uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 413
Підписники
+2224 години
+437 днів
+1 38430 днів
Архів дописів
ሌባ እየተለቀመ ነው ??? ጎንደር የጎንደር የአንድነት አደረጃጀት ሊበሰር 99.9% የደረሰ ሲሆን በሁለቱ አደረጃጀት ያሉ የፋኖ ሀይሎች በጋራ እያደረጉት ካለው አስደናቂ ታሪካዊ ጀብድ በተጨማሪ ዛሬ
ሌባ እየተለቀመ ነው  ???  ጎንደር የጎንደር የአንድነት  አደረጃጀት ሊበሰር  99.9% የደረሰ ሲሆን በሁለቱ አደረጃጀት ያሉ የፋኖ ሀይሎች በጋራ እያደረጉት ካለው አስደናቂ  ታሪካዊ ጀብድ በተጨማሪ ዛሬ በ23/02/2018 ዓ.ም እንዲህ ሆነ....?? ከማክሰኝት  ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ አንዲት የገጠር ጫካማ ሰፈር  በተደጋጋሚ ፋኖን መስለው የሚዘርፉባት አካባቢ ነች በዛሬው ዕለት አንድ በመካዝንና በብረታ ብረት ስራ ላይ  የተሰማራ መሀመድ/ሙሔ  የተባለ ወጣት  ከከተማው ዕቃ ጭኖ ወደ ባህር ዳር በሚወጣበት ጊዜ እኝህ ሌቦች ከከተማ በደረሳቸው የሌባ ለሌባ ጥቆማ ይህን ሰውየ ፍየል ውሀ ተብላ ከምትባለው ከተለመደችው ቦታ በመጠበቅ ግለሰቡን አስቁመው አፍነው ወደ ራቅ ወዳለ ጫካ ይወስዱታል... ይህን ክስተት የሰሙት በ4 ኪ.ሜ ርቀት የነበሩት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የኢትዮጵያ ትንሳኤ አብሳሪ  የሆኑት  የፋኖ ሀይሎች አካባቢውን ሰፊ እና አጭር ከበባ በማድረግ በአስደናቂ ጥበባዊ ኦፕሬሽን ግለሰቡን በ40 ደቂቃ ውስጥ ሁለቱን በመደምሰስ ከባንዳዎችና ሌቦች እጅ ያለምንም ጉዳት ፈልቅቀው አውጥተውታል ። ግለሰቡ በእንባና በለቅሶ ተንበርክኮ የፋኖ ሀይሎችን አመስግኖ ወደ ማክሰኝት ከተማ በመመለስ ቤተሰቡን ተቀላቅሏል  ።          ጎንደር    ጥቅምት 23/02/2018 ዓ.ም

ባለሽርጡ ክፍለጦር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ፣የምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ቀበሌ 032 ልዩ ቦታው ኮለቦና ጃሮታ በተባሉ ቦታዎች  በሶስት አቅጣጫ የመጣውን የአብይ አህመድ ወራሪና ጨፍጫፊ ሰራዊት  ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎናፀፈ። በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣው የአብይ አህመድ  ጭራቅ ሰራዊት በሀብሩ  ወረዳ   ከቢስቲማ ወደ ኮለቦ፣ከጊራና ወደ ፋጂ እንድሁም ከጣጣይቲ ወደ ሀብሩ በሶስት ጀኔራል ሲያመራመድፍና በአንድ ዙ_23  ታጂቦ የባለሽርጡ ክፍለጦርን ለማጥቃትና የክፍለጦሩን ነበር ይዞታዎች ወረራ ለማድረግ የመጣውን የስርዐቱን ዘረ_ፈጂ ሰራዊት በመደምሰስ ፣በማቁሰል እንዲሁም በመበታተን ፣የጠላት ሀይል አስቦት የመጣውን የጥፋት ዕቅድ ቅዠት በማድረግና በስርዐቱ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ስብዐዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ። ዛሬ ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም ከበረንዳ፣ከቀን ስራተኛ፣ከፑል ቤት እና ጎዳናዎች በግዳጅ እየሰበሰበ የ15 ቀን ለብለብ ስልጠና በመስጠት ፣መለዮ አልብሶ፣ያለምንም ወታደራዊ እውቀት ፣አማራ ጠልነትን አላብሶ ፣አማራን በዘፈቀደ ከባድ መሳሪያ እየተኮሱና ያገኙትንም እየገደሉ፣ንብረቱን እየዘረፉና እያቃጠሉ እንድሁም ሴቶች እንድደፍር ተልኮ ተሰጥቶት በማዕበል የመጣውን የስርዐቱን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ቁጥሩን ለማወቅ በሚታክት ሁኔታ ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። ከንጋቱ  12:00 እስከ ቀኑ 11:30! ድረስ በቆየው አውደ ውጊያና አሁን እንደቀጠለ ባለው ትንቅንቅ   የጥላትን  ቅጥረኛ ሰራዊት በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የአብይ አህመድ  ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረት እንዲደርስበት ማድረግ ተችሏል። በዚህ አውደ ውጊያ ከፍተኛ የሆነ የጠላት ሀይልን ሙትና ቁስለኛ በመደረጉ ስርዐቱ በበርካታ አንቡላንሶችና ኦራል  ቁስለኛውን ወደ መርሳና ወልዲያ ሆስፒታል ሲያጓጉዝ ውሏል።በዚህ የተበሳጫው የስርዐቱ ወታደር ጊራና ከተማ ባስቀመጣቸው ሶስት ጀኔራል መድፎች የዘወትር ልማዱ በሆነው የዘፈቀደ  ተኩስ በርካታ  የንፁሀን ቤቶችን እያቃጠለና የንፁሀንን ህይወት ሲቀጥፍ ውሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ መሀመድ ሞገስ ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! ጥቅምት 23/2081 ዓ/ም

ምኒልክ ዕዝ የሰልጣኞች የምርቃት ስነ-ስርዓት በዛሬው እለት አካሄደ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለጦር በርካታ የፋኖ ሰራዊት  በዛሬው ዕለት በደማቅ ሆኔታ አስመረቀዋል።  በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ተመራቂ ፋኖዎች በርካታ ወራት ቆላ ደጋ ወተው፤ሸለቆ ዳገት ወርደው ወተው የገነቡትን ተክለ ቁመና እና ያገኙትን የአካል ብቃት ወታደራዊ ልምድ በትርዒት አሳንተዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሰልጣኞች የወደፊት የሀላፊነት ቃለማህላ ስነ ስርዓትም ተፈፅሟል። ተመራቂዎቹ በበኩላቸው በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አዳጋ ሰልጥነው በተመረቁበት ሙያ በድል ለመወጣት ቃል ገብተዋል። የቀድሞው የልዩ ሀይል አሰልጣኝ የነበረው ምትኩ  አረጋ ለበርካታ ወራቶች ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በዛሬው እለት አብቅቶ ለምርቃት አድርሷል። ሰልጥነን እንዋጋለን እየሰለጠንን እንዋጋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለጦር! ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እንደቀጠሉ ነዉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮሩ  ነፃ ባወጣቸው በሰሜን  ወሎ ዞን  ላስታ  ወረዳ ከሚገኙ  ቀበሌዎች  መካከል ከገለሶት ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር  ህዝባዊ ውይይቶች ተደርጓል። ዛሬ በዕለተ እሁድ  በቀን 23/02/2018 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን በላስታ  ወረዳ ገለሶት ቀበሌ  ነዋሪ ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡ በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦችም 1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?   * ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ   * ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ   * የትግሉ ተግዳሮቶች    * የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ  *የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት አካባቢያቸውን ከፋሽቱና ወራሪው የአብይ አህመድ ሰራዊት እንድጠብቁ ግንዛቤ ተስጥቷል። 2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ   * በወታደራዊ ቁመና   * በፖለቲካ ተቀባይነት   * የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም 3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ   * የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት   * የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት   4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?  በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተሞክሯል፡፡ በነዚህ አንኳር ጉዳዮች ላይም የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ የፅህፈት ቤት ኋላፊ አርበኛ ደስታዉ መለስ እና የእዚሁ ዕዝ ም/ ህዝብ አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት መ/ር ፍቅሩ ፈንታዉ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በትላንትናዉ ዕለትም ከድብኮ ቀበሌ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት መደረጉ ይታወቃል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ጋዜጠኛ ደረበ መኮንን ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም

የአማራ ህዝብ በኖረባቸው የመከራ ዘመኖች ሁሉ የገጠመውን የተቋማት ምክነት ማስቆም ይገባል። ባለፉት አመታት አማራ እንደ ህዝብ ያስተናገደቸው ሰቆቃዎች ሁሉ የደረሱበት ተቋማዊ በሆነ መንገድ ችግሮቹን እንዳይከላከል በመደረጉ ነው። ስርዓታዊ በሆነ መንገድ የደረሱ ግፎችን ለመከላከል የሞከሩ ግለሰቦችና ቡድኖችም ገዥዎች በሚከተሏቸው ሶስት ወጥመዶች እየገቡ ከስመዋል።  የመጀመሪያው በግላቸውም ይሁን በቡድን ውስጥ ሆነው የሚታገሉ ግለሰቦችን በማታለል ወደገዥው መዋቅር መውሰድና ለአማራ ህዝብ ያላቸውን ወገንተኝነት ማስቀየር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ  ጉልበቱን ተጠቅሞ ታጋዩን ከነቤተሰቡ ማሰቃየትና ተስፋ ቆርጦ ከትግሉ እንዲወጣ የማድረግ ስልት ነው። ከሁለቱ አማራጮች ውጪ ሆነው ስለአማራ ህዝብ መገፋት የተቆረቅሩ ደግሞ በተለያዩ ስልቶች እንዲገደሉ ተደርጓል። በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የአማራ ህዝብ በፖለቲካው ዘርፍ እንደ ቡድን  ብአዴን፣ አብን፣ አዲሀን፣ መአህድና  ሌሎችም አንድም ከስመዋል ወይም በጠላትነት ቆመዋል። እንደግለሰብ ከቀድሞዎቹ  እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ተገድለዋል፤ ከአሁኖቹ እነክርስቲያን ታደለ፣ ሲሳይ አውግቼው፣ መስከረም አበራና ሌሎችም ታስረዋል። እነ በለጠ ሞላ፣ ተስፋሁን አለምነህ፣ ጣሂር መሐመድና ጋሻው መርሻ ደግሞ ክደዋል።  ከወታደራዊ ተቋማቱ  እንደቡድን የአማራ ልዩ ሀይል እንዲፈርስና እንዲበተን ተደርጓል። እንደ ግለሰብ እነጀኔራል አሳምነው ፅጌ፣ አስማረ ዳኜ፣ ጎቤ መልኬ፣ አስቻለው ደሴና ሌሎችም በግፍ ተገድለዋል።  በሰብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በአማራ ህዝብ ስም የተቋቋሙ የሀገር ውስጥና የውጪ  ድርጅቶችም  ከስመዋል፣ አላማቸውን ስተዋል  ወይም ተጠልፈዋል። አሁንም የቀረውን ብቸኛ ተቋም ፋኖን ለማፍረስ በሁሉም አቅጣጫ የተሰለፉ ጠላቶች እየተረባረቡ ነው። የአማራ ህዝብ የገጠመውን የተቋም ምክነት በማስቆም ፋኖን መታደግ የመጨረሻ ምርጫ ነው። በፋኖ ትግል ውስጥ የአማራ ህዝብ ያጣቸውን ሌሎች አደረጃጀቶችን ማግኘት እንደሚችል ይነገራል።  ፋኖ ጠንካራ ተቋም ሆኖ ከቀጠለ እንደህዝብ ያጣውን ዋነኛ ወታደራዊ ተቋም ማግኘት ያስችለዋል። በመዋቅሩ ውስጥ የሰለጠነ፣ የታጠቀ፣ የውጊያ አቅምና ወታደራዊ ዲስፕሊን ያለው የአማራ ወጣት እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም የውስጥ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ ማንም እየዘለለ የሚገባበትን ክልልና ህዝብ ለመጠበቅ፣ ውጤታማ ዲፕሎማሲ ለመስራት ያግዛል።  ወታደራዊ እድሉ የሚፈጥረው ጉልበት ደግሞ ታማኝነትና ተሰሚነት ያለው ፖለቲካዊ አደረጃጀት እንደሚፈጥር ይነገራል።  ስለሰብአዊነት የሚገዳቸው፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ  ሲቪክ ማህበራትን ለመፍጠር ፋኖን እንደተቋም ማስቀጠል ይገባል። በእያንዳንዱ የትግል ምዕራፍ ውስጥ የአማራ ህዝብን መከራ ማሰብ ለመዋቅሩ መጠንከር ከፍ ያለ ሚና አለው። ትግሉ የመነጨው ህዝቡ ላይ ከደረሱ ግፎች በመሆኑ በሂደቱም በውጤቱም ይህንን ማሰብ ይገባል።  ፋኖን እንደግዙፍ ተቋም ለማስቀጠል መጀመሪያ እንደትናንቱ ሁሉ በአገዛዙ ሰርገው ገብተው እንዲያፈርሱ ተልዕኮ የተሰጣቸውን ሆዳሞች ማስወገድ ይገባል። ሲቀጥልም ከትልቁ አላማ ወጥተው በጊዜያዊ ስልጣንና ጥቅማ ጥቅም የሚደለሉ ቅርብ አሳቢዎችን  የማስወገድ ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። እነዚህ ጉዳዮች ከብልፅግናው አገዛዝ ጋር ከሚደረገው የፊት ለፊት ትንቅንቅ ጋር እኩል መጓዝ አለባቸው። በተለይም የፋኖን የበታች መዋቅር የበለጠ ማደራጀትና መሪነትን ማለማመድ ይገባል። መዋቅሩ በግለሰቦች መምጣትና መሄድ የማይወሰን ህዝባዊ መሰረት የያዘ  እንዲሆንም ስራ ይጠይቃል።  የአማራ ህዝብ የተቋም ግንባታ ሂደት ውስጥ አሁናዊ ትግሉን እንደመታጠፊያ ተጠቅሞ  መስራት ያስፈልጋል።  የደረሱበት መከራዎች የሚጠገኑትና ቁስሎቶቹ የሚደርቁት ብቻ ሳይሆን ህልውናውም የሚቀጥለው ፋኖን እንደተቋም በማጠንከርና ትግሉን ከባለደሞች በመጠበቅ ነው።

ሰበር ዜና! የአገዛዙ ብልፅግና አመራሮች ዛሬም ስልጣናቸውን ጥለው  መኮብለላቸውን ቀጥለዋል። በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ካሉ ወረዳዎች መካከል አንዷ በሆነችው  ጎንደር ዙሪያ ወረዳ  የብልፅግና አመራር ሁነው በተለያዬ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የነበሩ 3 አመራሮች  ከዚህ በላይ ህዝባችን አንበድልም፣ አንጨፈጭፍም ፣ አናዘርፍም  በማለት ስልጣናቸውን ጥለው ጠፍተዋል ።    የጠፋ  አመራሮች እና ሀላፊነታቸውን ስንመለከት  ደግሞ። 1 :- አቶ ጌታሁን አማረ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊ 2:-አቶ ምትኩ  ተስፋ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገጠር መንገድ እና ትራንስፖርት  ጽ/ቤት ሀላፊ 3:- አቶ ፍቃዴ  ገበየሁ  የስራና  ስልጠና  ጽ/ቤት ሀላፊ   ናቸው።   በጠፋት አመራሮች ድንጋጤ ውስጥ የገባው የብልፅግና ስርዓት አዳዲስ ሆድ አደሮችንና የኦህዴድ አሸከሮችን በማፈላለግ ለመሾም ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አና ሌሎች አመራሮችም እንዳይጠፋ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው  እንደሆነ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስባቸው  ቀጠናዎች  ስልጣን ለቀው ከህዝባቸው ጎን ለሚሰለፋ አመራሮችና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋና በማቅረብ ለደህንነታቸውም  ከለላና ጥበቃ የሚያደርግ  ሲሆን ሌሎች በስልጣን ላይ ያሉ የብልፅግና  አመራሮች ከብልፅግና አሽከርና ሎሌነት ወጥተው  ታሪካዊ የአማራን ህዝብ  የህልውና ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ጥቅምት 23/2018 ዓም

መረጃ(ለፋኖዎቻችን የሚደርስ) ዛሬ 23/02/2018 ዓ.ም በዚህ ሰዓት የዓብይ ወንበርጠባቂ ከደ/ማርቆስ ወደ ሮብ ገባያ ስለተንቀሳቀሰ አቀባበል ይደረግለት

ይድረስ ለኦሮሞ ሕዝብ! Humni cubbuu mormee kaa'e cubbu hin dalagu. Nuti kan baanee gumaaf miti. Qabsoo Faannoon taasisaa jiru kan Guumaa osoo hin taane Qabsoo mirga ummattaa mirkaanessuu dha. Nuyii warri Faannoo qabsoo kan jalqabne Ummanni Amaaraa cunqurfamee taa'us cubbuun fi roorroon Ummattotaa Itiyoopia biroorratti dalagamuus cimsinee balaaleffannaa. Dhugaa dubbachuuf maqaa ummataa oromoon Angoo qabatani ummaataa Amaaraa irratti cubbuu kan dalagan Angaa'onni oromoo baay'een jiru. Kan Angoofi sirna qabatee Kan bitaa jiru paartii badhaadhinaa dha. Haa ta'u malee Loolli keenyaa sirna angoo qabate jiru wajjin malee Ummata oromoo walin miti. Ummataa Oromoo dabalatee ummanni Itiyoopiaa hundi Obbolessa keenyadha. Anga'a Olaanaa Faannoon Amaaraa wallo obbo Raddaa wubatuu Gaaffifi deebbii midiyaa marab wajjin taasisan irraa kan fudhatame. ትርጉም፦(ከአፋን ኦሮሞ ወደ አማርኛ ቋንቋ) ግፍን ተቃውሞ የተነሳ ኃይል ግፍ አይፈፅምም። እኛ የወጣነው ለበቀል አይደለም። ፋኖ እያደረገ ያለው ትግል የበቀል ሳይሆን ፍትሕ የማስፈን ትግል ነው። እኛ ፋኖዎች ትግል የጀመርነው የአማራ ሕዝብ ተበደለ ብለን ቢሆንም በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀም ግፍና መከራንም አጥብቀን እንቃወማለን። በርግጥ በኦሮሞ ሕዝብ ስም ስልጣን ይዘው በአማራ ሕዝብ ላይ በደል የሚፈፅሙ ብዙ ባለስልጣናት አሉ። እንደውም ገዢው ስርዓትን የተቆጣጠረው የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ነው። ሆኖም ግን ግጭታችን ከአገዛዙ ጋር እንጂ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አይደለም። የኦሮሞ ህዝብን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን ናቸው። 👉በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አርበኛ ረዳ ውበቱ እና አርበኛ ተሾመ ፈንታየ በአንድ ወቅት ከመረብ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቃለመጠይቅ ከተናገሩት የተወሰደ። Mereb media

ዛሬም ህዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል። ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ፩ኛ ክ/ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ በባህርዳር ዙሪያ ፈረስወጋ ቀበሌ ስኬታማ እና ችግር ፈች የሆኑ ህዝባዊ ውይይቶ
+2
ዛሬም ህዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል። ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ፩ኛ ክ/ጦር  የጣናው መብረቅ ብርጌድ በባህርዳር ዙሪያ ፈረስወጋ ቀበሌ ስኬታማ እና ችግር ፈች የሆኑ ህዝባዊ ውይይቶችን ከሰፊው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በወቅታዊ ጉዳዮችና በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ መጠነ ሰፊ ውይይቶችን ማካሄድ ተችሏል። ከመቸውንም ጊዜ በላይ አንድ የምንሆንበት ጊዜ ወቅት ላይ መሆናችን በማሳገንዘብ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣት በአንድነትም መቆም አለብን በማለት አጋርነታቸውን ማረጋገገጥ ተችሏል።     ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዥ 1ኛ ክ/ጦር  ህዝብ ግንኙነት።                   ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም

በድሬ ዳዋ እና ሀረር የምትኖሩ አማራዎች ቀጣይ በግልጽ የታቀደ ጭፍጨፋ እንዲደረግ እና ከኦሮሞ ዉጭ ያለ ህዝብን ሀብት ንብረት ዝረፉ የሚል ትዕዛዝ ለቄሮወች እንደተሰጣቸዉ ቢዛሞ ሚዲያ ከዉስጥ አዋቂወ
በድሬ ዳዋ እና ሀረር የምትኖሩ አማራዎች ቀጣይ በግልጽ የታቀደ ጭፍጨፋ እንዲደረግ እና ከኦሮሞ ዉጭ ያለ ህዝብን ሀብት ንብረት ዝረፉ የሚል ትዕዛዝ ለቄሮወች እንደተሰጣቸዉ ቢዛሞ ሚዲያ ከዉስጥ አዋቂወች ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል ። በጫት የደነዘዘ የሀረርጌ ቄሮን ለማንሳሳትም  ኢትዮጵያ ከባህር በር ከተለየች 30 ዓመት ሆናት ሀረር እና ድሬ ድዋም ከሀረርጌ  ከተለዩ 30 ዓመት አስቆጠሩ ለኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ሁሉ ለሀረርጌም  ድሬ ዳዋ እና ሀረር ያስፈልጓታል የሚል በራሪ ወረቀት እየተሰጣቸዉ ይገኛል። ነገደ አማራዊያን  አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ቢዛሞ ሚዲያ ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ጥቅምት 23 /2018 ዓ/ም ቢዛሞ ሚዲያ

አማራ ወደ ቤቱ /ፋኖነት /እየተሰባሰበ ነው ። በዳንግላ ከተማ ከሆድ አደሩ የአማራ ብልፅግና ጋር ተሰልፈው የነበሩ አባላት ወደ ፋኖ እየተቀበሉ ነው ። ከህዝባችን ጋር አንዋጋም በማለት የህዝብ ልጅ
+2
አማራ ወደ ቤቱ /ፋኖነት /እየተሰባሰበ ነው ። በዳንግላ ከተማ ከሆድ አደሩ  የአማራ ብልፅግና ጋር ተሰልፈው የነበሩ አባላት ወደ ፋኖ እየተቀበሉ ነው ። ከህዝባችን ጋር አንዋጋም በማለት የህዝብ ልጅ የሆነውን ፋኖ በመቀላቀል ለመጨረሻው የአማራ ህዝብ የስርአት ንቅለ ተከላ አቢዮት ራሳቸውን አዘጋጅተዋል ። 1,ጌታቸው ሙላት         የሻለቃ መሪ አጃቢ 2,አዝመራው ሙሉቀን      ጓድ መሪ 3,ይበሉ በሪሁን        አባል

ሕዝባዊ ውይይት በደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 6ኛ ክፍለ ጦር ቀስተ ደመና ብርጌድ ከየደንበኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ጥልቅ የሆኑ ሕዝባዊ ውይይቶችን አካሂደዋል። የአማራ
+3
ሕዝባዊ ውይይት በደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 6ኛ ክፍለ ጦር ቀስተ ደመና ብርጌድ ከየደንበኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ጥልቅ የሆኑ ሕዝባዊ ውይይቶችን አካሂደዋል። የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል በአስተማማኝ የድል መስመር ይጓዝና ተጠባቂ ዓላማውን ያለምንም እንከን ያሳከ ዘንድ ሁለንተናዊ መሠረትነት ያለውን ሕዝባችንን በየዕለቱ መጎብኘት፣ ማወያየትና ምክረ ሃሳቦችን መለዋወጥ መሠረታዊው ጉዳይ ነው። ሕዝባችን የትግላችን የማዕዘን ድንጋይና የጸና የዓለት መሠረት እንደመሆኑ ሁሌም ከሕዝባችን ጋር እንመክራለን። በትናንትናው ዕለትም የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 6ኛ ክፍለ ጦር ቀስተ ደመና ብርጌድ አመራሮችከየደንበኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ጥልቅ የሆነ ሕዝባዊ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱም በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ፣ በሕልውና ትግሉ ውስጥ የማሕበረሰቡ ሱታፌ ከምን እስከምን በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። በተጨማሪም የፋኖን ትግል እምርታ አስመልክቶ የስርጸት ስራ ተሰርቷል። ድል ለአማራ ፋኖ! ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም

የም/አርሲ የክርስቲያኖች እልቂት ተጠያቂው ኢብራሂም ከድር ማን ነው? ተጨማሪ መረጃዎች ደርሰውናል። ** በም/አርሲ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ "አልተፈጸመም" ብሎ የካደው ኢብራሂም ከድር በሻሸመኔው ጭፍጨፋ
+2
የም/አርሲ የክርስቲያኖች እልቂት ተጠያቂው ኢብራሂም ከድር ማን ነው? ተጨማሪ መረጃዎች ደርሰውናል። ** በም/አርሲ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ "አልተፈጸመም" ብሎ የካደው ኢብራሂም ከድር በሻሸመኔው ጭፍጨፋ ወቅትም የከተማው ምክትል ከንቲባ ነበር፣ ** ቀደም ብሎ የሄጦሳ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ የምስራቅ አርሲ ውኃ ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ** ከዚያም የሻሻመኔ ኦሕዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ፤ ** የሻሸመኔ ምክትል ከንቲባ፤ ** ከዚያም ምስራቅ ሸዋ የዞን ሰው ኃይል አስተዳዳሪ ነበር፤

.......... የአደረጃጀት ዜና !! ............ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ201ኛ ኮር የ64ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ። ክፍለጦሩ በአምስት  ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ይትባረክ አንዳርጌ ፣ በአርበኛ ማርሸት ፀሐው እና በመቶ አለቃ አበበ ሰው መሆን ዋና አስተባባሪነት እና በ201ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ላይችሉህ ገበየሁ እና በኮሩ አደረጃጀት ሀላፊ አርበኛ አንላይ እንየው ተባባሪ አስተባባሪነት ተጠናቋል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ጥቅምት 22/2018                    የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሸውን ሐሙሲት ከተማ በማድረግ ወደ ወረታና ደብረ ታቦር ከተማ እየተንቀሳቀሰ እያለ ጉማራ ከተማ ሢደርሥ በጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር አብራከ አናብስቶች ጣና ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በጥምረት ከቀኑ 6:00-7:00 በተፈጸመ ድንገተኛና ፈጣን የማጥቃት አውደ ውጊያ  ጉማራ ላይ የነበረው ጭራቅ ታጣቂ ቡድን ከሐሙሲት የመጣው ኃይል እግሬ አውጭኝ ሲል ከተማዋን ለቅቆ ፈርጥጧል። በዚህ ያልታቀደ ውጊያ ጠላት አሥከሬኑን ሁሉ ትቶ ፈርጥጧል።               አምበሶና ጣና ብርጌድ ጉማራ ላይ ጠላትን በየአቅጣጫው ሲበታትኑት የጣና ብርጌድ አካል የሆነችው ''እሸት ሻለቃ'' ደግሞ ሐሙሲት ከተማ በመግባት ተጨማሪ የአገዛዙ ታጣቂ ቡድን ወደ ጉማራ እንዳይንቀሳቀስ አድርጋዋለች። እሸት ሻለቃ ወደከተማዋ የገባው በአርሴማ በኩል ሲሆን አርሴማ ላይ የነበረውን የጠላት ሀይል ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት መድረሻ አሳጥተዋለች።      ድላችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ!!

በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አገዛዙ የአርሶ አደር  ትጥቆችን በኃይል መንጠቁ ታወቀ። ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ህጋዊ ጠመንጃዎች በሃይል መንጠቅ ጀምሯል። ብልጽግና የአማራ ፋኖን የኃይል እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በተለይም በአርሶ አደሮች ላይ የበቀል በትሩን ማሳረፍ ከጀመረ ውሎ አድሯል። የበቀል በትሩ በህይወት ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኢኮኖሚ ላይም ጭምር ነው። በትላንትናው እለት በሱፍቃራና በሌሎች ቀበሌዎች ከ15 በላይ የንጹሃን አርሶ አደሮችን ነብስ ወከፍ መሳሪያዎችን በየቤታቸው ገብቶ በመፈተሽ ዘርፈው ወስደዋል። በመከላከያና ሚሊሻ ዝርፊያ ተፈጸመበት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ቁጣ ላይ መሆኑም ታውቋል። ዝርፊያው ቀጣይም በሌሎች የምስራቅ ደንቢያ ቀበሌዎችና በሌሎች በሁሉም የደንቢያ አባቢዎች እንደሚቀጥል የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል። በዚህም መሠረት ሁሉም ትጥቅ ያለው የአማራ ተወላጅ በተጠንቀቅ እንዲቆም መልእክት ተላልፏል። በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያለበት እና አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አበክሮ እየሰራ ያለዉ የእናት ጡት ነካሹ እና ቆራጩ ብልፅግና በአማራ ምድር ላይ ያለ የሌለ ሀይሉን እያሰማራ እና እያሰፈረ ይገኛል። የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፫ኛ ኮር ተቆጣጥሯቸዉ እና እያስተዳደራቸዉ ባሉ ቀጠናወች ላይ ይህ ወራሪ ሀይል ይዞት እና እንደቀበሮ ተደብቆበት ከነበረዉ ጥቁር አስፓልት እና የወረዳ ብሎም የዞን ከተሞች ወጥቶ እንቅስቃሴ ሊያደርግ ሲል የ፫ኛ ኮር አካል ክ/ጦሮች እየገደቡትና እያሽመደመዱት ይገኛሉ።በዘሪማ ወደ ጥራይና ለመግባት ሙከራ አድርጎ ጭና እና ድብ ጠለምት ክ/ጦር በተቀናጀ መልኩ መብረቃዊ ጥቃት ሲያደርሱበት ወደ ደባርቅ ከተማ ተሠልሶ ገብቷል።በዚህም የተጠና እና ቅንጅታዊ የ2ቱ ክ/ጦር ሰራዊት በአደረሱበት ከፍተኛ በትር መጠነ ሰፊ ሙትና ቁስለኛ አስተናግዶ ተመልሷል።በጭና በኩል እንቅስቃሴ ያደረገዉ ገዳይ ሰራዊት አያሌዉ ብሩ ክ/ጦር በአደረሰበት ከፍተኛ ምት አፍሮና ተሸማቆ ተመልሶ ወደ ወቀን እንዲገባ ተድርጎ እና ተገዷል። ሌላዉ ገዳዩ እና አራጁ ስርአት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲል የፋኖ ጭንብል ለባሾችን በየቀጠናዉ  በማሰማራት ህዝብን      በማገት      በመዝረፍ      በመግደል  እና በማሰር ፋኖ ሰራቸዉ በማለት ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል ታላቅ ጥረት እያደረገ ነዉ።ይህን እኮይ ሴራቸዉን የነቃባቸዉ የአማራ የቁርጥ ቀን አናብስቶች ማፈን እና እርምጃ መዉሰድ ሲጀምር የፋኖ ትግል አላማ የሌለዉ መሆኑን ተገንዝበን እጅ ሰጥተናል ብሎ በገዳዩ ስርአት የሚዲያ መስኮት በመዉጣት መግለጫ ሲሰጡ ተመልክተናል። ታዲያ ገዳዩ ማን ነዉ?እጅ የሰጠዉ ማን ነዉ? ፋኖ ወይስ ጡት ቆራጩ ስርአት።                    ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።          አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ           ጥቅምት 22/2018ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር! የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሀይል 47ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመታ ጥቅምት 22/2018ዓ.ም በግዳን ወረዳ ልዩ ስሟ
+3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር! የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሀይል 47ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመታ         ጥቅምት 22/2018ዓ.ም በግዳን ወረዳ ልዩ ስሟ ወይራ በር በተባለች ቦታ መነሻውን ከሙጃ ከተማ ከሌሊቱ 7:00 በማድረግ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ስር የሚገኘውን ጥራሪ ክፍለ ጦር የትግስቱ ሻለቃን ለማፈን ጥረት አደርጎ የነበረ ሲሆን ጠላት አንገት አስደፊ ኪሳራ ገጥሞታል። በነበረው አውደ ዉጊያ ጠላት ያለ የሌለ ሀይሉንና ከመድፍ እስከ 107 በመጠቀም በአከባቢው ከባድ ድብደባ ቢያከናውንም ያልጠበቀው ነገር ገጥሞታል ።በአውደ ውጊያውም የተገኙ ቁሳቁሶችና ምርኮኞች የተማረከ ጥቁር ክላሽ=3  የክላሽ ተተኳሽ= 500 የብሬን ተተኳሽ 200 የተማረከ መከላከያ =3 የቆሰለ ሻለቃውን ጨምሮ 8 የተደመሰሰ 5 ሲሆን በአጠቃላይ ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሶበትና ሽንፈቱን ተከናንቦ ወደ መጣበት እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈርጥጦ ተመልሷል ። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጥራሪ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሞላ ተመስገን መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ጥቅምት 22 / 2018 ዓ.ም

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ጥቅምት 22/2018 የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሸውን ሐሙሲት ከተማ በማድረግ ወደ ወረታና ደብረ
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር ጥቅምት 22/2018                          የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሸውን ሐሙሲት ከተማ በማድረግ ወደ ወረታና ደብረ ታቦር ከተማ እየተንቀሳቀሰ እያለ ጉማራ ከተማ ሢደርሥ በጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር አብራከ አናብስቶች ጣና ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በጥምረት ከቀኑ 6:00-7:00 በተፈጸመ ድንገተኛና ፈጣን የማጥቃት አውደ ውጊያ  ጉማራ ላይ የነበረው ጭራቅ ታጣቂ ቡድን ከሐሙሲት የመጣው ኃይል እግሬ አውጭኝ ሲል ከተማዋን ለቅቆ ፈርጥጧል። በዚህ ያልታቀደ ውጊያ ጠላት አሥከሬኑን ሁሉ ትቶ ፈርጥጧል።               አምበሶና ጣና ብርጌድ ጉማራ ላይ ጠላትን በየአቅጣጫው ሲበታትኑት የጣና ብርጌድ አካል የሆነችው ''እሸት ሻለቃ'' ደግሞ ሐሙሲት ከተማ በመግባት ተጨማሪ የአገዛዙ ታጣቂ ቡድን ወደ ጉማራ እንዳይንቀሳቀስ አድርጋዋለች። እሸት ሻለቃ ወደከተማዋ የገባው በአርሴማ በኩል ሲሆን አርሴማ ላይ የነበረውን የጠላት ሀይል ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት መድረሻ አሳጥታዋለች።           በዚህ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ የሆነ የአካል፣ የቁሥና የሥነልቦናን ጉዳት አሥተናግዷል። ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ፍቅሩ ባዬ

ሃምሳ አለቃ ይርጋ ወንዳለ የአፋብኃ ደቡብ አማራ አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ አስተዳደር። የወንዶች ቁና በርታልኝ ወንድም አለም
ሃምሳ አለቃ ይርጋ ወንዳለ የአፋብኃ ደቡብ አማራ አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ አስተዳደር።       የወንዶች ቁና በርታልኝ ወንድም አለም