uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 039
Підписники
+6824 години
+3957 днів
+1 39230 днів
Архів дописів
በውስጥ መስመር የደረሰንን መርጃ ልናደርሳችሁ ነው። የብልፅግናው አብይ አህመድ እና የሳይበር ታማኞቻቸው (ደጋፊዎቻቸው)፤ የፋኖ አንድነት መጠናከርን ተከትሎ፣ ከቤተ-መንግሥት እስከ ክልል መዋቅሮች ድረስ እርስ በእርስ መተማመን በማጣታቸው የተጠያቂነት 'ዱላ ቅብብሎሽ' ላይ ይገኛሉ።" ​፩. የፋኖ አንድነት እና የመንግሥት ስጋት የፋኖ ኃይሎች በተለይም በአማራ ክልል ያላቸውን ቅንጅት ማጠናከራቸው እና በጋራ መንቀሳቀሳቸው፣ መንግሥት ቀደም ሲል የነበረውን "የመከፋፈል" ስልት እንዳይጠቀም አድርጎታል። ይህ አንድነት በመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። ​፪. የመተማመን መሸርሸር (ከቤተ-መንግሥት እስከ ክልል) የጦርነቱ መራዘም እና የሚፈለገው ወታደራዊ ውጤት አለመገኘት በመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል ጥርጣሬን ፈጥሯል። ​በክልል ደረጃ፡ የክልል አመራሮች "መንግሥት ጥበቃ ሊያደርግልን አልቻለም" በሚል ስጋት ውስጥ ሲገቡ፤ ​በፌዴራል ደረጃ፡ "መረጃዎች ወደ ፋኖ እየፈሰሱ ነው" የሚል ጥርጣሬ በከፍተኛ አመራሮች ዘንድ ተፈጥሯል። ይህ ሁኔታ አንዱ ሌላውን እንደ "ሰላይ" ወይም "ደካማ" እንዲያይ አድርጎታል። ​ ከመከላከያ ​ወታደራዊ አመራሩ ፖለቲከኛውን "ችግሩን በውይይት አልፈታህም" ሲል ይወቅሳል። ​ፖለቲከኛው ደግሞ ወታደሩን "ውጤታማ አይደለህም" ይላል። ​የክልል ባለሥልጣናት ደግሞ "ፌዴራል መንግሥቱ ትኩረት አልሰጠንም" በሚል ጣታቸውን ይቀስራሉ። ​፬. በማኅበራዊ ሚዲያ (ሳይበር) ላይ መንግሥትን የሚደግፉ አካላትም በዚህ ውጥረት ውስጥ ግራ ተጋብተዋል። ቀደም ሲል በአንድ ድምፅ ይሟገቱ የነበሩት አካላት፣ አሁን ላይ የትኛውን የመንግሥት ክንፍ መደገፍ እንዳለባቸው በማጣት እርስ በእርሳቸው መካሰስና መከፋፈል ውስጥ ገብተዋል። ​ባጠቃላይ፣ የፋኖ እንቅስቃሴ መሬት ላይ እያሳየ የመጣው ለውጥ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያለውን ነባር ስንጥቅ አጉልቶታል። ይህም በአብይ አህመድ ባለሥልጣናት መካከል ያለውን መተማመን አጥፍቶ፣ አገራዊ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ አንዱ በሌላው ላይ ጥፋት የማላከክ (ዱላ ቅብብሎሽ) ሥራ ላይ እንዲጠመዱ አድርጓቸዋል።

photo content

​👉 ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ቶሎ  ቀጥታውን ከግንባር መረጃዎችን እንዲደርሳችሁ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

photo content
+6

👉በ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው። ➡️በዛሬው ዕለት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም የደምበጫ ጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ንቅንቄ መድረክ በ
+2
👉በ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው። ➡️በዛሬው ዕለት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም የደምበጫ ጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ንቅንቄ መድረክ በዘለቃ ከተማ አካሄደ:- ========== ደንበጫ የጀግኖች መውጫ የባንዳ መቅጫ ተብሎ የተነገረለት የደንበጫ ወረዳ የዘለቃና አካባቢው ማህበረሰብ በአንድ ላይ በመሆን ከደንበጫ ጊዜያዊ መንግስት ጋር በጋራ ሲመክር ውሏል። የሀይማኖት አባቶች፣ የሀግር ሽማግሎች እና ወጣቶች በፕሮግራሙ ተሳትፈዋል። በውይይቱ የተሳተፉት የማህበረሰብ ክፍሎች የአማራ ፋኖ አንድነትን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከትግሉ ጎን እንደሆኑና ከአሁን በፊት ሲደርጉት ከነበረው በቀለጠ በሙሉ አቅማቸው ትግሉን እንደሚደግፉም ቃል ገብተዋል። በዕለቱ የ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የደንበጫ ወረዳ ጊዜያዊ ዋና አስተዳዳሪ በፕሮግራሙ የተሳተፉ ሲሆን ከተሰብሳቢው የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ በመስጠትና ቀጠናውን የሚያስተዳድሩ አዲስ አመራሮችን በሕዝብ ድምጽ ፍጹም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በማስመረጥ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር  20/2018 ዓ.ም ​👉 ከታች ባለው የቴሌግራም ሊንክ ቶሎ  ቀጥታውን ከግንባር መረጃዎችን እንዲደርሳችሁ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://www.facebook.com/profile.php?id=61586538705973 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

👉በ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው። ➡️በዛሬው ዕለት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም የደምበጫ ጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ንቅንቄ መድረክ በ
+1
👉በ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው። ➡️በዛሬው ዕለት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም የደምበጫ ጊዜያዊ መንግስት የህዝብ ንቅንቄ መድረክ በዘለቃ ከተማ አካሄደ:- ========== ደንበጫ የጀግኖች መውጫ የባንዳ መቅጫ ተብሎ የተነገረለት የደንበጫ ወረዳ የዘለቃና አካባቢው ማህበረሰብ በአንድ ላይ በመሆን ከደንበጫ ጊዜያዊ መንግስት ጋር በጋራ ሲመክር ውሏል። የሀይማኖት አባቶች፣ የሀግር ሽማግሎች እና ወጣቶች በፕሮግራሙ ተሳትፈዋል። በውይይቱ የተሳተፉት የማህበረሰብ ክፍሎች የአማራ ፋኖ አንድነትን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከትግሉ ጎን እንደሆኑና ከአሁን በፊት ሲደርጉት ከነበረው በቀለጠ በሙሉ አቅማቸው ትግሉን እንደሚደግፉም ቃል ገብተዋል። በዕለቱ የ109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የደንበጫ ወረዳ ጊዜያዊ ዋና አስተዳዳሪ በፕሮግራሙ የተሳተፉ ሲሆን ከተሰብሳቢው የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ በመስጠትና ቀጠናውን የሚያስተዳድሩ አዲስ አመራሮችን በሕዝብ ድምጽ ፍጹም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በማስመረጥ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር  20/2018 ዓ.ም

የጥንቃቄ መልዕክት!! ጥር 20/2018 ዓ.ም በአፋብን ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የጊዜያዊ መንግስት የተሰጠ የጥንቃቄ መልዕክት፦ እነሆ በአረመኔው ስርዓት ዘርፈ ብዙ መከራ ታቅዶልናል፣ ሠሞኑን በቢቸና ከተማ የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊና የባንኮች ስራ አስኪያጆች የገጠር የግብርና ባለሙያዎችን ሠብስበው ያስተላለፋት አስገዳጅ መልዕክት ፦ 1- ለኦህዴድ ብልፅግና የሚላላኩት የፖለቲካ አመራሩ የኤቲስቶች/እምነት አልባወች / እና ግብረሰዶማውያንን ተልኮ ያሳኩ ዘንድ ሁሉም ነገር ወደ ዲጅታል ፋይዳ መታወቂያ እያሉ አየዘመሩ ነው።በዚህ ስብሰባ ማጠቃለያም እያንዳንዱ የገጠር ባለሙያ በቀን 5 አርሶ አደሮችን ወደ ከተማ በድብቅ በመላክ ቴሌ ላይ ዲጅታል መታወቂያ እንዲያወጡ የማድረግ ግዴታ አለባችሁ ብሎ አስጠንቅቋል !! ባለሙያወቹ ግን ፋኖ እንዲህ አይነት ተግባር እንድንሰራ አይፈቅድልንም፣የፈቀደልን በየቀበሌዎች ተቀምጠን አርሶ አደሩን በሙያችን እንድናገለግል ብቻ ነው ብለዋል። 2-የ imf ተልኮ ፈፃሚው ባንክም የፋይዳ መታወቂያ ያመጡ አርሶ አደሮች በእርሻ መሬት ካርታቸው የፈለጉትን ገንዘብ ማበደር እችላለሁ በሚል መደለያና የዘመናዊ የባንክ ሲስተም በሚል የማታለያ ቃል በመጠቀም ፎርም አዘጋጅቶ ተባባሪነቱን አሳይቷል።በዚህ ሂደት የንግድ ባንክና የፀደይ ባንክ ቀዳሚውን ድርሻ ወስደዋል። ዳሩ ግን ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ነው ነገሩ፣ፈይዳ መታወቂያ ለማውጣት ናሙና የሚወሰደው ከአፍና ከአይን ሆኖ በአለም አቀፉ አንድ ኮምፒዩተር ሲስተም ይቆጣጠሩን ዘንድ የተዘየደ ሠይጣናዊ መላ ነው።በሌላ አገላለፅ ዘመናዊ ባርነት ሊባል ይችላል። ለጊዜው ፓለቲከኛቹ የቀጣዩን ምርጫ ምናልባት ቢሳካላቸው ኤሌክትሮኒክስ ለማድረግ የተጫኑትን ተልኮ ለመፈፀም እንዲችሉ ነው። ከዚህ የሚቀጥለውም ማይክሮ ችብስ (666 )የተባለው ይቀበርብንና አለም አንድ እምነት፣አንድ ቋንቋ ወደሚባልለት እምነት አልባነት ግሎባላይዜሽን ይጠቀልሉንና ሁሉ ነገራችን የእኛ አይሆንም። አለቀ !! ስለሆነ መላው የአማራ አርሶ አደርና የከተማ ነዋሪ ይህን በመረዳት ሰለባ እንዳትሆኑ እያስገነዘብን፣ በዚህ ተግባር ልትሳተፋ ተልኮ የተሰጣችሁ አካላት ከወዲሁ ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን !! አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ !! ጥር 20/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የ64ኛ ክፍለ ጦር ጊ/መንግስት

ዛሬም በላይ ዘለቀ ዕዝ እና ምኒልክ ዕዝ በጋራ በመሆን ታሪክ ሰርተዋል። በላይ ዘለቀ ዕዝ እና ሚኒልክ ዕዝ በጋራ በመሆን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመዉሰድ ድል ተጎናፀፉ። አማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ፣ ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ፣ ሸደሆ መቄት ሻለቃ እና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር የተዉጣጡ የፋኖ አባላት በብርሃኑ ጁላ ግትልትል ሰራዊት ላይ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዉበታል። መነሻዉን ከታሪካዊቷ ቦታ ላሊበላ ከተማ እና ላሊበላ ኤርፖርት (ሽምሽሃ) አድርጎ እሸት ክፍለ ጦርን አፍናለሁ በሚል አጎል ምኞት አዳሩን በአምስት አቅጣጫ አስፍቶ ቢመጣም በዉባንተ አባተ ልጆች እና በአሳምነዉ ልጆች  ተገርፎ አስክሬኑን እንኳን ሳያነሳ ወደ መጣበት ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ) እና ላሊበላ ከተማ ፈርጥጦ ተመልሷል። ዉጊያዉም ዛሬ ማለትም ቀን 20/2018 ዓ.ም ከለሊቱ 10-8 ሰዓት በፈጀዉ ትንቅንቅም ከ15 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ 20 በላይ ቁስለኛ ማድርግ ተችሏል። በመጨርሻም "አንድነታችን ሃይል ነዉ ካሁን በኃላ አማራ አንድ ድርጅት ፈጥረናል በጎጥ አጥር ሳንካለል ስንፈልግ ሸዋ ፣ ስንፈልግ ጓጃም ፣ጎንደር ፣ወሎ በማንኛዉም ቦታ ተወርዉረን ጠላትን አከርካሪዉን እንሰብረዋለን ሲሉ" የሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ እና የበላይ ዘለቀ ዕዝ ዉባንተ አባተ ኮር አዛዥ አርበኛ አመኑ አለም አንተ በጋራ መልዕክት አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ! ጥር 20/5/2018 ዓ.ም

##አምሃራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ 01ቀበሌ አስት ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና ፋሬታ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን በመንግስት ሃይሎች ቅርሱ ዘረፋ ተፈፅሞበት አድሯል። በአሁኑ ሰአ
##አምሃራ ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ 01ቀበሌ አስት ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን እና ፋሬታ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን በመንግስት ሃይሎች ቅርሱ ዘረፋ ተፈፅሞበት አድሯል። በአሁኑ ሰአት በአካባቢዉ ህዝበ ክርስቲያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል፤የበረታ ተኩስ አለ።ተጨማሪ መረጃ ይዥ እመለሳለሁ!! እስከዛው ሸርና ጆይን በማድርግ አማራዊ ግዲታችን እንወጣ።

ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር ደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በርካታ ጠላት በመደምሰስና በመማረክ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: አማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ጥር 19 ለ 20/2018 ዓ.ም ሌሊት ደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ልዩ ቦታው ቆሎ ባቄላ የሚባል ቦታ ላይ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: ጀግናውና አይበገሬው 24ኛ ክ/ጦር ረጅም ጉዞ በመጓዝ ከሌሊቱ 7:00 ወደ ጠላት ምሽግ ሰርገው በመግባት የጥይት ናዳ አውርደውበታል። ጠላት ጥቃቱ ሲፈፀምበት ጨለማ ስለነበር ግማሹ ገደል ሲገባ ግማሹ ደግሞ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። ልጅ እያሱ ኮር 24ኛ ክፍለ ጦር በተጋድሎው አስር የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት ምርኮኛ ያደረጉ ሲሆን አስራ አምስት ክላሾችንም በመማረክ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ! ጥር 20/2018 ዓ.ም

መረጃ! ከቀኑ 8:00 ሰዓት 2 ኮብራ ሲቪል ባለስልጣን የጫኑ ፥ 2 የመከላከያ ፖትሮል በዲሽቃ ታጅበው ወደ ኩታበር ገብተዋል ‼️ ጥር 20/2018 ዓ/ም
+1
መረጃ! ከቀኑ 8:00 ሰዓት 2 ኮብራ ሲቪል  ባለስልጣን የጫኑ ፥  2 የመከላከያ ፖትሮል በዲሽቃ ታጅበው ወደ ኩታበር  ገብተዋል ‼️ ጥር 20/2018 ዓ/ም

በአሁኑ ሰአት አክቲቭ ከሆኑትና የተተኳሽ እጥረት ተከስቶባቸው አለቆቻቸው እየተንከራተቱ ከሚገኙባቸው 3ት የድሮን ጣቢያዎች መካከል ሁለቱ በቪዲዮ ጎብኝተናል! የኮተቤውንም ላኩልንና እንጎብኝላችሁ!🤔

የብአዴን ስራ አስፈፃሜ የሰሜን ሽዋ የዞን አስተዳዳሪ የሆነው አቶ መካሽ አለማየሁ የተባለው ባንዳ አማራ ክልል በምንጃር ወረዳ "አውራ ጎዳና ቀበሌ ነዋሪዎችን በማስወጣትና ቤቶች በዶዘር እንዲፈርሱ በማድረግ፣ አካባቢው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ስር "ቆርኪ አውራ" ተብሎ እንዲጠራ በማድረግ የአማራን መሬት ለኦሮሞ አሳልፎ አንድ ቀበሌን ሙሉ በሙሉ የሸጠ የሽዋ ታሪካዊ ጠላታችን ነው። ​ ​በሰሜን ሸዋ (አጣዬ፣ ኤፍራታ፣ ማጀቴ እና ቀወት) በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋሚያ ከውጭ መንግስታት ወይም ከአለም ባንክ የተገኘ 1 ቢሊዮን ብር ለ22 ፕሮጀክቶች እንዲውል ተመድቦ ነበር። ​ይሁን እንጂ ግለሰቡ ያለምንም ጨረታ ፕሮጀክቶቹን ለኮንትራክተሮች በመስጠት፣ ከእያንዳንዱ ኮንትራክተር 10% (1,100,000 ብር) ኮሚሽን በመቀበል በዘረፋ ስራ ከተሰማሩት ሰዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ሰው ነው። ኤፍራት ላይ ያለውን የአለም ባንክ ፕሮጀክት አብረው እየዘረፉ ያሉ የወረዳ አመራሮች : 1, አቶ አበራ መኮንን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ 2,አቶ ነጋሽ ጋሻውበዛ የውረዳው ምክትል አስተዳዳሪ 3,አቶ ችሮታው ባሳዝን የወረዳው አልም ባንክ አስተባባሪ ነው አቶ መካሻ ​በዚህ ዘረፋ ባገኘው ገንዘብ በአዲስ አበባ መገናኛ ሲምሲ አካባቢ ፎቆችን በመግዛት ። በዚህ ድርጊትም "ችሮታው ባሳዝን" የተባሉ የዓለም ባንክ የአጣዬ ተወካይ ተባባሪ ጋር በመሆን አሁን ቀሪ 1,000.000 ብር ከአለም ባንክ ለመዝርፍ ኮንትራክተር አየመረጠ ይገኛል። በቡልጋ፣ አንጎለላ እና ጣራ አካባቢዎች ከሪል እስቴት እንቅስቃሴዎች 200 ሚሊዮን ብር በመቀበል፣ በራሱና በቤተሰቦቹ ስም በርካታ ሲኖ ትራኮችንና ኤክስካቫተሮችን ገዝቷል። ​በወጣቶች ላይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፦ግለሰቡ በሸዋ፣ በመንዝ፣ በይፋትና በመርሃቤቴ ወጣቶች ላይ ያነጣጠረ እስራትና እንግልት እንደሚፈጽም ተገልጿል። ለምሳሌ፦ ​በአጣዬ ከተማ እንዳትቃጠል ሲፋለም እና ሲታገል የነበተውን ከሽኔ ጋር በነበረ ወጊያ አንድያ ሂወቱ የሰጠው የአርበኛ አሳልፍ ሻረው የመጀመሪያ ልጅ ወጣት መሳፍንት አስልፍን እና 5 ጓደኞቹ በግፍ አስረሽኗል። ​በኤፍራታ ካራ ለጎማ አቶ ግርማ እንደዚሁ የት እንዳደረሰው አይታወቅም። ​በደብረ ብርሃን የሚሊኒየም ትምህርት ቤት መምህር አስገድሏል።በሸዋሮቢት ከ30 በላይ ወጣቶች፣​በመርሃቤቴ ከ10 በላይ ወጣቶች፣ ያለምንም ፍርድ በአሱ ቀጥተኛ ትዛዝ በአረመኒው አብይ አህመድ ጡት ቆራጩ መካላከያና የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻ እንዲገደሉ አድርጓል ። ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የዘረፈ ሲሆን፣ ይህንንም ሀብቱን በሱ ፍቃድ ሪል እስቴት ከሆነ ሸር ካምፓኔ ፣ በባለቤቱ፣ በልጁና "በሞጃ" ባለሀብቶች በኩል ያስተዳድራል። በዘመድ አዝማድ እያደረገ በቁጥር 9 የነዳጅ ማድያወች በተለያዩ ከተሞች ከፍቷል ። በተጨማሪም የይፋት፣ የመንዝ እና የመርሃቤቴ ተወላጆችን "ፅንፈኛ" ናቸው በማለት ከስልጣን እንዲወገዱና በዞን ደረጃ ስራ እንዳያገኙ ስራ ላይ የጎጥ ስራ እየሰራ ያለ አረመኔያዊ የብልፅግና ገርድ የብርሃኑ ተላላኪ ብቹላ ነው። ​በቀጣይ በፎቶ እና በማስረጃ የተደገፉ ፎቶወችን ይዘን እንመጣለን

photo content
+3

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ 206 ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የጐዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ከደንባ ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ የቀበሌ አመራሮችን ሹሟል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅ
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ 206 ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የጐዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ከደንባ ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ የቀበሌ አመራሮችን ሹሟል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ 206 ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የጐዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በትናንትናው ዕለት ከደንባ ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር በአማራ ፋኖ ትግል የእድገት ደረጃዎች ዙሪያና መሪ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አፋብን እየተጓዘ ያለበትን ሂደት ገለጻ ሰጥተዋል። ስብሰባውን የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች የመሩት ሲሆን በተጀመረው የመልሶ ማደረጀት መርሕ መሰረት ለቀበሌው አመራሮችን መርጦ አጽድቋል። መረጃው የጎዛምን ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ሚዲያና ግንኙነት ክፍል ነው። ጥር 20/2018 ዓ.ም ድል ለአማራ ፋኖ! የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት መቶ አለቃን ጨምሮ ሌሎች ወታደሮች ተደመሰሱ!! ከጥር 18ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ጠላት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሰበሰበውን ኃይል ወደ ምዕራብ ወሎ ሲያንቀሳቅስ በንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰራዊት ጥቃት እየተሰነዘረበት ይገኛል። በዚህም መሰረት ከትናንት በስቲያ ማለትም ጥር 1ቀን 2018 ዓ/ም በለጩማ ላይ ታሪክ ተሰርቷል። በበርካታ ተሽከርካሪዎች ጭኖ ወታደሮችን ወደ ምዕራብ ወሎ እያጓጓዘ ያለው ፋሽስታዊው መንግሥት በለጩማ ሲደርስ ያልታሰበ አደጋ ገጥሞታል። የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት የምዕራብ ወሎ ቀጠና ሰሞኑን ብዛት ያለው የጠላት ኃይል ከከባድ መሳሪያ ጋር እየተጋጓዘ እንደሆነ ይታወቃል። በቀጠናው የነበረው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር ሰራዊት ድጋፍ የፋኖን ጫና መቋቋም ስላልቻለ በቅርቡ የተመሰረተው 11ኛ ዕዝ ሰራዊት በድጋፍ ሰጭነት ወደ ቀጠናው ሲገባ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ ፋኖዎች በሰነዘሩበት የደፈጣ ጥቃት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። ከደሴ ተነስቶ በስተ ምዕራብ በኩል ሲጓጓዝ ከነበረው በርካታ ኃይል መካከል ወደ አማራ ሳይንት ሊገባ በ6 ኦራል እና በ4 ፓትሮል ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ የጠላት ኃይል ላይ እነ ሞት አይፈሬ በሰነዘሩት ጥቃት የደረሰው ጉዳት የሚከተለውን ይመስላል:- የተደመሰሰ 5 የመከላከያ መስመራዊ ወታደሮች እና 1 መቶ አለቃ እንድሁም 3 አድማ ብተና፤ በድምር 9 የጠላት ኃይል እስከወድያኛው ሲሸኝ 7 መከላከያ እና 9 አድማ ብተና በድምሩ 16 ጠላት ቁስለኛ ተደርጓል። የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ደምመላሾች በብርሀን ፍጥነት በድምሩ 25 የጠላት ኃይልን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል። ©የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!

photo content

ጥር ሃያ (20) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ሦስት (1913) ዓመተምህረት‼️ #ዝክረ_ታሪክ ከአንድ መቶ አምስት (105) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ታሪክን የኋሊት!! ከዛሬ አንድ መቶ አምስት (104) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት ሌፍተናት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ (የበጋው መብረቅ) የተወለዱበት ዕለት ነበር። ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ ወይም በፈረስ ስማቸው አባ ዳማ ጥር ሃያ (20) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ሦስት (1913) ዓመተምህረት በጅባትና ሜጫ አውራጃ በደንቢ ዮብዲ ወረዳ ዮብዶ በሚባል ቦታ ተወለዱ። ጃገማ የሚለው የኦሮምኛ ቃል ሲሆን በአማርኛ ሀይለኛ ማለት ነው።  ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ በአንድ ወቅት ስለ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ምን እንደሚያስቡ  ተጠይቀው ከባለቅኔው ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ስንኝ ተውሰው እንዲህ ብለው ነበር  «አገሬ ኢትዮጵያ ውዲቱ ውዲቱ፣ በሶስቱ ቀለማት የተሸለምሽቱ፣ ላንቺ የማይረዳ ካለ በህይወቱ፣ በረከትሽን ይንሳው እስከ እለተ ሞቱ።» በማለት የባለቅኔውን ስንኝ  ሰድረው ነበር። በሽምቅ (ጎሬላ) ውጊያ የተካኑት ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ በጦር ሜዳ ውሏቸው በፋሺስቱ የጣሊያን ወራሪ ጦር ላይ ካገኙት አንፀባራቂ ድል አንዱ በወረሃ ህዳር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ ሦስት (1933) ዓመተምህረት የተገኘው ነው፡፡ ይህም የአዲስ ዓለምን ጽዮን ማርያም ምሽግ በመሰበር ሰባ (70) የጣሊያንን ወታደሮች በመግደል አንድ ሺህ አምስት መቶ (1500) ጠመንጃ በመማረክ እንዲሁም ሰማኒያ (80) የወገን እስረኞችን በማስፈታት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ ሌፍተናት ጀነራል ጃገማ ኬሎ ለአገራቸው ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ከንጉሥ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ አገሮች ኒሻንና ሜዳዮችን ተሸልመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የአንገት ኒሻን የቅዱስ ጊዮርጊስ የጦር ሜዳ ጀግና ሜዳይ ባለ ሁለት ዘንባባ የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን ከእናት አገራቸው ኢትዮጵያ ተጠቃሽ ሲሆኑ ከሀገር ውጭ ደግሞ ከእንግሊዝ ከዩጎዝላቪያ እና ከላይቤሪያ የተለያዩ ኒሻኖችን አግኝተዋል።  ሌፍትናንት ጀነራል ጃካማ ኬሎ መጋቢት ሃያ ዘጠኝ (29) ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ (2009) ዓመተምህረት በአዲስ አበባ ከተማ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በዘጠና ስድስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። #የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️ #ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️ 20/ዐ5/2018 ዓ.ም

photo content

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የ2 ወር የግዳጅ አፈጻጸሞችን ገመገመ:- ============================== ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በ3 ግዙፍ ክ/ጦሮች የተዋቀረ ሲሆን መልሶ ማደራጀቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅና በስሩ የሚገኙ ክ/ጦሮችን በመገምገም እና ለአመራሩ አጭር ስልጠና በመስጠት ማጠናቀቁ ይታወቃል። ኮሩ በመልሶ ማደራጀቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ጠንካራ ጎኖች በማንሳት ለ2 ቀናት ጥልቅ ግምገማ ያደረገ ሲሆን የወደፊት የትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል። ስለሆነም የውስጥና የውጭውን የጠላትን ከፍተኛ ጫና በመቋቋም የ109ኛ ኮር መልሶ ማደራጀት በተሳካ ሁኔታ እውን እንዲሆን ተግታችሁ ለሰራችሁ ለቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለ109ኛ ኮር አመራሮች፣ ለ88ኛ፣ ለ99ኛ እና ለ77ኛ ክፍለጦር አመራሮች፣ በሁሉም ክ/ጦሮች ስር ተጠርንፋችሁ እየታገላችሁ ላላችሁ አባሎች፣ ለቴዎድሮስ ዕዝ ኮማንዶ ዩኒት እንዲሁም ለአካባቢው ማሕብረሰብ የ109ኛ ኮር ስራ አመራር ከፍተኛ አክብሮት እና ላቀ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል። አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 20/2018 ዓ.ም