ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 641
Підписники
+2024 години
+3787 днів
+1 08530 днів
Архів дописів
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር ህዝባዊ ውይይትና ወታደራዊ ስልጠና አካሔደ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ፣ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር በተቆጣጠራቸው ቀጠና ለሁለት ቀናት በግፍት እና ጭምብሬ ቀበሌዎች ህዝባዊ ውይይት አካሔዷል። በዚህ መድረክ ላይ የዕዝ እና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። በመድረኩም ለአባት አርበኞችና ለነዋሪው ማህበረሰብ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ለማህበረሰቡ ግንዛቤም ተሰጥቷል። ከማህበረሰቡ ስለ ፋኖ እንቅስቃሴ ያለውን አመለካከትና ጥቆማ በነፃነት ያነሳ ሲሆን፣ ከፋኖ አመራሮች በኩልም ምላሽና ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። በመድረኩ ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦
1.የትግሉን ለውጥ በተመለከተ ባለፉት ዓመታት ሲሰበኩ የነበሩት ፀረ-አማራ የፖለቲካ፣ የኃይል እና የትርክት አሰላለፎች በፋኖ ፅኑ ትግል መቀልበሳቸውና ይህም ዓለም አቀፋዊ እውቅና ማግኘቱ።
2.ሀገራዊ ስኬት በተመለከተ፦ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የትግሉ ተጽዕኖ ከአማራ ግዛት አልፎ መላ አገሪቱን ማዳረሱና የለውጥ ኃይሉን በአንድ ወገን ማሰለፍ መቻሉ እንደ ትልቅ ስኬት ተነስቷል።
3.የህዝብ ተሳትፎ በተመለከተ የአማራ ህዝብ ከደጋፊነት ባለፈ የትግሉ ባለቤት በመሆን አገዛዙን እንዲታገልና ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖ "አንድ መሪና አንድ ድርጅት አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን ድርጅታዊ ቤቱን የፈጠረው አንድነት ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ የአሸናፊነት ተምሳሌት መሆኑን ተሳታፊው ማህበረሰብ አንድነት የትግሉ የመጨረሻ ግብ መድረሻ መሆኑ ደስታችሁ ደስታችን ነው የአማራ ህዝብ በነጻነት የመኖር መብቱ የሚወሰነው በአማራ ፋኖ ብቻ ነው በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
መረጃው የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
የካቲት 13 /05/2018 ዓ.ም
አርበኛ ዘመነ ካሴ እና መሪ ድርጅታችን አ.ፋ.ብ.ን ከ ማንም ጋር ምናወዳድረው መሪ እና ድርጅት አይደለም !
መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ እና መሪ ድርጅታችን በአማራነት ተሰርቶ ፤ በኢትዮጵያ ልክ ተሰፍቶ ፤ ለአፍሪካዊያን የተበረከተ መሪ እና ድርጅት ነው ። በዚህም ምክንያት የ 30 ዓመት የኢህዲግ ምርት የሆነ ካድሬ ፤ በፖለቲካ ዕድሜው ብቻ የጎልማሳ እድሜ የያዘ ጡረተኛ ካድሬ ፤ የድርጅት እድገት ማለት ከኢህዴን ጀምሮ ፦ ብአዴን > አዴፓ > ብልፅግና መድረስ የሚመስለው የቤተ-መንግስት ለማዳ እንስሳ እና ዲፖሎማሲ ማለት ዶላር በኩንታል ተሸክሞ በየ ኢንባሲው በር ላይ ሎቢስት ፍለጋ መዞር ለሚመስለው ደረጃ አንድ ድኩማን ካድሬዎች ተደምረው ከአርበኛ ዘመነ ካሴ እና ከድርጅታችን አ.ፋ.ብ.ን ጋር መወዳደር በፍፁም አይችሉም ።
ከቤታችን ያስወጣን አንኳር ጉዳይ ' አማራ' የሚባል ገናና ማንነት ያለውን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት በቃላት የተዋበ ፀረ-አማራነት ሰነድ ተዘጋጅቶ ይሄ ሰነድ ደግሞ ህግ እና ህገ-መንግስታዊ መዋቅር ተሰርቶለት አሰፈፃሚ አካል ተመድቦለት ላለፉት 60 እና 70 ዓመታት በጋራ አገራችን ውስጥ የአማራን ህዝብ ብቻ ለይቶ መዋቅራዊ የዘር ፍጅት አድርሶበት እንደ ዘር ለመቀጠል ስንጠራጠር ይበቃናል አትግደሉን፣ አታግቱን ፣ አትዝረፉን፣ አታፈናቅሉን ብለን በደብዳቤም በስልፍም ስንጠይቅ ሰሚ አጠን ይባስ ብሎ ሞታችን ከጓሯችን ሲመጣ እንደ ህዝብ ህልው ሁኖ ለመቀጠል ሁሉን ነገር ንቀን ለአማራነታችን ጫካ እንድንወጣ ተገደናል ።
ጫካ በወጣንበት ወቅት ሁሉም ታጋይ ማስታወስ ያለበት ብልፅግና የዋለልንን ሁለት ውለታዎች በፍፁም መርሳት የለበትም የመጀመሪያው ብልፅግና እራሱ ፈርሶ መገኘቱ ነው ። ሁለተኛው ደግሞ ፈርሶም ጭምር ፍላጎቱ የአማራን ህዝብ ማጥፋት ምርጫው ማድረጉ ነው ። ሁለቱም ውለታዎቹ የአማራን ህዝብ በሁለት በኩል የተሳለ ቢላ እንዲሆን አስችለውታል ። በነዚህ ምክንያት ከጥንት አማራ አንገቱ አንድ ነው ብለው የነገሩንን የነ ደጃች ፀሐዩ እንቁስላሴን ሐሳብ በመውሰድ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እልቆቢስ የአማራነት ፅንሰ ሐሳቦች አዳብረን ፣ አንድ ሁኑ የሚለውን የሰማዕቱን ጄነራል አሳምነው ፅጌን ምከረ ሐሳብ አማራ ሲሏችሁ አትሸማቀቁ ከሚለው የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት ጋር ተዋህዶ አመራነትን ራስ-በቅ ሁኖ እንዲቆም መሠረት እና ጣራ ሁኖት ከዚህ እንዲደርስ አድርጎታል። ትውልዱም በሚገባ እያሻገረው ይገኛል ።
ከአሁን በኋላ ' አማራነት ' ሌሎች በእኩልነት ላይ በጋራ ለማደግ እና ለመወሰን ለሚፈልጉ ህዝቦች ሁሉ ከበረዶ የነፃ የሚታይ ፣ የሚዳሰስ እና የሚነገርለት መሠረቱ ብሔርተኝነት ያደረገ ነገር ግን ርዕዮቱ ለሁሉም የሆነ ትግል ለኢትዮጰያውያን እንካችሁ ያለ ትግል ይዞላችሁ መጧል ። ይሄን ትግል የሚመርጥ ለወጣበት ማህበረሰብ የሚቆረቆር ብቻ ነው ።
በመሆኑም መሪያችንም ሆነ ድርጅታችን ተስማምተን የመረጥነው እና የመሠረትነው የአዲሱን ትውልድ አስተሳሰብ በውስጡ የያዘ ተስፋችን ነው ። በአጠቃላይ አዲሱ ትውልድ የአንደኝነቱን ደረጃ ለመጋራት እንጅ ለሁለተኛነት ስለአልተፈጠረ ትብብር እና ችግርን በጋራ ለመፍታት የአንድ ማንኪያ ቅንነቱ ባለበት የተጠበቀ ሲሆን እናንተ ሳትሆኑ እኔ ብቻ ነኝ የምመራችሁም የምወስንላችሁም የሚለን ኃይል ከገጠመው ግን ከምንም ጀምረን ከዚህ ያደረሰውን ትግል ከሁሉም ፀረ-ብልፅግና ኃይሎች ጋር በመተባበር ቤተ-መንግሱት ለመቆጣጠር በትብብር እንድንቀሳቀስ እንገደዳለን ። ለዚህ ደግሞ ሁሉም ነገሮች ምቹ እና ዝግጁ ናቸው ።
መሪያችን እና መሪ ድርጅታችን የሚጠበቀው በኛ አዕምሮ እና በኛ የተባበረ ክንድ ነው ። ስለዚህ ምርጫችን ለህልውናችን በክንዳችን እንጅ የስንዴ ነዶ አይደለም ። የ ስንዴ ነዶው በዝቶ ካስቸገራችሁ ከ 10,000,000 ሚሊየን በላይ የምግብ ዋስትና ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን አድርሱላቸው !
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳስብ ፣ አዲስ ተስፋ!
©ግሩም ምሳሌ
በኤፍራታና ግድም ወረዳ ለሚገኙ የካቢኔ አባላትና ሚሊሻዎች የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ
በኤፍራታና ግድም ወረዳ የምትገኙ የካቢኔ አባላትና የሚሊሻ አመራሮች ሆይ! የታሪክ ተጠያቂነት ከመምጣቱ በፊት ሕዝባዊ ወገንተኝነታችሁን እንድታሳዩ የሚያስገድድ ወሳኝ ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ። ዛሬ በአርሶ አምባ ዘንቦ ቀበሌ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል የሰማይና የምድርን ቁጣ የሚቀሰቅስ ነው። ንጹሐን አርሶ አደሮች በገዛ ቀያቸው፣ በኦሮሞ ሚሊሻዎች ቤታቸው ሲቃጠል፣ ንብረታቸው ሲወድም እና የድካም ውጤት የሆኑ ከብቶቻቸው በጠራራ ጸሐይ ሲዘረፉ እያያችሁ "መንግሥት ያድነናል በሚል ከንቱ ተስፋ በዝምታ መመልከታችሁ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው የክህደት ተግባር ነው።
ነገ የኦሮሞ ብልፅግና አይታደጋችሁም! የኦሮሞ ብልፅግና ያድነኛል" ብላችሁ ከሕዝብ ይልቅ ለሥልጣን ያደራችሁ የካቢኔ ስብስቦች፣ የምትመኩበት ኃይል ነገ ለእናንተ እንደማይቆምላችሁ ልታውቁ ይገባል። ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ እየታረዱ፣ እናቶች ቤት አልባ እየሆኑ እናንተ ከብልፅግና ጎን ቆማችሁ ፋኖን መውጋታችሁ በታሪክ ማኅደር የማይፋቅ ጥቁር ጠባሳ እየጣላችሁ መሆኑን ተረዱ።
ጥብቅ ጥሪ እና ማስጠንቀቂያ
ለሚሊሻዎች መሣሪያችሁን ወደ ወገኖቻችሁ ላይ ከማዞር ይልቅ፣ ዛሬ በደል እየደረሰበት ያለውን ሕዝባችሁን ለመከላከል ባስቸኳይ ከፋኖ ጎን ቁሙ! ለካቢኔ አባላት፦ የሕዝብ እንባ እየፈሰሰ እናንተ በቢሮ ስብሰባና በፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ መሸሸጋችሁ አያድናችሁም። ነገ የታሪክና የሕዝብ ፍርድ ቤት ፊት ስትቆሙ የምትሰጡት መልስ አይኖራችሁም።
ዛሬ በዝምታ የምትመለከቱት በደል ነገ ወደ እናንተ ደጃፍ መምጣቱ አይቀሬ ነው? የሕዝብ ጠላት መሆናችሁን አቁማችሁ የህልውና ትግሉን ተቀላቅላችሁ ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ብትጠቀሙበት አይሻላችሁምን? ከሕዝብ ጎን መቆም ካልቻላችሁ ነገ የታሪክ ተወቃሽ እና ተጠያቂ መሆናችሁን በጽኑ እንድታውቁት እፈልጋለሁ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
የካቲት 13 /05/2018 ዓ.ም
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#ማርቲን ሉተር ኪንግ #ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ጋር የሚያመሳስላቸው ድንቅ ግብራቸው !!
#ማርቲን ሉተር ኪንግ በቀደመው ዘመን አፍሪካ አሜሪካውያን ከባርነት ቢላቀቁም በዘር ላይ ከተመሰረተው ዓይነተ ብዙ መድልዎና ጭቆና ነፃ ለመውጣት እልህ አስጨራሽ ትግልን ጠይቋቸዋል፡፡ ከነዚህ አይነታቸው የበዛ የመብት ማስከበሪያ ጥረቶቻቸው ውስጥ የዋሽንግተኑ ሠልፍ ተብሎ የሚታወቀው ክንውን አንዱ ነበር ፡፡
#ታዋቂው አፍሪካ አሜሪካዊ የመብት ተሟጋች ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ “ሕልም አለኝ” የሚለውን ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ያስገኘላቸውን አነቃቂ ንግግር ያደረጉት በዚሁ አጋጣሚ ነበር፡፡
በዚያን ጊዜ በአሜሪካ አፍሪካ አሜሪካውያኑ ተመርጠውና ተሾመው ለከፍተኛ ኃላፊነት ለመብቃት ይቅርና መሠረታዊ የመምረጥ መብታቸው በሰፊው ይጣስና ይጨፈለቅ ነበር፡፡
በ21 ግዛቶች ከነጭ ጋር መጋባት የሚከለክሉ ሕጐች ስራ ላይ ውለው የነበረ መሆኑ የመድልዎው አንድ ገፅታ ሆኖ ይነሳ ነበር ፡፡ በ2ኛ ደረጃ ዜግነት ከመታየታቸውም በላይ ይፈፀሙባቸው የነበሩ መድልዎች ሰብዕናቸውን የሚፈታተኑ ነበሩ፡፡
አፍሪካ አሜሪካውያኑ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በስነ-ልቦና ይፈፀምባቸው የነበረው ማግለልና ይደርስባቸው የነበረውን ፖለቲካዊ ጭቆና ለማስወገድ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የዘለቀ ትግልና ሙግት አድርገዋል፡፡
የአፍሪካ አሜሪካውያኑን ሁለገብ የመብትና የእኩልነት ትግል ፈር በማስያዝ የመሪነት ሚና ከተጫወቱት መካከል ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር አንዱ ናቸው፡፡
በታሪክ ታላቁ የዋሽንግተን ሰልፍ ተብሎ በሚታወቀው የአፍሪካ አሜሪካዊያኑ ሰልፍ ላይ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ያደረጉት መሳጭ ንግግር ዘመን የማይሽረው ሆኖ ይጠቀስላቸዋል፡፡
ኪንግ እስከ 300 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በተካፈሉበት በዋሸንግተኑ ሠልፍ ያደረጉት ንግግር የትንቢት ያህል ተቆጥሮላቸዋል፡፡
በዚያ ንግግራቸው አፍሪካ አሜሪካውያን ከባርነት ነፃ ካወጣቸው አዋጅ 100 ዓመት በኋላም ነፃ እንዳልሆኑ አነሱ፡፡
ያኔ ላይ ቆመው የወደፊቷ አሜሪካ የዘር መድልዎ ጭቆናና መብት አልባነት የሌለባት እኩልነት የሰፈነባት ሀገር እንደምትሆን ተመኙ፡፡ – “ሕልም አለኝ” አሉ፡፡
ይሄ ንግግራቸው በታሪክም “ሕልም አለኝ” የሚል መጠሪያን አገኘ፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ “ሕልም አለኝ” ንግግራቸው በ20ኛው ክፍለ ዘመን በአሜሪካ ለሕዝብ ከተደረጉ ንግግሮች ሁሉ በመሳጭና አነቃቂነቱ የላቀ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ “የሕልም አለኝ” አላማቸውን በሕንዱ የነፃነት አባት ማህተማ ጋንዲ መንገድ በሰላማዊ መንገድ ዓላማቸውን ለማሳካት ያደረጉት ጥረታቸው ዕውቅናው ገዝፎላቸው ከዋሽንግተኑ ሰልፍ ጥቂት ወራት በኋላ የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸነፊም ነበሩ ፡፡
#ማርቲን ሉተር ኪንግ በአሜሪካን ሃገር የአፍሪካውያን የፖለቲካ ጭቆናንና የሰባዊ መብት ጭፍለቃ በአሜሪካ ሰማይ ስር ሰልፉችንና መድረኮችንም ጭምር ተጠቅመው #ማርቲን ሉተር በአሜሪካ ምድር የአፍሪካውያን መብትና የፖለቲካ ምልክናቸው እንዲከበር ያደረጉና በመጨረሻም የሰባዊ መብት መከብርን በአሜሪካ ምድር ፅፈው የሰላም የኖቬል ሽልማት አሸናፊ ሁነዋል ። አሜሪካም ከዛ በኋላ የዲሞክራሲ ምህዳሯ ሰፍቶና የፖለቲካ የእኩልነት ተሳትፎዎች የገነኑበት ወርቃማ ጊዜ ሁኗል ።
#ኢትዮጵያም በዚህ ዘመን እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ አይነት የዲሞክራሲና የፖለቲካ ጠበብት ሰው ከአማራ ማህፀን ተፈልቅቆ የወጣ ጭቆናንና ባርነት የሚፀየፍ በአብሮነት የሚያምን የአዲሱ ትውልድ አርማና ምልክት የሆነ #አርበኛ ዘመነ ካሴ ተፈጥሯል ። ንግግሩም ትንቢታዊ ተግባሩም ለአፍሪካውያን የነፃነትና የአብሮነት ተስፋን የሚያበራ ባለ ሙሉ ማተብ ነው ። #አርበኛው ለኢትዮጵያውያን የአንድነት እሴት መቀነቻ ፣ የህብረ ብሔራዊነት ዋልታ፣የፍትኃዊነት ማገር የጀግንነት የኖቬል ተሸላሚ አሸናፊና አሻጋር በትውልዱ አእምሮ ፍቅርን እና መተሳሰብን የዘራ ለኢትዮጵያውያን ድንቅ መሪ ነው ።
#የማርቲን ሉተር ኪንግ ተምሳሌ የሰላም ምንጭ #አርበኛ ዘመነ ካሴ ነው ። በመተሳሰብና በመከባበር የነፃነት ግምጃን የሚፅፍ የህብረ ብሔራዊነታችን ምልከትና አምድ ነው ።
#በቃላችን_ተገንተናል!!!
የአማራ ህዝብ የነጻነት ዋዜው ላይ እንቅፋት እንዳይገጠመው ከሰራዊታችን እስከ ድርጅታችን ድረስ እንደ ንስር መታደስ ሁነኛ መፍትሄ ነው።
የተበተነውን መሰብሰብ፣ የደከመውን ማበርታት፣ የተጠራጠረውን ማጽናት፣ ያልገባውን ማስረዳት፣ የራቀውን ማቅረብ፣ ስህተቶቻችን እንዳይደገሙ መገምገምና ማረም ትግላችን የሚጠይቀው ወቅታዊ ጉዳይ ነው።
ስለሆነም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር የምድር ድሮኖች የሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች ከዚህ በፊት በገባነው ቃል መሰረት እንደ ንስር ታድሰን መጠናል።
ክፍት ለማንም በጎነት ለሁሉም ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ህዝባዊ ውይይት አካሔደ!!
ሆኖም ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ከሚያስተዳድራቸው ቀጠና ውስጥ አንዱ ከሆነው ከገተም ጎጆ ውሃ ቀበሌ ከማህበረሰቡ ጋር የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዕዝ፥ የኮር እና የክፍለጦር አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሔዷል። በመሆኑም ዋና ዋና የሚባሉት ነጥቦችን በማንሳት ግንዛቤ ግንዛቤ ማስጨበጥ ተችሏል።
1. የአፋብን ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ያለውን ጉዞና አሁን የደረሰበትን ቁመና በተመለከተ ለማህበረሰቡ ግልጽ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
2. ከድርጅቱ በሚከዱና በሚያፈነግጡ አካላት ላይ ማህበረሰቡ ሊደናገር እንደማይገባ ተገልጿል።
3. ድርጅቱ አስፈላጊውን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ በመውሰድ መስመር የሚያስይዝ መሆኑን ለማህበረሰቡ ገለፃ ተደርጓል።
4. የሚሰበሰበው ሀብት ለማንና ለምን ዓላማ እንደሚውል ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ በሂደቱ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል።
5. በብሔር ግጭት ምክንያት ያልታረሱ መሬቶችን አርሶ አደሩ ያለ ስጋት እንዲያርስ ፋኖ አስፈላጊውን ጥበቃና ድጋፍ እንደሚያደርግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች "ከሁሉ በላይ አንገታችንን ያስደፋን የነበረው የአንድነት አለመኖር ነበር በማለት፣ አሁን የተጀመረው አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። አክለውም ድርጅቱ የተሻለ የፍትህ ስርአትና መመሪያዎችን በማውጣት አካባቢውን እንዲያስተዳድር ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
የካቲት 13 /05/2018 ዓ.ም
የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አቡልታ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይቶችን እያካሄደ ነው።
በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አቡልታ ቀበሌ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ የአማራ ህዝብ ከጉሙዝ ማህበረሰብ ጋር ለዘመናት አብሮ የኖረ ስለመሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፋት ነዋሪወች የብልፅግና አገዛዝ በፈጠረው ሰው ሰራሽ ችግር ምክንያት የመተከል ቀጠና የህዝብ እልቂት መፈልፈያ ሆኖ መቆየቱ እንዲሁም ይህ ጉዳይ በትክክለኛው ግዜ ባለመቋጨቱ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ስንከፍል ቆይተናል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። እንዲሁም ሁለቱም ወገኖች ከሃብት ንብረታቸው ሲፈናቀሉና ውድ የሆነው የሰው ህይወት ሲጠፋ አይተናል፣ ስለሆነም ከዚህ በኃላ የአማራ ህዝብና የጉሙዝ ማህበረሰብን ጨምሮ በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ በአብሮነት በጋራ የመኖር እሴቱን ማስቀጠል ይገባል በማለት አንስተዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙ የማህበረሰብ ተወካዮች በአገዛዙ ሴራ ተፈጥሮ የቆየው ግጭት እንዲቆም እና ሠላም እንዲሰፍን የሁሉም ማህበረሰብ ጉዳይ መሆን እንዳለበት በማመን በአካባቢው የሚኖረው ህዝብ በሙሉ የተፈጠረውን የአንድነት መንፈስ ለመጠበቅ በጋራ በንቃት እንሰራለን ብለዋል።
ውይይቱን በጋራ የመሩት የአፋብን ቴወድሮስ እዝ እና ጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አመራሮችም ለህዝቦች አንድነት በጋራ እንደሚሰሩ ጠቅሰው በየትኛውም ቦታ ተዘዋውሮ ስለመስራት፣ አርሶ እና ነግዶ ለመኖር እንዲሁም ማንኛውንም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አገዛዙን በጋራ ታግሎ ማስወገድ እና በምትኩ ህዝባዊ መንግስት መመስረት እንደሚያስፈልግ በትኩረት አንስተዋል።
በመተከል አካባባቢ ተመሳሳይ ተግባራትን በማከናወን አካባቢውን የሰላም ቀጠና በማድረግ ህዝባችን ማህበረ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴውን በዘላቂነት እንዲከውን ለማድረግ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
+1
የደረስንበት ደረጃ የመጣንበትን የትግል መንገድ ውጣውረድ ሁሉ በሚገባ ላይገልፀው ይችላል። ያለምንም ማቅማማት ግን ህዝባችንን ከየትኛውም ጥቃት መከላከል የሚያስችል የኃይል ግንባታ ላይ የተሳካ ሚናን ተወጥተናል። በዚህ የኃይል መደርጀት ውስጥ የጠላትን ወ ገብ አገ-ዳው ላይ ተሰ ብሮ እንዲ ልወሰወስ ካደረጉት ፊታውራሪዎቻችን፣ የብሬኑ ቄስ፣ በጣት የሚቆጠር ኃይል እየመራ ሙሉ ክፍለጦር እንደቤርሙዳ ዋጥ አርጎ ያስቀረ፣ የዲሽቃ እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ክምር እና ዙ-23 ማርከህ ያሳየኸን፣ ንግግር አዋቂው፣ የውትድርና አቅም ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውንም በቅጡ የተረዳ፣ የትግሉ እርሾዎችና ወጋግራዎች ውስጥ አንዱ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ነው።
ሁለንተናዊ ከትላንት የተሻለ አቅምን እየፈጠርን ወደፊት ለምናደርገው ፈጣን ግስጋሴ አብረን የመከርንባቸውን እያንዳንዷን ሰከንድ ሁሉ ደስ የሚሉኝ ናቸው። ከዚህ የተሻሉ ተአምራዊ ትዕይንቶችን ከአንተ እንጠብቃለን።
ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል መወለድህን አትርፈንበታልና በድጋሜ እንኳን ተወለድህ ወንድሜ! የትግልህን ፍሬ ለማየት ያብቃህ!
♦በእነ ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ መዝገብ ተከሳሾች ለጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል።
እነ ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ (23) በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች የመናገር እና አቤቱታ የማቅረብ መብታቸውን ተጠቅመው የፍትህ ሂደቱን እና በተከሳሾች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እና በደል በዳኞች ፊት በመግለጻቸው ጉዳዩ ከችሎት መድፈር ጋር ተያይዞ በፕላዝማ እንዲከታተሉ ከተደረገ ወራት ተቆጥሯል።
በዚህ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግስትና የፀረ ሽብር ችሎት ውሳኔ ቅር የተሰኙት ተከሳሾች በአካል በችሎት እና በዳኞች ፊት ተገኝተን የፍትህ ሂደቱን ልንከታተል ይገባል በማለት በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማለታቸው እና ሲከራከሩ መቆየታቸው ይታወቃል።
የካቲት 12/2018 በነበረው የፕላዝማ ችሎትም ይግባኝ ሰሚ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ እና የግራ ቀኙን ክርክር መመርመሩን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ከማድረግ አልፎ ነተከሳሾች ጉዳይ ከችሎት መድፈር ጋር መያያዙ ካልሆነ በስተቀር በቴክኖሎጅ እየታገዙ የፍትህ አገልግሎቱን ከማሳለጥ አንጻር የተያዘ አቅጣጫ በመሆኑ በዛው በፕላዝማ ችሎት መቀጠላችሁ አግባብ ነው ሲል መወሰኑን አስታውቋል።
ተከሳሾች በውሳኔው ቅር መሰኘታቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ምንጫችን እንደገለጹት ውሳኔው አገዛዙ ከለመደው ድምፅን የማፈን መመሪያ ፣ አቅጣጫ እና አቋም ጋር ተያይዞ እና ተመሳስሎ የተሰጠ ብይን ነው ብለው እንደሚያምኑ ለማወቅ ተችሏል።
በእለቱ ከተከሳሾች መካከል ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በፍ/ቤቱ ውሳኔ ቅር መሰኘቱን በመግለጽ በታሪክ ፊት እንገናኛለን ማለቱን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በዚሁ መዝገብ ተከሰው ጉዳያቸውን በቂሊንጦ እና በቃሊቲ ማ/ቤት ሆነው እየተከታተሉ ከሚገኙ 23 ተከሳሾች መካከል ጥር 28/2018 በተሰጠው የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል እና የሰነድ ማስረጃ አስተያየት ብይን ከሶስት ዓመታት ገደማ የእስር ቆይታ በኋላ ስድስቱ በነጻ ሲሰናበቱ የሁለት ተከሳሾችን አንቀጽ መሻሻሉ ይታወቃል።
ይሁን እንጅ 15 የሚሆኑ ከእየቤታቸውና ስራ ቦታቸው ተወስደው በግፍ እስር ከከረሙት ተከሳሾች መካከል 15 የሚሆኑትን ከ15 ዓመት ጀምሮ እስከ እድሜ እና ሞት በሚያስፈርድ የሽብር አዋጅ አንቀጽ 3 (2) ሳያሻሽል ተከላከሉ ማለቱ የፍትህ ተቋማት ምን ያህል የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ የጥላቻ እና የማጥቂያ መሳሪያ መሆናቸውን በግልጽ ያመላከተ መሆኑ ተገልጧል።
(አውሎግሶን አንድነት )
ፋኖ በመርሀቤቴ ግንባር ሬማ ከተማ አከባቢ በነበረ የአገዛዙ ኃይል ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ ወታደሮች ተገደሉ!
በዚኸው ቀጠና ከፋኖ እርምጃ የተረፉ በርካታ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ፋኖን መቀላቀላቸውን የመረብ ሚዲያ የጦር ግንባር ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል።
ከሬማ ከተማ በቅርብ ርቀት ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ነው ፋኖ ዛሬ ማለዳ ጀምሮ የአገዛዙ ወታደሮችን 360° በመከበብ ከባድ እርምጃ የወሰደባቸው።
ፋኖ የአገዛዙ ወታደሮች የሰፈሩበትን ካምፕ ጥሶ በመግባት በሚፈፅመው ጥቃት፡ እራሱን ተከላክሎ ማዳን ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል የአፈሙዝና የቦምብ ሲሳይ ሆኖ እየቀረ ይገኛል።
አሳምነው ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ሳንቃ ከተማ ዙሪያ በርካታ የጠላትን ሰራዊት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
አሳምነው ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ወልድያ ከተማ ዙሪያ ከገዶበር እስከ ሳንቃ መግቢያ ወጥሮ አመራር ለማሳለፍ ያሰበን በርካታ የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ማጥቃት በማድረግ ልዩ ስሙ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ በርካታ ሃይሉን በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
በተጋድሎው የአሳምነውን ልጆች ክንድ መቋቋም ያቃተው ጠላት በርካታ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ ቦታውን አስረክቦ ወደ ወልድያ ከተማ ለመሸሽ ተገዷል:: የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ባለፈው ጊዜ እዚሁ ሳንቃ ከተማ መግቢያ ዘንዶ ጅራት የተባለ ቦታ ላይ ተደጋጋሚ ጊዜ ተደምስሶ ዙ23 ጭምር መማረኩ ይታወሳል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
