ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше4 413
Підписники
+2224 години
+437 днів
+1 38430 днів
Архів дописів
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ጥቅምት 22/2018
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሸውን ሐሙሲት ከተማ በማድረግ ወደ ወረታና ደብረ ታቦር ከተማ እየተንቀሳቀሰ እያለ ጉማራ ከተማ ሢደርሥ በጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር አብራከ አናብስቶች ጣና ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በጥምረት ከቀኑ 6:00-7:00 በተፈጸመ ድንገተኛና ፈጣን የማጥቃት አውደ ውጊያ ጉማራ ላይ የነበረው ጭራቅ ታጣቂ ቡድን ከሐሙሲት የመጣው ኃይል እግሬ አውጭኝ ሲል ከተማዋን ለቅቆ ፈርጥጧል። በዚህ ያልታቀደ ውጊያ ጠላት አሥከሬኑን ሁሉ ትቶ ፈርጥጧል።
አምበሶና ጣና ብርጌድ ጉማራ ላይ ጠላትን በየአቅጣጫው ሲበታትኑት የጣና ብርጌድ አካል የሆነችው ''እሸት ሻለቃ'' ደግሞ ሐሙሲት ከተማ በመግባት ተጨማሪ የአገዛዙ ታጣቂ ቡድን ወደ ጉማራ እንዳይንቀሳቀስ አድርጋዋለች። እሸት ሻለቃ ወደከተማዋ የገባው በአርሴማ በኩል ሲሆን አርሴማ ላይ የነበረውን የጠላት ሀይል ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት መድረሻ አሳጥተዋለች።
ድላችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ!!
በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አገዛዙ የአርሶ አደር ትጥቆችን በኃይል መንጠቁ ታወቀ።
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ህጋዊ ጠመንጃዎች በሃይል መንጠቅ ጀምሯል።
ብልጽግና የአማራ ፋኖን የኃይል እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በተለይም በአርሶ አደሮች ላይ የበቀል በትሩን ማሳረፍ ከጀመረ ውሎ አድሯል።
የበቀል በትሩ በህይወት ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኢኮኖሚ ላይም ጭምር ነው።
በትላንትናው እለት በሱፍቃራና በሌሎች ቀበሌዎች
ከ15 በላይ የንጹሃን አርሶ አደሮችን ነብስ ወከፍ መሳሪያዎችን በየቤታቸው ገብቶ በመፈተሽ ዘርፈው ወስደዋል።
በመከላከያና ሚሊሻ ዝርፊያ ተፈጸመበት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ቁጣ ላይ መሆኑም ታውቋል። ዝርፊያው ቀጣይም በሌሎች የምስራቅ ደንቢያ ቀበሌዎችና በሌሎች በሁሉም የደንቢያ አባቢዎች እንደሚቀጥል የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።
በዚህም መሠረት ሁሉም ትጥቅ ያለው የአማራ ተወላጅ በተጠንቀቅ እንዲቆም መልእክት ተላልፏል።
በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያለበት እና አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አበክሮ እየሰራ ያለዉ የእናት ጡት ነካሹ እና ቆራጩ ብልፅግና በአማራ ምድር ላይ ያለ የሌለ ሀይሉን እያሰማራ እና እያሰፈረ ይገኛል።
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፫ኛ ኮር ተቆጣጥሯቸዉ እና እያስተዳደራቸዉ ባሉ ቀጠናወች ላይ ይህ ወራሪ ሀይል ይዞት እና እንደቀበሮ ተደብቆበት ከነበረዉ ጥቁር አስፓልት እና የወረዳ ብሎም የዞን ከተሞች ወጥቶ እንቅስቃሴ ሊያደርግ ሲል የ፫ኛ ኮር አካል ክ/ጦሮች እየገደቡትና እያሽመደመዱት ይገኛሉ።በዘሪማ ወደ ጥራይና ለመግባት ሙከራ አድርጎ ጭና እና ድብ ጠለምት ክ/ጦር በተቀናጀ መልኩ መብረቃዊ ጥቃት ሲያደርሱበት ወደ ደባርቅ ከተማ ተሠልሶ ገብቷል።በዚህም የተጠና እና ቅንጅታዊ የ2ቱ ክ/ጦር ሰራዊት በአደረሱበት ከፍተኛ በትር መጠነ ሰፊ ሙትና ቁስለኛ አስተናግዶ ተመልሷል።በጭና በኩል እንቅስቃሴ ያደረገዉ ገዳይ ሰራዊት አያሌዉ ብሩ ክ/ጦር በአደረሰበት ከፍተኛ ምት አፍሮና ተሸማቆ ተመልሶ ወደ ወቀን እንዲገባ ተድርጎ እና ተገዷል።
ሌላዉ ገዳዩ እና አራጁ ስርአት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲል የፋኖ ጭንብል ለባሾችን በየቀጠናዉ በማሰማራት ህዝብን
በማገት
በመዝረፍ
በመግደል እና በማሰር ፋኖ ሰራቸዉ በማለት ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል ታላቅ ጥረት እያደረገ ነዉ።ይህን እኮይ ሴራቸዉን የነቃባቸዉ የአማራ የቁርጥ ቀን አናብስቶች ማፈን እና እርምጃ መዉሰድ ሲጀምር የፋኖ ትግል አላማ የሌለዉ መሆኑን ተገንዝበን እጅ ሰጥተናል ብሎ በገዳዩ ስርአት የሚዲያ መስኮት በመዉጣት መግለጫ ሲሰጡ ተመልክተናል።
ታዲያ ገዳዩ ማን ነዉ?እጅ የሰጠዉ ማን ነዉ?
ፋኖ ወይስ ጡት ቆራጩ ስርአት።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ጥቅምት 22/2018ዓ.ም
+3
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር!
የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሀይል 47ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመታ
ጥቅምት 22/2018ዓ.ም
በግዳን ወረዳ ልዩ ስሟ ወይራ በር በተባለች ቦታ መነሻውን ከሙጃ ከተማ ከሌሊቱ 7:00 በማድረግ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ስር የሚገኘውን ጥራሪ ክፍለ ጦር የትግስቱ ሻለቃን ለማፈን ጥረት አደርጎ የነበረ ሲሆን ጠላት አንገት አስደፊ ኪሳራ ገጥሞታል።
በነበረው አውደ ዉጊያ ጠላት ያለ የሌለ ሀይሉንና ከመድፍ እስከ 107 በመጠቀም በአከባቢው ከባድ ድብደባ ቢያከናውንም ያልጠበቀው ነገር ገጥሞታል ።በአውደ ውጊያውም የተገኙ ቁሳቁሶችና ምርኮኞች የተማረከ ጥቁር ክላሽ=3 የክላሽ ተተኳሽ= 500 የብሬን ተተኳሽ 200
የተማረከ መከላከያ =3 የቆሰለ ሻለቃውን ጨምሮ 8 የተደመሰሰ 5 ሲሆን በአጠቃላይ ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሶበትና ሽንፈቱን ተከናንቦ ወደ መጣበት እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈርጥጦ ተመልሷል ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጥራሪ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ሞላ ተመስገን መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 22 / 2018 ዓ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ጥቅምት 22/2018
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሸውን ሐሙሲት ከተማ በማድረግ ወደ ወረታና ደብረ ታቦር ከተማ እየተንቀሳቀሰ እያለ ጉማራ ከተማ ሢደርሥ በጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር አብራከ አናብስቶች ጣና ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በጥምረት ከቀኑ 6:00-7:00 በተፈጸመ ድንገተኛና ፈጣን የማጥቃት አውደ ውጊያ ጉማራ ላይ የነበረው ጭራቅ ታጣቂ ቡድን ከሐሙሲት የመጣው ኃይል እግሬ አውጭኝ ሲል ከተማዋን ለቅቆ ፈርጥጧል። በዚህ ያልታቀደ ውጊያ ጠላት አሥከሬኑን ሁሉ ትቶ ፈርጥጧል።
አምበሶና ጣና ብርጌድ ጉማራ ላይ ጠላትን በየአቅጣጫው ሲበታትኑት የጣና ብርጌድ አካል የሆነችው ''እሸት ሻለቃ'' ደግሞ ሐሙሲት ከተማ በመግባት ተጨማሪ የአገዛዙ ታጣቂ ቡድን ወደ ጉማራ እንዳይንቀሳቀስ አድርጋዋለች። እሸት ሻለቃ ወደከተማዋ የገባው በአርሴማ በኩል ሲሆን አርሴማ ላይ የነበረውን የጠላት ሀይል ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት መድረሻ አሳጥታዋለች።
በዚህ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ የሆነ የአካል፣ የቁሥና የሥነልቦናን ጉዳት አሥተናግዷል።
ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
ፍቅሩ ባዬ
ሃምሳ አለቃ ይርጋ ወንዳለ የአፋብኃ ደቡብ አማራ አሳምነው ዕዝ ወታደራዊ አስተዳደር።
የወንዶች ቁና በርታልኝ ወንድም አለም
+5
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ከአበባ 60 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በቡልጋ ከተማ አሥተዳደር ቱለፋ ከተማ ላይ ድንቅ ኦፕሬሽን ፈፀመ::
የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አናብሥቶች የ3ኛ የሰላም ሰው አንዳርጌ ሬጂመንት እንደሁልጊዜ የእረፍት የለሽ ኦፕሬሽን ድል ቁርሷ በአዲሥ አበባ ዙሪያ ቱለፋ ከተማ አሥተዳደር ውሥጥ በመግባት አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ የብልፅግና ካምፖና ምሽግ እንዲሁም የከተማ አሥተዳደር መቀመጫ ህንፃ ውስጥ በመግባት አሥደማሚና አሥደናቂ አፕሬሽን የፈፀመች ሲሆን በተኩሥ ልውውጡ ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ ኪሳራ እና የፋኖን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ሰራዊቱ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ኦሮሚያ ክልል ፍቼ ገነትና በዙሪያው ያለው ግዛት ከተማውን ጥሎ ለቆ ፈርጧል።
ፋኖም ከአሥደናቂው የከተማ ኦፕሬሽን መልሥ ወደተቆጣጠረበት ግዛት የእምዬ ሚኒሊክ የጦር ግምጃ ቤት ወደኮረማሽ ንዑሥ ወረዳ ቀበሌዎች በድልና በጀግንነት ተመልሠዋል::ይህም የከተማ አፕሬሽን እንደሚቀጥል የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ኃይለ ማርያም ማሞ ከ/ጦር ም/አዝዥ ለኦፕሪሽናልና ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አሥታውቀዋል::
መረጃውን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል
ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
በቁርጠኛ ተጋድሎ እንጅ ገዳይን በመለማመጥ ነፃ የወጣ ህዝብ በዓለም ላይ የለም!!!
(በአርሲ ዞን በክርስቲያን ወገኖች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአፋብኃ የተሰጠ መግለጫ)
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
በአርሲ ዞን በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ካህናት በተለይም አማራወች ላይ ላይ ሲፈፀም የቆዬው ግድያ እና ስቃይ እጅጉን ተባብሶ መቀጠሉን ተገንዝበናል።
የአማራ ፋኖን ወደ ጫካ የገፋው ዋናው ምክንያት አገዛዙ በአማራ ህዝብ እና በቤተ እምነቶች ላይ የሚፈፅመውን መዋቅራዊ ጥቃት እንዲያቆም በተደጋጋሚ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያችዎችን ሲጠይቅ አረመኔው የአብይ አህመድ አገዛዝ ይህንን ጥያቄውን ከመስማት ይልቅ በጩኸት በመመሰል ወደ ሙሉ ዘር ማጥፋት ጦርነት በመግባቱ እንደሆነ መላው ህዝባችን የሚውቀው ነው፡፡
ይህ መዋቅራዊ ጥቃት የአብይ አህመድ አገዛዝ ወደ ስልጣን ከወጣበት ግዜ ጀምሮ እጅጉን ተባብሶ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል በካህናት እና መሻይኮች፣ በኦርቶዶክስ እና በእስልምና ምዕመናን ላይ በግልፅ እና በስውር ጭፍጨፋ ሲፈፅም ከመቆዬቱ ባሻገር በአርሲ አካባቢ የተፈፀመው ማንነት ተኮር ጭፍጨፋም የዚሁ ነፀብራቅ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው።
ጥቃቱን ይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት አገዛዝ ለጨፍጫፊዎች መሳሪያ ማደልን ጨምሮ በቀጥታ በግድያዎች ላይ እየተሳተፈ የሚፈፅመው መሆኑ ነው፡፡ ይህ ተግባርም አገዛዙ የአማራን ህዝብ እና ቤተ-እምነቶቹን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋት የእቅዱ አካል መሆኑን በቂ ማሳያ ነው።
አገዛዙ እነዚህን እና መሰል ድርጊቶች እየፈፀመ ያለው የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር በቁጥጥር ስር በማስገባት ጭምር በመሆኑ ኃላፊነት ያለባቸው መንፈሳዊ አባቶች አገዛዙ ድርጊቱን እንዲያቆምና እንዲያስቆም በቂ ትግል ማድረግ ቀርቶ ጥቃቱን ለማውገዝ እንኳን ዳተኝነት እንዲታይባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡
የጥቃቱ ሰለባዎችን ማንነት የሚጋራው ህዝብም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ የጥፋት ተልዕኮ ይዞ የተነሳውን አገዛዝ ማስወገድ ላይ ከማተኮር ይልቅ ከገዳይ ፍትህን የመናፈቅ አደገኛ አስተሳሰብን በመሸከም ዛሬም እንደ ትላንቱ ሻማ በማብራት እና ፍትህ በመለመን ሞቱን የሚጠባበቅ መሆኑ መጭውን ግዜ አስከፊ ያደርገዋል፡፡
በዝምታ እያየው ያለው ሁሉ የአገዛዙ የጥፋት እቅድ እንዲቀጥል ድጋፍ እያደረግለት መሆኑም መታወቅ አለበት። በሰው ልጆች እልቂት ማዘን ሰብአዊ ባህሪ ቢሆንም በቁርጠኛ ተጋድሎ እንጅ በሀዘን እና እርግማን ነፃ የወጣ ህዝብ በዓለም ላይ የለም፡፡ በመሆኑም ሀዘንና እርግማን የሚለውጠው ነገር እንደሌለ ታውቆ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ እራሱን በማደራጀት አገዛዙን በሁሉም ረገድ ታግሎ እንዲያስወግደው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አመራር እና ሰራዊቱ የሽብር እና የጭካኔ ተግባራት የሚቆሙት አረመኔውን የአብይ አህመድን አገዛዝ ፍትህ በመለመን ሳይሆን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች በአፈሙዝ በታገዘ ሁሉን ዓቀፍ ህዝባዊ እምቢተኝነት በሚደረግ ትግል ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ለዚህም ድርጅታችን ሲያደርግ የቆየውን ተጋድሎ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎቻችንን ደም የሚያፈሰውን አገዛዝ በማስወገድ ኦርቶዶክሳዊያንን ጨምሮ ለመላው ህዝብ የሰላም አየር ይመጣ ዘንድ መስዋዕትነት መክፈሉን ይቀጥላል።
በመጨረሻም በዚህ በአገዛዙ ይሁንታ በሚደረግ አሰቃቂ ኢሰብአዊ የጭካኔ ድርጊት የወደቁ ሰማዕታትን ነፍስ ይማር እያልን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕምናን እና ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን፡፡
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል
+6
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ነፃ ባወጣቸዉ ቀጠናዎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየፈታ ይገኛል።
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ከሚያስተዳድራቸዉ ከ ዘጠኝ በላይ ወረዳወች አንዱ የሆነዉ ላስታ ወረዳ ሲሆን ይህ ወረዳም 28 ቀበሌዎችን ያቀፈ ሲሆን ከነዚህ ቀበሌዎች መካከል ድብኮ ቀበሌ አንዱ ሲሆን ከዚህ ቀበሌ ማህበረሰብ ጋር በዛሬዉ ዕለት ማለትም 22/2/2018 ዓ.ም ዉይይት ተደረጓል።
በዚህ ወይይት ላይም የተለያዩ ጥያቄወች እና ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን ማህበረሰቡ ላንሱት ጥያቄ እና ሃሳብም የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ፅህፈት ቤት ኋላፊ አርበኛ ደስታዉ መለሰ ፣ የእዚሁ ዕዝ ም/ህዝብ አስተዳደር የሆኑት መ/ር ፍቅሩ ፈንታዉ እና ሌሎች የኮር አመራሮች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ማህበረሰቡም በተሰጣቸዉ ምላሽ ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ አክለዉም ለጠየቋቸዉ ጥያቄወች አፋጣኝ ምላሽ እንደተሰጣቸዉ እና በተሰጣቸዉ ፈጣን ምላሽም መደሰታቸዉን ገልፀዉ ከጎናቹህ ነን ሲሉ ተናግረዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል
ኀልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኋላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን!
ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ከቢስቲማ ወደ ቦከክሳና ሀደሬ ሲንቀሳቀስ በነበረው የስርዐቱ ወታደር ላይ በተያዘ የክፍለጦሩ ቃኞች የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተጎናፀፈ።
በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣው የአብይ አህመድ ጭራቅ ሰራዊት በወረባቦ ወረዳ ከቢስቲማ ወደ ቦከክሳ ሲያመራ የነበረውን የስርዐቱን ወታደር ልዩ ስሙ ጠቢሳ በሚባል ቦታ ላይ በክፍለጦሩ ቃኞች በተያዘ ውጤታማ ደፈጣ ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት የጠላት ሀይልን ስበት በማድረግ የጥላትን ሰራዊት ወደ ሞት ምድብ ስቦ በማስገባት ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ገሚሱን ሙት እና ገሚሱን ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
ከንጋቱ 12:30 እስከ እረፋድ 3:30 ድረስ በቆየው አውደ ውጊያ የጥላትን ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ መሬት በግስላዎቹ ነፍጥ እየተፈለፈለ የረገፈ ሲሆን፤ ከፊቱ የሚነጠፈውን ጓዱን የተመለከተ ጥላት ለተዎሰነ ሰዓት ባለበት ቁሞ ሞደስ ናፈቀኝ እሮሮውን ቢያላዝንም ግስላው ፋኖ ወደ ፊት በማጥቃት ከሞደስ ናፍቆት ወደ ማይቀረው ሲዖል ሸኝቶቷል። "አንድ ጥይት ለአንድ ጥላት" በሚል የአማራ ብሂል ለአንድ ጥላት በአንድ ጥይት ግንባር ግባሩን ተበርጭሷል።
በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የአብይ አህመድ ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረትን በማስተናገድ ፣አቅዶት የመጣውን እቅዱን ሳያሳካ ወደ መጣበት ወደ ቢስቲማ ከተማ መመለስ ተችሏል።አገዛዙ ክፉኛ የቆሰለውን ሰራዊቱን በፓትሮል ወደ ቢስቲማ ጤና ጣቢያ እያጋዘ ውሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ መሀመድ ሞገስ
ጥቅምት 22/2081 ዓ/ም
#ጠያቂም_ተጠያቂም_ባለመኖሩ_መግደል_ቀላል_ኾኗል!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ
በአገራችን ኢትዮጵያ ተጠያቂነት ከመዝገበ ቃላችን የጠፋ ያኽል ሥርዓት አልበኝነት ነግሶ ዜጎችን መጨፈጨፍ የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል። በአንዱ አካባቢ የተሰማ እልቂት ሳይውል ሳያድር በሌላኛው አካባቢ ደግሞ በበለጠ ዘግናኝ እልቂት ዑደቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል እየተፈፀመ ላለው ፍጅት በዝምታ ማየት በተባባሪነት የተረጋገጠ መስሎ ይታየናል። ሥርዓቱም በሕልሙ በፈጠረው የቅዥት ዓለም እየዋኜ ለምለሙ መስክ እንጂ እልቂቱን ሊመለከት አልፈለገም፤ አይያም አይሰማም፤ ወይም ኾነ ብሎ ድርጊቱ በሌላ መሰል ድርጊት እየተዳፈነ እንዲረሳሳ እንደሚያደርግ ግንዛቤ እንድንይዝ አድርጓል። ከመጋረጃ ጀርባው ሊኖር የሚችለውን ሤራ ትተነው በአደባባይ የተነገሩ መልዕክቶችን ብናወሳ "ሰበርናቸው"፣ "አኹን ቀና እንዳይል አድርገነዋል"፣ በቅርቡ ደግሞ "ዱላህን ወደ ክላሽ እንቀይርልሃለን ባለበት ጨፍጭፈው" እና መሰል መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ ያሉ የእልቂት ቅስቀሳዎች ያለ ሃይ ባይ በመንግሥት ሚዲያዎች ጭምር እንደናኙ ናቸው። አንደኛው ወገን ዱላው ወደተተኳሽ እንደሚቀየርለት ቃል ሲገባለት ሌላው ደግሞ ራሱንና ቤተሰቡን አፍጥጦ ከመጣ ሞት ሊከላከልበት ጥማድ በሬውን ሸጦ የገዛውን መሣሪያ በመከላከያው ጭምር እንዲገፈፍ እየተደረገ ለበላተኛ ተመቻችቶ፣ ተሳስሮ ሞቱን እንዲጠብቅ እየተደረገ ነው። ድርጊቱን በውጤቱ መገምገም ለማንም ቀላል እንቆቅልሽ ስለኾነ።
በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ በጉናና መርቲ ወረዳዎች ልዩ ቦታው ኖኖ ሄቾ ቀበሌ ጥቅምት 13 ቀን እኩለ ሌሊት 5:00-6:00 ላይ በተቀናጀና በተጠና አኳኋን አሥራ ስድስት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ንጹሓን ዜጎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል። የእልቂቱ ሰለባዎች ከ 2 ዓመት ጨቅላ ሕጻን ጨምሮ እስከ 70 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል፤ ለአብነት ያኽል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መኾናቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡ "በአካባቢው የሚኖሩ የቀሩ ክርስቲያኖች እነዚኹ ነበሩ በተጠና መልኩ ለዘር እንዳይቀሩ ነው የጨፈጨፏቸው" የሚሉት አንድ እማኝ "የፀጥታ ኃይል ጠዋት እንኳን እንዳልደረሰ፣ ሰውም ለቀብር ስለጠፋ አምስቱን በአንድ ጉድጓድ ለመቅበር ተገደናል" ይላሉ። በተመሳሳይ ኹኔታ በዞኑ ሽርካ ወረዳ፣ ሄላ ዘባባ ቀበሌ ጥቅምት 17 ሌሊት በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ታግተው ሦስቱ ወዲያው ሲገደሉ ቀሪዎቹ እስከአኹን የደረሱበት አልታወቀም። እንዲኹም ጥቅምት ጥቅምት 18 ሌሊት በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ አምስት የእምነቱ ተከታዮች ተጨፍጭፈዋል፡፡
የቅንጅቱ ፓርቲዎች አካባቢው የእልቂት ምድር መኾኑን በመግለጽ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ብንሰጥም ከመካድና ከመፈረጅ የዘለለ መልስ አልተገኘም። ይኽም የዘር ፍጅትና ዘር ማሳሳት መገለጫ አድርገን እንወስደዋለን። አኹን ላይ ካለው ጥላቻና መዋቅራዊ ጥቃት እንዲኹም ጥቃቱን በተለምዶ ኦነግ ሸኔ አደረሰው ከሚባለው ዘፈቀዳዊ ግድያ ዘለል ያለና ነገሩ ቀጠናዊ ሽብር ቡድኖች ጋር የተገናኘ ሊኾን እንደሚችል ማየት ተገቢ መስሎ ይሰማናል።
ቅንጅታችን እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍ ኢሰብዓዊ ድርጊት በጽኑ ያወግዛል፤ እልቂት የየቀን ገጠመኙ ለኾነው የአካባቢው ማኅበረሰብም ብርታትና መጽናናትን እየተመኘን፤
1. ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃት መንግሥታዊ መዋቅርን የተከተለ፣ሥርዓታዊና ተጨማሪ እጅ ያለበት ስለመኾኑ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን።
2. በተለይ የአርሲ ዞን ነዋሪዎች መንግሥታዊ መዋቅሩ ይጠብቀናል ከሚል አዘናጊ እሳቤ ወጥታችሁ ተፈጥሮዊ በኾነ ራስን ከሞት መከላከልና ከእልቂት ለመዳን በመዘጋጀት ራሳችሁን ከጨፍጫፊዎች መጠብቅ እንዳላባችሁ እናሳስባለን።
3. በፍርሓት ቆፈን እና መንግሥታዊ ጫና ተቀፍድደው ቃል መተንፈስ ያልቻሉ የሃይማኖት አባቶች እልቂቱ መሐል አዲስ አበባ ከመምጣቱ በፊት መንግሥትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ላይ ጫና እንዲፈጥሩ እንጠይቃለን። የኹሉም ቤተዕምነት አባቶች ጋር በመኾን ለሕዝቡ ጥሪ በማድረግ በጣም ሳይረፍድ አባታዊ ግዴታችኹን እንድትወጡ እናሳስባለን።
4. በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኾናችሁ ፊት ለፊትም ከመጋረጃ ጀርባም እልቂት የምትጠምቁ ባለስልጣናት፣ ድርጊቱን በቸልታ ያለፋችኹ የፀጥታ አካላት፣ በደሃው ግብር የተቋቋማችኹና ይኽን የግፍ ግፍ እንዳላየ እንዳልሰማ ያለፋችኹ የመንግሥት ሚዲያ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ፍትሕ ሲሰፍን ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ ልናሳችኹ እንወዳለን፡፡
ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት
ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት ውስጥ በእግዚአብሔር ቸርነት ለተረፈው ሕፃን 70,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ።
EOTCMK TV ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ከሰሙበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ ማዘናቸውን እና ለሞቱት እረፍተ መንግሥተ ሰማያት፤ ቤተሰባቸውን ላጡ መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝተዋል ።
ብፁዕነታቸው የሰው ልጅ ሰው ሆኖ ከመኖር ይልቅ አውሬ እየሆነ ያስቸገረበት ዘመን ላይ መድረሳችን እጅግ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።
እርስ በእርስ እንዋደድ ዘንድ የታዘዝነውን የአምላክ ቃል ወደ ጎን በመተው ሌሊትን ተገን በማድረግ ለተፈጸመው ድርጊት ነገ እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል በማለት መልእክታት አስተላልፈዋል።
ከእነዚህ ከተገደሉት ምእመናን ዛሬ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ የሚገኘውን ዕድሜው 4 ዓመት የሆነው ሕፃን ላይ እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበትን አረመኔያዊ ተግባር መፈጸም እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ቆም ብለን ማሰብና ወደ ልቦናችን መመለስ የሚገባበት ዘመን ስለሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን በአንድነት ዘብ የምንቆምበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን ያሳያል በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል ።
ይህ ሕፃን በደረሰበት አደጋ ሕክምናውን አጠናቆ እስከሚወጣ ድረስ ድጋፋቸው እንደማይቋረጥ የገለጹት ብፁዕነታቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ ገዳማት እና አድባራት መመሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም መልእክታቸውን ያስተላለፋት የወላይታ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቀሲስ ቦክቻ ኤንጋ ዛሬ ሰማዕትነትን በተግባር ያየንበት ዘመን ነው ያሉ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን በሰማዕታት ደም የፀናች መሆኗን በተለይ በአንዳንድ አካባቢ የሚታየው የቤተክርስቲያን የፈተና እና የሰቆቃ ዘመን መሆኑን ገልጸው ሕፃኑ ሕክምናውን እስኪያጠናቅቅ የሀገረ ስብከቱ ክትትል እና ድጋፍ እንደማይለይ ሕዝበ ክርስቲያኑንም በማስተባበር ኮሚቴ በማዋቀር በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናንን የዚህ በረከት ተሳታፊ በማድረግ ዝግጅት እንደሚደረግ አሳስበዋል ፡፡
ብፀዕነታቸው በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ ላሉ ታካሚዎች ጸሎት አድርገል፡፡ በጉብኝት መርሐ ግብሩም የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ኃላፊዎች የገዳማት እና አድባራት አበምኔቶች አስተዳዳሪዎች እንዲሁ በማኅበረ ቅዱሳን የወላይታ ሶዶ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ የሀገረ ስብከቱ እጨጌ ሚዲያ እና ምእመናን ተገኝተዋል።
ዘገባው በማኅበረ ቅዱሳን የወላይታ ሶዶ ማእከል ነው።
⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️ ባለጊዜ የዳንግላ ባንዳ መዘጋጃ ቤት ሀላፊ ተብየዎች ነዋሪዎችን የመዝረፊያ ዘዴዎችን በመቀየስ እሰከ ታህሳስ 20 ገንብቶ የይዞታ site ማረጋገጫ ያልያዘ ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ በማስገባት፤ እርምጃ እንወስዳለን፤100% በተግባር እናደርገዋለን፤ በማለት፤ በዚህ ወቅት በኢኮኖሚ ሽባ ሆነው መስራት፤መገንባት ያልቻለ ማህበርሰብን ግምት ውስጥ ያላስገባ እና ያላገናዘበ ውሳኔ ነው ብለን ብንጠይቃቸውም፤ ከቻልክ ስራ፤ካልቻልክ ትነጠቃለህ የሚል ምላሽ ሰጥተው፤ ህ/ ሰቡን በማስጨነቅ፤ ድባቴ ውስጥ በመክተት በጭንቀት ውስጥ ተወጥሯል፤ መላ ሊባሉ ይገባል፨
✊የአማራ ልዩ ሀይል ፈርሶ ከካምፕ ወደ ጫካ ሲገባ የመጀመርያው ፈር ቀዳጅ አቸፈሬው ኮማንዶ ፈቃዱ ጌትነት!
ያኔ ይህንን ብሎ ነበር :: "አሁን እኛ ወደ ጫካ እየገባን ነው ማን መጦ ትጥቅ እንደሚያስፈታን እናያለን::
የፌድራል መንግስት ትጥቅ ሊያስወርደን ከመጣ ያለምንም ማመንታት እንገጥመዋለን:: ግን ደግሞ እኛ የማን ልጆች መሆናችንን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አይሞክሯትም ከሞከሯት ይምጡ ደስተኞች ነን::
"የክልሉ መንግስትም አሻፈረኝ ብሎ እኛን ትጥቅ ሊያስወርድ የሚመጣ ካለ እንዳስፈላጊነቱ እሱም ይመታል በማለት ድምጹን አስተጋባ::
ብዙዎችም ተከተሉት:: ';አርበኛ ኮማንዶ ፍቃዱ'' በስሙ እና በደሙ ተቋም ገንብቶ አለፈ::
እኛም ወንድሞቹ የወደቀለትን ትግል በጽናት እናሻግራለን ይህ የማይታበይ ቃላችን ነው::
በሱዳን አማፅያን የኤል ፋሸር ከተማን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከ2,000 በላይ ንፁሃን ገድለዋል ተባለ
የሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት የጀመረው በፈረንጆቺ በሚያዝያ 2023 ሲሆን፣ በጦር ሠራዊቱ እና ቀደም ሲል ለመንግሥት ይገዛ በነበረው ፈጣን ምላሽ ሰጪ ኃይል (Rapid Intervention Forces - RIF) መካከል ነው።
የሱዳን ዶክተሮች ኔትዎርክ እንደገለጸው፣ ታጣቂዎቹ ከተማዋን ከተቆጣጠሩ በኋላ በአካባቢው በሚገኘው ሆስፒታል ውስጥ የነበሩትን ሁሉንም ሰው ገድለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትጥቅ ያልታጠቁ ወንዶች ሲተኮሱ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መኖራቸውን ገልፇል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ታግተው የተያዙ ሲሆን፣ እስከ 10 ሚሊዮን የሱዳን ፓውንድ የሚደርስ ቤዛ እንዲከፈልባቸው እየተጠየቁ ነው።
በከተማዋ ውስጥ ወደ 260,000 የሚጠጉ ሰዎች፣ ግማሾቹ ህፃናት ሲሆኑ፣ ቀርተዋል፤ በረሃብ ምክንያትም የእንስሳትን መኖ እየበሉ ነበር። ከግጭቱ መጀመሪያ አንስቶ ከ150,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከ3.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ስደተኞች መሆናቸውን የሚዲያ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ቪዲዮ: የማኅበራዊ ሚዲያ።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የጎንደሬ በጋሻው ክ/ር አባላት ሰብል ስብሰባ ማህበረሰቡን በማገዝ ላይ።
+6
~~~~~~~~~~~|
አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነሰላም ላይ ሚሊሻ ሲሞት ሃይማኖቱ ተፈልጎ ይለቀስለታል። ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሰፈር እየተለቀሙ ሲ'ታረዱ ግን ሃይማኖት የላቸውም።
በሌላ በኩልም ቢሆን የ1000 አማራ ህዝብ ሞት ከአንድ የቀቤና ማህበረሰብ ንብረት የሆነች ፍየል በመኪና ተገጭታ መሞት ጋር እኩል ሚዛን እንዳይኖረው ተደርጎ የተሠራ ትርክት እና ሃገራዊ ሥርዓት ውስጥ ነው የምንኖረው።
በኦህዴድ/ብልፅግና የምትመራዋ ሃገር ማለት ይህቺ ናት።
እንዴት እንደምንቀጥል ወደ ፊት እንነጋገራለን!
