ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 619
订阅者
+124 小时
+3977 天
+1 06030 天
帖子存档
አፋብን |ቴዎድሮስ ዕዝ
ዘመቻ ሽመልስ በአድዋ ድል መታሰቢያ 206ኛ ኮር በአምስት ግምባሮች በከፈተው የተቀናጀ ማጥቃት ደማቅ ድል አስመዝግቧል።
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
=====================================
በወርሀ የካቲት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን በልዩ ግዳጅ ታሪክ ሰርቶ በጃዊ በተሰዋው እንቁ ታጋይ በሽመልስ ዘመቻ ያወጀው 206ኛ ኮር፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በከፈተው የተጠናከረ ውጊያ በውሀ ጋኑ የመሸገውን ጠላት 14ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ሻለቃ በሞርተር በመታገዝ ባደረገችው ማጥቃት ጠላትን በምሽጉ አንገቱን ቀልተዋለች።
ባልተጠበቀ ሰዓት የታቀደ ውጊያ የከፈተው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ እስከ ንጋቱ 1:00 በመፋለም አስደናቂ ጀብድ የፈፀመ ሲሆን ፤በተመሳሳይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 4:00 ሰዓት በሊባኖስ ከተማ የመሸገውን ጠላት የተናነቀው 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት አስክሬን ላይ እየተረማመደ የማይደፈሩ የሚባሉ የቁም ምሽጎችን ሲንዱ አርፍደዋል ። በዚህ አውደ ውጊያ የጠላት የጦር አመራሮች ጨምሮ ሚኒሻና አድማ ብተናዎች መገደላቸው ተረጋግጧል።
ጠላት እንዳይተሳሰር ከደብረ ማርቆስ ደጀን ቁይ ድረስ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተው 206ኛ ኮር የጠላትን ዋና ወታደራዊ ካምፕ አድርጎ የተቀመጠበትን የየትኖራ ወታደራዊ ሰፈር በሞርተር በመደብደብ የኃይል ሚዛኑን ያዛባው 34ኛ ክ/ጦር በደጀን ወረዳ በጉብያ ከተማ በመሸገው ጠላት ላይ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ባደረገው የሙሉ ድምሰሳ ውጊያ ከ60 በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ጠላት ዙ-23 ሞርተር መድፍና BM ቢጠቀምም የኃይል ብልጫ መውሰድ አልቻለም።
በቅጥል ስሙ "ኮከብ" ተብሎ የሚጠራው የአድማ ብተና ዘመቻ መሪ በተገደለበት የጉብያ ግምባር 34ኛ ክ/ጦር ከጠላት ጋር በመተናነቅ ጠንካራ የሚባሉ ምሽጎችን በቦምብ በማፈራረስ ጠላት የሚመካባቸው የሚኒሻ አመራሮችም ተገድለዋል።
በሌላ ግምባር 24ኛ ክ/ጦር በቁይ ከተማና አቅራቢያ በአደረገችው ማጥቃት የደባይ ጮቄ ሻለቃ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት በመወጣት በርካታ የጠላት ኃይል መደምሰሷም የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች እስከ 6:30 በተፈፀመው ማጥቃት ከ125 በላይ የጠላት ኃይል ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።
በጀግናው ሽመልስ ዘመቻ ሰይሞ የጠላትን ኃይል በማዛነፍና የግንኙነት መስመሩን በመበጣጠስ በጉብያ የመሸገውን ጠላት መሉ ድምሰሳ የፈፀመው 206ኛ ኮር በኮሩ ወታደራዊ አመራሮች እና የክ/ጦር ወታደራዊ አመራሮች ሻለቆችን በማቀናጀት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ውጊያ የጠላትን ማዘዣ ጣቢያን ጨምሮ በአምስት ግምባሮች ድል መቀናጀታቸውን የ206ኛ ኮር ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
የአፋብን ምኒልክ ዕዝ የህዝብ አስተዳደር መምሪያ ሃላፊው አርበኛ እስራኤል እሸቴ ባለቤት በፋሽስቱ አገዛዝ ኮምቦልቻ በግፍ ታስራ ትገኛለች:: የአርበኛው ባለቤት የአምስት ወር መንታ ህፃን እመጫት ስትሆን ከልጆቿ ተለይታ ስለታሰረች መንታ ህፃናቶቹ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ::
የካቲት 23/2018 ዓ/ም
በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ እዝ የልጅ እያሱ ኮር አመራሮች በደቡብ ወሎ ዞን ለገሒዳ ወረዳ ሽክፍና አካባቢ ካሉ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የተደረገ ውይይት።
በውይይቱ ላይ የተገኙ አመራሮች
1ኛ አርበኛ እንዳሻው ጌታሁን የልጅያሱ ኮር ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
2ኛ ሀምሳ አለቃ ሞላ የልጅ እያሱ ኮር ም/ወታደራዊ አዛዥ
3ኛ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ የልጅ ዕያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊየተገኙና መድረኩን የመሩት ሲሆን በውይይቱ ላይ የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል አላማ፣ትግሉ የደረሰበት ደረጃ፣ትግሉን ለመጥለፍ ለማጠልሸት ጥላቶቻችን የሚሰሩት ሴራና ወደፊት ከውጭም ከውስጥም ትግላችንን ከሚገጥሙ ፈተናዎች እንደት መጠበቅ እንዳለበትና ትግሉን ደግፎ ለማስቀጠል ጠንከር ያለ አቋም በመያዝ ጭምርና በአፋብን መመስረት ያላቸውን ደስታ ጭምር በመጥቀስ የተሰራውን አንድ አማራዊ ቤትም እንደአይን ብሌናቸው እንደሚጠብቁት በማረጋገጥ ጭምር የአማራ ህዝብ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ በመደገፍ ከፋኖ ጎን እንደሚቆሙ በደስታና ወኔ አረጋግጠውልናል።በተጨማሪም የለገሂዳ ንዑስ ወረዳ አስተዳደር ተመስርቶ የስራድርሻ ሀላፊነትና ተግባር በማሳወቅ በህብ ፊት የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ቃለ መሀላ ፈፅመው ተረሀክበዋል።
የአማራ ህዝብ ነፃነት በልጆቹ ተጋድሎ ይረጋገጣል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
ሪፖርት አቅራቢ
አርበኛ ሱልጣን የሱፍ
አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር
ህ/ግንኙነት ።
አፋብን |ቴወድሮስ ዕዝ 130ኛውን የአድዋ ድል የሚያስታውስ ገድል ፈፅሟል።
የካቲት 23/2018 ዓ/ም
በጎጃም ጃዊ ቀጠና ኩንብር ከተማ እና አካባቢው የሰፈሩት የጠላት አሃዶች ላይ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ፣ የ206ኛ እና 201ኛ ኮሮች በጥምረት ባደረጉት መብረቃዊ ጥቃት 2ዲሽቃ፣ 10 ብሬን፣ 4 ስናይፐርን እና የክፍለ ጦር መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርከዋል።
ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አነጋግ ላይ በተደረገው ዉጊያ የጠላት ወታደራዊ መኮንኖች ከእነ እግረኛ ሰራዊታቸው ተደምስሰዋል።
ከሶስቱ ክንደ ብርቱ ኮሮች የተውጣጣ ኃይል አቅደው በተሳተፉበት ዘመቻ ጠላት የቁም ምሽግ ቆፍሮ ከተቀበረበት ዘልቆ በመግባትና አፈና በመፈጸም የጠላትን ሎጀስቲክስና የሠው ሀይል መማረክና መደምሰስ ተችሏል። የእጅ ቦንቦችን በብዛት በመጠቀም በተፈፀመው በዚህ አስደናቂ ወታደራዊ ጀብዱ ከተማረኩት ቁሳቁሶች መካከል:-
1 ከ200 (ሁለት መቶ) በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች፣
2) 8 (ስምንት ) ብሬን/መትረዬስ፣
3) 4 (አራት) ስናፐር፣
4) 2 (ሁለት) ዲሽቃ እስከሙሉ ክሻፋው፣
5) 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በመጋዘን የተቀመጠ የክላሽ እና የብሬን ጥይት፣
6) 4 (አራት) መገናኛ ሪዲዮኖች
7) በርካታ የእጅ ቦንቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።
እንዲሁም 32 (ሰላሳ ሁለት ) የመከላከያ አባላት በእጅ ሲማረኩ አንድ ማዕረጉ እና ማንነቱ እየተጣራ ያለ ከፍተኛ አዛዥን ጨምሮ ከ150 በላይ የጠላት ሰራዊት ተደምስሷል።
የፋሺዝም መንፈስ ወራሽ የሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝ ከባዕዳን ኃይሎች ጋር በመተባበር በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ቆርጠን መነሳታችንን በእለተ አድዋ ቃላችን በድጋሚ በማደስ እናረጋግጣለን።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና!
መብረቅ ክፍለ ጦር ስትራቴጂካዊቷ ወግዲ ከተማ ዘልቆ በመግባት የግፍ እስረኞችን በማስፈታት ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
ወግዲ | የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም
ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን የምትገኘው ስትራቴጂካዊቷ ወግዲ ከተማ በፋኖ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውላለች። በንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚንቀሳቀሰው መብረቅ ክፍለ ጦር በከተማዋ በነበረው የመንግስት የፀጥታ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ከተማዋን አዳሩን ተቆጣጥሯል።
እንደ ግንባር ምንጮች መረጃ፣ የፋኖ ኃይሎች ጥቃቱን ያከናወኑት በበርካታ አቅጣጫዎች ከበባ በማድረግ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ 01 ቀበሌ (ከተማ)፣ 02 ሰርቶ ማሳያ ቀበሌ፣ በደርቢቱ እና 05 ቀበሌ እንዲሁም 03 ቀበሌ ዙሪያውን በመክበብ ኦፕሬሽኑ ተከናውኗል::
ከዚህም ተያይዞ የፋኖ ኃይሎች የወግዲ ማረሚያ ቤትን በመስበር በውስጡ የነበሩ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁ አድርገዋል። በመንግስት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካታ ቁስለኞች በአምቡላንስና በፓትሮል ሲጓጓዙ መታየታቸው ተጠቁሟል።
ይህ ወታደራዊ እርምጃ የተከናወነው በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የሚከበረውን የ130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ተገን በማድረግ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አባላት ገልጸዋል። "የዛሬው ድል የአድዋ አርበኞችን ታሪክ የደገመ ነው" ሲሉ የጦር ግንባር ምንጮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት የወግዲ ከተማ መያዝ በደቡብ ወሎ ያለውን የኃይል ሚዛን በእጅጉ ሊቀይረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
ከአርበኛ አማረ ታዘዘ ለተመራቂ ሰልጣኞች የተላለፍ የእንኳን አደርሳችሁ መልክት!!
የተከበራችሁ የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች፤ የተከበራችሁ የአሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች፣የተከበራችሁ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በስሩ ያላችሁ የክፍለ ጦር አመራሮች እንደ እየ ማረጋችሁ እንዲሁም የአሳምነው ዕዝ የፋኖ አባላት እና በምርቃት ስነስርዓት ላይ የተከኛችሁ በሙሉ!!
ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ ውጣ ውረዶች በማለፍ ለዚህ ለተቀደሰች የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
በአለም ታሪክ ውስጥ ግፍና ጭቆናን እምቢ ብለው የተነሱ ትግል ውስጥ የገቡ ማህበረሰቦች ብዙ ናቸው። ሃቀኛ የትግል መስመርና ምክንያት ያላቸው አሸንፈው ነጻ ወጥተዋል። ያላሸነፉት ደግሞ አሉ።
ከተነሱባቸው መካከል የሄይቲ ማህበረሰቦች አንዱ ሲሆኑ ፈረንሳይ ታሰቃያቸው የነበረውን ጭቆና ማብቃትና እውቀታቸውን አሸንፈው የመጀመሪያ የጥቁር ሪፐብሊክ መሆን ችለዋል። ቬትናሞች በመጀመሪያ ፈረንሳይን በመቀጠል አሜሪካን በማሸነፍ አምባገነናውያንን በመርታት ነጻነታቸውን ተቀዳጅተዋል።
በነጻነት ትግል ድል ያላቀናቸው እንደ ታሚል ነጻነት ግንባር እና የቺቺኒያ እንቅስቃሴ ያሉ አብዮቶች አሉ።
እናም እነዚህን ታሪኮች ስንመለከት መግፋትና መበደልን መንግሎ መጣል ወሳኝ ከሆኑ መሰረታዊ ነገሮች መካከል ጠንካራ የሠራዊት አንድነት፣ የጠራ የትግል መነሻና መድረክ ራዕይ መኖር፣ ህዝባዊ መሠረትና ድጋፍ፣ ኃቀኛ መሪና ተመሪ የነበራቸው ትግል ሁሉ ውጤታማ ናቸው።
ውድ የዛሬ ተመራቂዎች፣ እናንተም የአማራ ፋኖ አንድነት ከተመሠረተ በኃላ የተመረቃችሁ በመሆኑ ከላይ የጠቀስናቸው የጥራት መለኪያዎች በሚያማላው ድርጅቶች አፋብን ውስጥ አረመኔውን ስርዓት በአጭር ጊዜ ለመገርሰስ ሚናችሁ የጎላ ነው። እራሳችሁን አዘጋጅታችሁ ጊዜ ሳታባክኑ መሳተፍ የአባቶቻችሁ አደራ ነው። እንዲህ ስትሆኑ ነው ድል መምጣት የሚችለው። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ።
ውድ ጀግኖቻችን ይህንን ትግል በቅርቡ እናሸንፋለን። ማንንም ሳንበድል በማንም በኃይል ማንንም ላንገዛ ለማንም ላንገዛ የሁሉም ለሁሉም የሆነች ሃገር እና ስርዓት እንፈጥራለን። - የሁሉንም ነፃነት፣ የሁሉንም ሃገርና ዝና ታሪክ እንጠብቃለን፤ ያለ አድልዎ ይሁን። ድል የራቀ አይደለም፤ ድሉ ላልታያቸው ከእኛ በተቃራኒ ለቆሙት የስርዓቱ አሽከሮች መልዕክት አለኝ።መልዕክቴን በአንድ ተረት እቋጫለሁ።
አንድ ተኩላ እና አንድ ውሻ የጌታውን ቅጥር ግቤ እየጠበቁ ያገኛቸዋል። ውሻው በጣም ወፍራም ነው። በምቾት እንደሚኖር ተጠለው ይገምታል። በጣም በምችት የምትኖር ትመስላለህ ይለዋል ተኩላው አንገትህ ላይ ያለው ጠባሳ ግን ምንድን ነው ይለዋል ውሸታሙ ጌታ በሚበላው አይደነግጥም። ነገር ግን ቀን ቀን ሲሆን በሰንረለት ስለሚያስረኝ አንገቴ ተልጦ ነው አለው።
ለዚህም የአማራና የሌላውም ኢትዮጵያዊ ጠንቅ የሆነው ስርዓት እንደ ውሻው ስጋታችን ለማድለብ የምትታገሉት የአማራ ተወላጆች ህሊናችሁ እንደ ውሻው አንገት እየተላጠ በፀጉር ከመኖር በመጨረሻም ከሚሸነፈው ስርዓት ጋር አብሮ ለመቀበር የጠራ መስመር ካለው ከተማሩ እና ተናዳፊ ወታደሮች ከሚመራው የአማራ የኢትዮጵያ ተስፋና የአማራ መዳኛ ከሆነው አፋብን ጋር እንደሰሩ ጥሪ እናስተላልፋለን ድልን!!
"በጭቆና ውስጥ ከሚበላ ዳቦ በቅቤ ቀነፃነት የሚቆርጥ ጥሬ"
የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ እንደ ኢትዮጵያ ተወልደን እንደ አማራ ከምድር ገፅ እንድንጠፋ ለተፈረደብን አማራዎች ዛሬ በአንድ ልብ በአንድ ወኔ ይዛችሁ ለአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት አንድዬ ነፍሳችሁን ለመስጠት የዛሬ ተመራቂ የፋኖ አባላት በሙሉ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የምረቃ ቀን አደረሳችሁ። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
የካቲት 23/06/2018 ዓ.ም
ከአርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ለተመራቂ ሰለጣኞች የተላለፍ የእንኳን አደርሳችሁ መልክት!!
የተከበራችሁ የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች፤ የተከበራችሁ የአሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች፣የተከበራችሁ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በስሩ ያላችሁ የክፍለ ጦር አመራሮች እንደ እየ ማረጋችሁ እንዲሁም የአሳምነው ዕዝ የፋኖ አበላት በምርቃት ስነስርዓት ላይ የተገኛችሁ
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ኮማንድ እጩ የሰራዊት አባላት፣ የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክቡራት እና ክቡራን !! በቅድሚያ አድካሚ የሆነውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ ውጣ ውረዶች ተራራ እና ገደሉን ብርዱን እና በርሃውን በማለፍ ለዚህ ለተቀደሰች የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
የቆራጥነትን ጥምቀት ተጠምቃችሁ፣ የጀግንነትን መንገድ መርጣችሁ እዚህ ደርሳችኋል። እንኳን ደስ አላችሁ! እናንተ ዛሬ ተመራቂዎች ብቻ አይደላችሁም፤ የሕዝባችሁ ጋሻ፣ የሀገራችሁ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ።የእናንተን ስልጠና ማጠናቀቅ ብቻ አይደለም፤ የሕዝባችንን ተስፋ መለምለም ነው። ይህንን የጥበብና የጥንካሬ ልብስ ለብሳችሁ ለቆማችሁት ሁሉ፣ በጀግናው ፋኖ ስም ታላቅ ኩራት ይሰማኛል። በድጋሜ እንኳን ለዚህ የድል ቀን አበቃችሁ!"
ይህ መሣሪያ በእጃችሁ የገባው ሕዝብን ለማስፈራራት ሳይሆን የሕዝብን እንባ ለማበስ ነው። ፋኖ ማለት መሣሪያ የታጠቀ ገበሬ፣ መጽሐፉን ያኖረ ተማሪ፣ ወይም መዶሻውን የሰቀለ ሰራተኛ ብቻ አይደለም። ለሕዝቡ ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ 'የሕዝብ አገልጋይ' ነው። ከሕዝባችሁ ጋር ስትሆኑ እናንተ ጠባቂዎች ናችሁ። እናት ስትመለከቱ እናታችሁን፣ አባት ስትመለከቱ አባታችሁን ታያላችሁ። ሕዝብ መጠጊያችሁ ነው፤ እናንተም ለሕዝባችሁ ጥላ የሕዝብ ልጅ፣ የሕዝብ አገልጋይ ማለትም ጭምር ነው።ወደ እናቶቻችሁና አባቶቻችሁ ስትሄዱ በትህትና፣ ወደ ጠላቶቻችሁ ስትሄዱ ደግሞ በጭካኔና በቆራጥነት ይሁን። ወደ ጦር ግንባር ስትሰማሩ፣ የሚሰጣችሁ ግዳጅ ቀላል ላይሆን ይችላል።
ነገር ግን በውስጣችሁ ያለው የዓላማ ጽናት ከማንኛውም ተራራ ይበልጣል። ትዕዛዝን ማክበር፣ ለአጋር አጋርነትን ማሳየትና በወታደራዊ ሳይንስ መመራት የድል ቁልፎች ናቸው። እያንዳንዱ ጥይት፣ እያንዳንዱ እርምጃ ለነፃነትና ለፍትህ መሆን አለበት ወታደራዊ ሳይንስን ከጥንታዊው አባቶቻችሁ ጀግንነት ጋር አዋህዱት። ግዳጅ ሲሰጣችሁ በድል ለመወጣት የሚያስፈልገው መሣሪያ ብቻ ሳይሆን ጽኑ እምነት ነው። ስነ-ስርዓት ያለ ስነ-ስርዓት የሚመራ ኃይል ድልን ሊያገኝ አይችልም። ትዕዛዝን ማክበርና በህብረት መንቀሳቀስ ደግሞ የእናንተ ዋነኛ መመሪያ ሊሆን ይገባል።
ሆኖም ዛሬ የገባችሁት ቃል ከሕዝብ ጋር ነው። ይህ ቃል ደግሞ በታሪክ መዝገብ ላይ ይጻፋል። ዛሬ የነፃነት ቀን ነው፤ ክብርም ነው። በግዳጅ ቀጠና ሔዳችሁ! ሕዝባችሁን የምትታደጉበ ለሀገርና ለወገን የሚከፈል መስዋዕትነት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር የምትከፍሉ የሚሰጣችሁን ተልዕኮ በድል አጠናቃችሁ ለሕዝባችሁ የምስራች ይዛችሁ እንደምትመለሱ አልጠራጠርም።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ!!
ከአርበኛ ኢሳያስ ደመቀ ለተመራቂ ሰልጣኞች የተላለፍ የእንኳን አደርሳችሁ መልክት!!
የተከበራችሁ የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አመራሮች፤ የተከበራችሁ የአሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች፣የተከበራችሁ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በስሩ ያላችሁ የክፍለ ጦር አመራሮች እንደ እየ ማረጋችሁ እንዲሁም የአሳምነው ዕዝ የፋኖ አበላት በምርቃት ስነስርዓት ላይ የተገኛችሁ
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ኮማንድ እጩ የሰራዊት አባላት፣ የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክቡራት እና ክቡራን !! በቅድሚያ አድካሚ የሆነውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ ውጣ ውረዶች ተራራ እና ገደሉን ብርዱን እና በርሃውን በማለፍ ለዚህ ለተቀደሰች የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
የቆራጥነትን ጥምቀት ተጠምቃችሁ፣ የጀግንነትን መንገድ መርጣችሁ እዚህ ደርሳችኋል። እንኳን ደስ አላችሁ! እናንተ ዛሬ ተመራቂዎች ብቻ አይደላችሁም፤ የሕዝባችሁ ጋሻ፣ የሀገራችሁ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁ።የእናንተን ስልጠና ማጠናቀቅ ብቻ አይደለም፤ የሕዝባችንን ተስፋ መለምለም ነው። ይህንን የጥበብና የጥንካሬ ልብስ ለብሳችሁ ለቆማችሁት ሁሉ፣ በጀግናው ፋኖ ስም ታላቅ ኩራት ይሰማኛል። በድጋሜ እንኳን ለዚህ የድል ቀን አበቃችሁ!"
ይህ መሣሪያ በእጃችሁ የገባው ሕዝብን ለማስፈራራት ሳይሆን የሕዝብን እንባ ለማበስ ነው። ፋኖ ማለት መሣሪያ የታጠቀ ገበሬ፣ መጽሐፉን ያኖረ ተማሪ፣ ወይም መዶሻውን የሰቀለ ሰራተኛ ብቻ አይደለም። ለሕዝቡ ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ 'የሕዝብ አገልጋይ' ነው። ከሕዝባችሁ ጋር ስትሆኑ እናንተ ጠባቂዎች ናችሁ። እናት ስትመለከቱ እናታችሁን፣ አባት ስትመለከቱ አባታችሁን ታያላችሁ። ሕዝብ መጠጊያችሁ ነው፤ እናንተም ለሕዝባችሁ ጥላ የሕዝብ ልጅ፣ የሕዝብ አገልጋይ ማለትም ጭምር ነው።ወደ እናቶቻችሁና አባቶቻችሁ ስትሄዱ በትህትና፣ ወደ ጠላቶቻችሁ ስትሄዱ ደግሞ በጭካኔና በቆራጥነት ይሁን። ወደ ጦር ግንባር ስትሰማሩ፣ የሚሰጣችሁ ግዳጅ ቀላል ላይሆን ይችላል።
ነገር ግን በውስጣችሁ ያለው የዓላማ ጽናት ከማንኛውም ተራራ ይበልጣል። ትዕዛዝን ማክበር፣ ለአጋር አጋርነትን ማሳየትና በወታደራዊ ሳይንስ መመራት የድል ቁልፎች ናቸው። እያንዳንዱ ጥይት፣ እያንዳንዱ እርምጃ ለነፃነትና ለፍትህ መሆን አለበት ወታደራዊ ሳይንስን ከጥንታዊው አባቶቻችሁ ጀግንነት ጋር አዋህዱት። ግዳጅ ሲሰጣችሁ በድል ለመወጣት የሚያስፈልገው መሣሪያ ብቻ ሳይሆን ጽኑ እምነት ነው። ስነ-ስርዓት ያለ ስነ-ስርዓት የሚመራ ኃይል ድልን ሊያገኝ አይችልም። ትዕዛዝን ማክበርና በህብረት መንቀሳቀስ ደግሞ የእናንተ ዋነኛ መመሪያ ሊሆን ይገባል።
ሆኖም ዛሬ የገባችሁት ቃል ከሕዝብ ጋር ነው። ይህ ቃል ደግሞ በታሪክ መዝገብ ላይ ይጻፋል። ዛሬ የነፃነት ቀን ነው፤ ክብርም ነው። በግዳጅ ቀጠና ሔዳችሁ! ሕዝባችሁን የምትታደጉበ ለሀገርና ለወገን የሚከፈል መስዋዕትነት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር የምትከፍሉ የሚሰጣችሁን ተልዕኮ በድል አጠናቃችሁ ለሕዝባችሁ የምስራች ይዛችሁ እንደምትመለሱ አልጠራጠርም።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደቡብ አማራ ቀጠና፣ የአሳምነው ዕዝ፣ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር እና የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና አባላት ከአባት አርበኞች ጋር በመሆን በታሪካዊት ከተማ ማጀቴ 130ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በታላቅ ድምቀት አከበሩ።
አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የኢትዮጵያ የነፃነት ማንነት ማህተም "የአማራ ፋኖ የዛሬው ተጋድሎ ልክ እንደ አድዋ የመኖርና የነፃነት ምልክት ነው የአብይ አህመድ አስተዳደር አማራን ለማጥፋት በአራት አቅጣጫዎች ጦርነት በከፈተበት በዚህ ወቅት፣ የፋኖ አባላት የአባቶቻቸውን ፈር ተከትለው እየተዋደቁ ይገኛሉ። የኦሮሙማውን ሥርዓት ለመመከት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ነፍሳቸውን ሳይሳሱ ዛሬም እንደ ትላንቱ ተጋድሎ እያደረጉ መሆናቸው ይገኛሉ። ትላንት በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክና በእቴጌ ጣይቱ መሪነት የተመዘገበው ድል፣ ዛሬም ፋኖ ሀገሩንና ሕዝቡን ከወራሪው የአብይ አህመድ ቡድን ነፃ ለማውጣት ለሚያደርገው ጉዞ ትልቅ ጉልበት ነው።
የኦሮሙማውን ስርዐት ለመመከት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ነፍሳቸውን ሳይሳሱ እየተፋለሙ ትናንት አባቶቻችን በደማቸው ኢትዮጵያን እንዳቆዩ ዛሬም የፋኖ ብረት የአረመኔያዊ አገዛዝ አብይ አህመድ ስርዓት ለመገርሰስና ህዝባችንን ነፃ ለማውጣት እየተዋደቁ ይገኛል። የአባት አርበኞችና የፋኖ አንድነት በዕለቱ የነበረውን ድባብ ልዩ ካደረጉት ኩነቶች መካከል የአባት አርበኞች መገኘት ዋነኛው ነበር።
በመጨረሻም፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ህዝብ እንዲሁም የአባት አርበኞች የኦሮሙማውን ስርዓትና ወራሪን የብልፅግና ጦር በመመከት ህዝቡን ነፃ ለማውጣት ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብቷዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
የካቲት 23/06/2018 ዓ.ም
+2
አሳዛኝ ዜና!!!
የአብይ አህመድ አገዛዝ ንፁሀንን ያነፃፀረ የድሮን ጥቃት በሻሁራ ከተማ ላይ ፈፀመ!!!
ጨፍጫፊውና አውዳሚው ደም መጣጭ ፀረ አማራ የአገዛዙ ሰርአት በእግረኛ ሜካናይዝድ ጦር የአማራን ህዝብ ለእልቂትና ለስቃይ መዳረጉ አልበቃው ብሎ፤ አሁን ላይ በየ ሀገራቱ ተንከራቶና ለምኖ በሚያስገባቸው ድሮኖች ንፁሀንን ያነፃፀረ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።
በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ የድሮን ጥቃትና ቅኝት በተለይ በዚህ አንድ ሳምንት በማያቋርጥ መልኩ በቀንም በማታም የተደጋገመ ሲሆን ህዝባችን ለሽብርና ለሞት እየዳረገ ይገኛል። በዛሬው እለት የካቲት 23/2018 ከጧቱ 1:00 ስአት ገደማ ሻሁራ ከተማ ቀበሌ01 ዉሀ የሚቀዱ ንፁሀን ላይ ያነፃፀረ ጥቃት ተፈፅሟል። በዚህ ጥቃት ወ/ሮ አንጓች የሀለም፣ ወጣት ናንየ ደጉ እና አቶ አለሙ አቢታ ለእልፈተ ሞት ሲዳረጉ ዋወይ የሚባል ንፁሀንም ከባድ ቁስለኛ ሆኗል። እንዲሁም አንድ የንፁሀን ቤት ሊወድም ችሏል።
ተስፋ ቆራጩ የአገዛዙ ስርአት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶት የጀግኖችን የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ክንድ መቋቋም ሲያቅተው እና ከወረዳው ሰራዊቱን በመደምሰስና በመማረክ አቅመቢስ የሆነው፤ አሁን ላይ እንደ አማራጭ ንፁሀን ህዝባችን ላይ ሂሳብ ለማወራረድ የሚሄድበትን እርቀት ምን ያህል በወታደራዊም ሆነ በፓለቲካዊ ዘርፍ የወረደና የተቀዣቀዠ መሆኑ የአራት ኪሎ እድሜው ያበቃ እንደሆነ ያሳያል።
ፈጣሪ የተሰው ንፁሀንን ነብስ ይማር!!! ወዳጅ ዘመዶቻቸውን መፅናናት ይስጥልን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
የካቲት 23/2018
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ለተከታታይ ሶስት ወራት ወታደራዊ ፖለቲካዊ ስልጠና ያሰለጠናቸውን ምልምል የፋኖ ወታደሮች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።
የአብይ አህመድ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመው ያለውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እና የህዝቡን ነፃነት ለማስከበር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር እንደ ንስር ተወርዋሪ የፋኖ አባላትን አስመርቁን ቀጥሏል።
ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ከአዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅርብ ርቀት ላይ የአብይን አየር ወለድ ኮማንድ በገባበት እየገባ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝቡን ሰላም ለማስከበር ከሊቅ እስከ ደቂቅ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል።
ሆኖም በዛሬ ዕለት ከ400 በላይ የሚሆኑ የኮሩ ፋኖ አባላት በስነ ልቦናና በአካል ብቃት የበቁ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን እንደ ንስር ተወርዋሪ ተዋጊዎቹ የሕዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ በብቃት የተዋጣላቸው ሰልጣኞችን አስመርቋል ሆኖም ሰልጣኞች በቀጣይ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ስልጠና አንድ ይለህልውና አደጋ ላይ ያልን እዝብ ነጻ ለማውጣት ብቻ ነው ። ስርዓቱ የሞት ድግስ ደግሶብን ከምድር ገፅ ለማጥፋት እየሰራ ባለበት ስዓት በዱር በገደሉ የህይወት ድልድይ እየገነባን የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በመሆን ሰልጣኞቹ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በሚሰጠን ማንኛውንም ግዳጅ ለመቀበልና በድል ለመወጣት የሀገራችንን ሉዓላዊነት እና የህዝባቸውን ነፃነት በአጥንታቸው ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል።
በዚህ ቅዱስ በሆነው የአማራ ህዝብ የትጥቅ ትግል በስም ዘርዝረን የማንጨረሳቸው ጀግኖች የትግል ጓዶች ከጠላት ጋር ተናንቀው ብዙ ዋጋ የከፈሉበት የህልውና ትግል ነው። በመሆኑም ድርጅታችንን እና መሪዎቻችንን ከትግል ጠላፊዎች እንድትጠብቁ አደራ አለባችሁ ለእናተ አደራ የምንሰጣቹህ መሪዎቻችን በብዙ ስቃይ እና መከራ ውጣ ውረድን በማለፍ ፣ ጀግኖች ውድ ህይወታቸውን የገበሩበት ትግል ተቀብላቹህ የድል ባለቤት እንድታደርጉት አደራ እንላለን ሲል የ አሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ እያሱ መልዕክቱን አስተላልፏል።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት በመላው አማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀውን የአብይ አህመድ የአረመኔዊ ድርጊት በረካታ ግፎች እና ወንጀሎችን እየሰራ የሚገኜው የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አረመኔዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ስለሚጠበቅብን ሁላችንም በዚህ የምረቃ ፕሮግሬም የምትገኝ በሙሉ ራሳችሁን ዝግጁ እንድታደርጉ እያልኩ ለተመራቂ ፋኖዎች መልካም የምረቃ ጊዜ እንመኛለሁ።
እንደራጃለን፣ እንሰለጥናለን፣ እንታጠቃለን፣ የአማራን ህዝብ ከአረመኔው ጡት ቆራጭ አራጅ ሰራዊት ነፃ እናወጣዋለን።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
የካቲት 23/06/2018 ዓ.ም
