ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 641
Підписники
+2024 години
+3787 днів
+1 08530 днів
Архів дописів
*ሰበር ዜና*
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በ13/06/18 ውጊያ የዕለቱ ታጋድሎ።
እራሱን ጥምር ኃይል እያለ የሚጠራው ጨፍጫፊውና አራጁ የአብይ አህመድ የገብሥ ገለባ ሰራዊት ወደ ጎርፎ ከተማ ለመግባት ያደረገው ሙከራ በጀግኖቹ በ ኃይለማርያም ማሞ ፋኖ ተጋድሎ ሳይሳካለት ቀርቷል።
በሶስት አቅጣጫ ወደ ጎርፎ ከተማ ለመግባት ዓመታዊ የእግዚአብሔር አብን ክብረ በዓል ለማደናቀፍ አስቦ ለሊት ሲነጋጋ በግምት 11:30 ጀምሮ በጎርፎ የቁር ጎጥ አቅጣጫ የተንቀሳቀስውን የጠላት ኃይል ጀግኖቹ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሻለቃ አንድ ቤዛ ሬጅመንት ደፈጣ በማድረግ (2) አብሪውን የቀነደሹት ሲሆን ሶስት የሚሆኑ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።
በሌላ በኩል ከማለዳው በግምት 12:00 አካባቢ በመክበቢያን ማርያም ወደ ጎርፎ ከተማ ለመግባት የተንቀሳቀሰውን የጠላት ኃይል የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ቃኚ ሻለቃ የደፈጣ ጥቃት በማድረግ የጠላትን ኃይል አራግፈውታል።
ይህን ጥቃት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከሀገረ ማርያም ከተማ ተጨማሪ ኃይል እንዲላክለት በመጠየቅ በግምት ከጠዋቱ ሁለት ሰአት አካባቢ ሁለት አይሱዙ መኪና ተጨማሪ ኃይል የተላከለት ቢሆንም በቁና ተራራ እና አካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሰው ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ዳኛቸው ሻለቃ የደፈጣ ጥቃት ተመቶ መንገድ ላይ በአራት ጠላት ላይ ጥቃት በማድረሥ ለእርዳታው ሳይደርሥ ቀርቷል።
በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት የጎርፎ ከተማን ለመያዝ ያቀደው የጠላት እንቅስቃሴ በከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር የተሳካ የደፈጣ ጥቃቶች እቅዱ ሳይሳካ ከመቅረቱም በላይ የጠላት ኃይል በርካታ ሙት እና ቀስለኛ ሆኖ የተቀጠቀጠው የጠላት ኃይል ቁስለኞቹን እና አስክሬኖቹን ጭኖ ተመልሷል።
ዘገባውን ያደረሰን የኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ሪፖርተር አረበኛ ሀቀኛው ይታፈር ነው!!!!
➔ድል ለአፋብን!!!!
➔ድል ለአማራ ህዝብ!!!
@የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!!
ይህ የምታዩት ለማታለያነት የተሠራ የኮሪደር ብልጭልጭ ልማትም አይደለም።
ለአፍሪካ መሪዎች ተብሎ ደምቀው የዋሉት ሠው አልባ የቦሌ እና አራት ኪሎ መንገድ ላይም የተወሰደ ፎቶ አይደለም።
በብአዴን እና በኦህዴድ ዘመን የጥፋት አዋጅ ታውጆበት እየነደደ ያለ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ አርሶምባ ዘንቦ ቀበሌ ሀይማ ቆላ የተባለ ቦታ ነው።
በዚህ ቃጠሎ እንስሳት፣የጎተራ እህል፣ሀብት ንብረት፣አልፎም የሰው ልጅ ከነ ነፍሱ እየተቃጠለበት ያለ ወረራ ነው።
ይህ ቦታ ከስምንት ቀን በፊት በአገዛዙ ጥምር ጦር የተዘረፈ ቦታ ሲሆን አሁን ደግሞ እንዳያገግም በሚል በአገዛዙ ትዛዝ ዳግመኛ እየጠፋ ያለ አካባቢ ነው።
ይሄን ተፀይፎ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመታገል እና ርስቱን ለማስከበር የማይወጣ አማራ ካለ እጣ ፋንታውን ከወዲሁ አውቆ ተቀብሏል።
መዝግብ አማራ።
የብዕር ግዞተኞች እና የሆድ አምላኪዎች ፍልሚያ
የከተማዋ የምሽት ቆይታ በወሬ ነፋስ ታውኳል። በግርግም ውስጥ የተደበቁት "ደናቁርት" እና በብርሃን ስር የሚራመዱት "ጀግኖች" ፍልሚያ ግልፅ እየሆነ መጥቷል።
ታሪኩ የሚጀምረው በሁለት ተቃራኒ ዓለማት ውስጥ ባሉ ሰዎች ነው። በአንድ በኩል፣ ስለ ሀቅና ስለ ማንነታቸው ሲሉ የብረት አጥሮች የከበቧቸው፣ በግዞት ቤት የሚማቅቁ እውነተኛ የሙያ ባለቤቶች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የጋዜጠኝነትን ክብር እንደ ካባ ደርበው፣ ነገር ግን ውስጣቸው በሆዳምነትና በክህደት የጠቆረ "ባንዳዎች" ይኖራሉ።
ኤልያስ ደባሱ የተባልክ ሆይ!" ድምፅ ከጨለማው ውስጥ እንደሚወጣ ነጎድጓድ። "የአባታችን የአስራት ወልድዬን ተጋድሎ የዘነጋህ፣ በሽንቁር ውስጥ ተሸሽገህ የምታደባ ደነቆሮ! ዛሬ የአማራን ህዝብ ስም እየጠራህ ስትምል፣ በውስጥህ ግን ለራስህ ጥቅምና ለጊዜያዊ ሽልማት ስትሰግድ አየንህ።"
"ጋዜጠኝነት ለጀግኖች የሚሰጥ የክብር አክሊል እንጂ፣ ለሆዳሞች የሚሆን ጭንብል አይደለም። ዛሬ ትክክለኛዎቹ የብዕር አንበሶች በጨለማ ቤት ሆነው ስለ እውነት ዋጋ ሲከፍሉ፣ አንተ ግን ያለ ሙያህ በክብር ወንበር ላይ ተቀምጠህ የታሪክ መዘባበቻ ሆንክ። ለአይሻ ማህመድ ያልሆንክ፣ ለራስህ ወገን ያልቆምክ 'ሰው' ዛሬ ስለ አብይ አህመድ ጡት ቆራጭ ወታደር ስታወራ ማየት ምንኛ የሚያሳዝን ትዕይንት ነው!"
ሆኖም የመስዋዕትነት መንገድ፦ በእስር ቤት ሆነውም ለሙያቸው ታማኝ የሆኑት።
የክህደት መንገድ፦ ሆዳቸውን አምላክ አድርገው፣ በሰው ስም የሚነግዱት እንደ አንተ ያሉት ሆድ አምላኩ ኤልያስ ደባሱ ናቸው።
"ታሪክ የማይረሳው አንድ እውነት አለ፦ የሀሰት ካባ የለበሱ 'ደናቁርት' በጊዜያዊ ድል ቢፈነጥዙም፣ የሙያውን ክብር የጠበቁት ግን በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ይፃፋሉ። ኤልያስና መሰሎቹ ግን በገዛ ህሊናቸው ግዞት ውስጥ ወድቀዋል። Dawit Amhara
ኧረ መብገን - ፋኖ ደፋሩ ጌትነት | Ere Mebgen - Fano Defaru Getinet | አዲስ ምርጥ ወኔ ቀስ...
https://youtube.com/watch?v=Tm1viXTMlfo&si=TJlST2Ev8MmvbuaW
ኧረ መብገን - ፋኖ ደፋሩ ጌትነት | Ere Mebgen - Fano Defaru Getinet | አዲስ ምርጥ ወኔ ቀስ...
https://youtube.com/watch?v=Tm1viXTMlfo&si=TJlST2Ev8MmvbuaW
፲ አለቃ ኤርሚያስ ሻታን ጨምሮ ሰባት የአረመኔው ሰራዊት አባላት የምህረት አዋጁን በመቀበል 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የካቲት 13/2018 ዓ.ም
=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=
አፋብን ባለፈው ሳምንት ለ15 ቀናት ይቆያል ባለው የምህረት አዋጅ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት ጥሪውን ተቀብለው 206ኛ ኮርን የተቀላቀሉ ሲሆን ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ 7 የአረመኔው ሰራዊት አባላት 14ኛ፣ 24ኛ እና 34ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።
፲ አለቃ ኤፍሬም ሻታ እና ብሩክ ጫሜባ ለሬቦና ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመውጣት 14ኛ ክ/ጦርን ሲቀላቀሉ ታደለ አዳምቅ እና ፈንታሁን ድረስ እንዲሁ ከጃማ ከተማ በመውጣት 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
ወርቁ ላመስግን፣ አዲሱ ፈጠነ ምህረቴ ከቁይ ከተማ እና ተፈራ ጫኔ ከደብረ ማርቆስ ከተማ በመውጣት 24ኛ ክ/ጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የተቀላቀሉ ሚኒሻዎች እንደሆኑም ተገልጿል ።
የአረመኔውን ስርዓት በመተው የምህረት አዋጁን የተቀበሉት በበኩላቸው ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለጠላት ተልዕኮ ተባባሪ ከመሆን በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ጥቃት ከአፋብን ጋር በመሆን እንዲመክቱ ለሚኒሻዎች፣ ለአድማ ብተና፣ ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ ትውልድ አዲስ አሰሰተሳብ አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የኦሮሙማው ዘራፊ እና ጡት ቆራጭ ሰራዊት ብትንትኑ እየወጣ ነው፡፡ ለብስኩት ብሎ የገባ ሁሉ አሁን መድረሻ አጦ እየተንከራተተ ነው፡፡ አሁን መሪዎች አገር ጥለው ይሄዳሉ ወይስ ይጎተታሉ፡፡
ልሂድ ቢሉስ የት ይገቡ ይሆን?
#አዳኝ_ቡድን‼️
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የአዳኙ ኦፕሬሽን ቡድን አባል የሆነ አንድ ጓድ ዛሬ በሊባኖስ ከተማ አንዱን ሆዳም አድማ ብተና በጠራራ ፀሐይ በክላሽ ጥይት ግምባሩን በርቅሶት ወጧል።
የካቲት 13/2018 ዓ.ም
ድል ለጀግኖቹ!
13/ዐ6/2018 ዓ.ም
አሳዛኝ ዜና‼️
በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በወርጌቻ ደብረ-ፀሃይ ቀበሌ የአገዛዙ ሰራዊት በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ አደረገ ።
ይካቲት 13/2018 ዓ.ም፡ ጦርነትን የዘወትር ስራው አድርጎ የያዘው የብልፅግናው ገዢ ቡድን አመታቶች በተቀያየሩ ቁጥር የጦርነት አውድማውን በመቀያየርና በፋብሪካ ፋንታ በየ ቦታው መድፍና ታንክ እየተከለ የአማራን ህዝብ፤ ብሎም መላውን የኢትዮጵያን አርሶ-አደር ገበሬዎችን በማሰቃየትና በመጨፍጨፍ የቀጠለው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ አሸባሪው መከላከያ ተብየው የለመደውን የንፁሃን ንብረት ማቃጠሉንና አርሶ-አደሮችን ከቤት እያስወጣ መረሸኑን ቀጥሏል ።
ይህም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በወርጌቻ ደብረ-ፀሃይ ቀበሌ የገባው የአገዛዙ ሰራዊት "ቤታችንን ጥለን አንሸሽም" ባሉ ሰባት (7) ንፁሃን አርሶ-አደሮችን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥቶ እንደረሸናቸው የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰውናል ።
እነኝህ አርሶ-አደሮች መከላከያ የረሸናቸው ወንጀል ኖሮባቸው ሳይሆን በአማራነታቸውና ንብረታቸውን ለዘራፊ ሌባ ጥለን አንሄድም በማለታቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ። ይህ አማራን ለማጥፋት ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል ቀቢፀ-ተስፋ የገባው የብልፅግና ሰራዊት በተቃራኒው በፋኖዎች ጠንካራ ምት ሲያይልበት ይዞት የገባውን ትጥቅና ስንቅ እየተማረከበት የፋኖዎችን ፀረ ሽምቅ ማጥቃት መቋቋም ያቃተው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በአሁኑ ሰዓት "ሁሉም አማራ ፋኖ ነው" በማለት የጅምላ ጭፍጨፋ እንደጀመረ የዛሬው የንፁሃን ግድያ፤ እንዲሁም ከሰሞኑ በፈፀማቸው አሰቃቂ ድርጊቶች ትልቅ ማሳያ ነው ።
በግዳጅ ሲያፍስና ሲያስገድድ የከረመው የብልፅግና ሰራዊት በአሁኑ ሰዓት የአማራን ንብረቶችን መዝረፍና ማውደም ፥ "የተገኘውን ሰውም መረሸን" የሚል መመሪያ እንደወረደላቸው፤ አንድ የሰራዊቱ አባል የነበረና በአሁኑ ሰዓት ከፋኖ ጋር ተቀላቅሎ በመታገል ላይ የሚገኝ ጓዳችን ፲ አለቃ እሸቱ የኮቦታው ሳለ ያዳመጠውንና የታዘበውን ስርዓቱ በአማራ ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት የተጠናና ስልታዊ በሆነ መንገድ እየተገበረው እንደሆነ መረጃውን አጋልጧል፤ ፲ አለቃ እሸቱ ማለት የአገዛዙን ግፍና ሰቆቃ በመረዳት በቅርቡ አንድ የቡድን መሣሪያ (ብሬን) እና ሐዲድ ክላሽ ይዞ ነበልባል ክፍለጦር'ን የተቀላቀለ ጀግና የአማራ ልጅ ነው፤ ሲል አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን መረጃውን አድርሶናል ።
© አፋብን ደ.አ.ቀ. አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አርበኛና ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ ።
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና በአውደ ውጊያ አይሳካለት ሲል ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃኖችን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ቀጥሏል‼️
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 08 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጣምሬ የተባለ ቦታ ላይ ተደጋጋሚ የመድፍና የሞርተር 120 mm ድብደባ በመፈፀም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: በዚህም በተጠቀሰው የመቅደላ ወረዳ በተንቀሳቃሽ ምስል በሚታየው መልኩ ህዝብ በብዛት ወደሚኖርበት ቀበሌ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ ጉዳት አድርሷል::
በዚህም ፋሽስቱ አገዛዝ የአብይ አህመዱ ብልፅግና ሰራዊቱ በአውደ ውጊያ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የከባድ መሳሪያ ሽፋንና ድጋፍ በሚያገኝበት ሁኔታ በአስተኳሽቹ በኩል ወደ ገጠር መንደሮችና ታዳጊ የገጠር ከተሞች ጭምር በተደጋጋሚ እንዲወነጨፍ በማድረግ የንፁሃኖችን ህይወት በጅምላ እየቀጠፈና አካል እያጎደለ እንስሳቶችንም እያስጨፈጨፈ ቤትና ንብረትም እያወደመ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 13/2018 ዓ.ም
13/ዐ6/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር ህዝባዊ ውይይትና ወታደራዊ ስልጠና አካሔደ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር በተቆጣጠራቸው ቀጠና ለሁለት ቀናት በግፍት እና ጭምብሬ ቀበሌዎች ህዝባዊ ውይይት አካሔዷል። በዚህ መድረክ ላይ የዕዝ እና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። በመድረኩም ለአባት አርበኞችና ለነዋሪው ማህበረሰብ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ለማህበረሰቡ ግንዛቤም ተሰጥቷል። ከማህበረሰቡ ስለ ፋኖ እንቅስቃሴ ያለውን አመለካከትና ጥቆማ በነፃነት ያነሳ ሲሆን፣ ከፋኖ አመራሮች በኩልም ምላሽና ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። በመድረኩ ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦
1.የትግሉን ለውጥ በተመለከተ ባለፉት ዓመታት ሲሰበኩ የነበሩት ፀረ-አማራ የፖለቲካ፣ የኃይል እና የትርክት አሰላለፎች በፋኖ ፅኑ ትግል መቀልበሳቸውና ይህም ዓለም አቀፋዊ እውቅና ማግኘቱ።
2.ሀገራዊ ስኬት በተመለከተ፦ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የትግሉ ተጽዕኖ ከአማራ ግዛት አልፎ መላ አገሪቱን ማዳረሱና የለውጥ ኃይሉን በአንድ ወገን ማሰለፍ መቻሉ እንደ ትልቅ ስኬት ተነስቷል።
3.የህዝብ ተሳትፎ በተመለከተ የአማራ ህዝብ ከደጋፊነት ባለፈ የትግሉ ባለቤት በመሆን አገዛዙን እንዲታገልና ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖ "አንድ መሪና አንድ ድርጅት አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን ድርጅታዊ ቤቱን የፈጠረው አንድነት ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ የአሸናፊነት ተምሳሌት መሆኑን ተሳታፊው ማህበረሰብ አንድነት የትግሉ የመጨረሻ ግብ መድረሻ መሆኑ ደስታችሁ ደስታችን ነው የአማራ ህዝብ በነጻነት የመኖር መብቱ የሚወሰነው በአማራ ፋኖ ብቻ ነው በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
መረጃው የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
የካቲት 13 /05/2018 ዓ.ም
አርበኛ ዘመነ ካሴ እና መሪ ድርጅታችን አ.ፋ.ብ.ን ከ ማንም ጋር ምናወዳድረው መሪ እና ድርጅት አይደለም !
መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እና መሪ ድርጅታችን በአማራነት ተሰርቶ ፤ በኢትዮጵያ ልክ ተሰፍቶ ፤ ለአፍሪካዊያን የተበረከተ መሪ እና ድርጅት ነው ። በዚህም ምክንያት የ 30 ዓመት የኢህዲግ ምርት የሆነ ካድሬ ፤ በፖለቲካ ዕድሜው ብቻ የጎልማሳ እድሜ የያዘ ጡረተኛ ካድሬ ፤ የድርጅት እድገት ማለት ከኢህዴን ጀምሮ ፦ ብአዴን > አዴፓ > ብልፅግና መድረስ የሚመስለው የቤተ-መንግስት ለማዳ እንስሳ እና ዲፖሎማሲ ማለት ዶላር በኩንታል ተሸክሞ በየ ኢንባሲው በር ላይ ሎቢስት ፍለጋ መዞር ለሚመስለው ደረጃ አንድ ድኩማን ካድሬዎች ተደምረው ከአርበኛ ዘመነ ካሴ እና ከድርጅታችን አ.ፋ.ብ.ን ጋር መወዳደር በፍፁም አይችሉም ።
ከቤታችን ያስወጣን አንኳር ጉዳይ ' አማራ' የሚባል ገናና ማንነት ያለውን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት በቃላት የተዋበ ፀረ-አማራነት ሰነድ ተዘጋጅቶ ይሄ ሰነድ ደግሞ ህግ እና ህገ-መንግስታዊ መዋቅር ተሰርቶለት አሰፈፃሚ አካል ተመድቦለት ላለፉት 60 እና 70 ዓመታት በጋራ አገራችን ውስጥ የአማራን ህዝብ ብቻ ለይቶ መዋቅራዊ የዘር ፍጅት አድርሶበት እንደ ዘር ለመቀጠል ስንጠራጠር ይበቃናል አትግደሉን፣ አታግቱን ፣ አትዝረፉን፣ አታፈናቅሉን ብለን በደብዳቤም በስልፍም ስንጠይቅ ሰሚ አጠን ይባስ ብሎ ሞታችን ከጓሯችን ሲመጣ እንደ ህዝብ ህልው ሁኖ ለመቀጠል ሁሉን ነገር ንቀን ለአማራነታችን ጫካ እንድንወጣ ተገደናል ።
ጫካ በወጣንበት ወቅት ሁሉም ታጋይ ማስታወስ ያለበት ብልፅግና የዋለልንን ሁለት ውለታዎች በፍፁም መርሳት የለበትም የመጀመሪያው ብልፅግና እራሱ ፈርሶ መገኘቱ ነው ። ሁለተኛው ደግሞ ፈርሶም ጭምር ፍላጎቱ የአማራን ህዝብ ማጥፋት ምርጫው ማድረጉ ነው ። ሁለቱም ውለታዎቹ የአማራን ህዝብ በሁለት በኩል የተሳለ ቢላ እንዲሆን አስችለውታል ። በነዚህ ምክንያት ከጥንት አማራ አንገቱ አንድ ነው ብለው የነገሩንን የነ ደጃች ፀሐዩ እንቁስላሴን ሐሳብ በመውሰድ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እልቆቢስ የአማራነት ፅንሰ ሐሳቦች አዳብረን ፣ አንድ ሁኑ የሚለውን የሰማዕቱን ጄነራል አሳምነው ፅጌን ምከረ ሐሳብ አማራ ሲሏችሁ አትሸማቀቁ ከሚለው የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት ጋር ተዋህዶ አመራነትን ራስ-በቅ ሁኖ እንዲቆም መሠረት እና ጣራ ሁኖት ከዚህ እንዲደርስ አድርጎታል። ትውልዱም በሚገባ እያሻገረው ይገኛል ።
ከአሁን በኋላ ' አማራነት ' ሌሎች በእኩልነት ላይ በጋራ ለማደግ እና ለመወሰን ለሚፈልጉ ህዝቦች ሁሉ ከበረዶ የነፃ የሚታይ ፣ የሚዳሰስ እና የሚነገርለት መሠረቱ ብሔርተኝነት ያደረገ ነገር ግን ርዕዮቱ ለሁሉም የሆነ ትግል ለኢትዮጰያውያን እንካችሁ ያለ ትግል ይዞላችሁ መጧል ። ይሄን ትግል የሚመርጥ ለወጣበት ማህበረሰብ የሚቆረቆር ብቻ ነው ።
በመሆኑም መሪያችንም ሆነ ድርጅታችን ተስማምተን የመረጥነው እና የመሠረትነው የአዲሱን ትውልድ አስተሳሰብ በውስጡ የያዘ ተስፋችን ነው ። በአጠቃላይ አዲሱ ትውልድ የአንደኝነቱን ደረጃ ለመጋራት እንጅ ለሁለተኛነት ስለአልተፈጠረ ትብብር እና ችግርን በጋራ ለመፍታት የአንድ ማንኪያ ቅንነቱ ባለበት የተጠበቀ ሲሆን እናንተ ሳትሆኑ እኔ ብቻ ነኝ የምመራችሁም የምወስንላችሁም የሚለን ኃይል ከገጠመው ግን ከምንም ጀምረን ከዚህ ያደረሰውን ትግል ከሁሉም ፀረ-ብልፅግና ኃይሎች ጋር በመተባበር ቤተ-መንግሱት ለመቆጣጠር በትብብር እንድንቀሳቀስ እንገደዳለን ። ለዚህ ደግሞ ሁሉም ነገሮች ምቹ እና ዝግጁ ናቸው ።
መሪያችን እና መሪ ድርጅታችን የሚጠበቀው በኛ አዕምሮ እና በኛ የተባበረ ክንድ ነው ። ስለዚህ ምርጫችን ለህልውናችን በክንዳችን እንጅ የስንዴ ነዶ አይደለም ። የ ስንዴ ነዶው በዝቶ ካስቸገራችሁ ከ 10,000,000 ሚሊየን በላይ የምግብ ዋስትና ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን አድርሱላቸው !
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳስብ ፣ አዲስ ተስፋ!
©ግሩም ምሳሌ
