cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Більше
Рекламні дописи
200
Підписники
+424 години
+37 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ስኬትን ፍለጋ “ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡ ለስኬት የሚኖር ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል፡፡ ለአላማ የሚኖር ሰው ግን ስኬት ያላገኘ ቢመስለውም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል፣ ምክንያቱም አላማ የተሰኘውን የስኬቶችን ሁሉ ስኬት በእጁ ጨብጧልና ነው፡፡ “የምትወደውንና መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፣ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው” የሚለው አባባል እውነት ነው፡፡ ስኬትን ፍለጋ ከአላማህ ውጪ የሆነን “ታላቅ” ነገር ከማድረግ፣ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል፡፡ From Dr.Mihrat Debebe በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇 https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
Показати все...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Repost from Dr. Eyob Mamo
ከአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር (“Trauma Bonding”) የመላቀቅ እርምጃዎች? 1. ችግሩ እንዳብን አምኖ መቀበል 2. የግል ቀይ መስመርን ማበጀት መማር 3. ከሰዎቹ ውጪ መኖር እንደምንችል ራስን መሳመን 4. የግል ሕይወት እድገት ላይ ማተኮር 5. የጤንነት አደጋ ላይ ከደረሰ መለየር 6. ለሰወቹ ስሜት ምንም ሃላፊነትን እንደሌለን መገንዘብ 7. ለስላሳ ግን ጠንካራ መሆን 8. ስሜታዊ በመሆን አቅርቦት አለመስጠት 9. እርዳታን መፈለግ ከዚህ በታች የቀረበላችሁን የቲክቶክ ሊንክ በመጫንና በመመልከት ራሳችሁን አንቁ! ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ለመረጃው @DrEyobmamo ቴሌግራም inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Показати все...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

10 አስገራሚ የማንበብ ጥቅሞች For more : @Bemnet_Library
Показати все...
ክርስቶስ የእውነተኛ ፍቅር ምሳሌ ነው በዓለማችን ላይ ብዙ ፍቅሮች አሉ ማለቴ ፍቅር የሰው ስም ሳይሆን የፍቅር አይነቶች ማለቴ ነው፡ እና ሁሉም ፍቅር መጀመሪያና መጨረሻ አለው ነገር ግን የሁሉም ፍቅሮች ባለቤትና መሠረት እንድሁም መነሻና መድረሻ ራሱ ፍቅር የሆነው የኢየሱስ ፍቅር ብቻ ነው ደግሞ የኢየሱስ ፍቅር መለኪያ ምዛኑ ምንም ሳይሆን ያው እንድሁ የሆነ ፍቅር ነው ርኅራኄ ነው ከዚያ ውጪ ምንም!! የሰው ልጆች የፍቅር ምዛኑ ዘር፣ ጎሳ፣ መልክ፣ ቀለም፣ሃብትና ዝና: ብቻ የተለያዩ ነገሮች ልሆኑ ይችላሉ ነገር ግን እነዚያ ነገሮች ሁሉም ገደብ አላቸው። መልክ ቢሆን ይጠወልጋል፣ዘር ቢሆን ይክዳል፣ሃብት ቢሆን ያልቃል፣ዝናም ቢሆን ይረግፋል፡ አዎ ሁሉም ነገር ዛሬ ትልቅና ግርም የሚለን ነገር ሁሉ ለጊዜው ነው በጊዜው እርፍ ይላል። የማያልቅ አንድ አለ፤ የዘላለም ፍቅር የሆነው ኢየሱስ፣ እንግዲህ እኛ እርስ በራሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እውነተኛ ፍቅር ምንጩ ቅንነት ነው፣ ትህትና ነው፣ በጎነት ነው፣ ደግሞ መሠረቱም በልብ እንደመሆኑ ሁሉንም ሰው ይወዳል እናም ፍቅሩ ራሱ በርኅራኄ የተሞላ ነውና ብዙ ጊዜ በቸርነትና በሥጦታ ይገለጣል። እኛኮ ክርስቶስ ለኔ ርቃኑን ተሰቀለልኝ እያልን እንደመጣለን ግን በአጠገባችን የታረዘውን #ወንድም:ክርስቶስ አንመለከትም ደግሞም ከጎረቤት እስከ ጎዳና ዳር ብዙ ክርስቶሶች ተርበው ተጠምተው  እያየን አሯ ክርስቶስ ለኔ ነው የተጠማው እያልን ከንፈችንን እንሞጥጣለን!! ለነገሩማ ኢየሱስ እኮ መከራ የተቀበለው ፍቅሩን አሳይቶልን እኛም ለሌሎች ፍቅር እንድናጋራላቸው ዘንድ ነው። ሌላ ደግሞ በፍቅር ውስጥ ይቅርታ ትልቅ ስፍራ አለው እኛ ግን ይቅርታን በወጉ አናቅም ማለት ኢየሱስ በመስቀል ምህረት ሲያደርግልን እና ሲያስደርግልን ምንም ድርድርና ክርክር አላደርገውም ዛሬ ዛሬ ይቅርታ በማስፈርትና በተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች እየተደረጉ ይገኛል። ታድያ ፍቅርን ከይቅርታ ነጥሎ ማያት ከአይን ብሌን ቆብውን ማንሳት ነው!! ስለዚህ ሁለቱም የተጣመሩ ናቸው። በአጠቃላይ ፍቅራችን ያለግብዝነት ይሁን የሚወደንን ብቻ መውደድ ጨው ላይ ሱካር መጨመር ነውና ደካሞችን የተጣሉትንም እንቅረባቸው የልባችንን ማዕድ እናጋረው❤❤ share share🙏 God be we with us🙋💓💓❤ xuma hosehe🙏🙏❤❤ Share share 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
Показати все...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

እንፋሎት ነን " ነገ የሚሆነውን አታውቁምና፥ ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።”— ያዕቆብ 4፥13-14        ስለነገ በእርግጠኝነት የምናውቀው ነገር ቢኖር አለማወቃችንን ነው። ስለ ነገ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች መሀል አንዱም ዋስትና አይሰጠንም። ነገ በእግዚአብሔር የተጠቀለለች እርሱ ብቻ ያያትና የሚያውቃት ስጦታ ናት።      ህይወት ትነት መሆኑን አውቆ መኖር ከመኖር የተለየ ነው። እዚህ ያሉት የሚታዩት፣ ልትይዛቸው የምትጓጓላቸው ነገሮች ሁሉ ያልፋሉ። የሚጸናውን ነገር አጥብቀህ መያዝ አለብህ።  አስፈላጊ የሆነውን ነገር አጣጥሙ። ህይወት አጭር ናት፤ ዘላለማዊነት ረጅም ነው። እንደዚህ መኖር አለብን።       የምወዳቹ እህት እና ወድሞቼ ዛሬ ያዝኩት የምትሉት፣ አለኝ የምትሉት ገንዘብ ቢሆን ቁመና፣ ጤና ቢሆን ስራ፣ ሰው ቢሆን ንብረት ይቅርና እኛ ራሱ ትነት ነን። አሁን ታይተን በኋላ የምንሰወር፤ ነበሩ ለመባል ቅርብ የሆንን ነን። ታዲያ የማይዘልቅ ሐብት፣ የማይከርም ንብረት፣ ዘላለም የማያስቆጥር እውቀትና ሙያ ይዞ መኩራት ልክ አይደለም። እንኳን ያለን ነገር ሕይወታችንም አታኮራም።       ሕይወትን እንደ እንፋሎት ስትቆጥር ከሰው ጋር በፍቅር እንጂ በጸብ ለመኖር አትከጅልም፤ ከሰው ጋር በትህትና እንጂ በትዕቢት ለመኖር አታቅዱም። አዎ ሕይወት እንፋሎት መሆኗ ሲገባን ክርስቶስን እያሰባቹ ከሰውም ከእግዚአብሔርም ጋር በሰላም ትኖራለቹ።       ይህ የያዕቆብ ጥቅስ ልባችሁን ዘልቆ እንዲገባ መንፈስ ቅዱስ እንዲገልጥላችሁ እጸልያለሁ። ሕይወት በጭጋግ የተመላች እንፋሎት ናት። ሁሉ ለመጥፋት የሚቸኩል ነው። እዚህ ያለን ጊዜ ከዘላለም ህይወት አንጻር እጅግ ትንሽ ናት። ዛሬን በደንብ ልንወዳት፣ ዛሬን በጥሩ ሁኔታ እንድንኖር፣ ዛሬን በፍጹም ልባችን፣ በፍጹም ሃሳባችን፣ በፍጹም ኃይላችን እግዚአብሔርን ልንወድ ይገባል። ዛሬ በአካባቢያችን ያሉትን ሰዎች በደንብ ልንወድ ይገባል።       ዛሬ በገንዘባችን ላይ ልንሰለጥንበት ለወደቁት ረድተነው፣ ለተራቡት አጉርሰነው ሰጥተን እንጂ እኛ የማንበላውን ገንዘብ ለሌሎች በባንክ አስቀምጠን ማለፍ የለብንም። አልበላም አላበላም፤ አልጠጣም አላጠጣም ብላችሁ በባንክ የቆጠባችሁት ገንዘብ ስታልፉ የሚያዝበት ያልቆጠበው ያላጠራቀመው ሰው ነው። ሕይወት እስካለች ባላችሁ ነገር እዘዙበት እግዚአብሔርን የሚያስደስት ስራ ሰርታችሁ እለፉበት።      ክርስትና የመስጠት መርህ እንጂ የመቆጠብ መርህ አይደለም። መቆጠብ መርሁ ቢሆን እግዚአብሔር ያለውን አንድያ ልጁን በቆጠበው ነበር። ክርስትና ግን መርሁ መስጠት መቆረስ ነውና ያለውን ሰጥቶ ያልረካው እግዚአብሔር ልጁንም ሰጠን። ታዲያ በልጁ ሕይወት ያልሳሳ አምላክን እየተከተልን ገንዘብን ለምስኪኖች መቆጠብ፤ ማበረታቻ ቃልን ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች መንፈግ ምን የሚሉት ህይወት ነው።       ወዳጆቼ የውሸት እየኖርን የእውነት እንዳንሞት እንጠንቀቅ።👈
Показати все...
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን !! በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብና የመረዳዳት እንድሆንላችሁ እንመኛለን ። እንዲሁም በበዓሉ ወቅት ከምንበለውና ከምንጠጠው ሁሉ ለሌላቸው እንድናቆርስላቸው በታላቅ ፍቅር ጥሪ ለማስተላለፍ እንወዳለን ። አንድነት ።።።መልካም በዓል ።።።።በአማ ከአንድነት በአማ 🙏🙏❤ ከዋና ጽ/ቤት join us ..share..comment https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
Показати все...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለን።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

👍 1
👍 1
#የሚደንቅ ቀን በትላንትናው ዕለት አንድነት በጎ አድራጎት ማኀበር የስቅለትና የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ አባላቱ ልዩ የሕብረት ጊዜ ማሳለፍ ችለዋል። በዕለቱም ደማቅ ጊዜ ያሳለፉ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ ጥቂት እንግዶችና ከ90% በላይ የማኀበሩ አባላት መገኘት ችለዋል ። በፕሮግራሙ ዝግጅት ላይ የተካተቱ ነገሮችን ለማስታወስ ያክል ፦የውይይትና የስብሰባ ጊዜ፣ የአባላት እርስ በርስ የመተዋወቅ ጊዜ ፣ ስለ ማኀበሩ ያላቸውን ቦታ በቃላት የሚገልጽበት ጊዜ ፣ ደግሞ ለማኅበሩ እድገት ትልቅ ሚና ለመጫወት ቃል የመግባት ጊዜ ፣ የመመካከርና የጭውውት ጊዜ እንዲሁም አዝናኝና አስተማሪ ጥያቄዎችን የመጠያየቅ ጊዜ እያለ ፍጻሜውን በጋራ የphoto ጊዜ በማድረግ ተጠናቋል ። በአጠቃላይ ከሚባለው በላይ #አስደማሚ ጊዜ እንደነበር የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በግልጽ አስታያየት መስጠት ችለዋል ። የፕሮግራሙ ክፍል ሁለት በቀጣይ ወር ከልዩ #ሥልጠና ጋር የሚካሄድ ሲሆን ከዚያ በፊት ደግሞ በመጪው በትንሣኤ በዓል ዕለት በአንዲት #ተፈናቃይ እናት ቤት በዓልን አብሮ ለማሳለፍ ታቅዶ እየተዘጋጀበት ይገኛል ። ስለሆነም ከአሁን ጀምሮ የማኀበሩ አባል በመሆንም ሆነ ስፖንሰር በመሆን በዚህ ሥራ ላይ የበኩላችሁን ትብብር ለማድረግ እንድትችሉ በታላቅ ፍቅር ጥሪ እናቀርባለን ። ከማኅበሩ ዋና ጽ/ቤት https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
Показати все...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለን።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Repost from N/a
እንደምን ከረማችሁ ወዳጆች ከነገ ጀምሮ ስለ ሕማማት ሳምንት በጣም ምገራርሙ ትምህርቶችን እንከፋፈላለን በደምብ ለመከታተል ሞክሩ ! ደግሞ ወዳጆቻችንን በመጋበዝ እንድንተባበር በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ የሕማማት ሳምንት ትምህርት በተላይ ጌታችን ኢየሱስ በሕይወቱ ማብቂያ ላይ የተናገራቸው የኑዛዜ ንግግሮችም ስለሆኑ ትኩረት ልሰጥበት ይገባል ። እንግዲህ በትዕግሥትና በትህትና እንትጠብቁኝ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ ። I love so much in the chirst name Join us https://t.me/ZOEEternallife Join us https://t.me/ZOEEternallife
Показати все...
ZOE (ዞዊ) Eternal life

የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላ 3:24 ማደግህ በነገር ሁሉ እንድገለጥ ይህን አስብ ፥ ይህንም አዛወትር... ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። 1ጢሞ 4:15-16 @ዞዊ ማለት የእግዚአብሔር ሕይወት ወይም ዘላለማዊ ሕይወት ማለት ነው ። መገኛ ምንጩም የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤውን በማመን ነው ።