርና በማንገላታት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ አስመልክቶ ዛሬም ድረስ የንጹሃንን ደም ከማፍሰስ ባሻገር የንጹሃንን ማህበረሰቡ ሃብትና ንብረት እየዘረፉ መሆኑን አረጋግጠናል።
በእነማይ ወረዳ ሆድ አደር ፖሊስና ቅጥርኛ ሚሊሻ የሚመራው የጥፋት ቡድን
የካቲት 22/2018 ዓ.ም
1ኛ. ቄስ ታዴ አበባውን
2ኛ. አቶ መኩሪያው ዋለን በማሰር በማንገላታት በእንግርግሮ ሲያዋክቡ ውለዋል።
1ኛ. ከአቶ መኩሪያው ዋለ የኪስ ጥሬ ገንዘብ በመቀበል
2ኛ. ቄስ ታዴ አበባውን በቀጥታ በጥይት እንመትሀለን የፋኖ ተላላኪ ነህ፣ ከፋኖ ጋር በመቀራረብ እርቅ ትፈጽማለህ በሚል አገላለጽ ካሰቃዩትና ካንገላቱት በሆላ ከእስር መልቀቃቸውን ማረጋገጥ ችለናል፡፡ ድርጊቱን ከፈፀሙት አካላት ውስጥ:-
1ኛ. ሚሊሻ ጌታነህ ውበት መሪነት
2ኛ. ሚሊሻ መኳንንት ገናነው
3ኛ. ሚሊሻ ንጉሴ አባቴነህ
4ኛ. ሚሊሻ ተሰው አሰፋ
5ኛ.ሚሊሻ ጌታነህ ውበት የተባሉ የአገዛዙ ቅጥረኛ የሚሊሻ አባላት በወይራ ቀበሌ በተፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ተሳትፈዋል።
የካታት 24/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ውድ የፍኖተ-አማራ ሚዲያ ተከታታዮች በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም ያላችሁ በሙሉ ድላችን ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ሆኖም ግንባር ላይ ሁነን የአማራ ፋኖ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎች እየሰራን ለመላው ህዝባችን በብርሃን ፍጥነት እያደረስን እንገኛለን። ሆኖም ሚዲያችን ተደራሽ እንዲሆን ሸር እንዲሁም ለሚዲያችን አዲሲ የሆናችሁ ይወዳጁን!!
አሳዛኝ መረጃ...ከአፋር!
የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ የገባ የጅቡቲ መንግስት ሰው አልባ አውሮፕላን በአፋር ክልል በፈፀመው ጥቃት በርካታ ንፁኋኖች ተገደሉ!
ጥቃቱ የተፈፀመው በትናንትናው ዕለት የካቲት 23/2018 ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ ሲሆን፡ ጥቃቱ የተፈፀመበት ቦታ ደግሞ በአፋር ክልል ገገዴ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ መሆኑን የአከባቢው ነዋሪዎች ለፍኖተ-አማራ ሚዲያ ተናግረዋል።
በጥቃቱ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ አርብቶ አደሮች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸው ታውቋል።
በተጨማሪም በርካታ የቤት እንስሳት የተገደሉ ሲሆን መኖሪያ ቤቶችም ወድመዋል።
ኢትዮጵያ የውጭ ወራሪን በመመከት ዳር ድንበራን ያስከበረችበትን 130ኛ ዓመት የዓድዋ ድል ቀንን እያከበረች በምትገኝበት እለት ድንበሯ ተደፍሮ በዜጎቿ ላይ እንዲህ አይነት ዘግናኝ ጥቃት መፈፀሙ እጅግ ልብ ሰባሪ ነገር ነው ሲሉ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ጨምረው ገልፀዋል።
የጅቡቲ መንግስት የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በመግባት በአፋር ክልል ንፁኋኖች ላይ ያነጣጠረ የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ ሲፈፅም ይህ ለ3ኛ ጊዜው ነው።
የኢትዮጵያ ሰማይ በጎረቤት ሀገር ያሉ ታጣቂዎች ድሮኖቻቸው እንዲሁም የጎረቤት ሀገራት መንግስታት የጦር ጄቶችና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ያለ ከልካይ በኢትዮጵያ ሰማይ እየተሽከረከሩ ሕዝቡን በቦምብ አረር የሚገድሉበት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል።
+1
ሰበር የምሽት የድል ዜና!!
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
የአረመኔው ሰራዊት ከምሽቱ 3:15 ከደብረ ማርቆስ ከተማ በመነሳት ወደ ስናን በመሔድ ላይ እያለ በ206ኛ ኮር ነበልባሎች በተወሰደበት የደፈጣ ጥቃት እየፈረጠጠ ይገኛል።
ጨለማን ተገን በማድረግ በ 4 ሲኖትራክ ተጭኖ ወደ ስናን ረቡዕ ገበያ በሜሔድ ላይ የነበረው የአረመኔው ሰራዊት እነራታ ከተማን በመውጣት ላይ እያለ በተከፈተበት ድንገተኛ ጥቃት በርካታ የሰራዊት አባላት የተደመሰሱ ሲሆን ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ ተረጋግጧል። ከምሽቱ 3:40 እስከ 4:20 በወሰደው ጥቃት የጠላት ኃይል በትንትኑ ወጦ በየ ጫካው እየፈረጠጠ ነው።
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የንጉስ ተክለሃይማኖት ሻለቃ ልዩ የደፈጣ ስፔሻሊስቶች በወሰዱት የተጠና ጥቃት ባልተገመተ ሁኔታ በተዘናጋ የጠላት ኃይል ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም ድል ማስመዝገባቸው ታውቋል። ሙሉ የጥቃቱን ዝርዝር በነገው ዕለት ይዘን እንመለሳለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የትራንስፓርት አገልግሎት በተወሰኑ ቦታዎች ላልተወሰነ ጊዜ መከልከሉን በተመለከተ ከንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሰጠ መግለጫ!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ከሚንቀሳቀስባቸው ወረዳዎች መካከል በሁለቱ ወረዳዎች ማለትም በመቅደላ እና ተንታ ወረዳዎች ውስጥ ከዛሬ ማለትም የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የተከለከለ ሲሆን ከዛሬው እለት ጀምሮ ወደ መቅደላ እና ተንታ ወረዳዎች ለመግባት የሚሞክር ወይም ከሁለቱ ወረዳዎች ለመውጣት የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ላይ እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እናሳውቃለን::
ማንኛውም የተሽከርካሪ ባለንብረት እና አሽከርካሪ ኮራችን ይፋ ያደረገውን የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ በማክበር ድርጅቱ መልሶ መግለጫ እክካላወጣ ድረስ ራሱን እና ንብረቱን ከጥፋት ይጠብቅ ዘንድ ከወድሁ እንመክራለን ሲል ኮሩ ለሚመለከተው አካል ይድረስልኝ ብሎ በላከው መግለጫ አስታውቋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም
+4
ጃዊ !
የአድዋ ድልን የሚያስታውስ ገድል ተፈጽሟል‼️
የካቲት 23/2018 ዓ/ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ፣ የ206ኛና 201ኛ ኮር በጥምረት ከማረኳቸው አባላትና ትጥቆች በከፊል።
ሙሉ ሬጅመንት የተደመሰሰበት የውጊያ መረጃ ጎጃም!!
በጎጃም ጃዊ ቀጠና ኩንብር ከተማ እና አካባቢው የሰፈሩት የጠላት አሃዶች ላይ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ፣ የ206ኛ እና 201ኛ ኮሮች በጥምረት ባደረጉት መብረቃዊ ጥቃት 2ዲሽቃ፣ 10 ብሬን፣ 4 ስናይፐርን እና የክፍለ ጦር መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል።
1 ከ200 (ሁለት መቶ) በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች፣
2) 10(አስር) ብሬን/መትረዬስ፣
3) 4 (አራት) ስናፐር፣
4) 2 (ሁለት) ዲሽቃ እስከሙሉ ክሻፋው፣
5) 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በመጋዘን የተቀመጠ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣
6) 4 (አራት) መገናኛ ሪዲዮኖች
7) በርካታ የእጅ ቦንቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።
እንዲሁም 32 (ሰላሳ ሁለት ) የመከላከያ አባላት በእጅ ሲማረኩ አንድ ማዕረጉ እና ማንነቱ እየተጣራ ያለ ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ ከ150 በላይ የጠላት ሰራዊት ተደምስሷል።
ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር የአመራርና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት አካሄደ!
የካቲት:-23/2018 ዓ/ም
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ እያለ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ወቅቱን የዋጀ የፋኖ አመራርና የክፍለ ጦሮች አደረጃጀት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በተደረገ ብስለት የተሞላበትና በስክነት በመወያየት የክፍለ ጦሮች አደረጃጀትና ስያሜ እንዲሁም የኮሩን ስያሜና አመራር መልሶ ማደራጀት እንደሚከተለው ሰርቷል ፤ በድጋሜ እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።
1ኛ. የኮሩ ስያሜ:- ቀድሞ ከነበረው ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ወደ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር በሚል ስያሜው ተቀይሯል::
2ኛ. የክፍለ ጦሮች መልሶ ማደራጀትን በተመለከተ ኮሩ ከነበረው ስምንት ክፍለ ጦሮችና ሁለት ብርጌዶች ለአሰራርና ቁጥጥር ያመች ዘንድ ወደ አምስት ክፍለ ጦር የተደራጄ ሲሆን :-
2.1. ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣ እሸት ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ በአንድ በመዋሀድ 19ኛ ክፍለ ጦር ፣
2.2. ተከዜና ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 21ኛ ክፍለ ጦር፣
2.3. ኃይሉ ከበዴና ጥራሪ ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 14 ክፍለ ጦር፣
2.4. ውባንተ አባተና ራስ አንችም ክፍለ ጦሮች በመዋሀድ 81ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም፣
2.5. ከሁሉም ክፍለ ጦሮች በማውጣጣት የተቋቋመው ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ክፍለ ጦር 16ኛ ክፍለ ጦር በሚል የክፍለ ጦሮች መልሶ ማደራጀት ተሰርቷል።
3ኛ. የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር የአመራር መልሶ ማደራጀት የተሰራ ሲሆን:-
1. ኮር ሰብሳቢ:- አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉዬ
2. ኮር ም/ሰብሳቢ:- አርበኛ ታዘበው ሻምበል
3. ወታደራዊ አዛዥ:- አርበኛ ኮማንዶ ብርሐን አሰፋ
4. ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ:- አርበኛ በሪሁን ደምሌ
5. ኮር አስተዳደር:- አርበኛ ሞላ አዳነ
6. መረጃና ደህንነት:-𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
7. ምክትል ወታደራዊ አዛዥ:- አርበኛ ጣሰው አለልኝ
8. ዘመቻ መምሪያ:- አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ
9. ምክትል ዘመቻ (ስምሪት):- አርበኛ አያናው እንየው
10. መገናኛና ኦፕሬተር:- አርበኛ አማሪው አያናው
11. ሎጅስቲክ መምሪያ:- አርበኛ መልኩ አለምዬ
12. ኦርዲናንስ መምሪያ:- አርበኛ ብርቁ አራጋው
13. ጥገና ክፍል:- መቶ አለቃ ተስፋዬ አበበ
14. ስልጠና መምሪያ:- ሃምሳ አለቃ መልካሙ ገበየሁ
15. ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ:- አርበኛ ፀጋዬ አካልነው
16. ህዝብ ግንኙነት መምሪያ:- አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን
17. ህዝብ አስተዳደር መምሪያ:- ሃምሳ አለቃ መንግስቱ ካሳ
18. አደረጃጀት መምሪያ:- አርበኛ ጋሻው አበበ
19. ህግ ክፍል:- አርበኛ ዋኘው አደራው
20. ምክትል ህግ ክፍል:- ሳጅን አድሱ አራጋው
21. ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ ግርማ ቅባቴ
22. ሴቶች ጉዳይ መምሪያ:- አርበኛ አባይ ውበቴ
23. ፋይናንስ መምሪያ:- አርበኛ ሲሳይ ተስፋው
24. የሰው ኃይል መምሪያ:- አርበኛ ጥጋቡ ሲሳይ
25. ሐብት አፈላላጊ:- አርበኛ አለበል ነጋሽ
26. ጤና መምሪያ:- አርበኛ ምስጋናው አዱኛው
27. ኦዲተር:- አርበኛ ባለሟል ሽመልስ
28. ምክትል መረጃና ደህንነት:-𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
29. ፀረ-መረጃ:- 𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥𝑥
30. ወታደራዊ አማካሪ :- አርበኛ ተመቼ ቢራራ
31. ፖለቲካዊ አማካሪ:- አርበኛ ፍቅረማርያም ደሴ ሆነው በመመረጥ ኮሩ የአመራርና የኮር መልሶ ማደራጀትና የስያሜ ለውጥ ከዛሬ የካቲት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ያደረገ መሆኑን እናሳውቃለን።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
አፋብን |ቴዎድሮስ ዕዝ
ዘመቻ ሽመልስ በአድዋ ድል መታሰቢያ 206ኛ ኮር በአምስት ግምባሮች በከፈተው የተቀናጀ ማጥቃት ደማቅ ድል አስመዝግቧል።
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
=====================================
በወርሀ የካቲት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን በልዩ ግዳጅ ታሪክ ሰርቶ በጃዊ በተሰዋው እንቁ ታጋይ በሽመልስ ዘመቻ ያወጀው 206ኛ ኮር፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በከፈተው የተጠናከረ ውጊያ በውሀ ጋኑ የመሸገውን ጠላት 14ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ሻለቃ በሞርተር በመታገዝ ባደረገችው ማጥቃት ጠላትን በምሽጉ አንገቱን ቀልተዋለች።
ባልተጠበቀ ሰዓት የታቀደ ውጊያ የከፈተው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ እስከ ንጋቱ 1:00 በመፋለም አስደናቂ ጀብድ የፈፀመ ሲሆን ፤በተመሳሳይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 4:00 ሰዓት በሊባኖስ ከተማ የመሸገውን ጠላት የተናነቀው 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት አስክሬን ላይ እየተረማመደ የማይደፈሩ የሚባሉ የቁም ምሽጎችን ሲንዱ አርፍደዋል ። በዚህ አውደ ውጊያ የጠላት የጦር አመራሮች ጨምሮ ሚኒሻና አድማ ብተናዎች መገደላቸው ተረጋግጧል።
ጠላት እንዳይተሳሰር ከደብረ ማርቆስ ደጀን ቁይ ድረስ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተው 206ኛ ኮር የጠላትን ዋና ወታደራዊ ካምፕ አድርጎ የተቀመጠበትን የየትኖራ ወታደራዊ ሰፈር በሞርተር በመደብደብ የኃይል ሚዛኑን ያዛባው 34ኛ ክ/ጦር በደጀን ወረዳ በጉብያ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ባደረገው የሙሉ ድምሰሳ ውጊያ ከ60 በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ጠላት ዙ-23 ሞርተር መድፍና BM ቢጠቀምም የኃይል ብልጫ መውሰድ አልቻለም።
በቅጥል ስሙ "ኮከብ" ተብሎ የሚጠራው የአድማ ብተና ዘመቻ መሪ በተገደለበት የጉብያ ግምባር 34ኛ ክ/ጦር ከጠላት ጋር በመተናነቅ ጠንካራ የሚባሉ ምሽጎችን በቦምብ በማፈራረስ ጠላት የሚመካባቸው የሚኒሻ አመራሮችም ተገድለዋል።
በሌላ ግምባር 24ኛ ክ/ጦር በቁይ ከተማና አቅራቢያ በአደረገችው ማጥቃት የደባይ ጮቄ ሻለቃ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት በመወጣት በርካታ የጠላት ኃይል መደምሰሷም የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች እስከ 6:30 በተፈፀመው ማጥቃት ከ125 በላይ የጠላት ኃይል ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።
በጀግናው ሽመልስ ዘመቻ ሰይሞ የጠላትን ኃይል በማዛነፍና የግንኙነት መስመሩን በመበጣጠስ በጉብያ የመሸገውን ጠላት መሉ ድምሰሳ የፈፀመው 206ኛ ኮር በኮሩ ወታደራዊ አመራሮች እና የክ/ጦር ወታደራዊ አመራሮች ሻለቆችን በማቀናጀት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ውጊያ የጠላትን ማዘዣ ጣቢያን ጨምሮ በአምስት ግምባሮች ድል መቀናጀታቸውን የ206ኛ ኮር ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ የህዝብ አስተዳደር መምሪያ ሃላፊው አርበኛ እስራኤል እሸቴ ባለቤት በፋሽስቱ አገዛዝ ኮምቦልቻ በግፍ ታስራ ትገኛለች:: የአርበኛው ባለቤት የአምስት ወር መንታ ህፃን እመጫት ስትሆን ከልጆቿ ተለይታ ስለታሰረች መንታ ህፃናቶቹ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ::
የካቲት 23/2018 ዓ/ም
በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ እዝ የልጅ እያሱ ኮር አመራሮች በደቡብ ወሎ ዞን ለገሒዳ ወረዳ ሽክፍና አካባቢ ካሉ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የተደረገ ውይይት።
በውይይቱ ላይ የተገኙ አመራሮች
1ኛ አርበኛ እንዳሻው ጌታሁን የልጅያሱ ኮር ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
2ኛ ሀምሳ አለቃ ሞላ የልጅ እያሱ ኮር ም/ወታደራዊ አዛዥ
3ኛ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ የልጅ ዕያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊየተገኙና መድረኩን የመሩት ሲሆን በውይይቱ ላይ የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል አላማ፣ትግሉ የደረሰበት ደረጃ፣ትግሉን ለመጥለፍ ለማጠልሸት ጥላቶቻችን የሚሰሩት ሴራና ወደፊት ከውጭም ከውስጥም ትግላችንን ከሚገጥሙ ፈተናዎች እንደት መጠበቅ እንዳለበትና ትግሉን ደግፎ ለማስቀጠል ጠንከር ያለ አቋም በመያዝ ጭምርና በአፋብን መመስረት ያላቸውን ደስታ ጭምር በመጥቀስ የተሰራውን አንድ አማራዊ ቤትም እንደአይን ብሌናቸው እንደሚጠብቁት በማረጋገጥ ጭምር የአማራ ህዝብ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በመደገፍ ከፋኖ ጎን እንደሚቆሙ በደስታና ወኔ አረጋግጠውልናል።በተጨማሪም የለገሂዳ ንዑስ ወረዳ አስተዳደር ተመስርቶ የስራድርሻ ሀላፊነትና ተግባር በማሳወቅ በህብ ፊት የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ቃለ መሀላ ፈፅመው ተረሀክበዋል።
የአማራ ህዝብ ነፃነት በልጆቹ ተጋድሎ ይረጋገጣል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
ሪፖርት አቅራቢ
አርበኛ ሱልጣን የሱፍ
አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር
ህ/ግንኙነት ።
