cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Abbay News™

Addisababa, Ethiopia🇪🇹

Більше
Рекламні дописи
26 415
Підписники
+40724 години
+3 4307 днів
+11 85130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

➡️Join @Abbay_News1   🔔
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው ስደተኛ በአሜሪካ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ አሸናፊ ሆነ ከካንሰር ህመም ጋር እየታገለ ያለው የላኦስ ተወላጁ ስደተኛ በአሜሪካ 1.3 ቢሊዮን ዶላር የሎተሪ ጃክፖት አሸናፊ ሆነ።የ46 ዓመቱ ቼንግ ሳፋን ፓወርቦል በተሰኘው የሎተሪ ጃክፖት ጨዋታዎች እድለኛ መሆኑን የውድድሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።ቼንግ ዕድለኛ ያደረገውን የሎተሪ ቲኬት የገዛው በኦሪጎን ግዛት በፖርትላንድ ከተማ ከሶስት ሳምንት በፊት ነበር። ግለሰቡ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ግብር ተቀንሶ 422 ሚሊዮን ዶላር ያህል የሚደርሰው ሲሆን ይህንንም ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር እኩል እንደሚካፈሉ አስታውቋል።“አሁን ቤተሰቤን አንበሻብሻለሁ። ለራሴም ጥሩ ዶክተር መቅጠር እችላለሁ” ሲል አስረድቷል።“ህይወቴ ተቀይሯል” ሲል ለሲቢኤስ አጋር የሆነው ኮይን የተናረው ቼንግ አምላኩ እንዲረዳው በጸሎት መማጸኑን አስረድቷል። ቼንግ አክሎም ለቤተሰቡ ሲያልሙት የነበረውን ቤት መግዛት እንደሚፈልግ እና ፓወርቦል የሎተሪ ጃክፖት መጫወቱን እንደሚቀጥል ተናግሯል።“እንደገና እድለኛ ልሆን እችላለሁ” ሲል ተስፋውን አስረድቷል።ላለፉት ስምንት ዓመታት በኬሞቴራፒ ህክምና ውስጥ ያለው ቼንግ ከባለቤቱ እና ጓደኛው ጋር በመተባበር ከ20 በላይ የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶችን መግዛታቸውን ተናግሯል።የሎተሪ ቲኬቶቹ አሸናፊ ቁጥሮች 22፣ 27፣ 44፣ 52፣ 69 እና ቀይ ፓወርቦል 9 ነበሩ ተብሏል። በፓወርቦል ታሪክ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የገንዘብ ሽልማት መሆኑ የተነገረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በከፍተኛ ደረጃ የተቀመጠው በ2022 አሸናፊ የነበረው የ2.04 ቢሊዮን ዶላር ሽልማት ነው።የፓወርቦል የሎተሪ ቲኬቶች በ45 አሜሪካ ግዛቶች፣ በኮሎምቢያ እንዲሁም በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ የቨርጂን ደሴቶች እያንዳንዳቸው በ2 ዶላር ነው የሚሸጡት።የሎተሪ ቲኬቶች ዋጋ መጨመሩ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላር ሽልማቶች በጣም የተለመዱ ሆነዋል።
Показати все...
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች መቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ፡፡ ለበጎ አድራጎት ድርጅቱ ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ ተደርጓል፡፡          ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የሚመራው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ቡድን የመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልን በመጎብኘት ግምታቸው ከ1.9 ሚሊዮን  ብር የሚውጡ የምግብ ዘይት ፣  ኮፒውተሮች ፣ ፕሪንተሮች፣ ቴሌቪዥኖች እና ልዩ ልዩ ለፅህፈት አገልግሎት የሚውል ቁሳቁሶች  ፣ የንፅህና መጠበቂያ ሶፍት፣ ሳሙና እንዲሁም ልዩ ልዩ አልባሳትና ጫማ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ለክቡር ዶክተር አቶ ቢኒያም በለጠ በአዲስ አበባ ፖሊስ ስም ድጋፉን አስረክበዋል፡፡   መቄዶኒያ እየሰራ ያለውን ተግባር ኮሚሽነር ጌቱ አድንቀው አዲስ አበባ ፖሊስም ከመደበኛው ተልእኮዎቹ ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ኮሚሽነሩ  ገልፀው ዛሬ ለመቄዶኒያ ያደረግነው ድጋፍ ይህንኑ የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ ፖሊስ ከመቄዶኒያ እና ከሌሎች አገር በቀል መርጃ ማዕከላት ጋር እየሰራ ያለውን ስራና እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ  ዶክተር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት መቄዶኒያ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ልዩ ልዩ ድጋፎች ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰው ዛሬ በተደራጀ መልኩ  መጥተው ማዕከሉን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ለተደረገውም ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከፍተኛ አመራሩ በማዕከሉ የሚከናወኑ የግንባታና ልዩ ልዩ የእጀ ጥበብ ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን ከርክክቡ በኃላ የተገኙ አረጋውያንም በተረጂዎቹ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
" ፖሊሲያችንን ግልጽ አድርገናል ፤ ቡድኑን ለመቀላቀል ወስነናል " - ማሌዢያ ማሌዢያ የ ' BRICS+ ' ን ለመቀላቀል እንደምትፈልግ አሳውቀች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስብሰቡን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው። የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ከአንድ የቻይና ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ ሀገራቸው የBRICS+ ቡድንን ለመቀላቀል እንደምትፈልግ ገልጸዋል። ስብሰቡን የመቀላቀል ሂደት በቅርቡ እንደምትጀምር አሳውቀዋል። " ፖሊሲያችንን ግልጽ አድርገናል ፤ ውሳኔያችንንም ወስነናል። በቅርቡ መደበኛውን ሂደት እንጀምራል " ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የአሜሪካን ዶላር በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ያለውን ከፍተኛ የበላይነት በመተቸት የሰጡትን አስተያየትም ደግፈዋል። በባለፈው አመት ላይ ማሌዢያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደነበራት  ነገር ግን ገንዘቡ አሁንም እንደተመታ እንደሆነ አመልክተዋል። " ለምን ? ከ2ቱ አገሮች የንግድ ሥርዓት ውጪ የሆነና በአገሪቱ ውስጥ ካለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አንፃር የማይገናኝ ምንዛሪ የበላይ ለመሆን የበቃው ለዓለም አቀፍ ምንዛሪነት ስለሚውል ብቻ ነው " ብለዋል። በቅርብ ቻይናን ጎብኝተው የነበሩት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ሀገራቸው ቱርክ የBRICS+ ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ሲሉ መልሰው እንደነበር ይታወሳል። BRICS+  🇧🇷 የብራዚል 🇷🇺 የሩስያ 🇮🇳 የሕንድ 🇨🇳 የቻይና 🇿🇦 የደቡብ አፍሪካ 🇪🇹 #የኢትዮጵያ 🇮🇷 የኢራን 🇪🇬 የግብፅ 🇸🇦 የሳዑዲ አረቢያ 🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስብሰብ ነው።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"መንግሥት ተደጋጋሚ ጥቃትና ከፍተኛ ጫና እያደረሰብን ነው" 12 የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች በመንግስት በኩል እየተፈጸሙ ያሉት "ክልከላዎች፣ ጫናዎችና ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መሆናቸውን" አስራ ሁለት ሀገር በቀል የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ትላንት ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ድርጅቶቹ "ጠንካራ የውትወታ ሥራን ከመሥራታችን ጋር በተያያዘ በአንዳንዶቻችን ላይ ከመንግሥት በኩል ተደጋጋሚ ጥቃትና ከፍተኛ ጫና እየደረሰብን ይገኛል" ሲሉ መግለጻቸውን ዶቼ ቨሌ ዘግቧል። በአንዳንድ የድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች፣ የቦርድ አመራሮችና ሠራተኞች ላይ "ከፍተኛ የሆኑ ማስፈራሪያዎች፣ ዛቻዎችና ጫናዎች ተፈጽመዋል አሁንም እየተፈጸሙ ይገኛሉም” ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብት፣ሴታዊት፣ ትምራን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ሕብረትን ጨምሮ አቋማቸውን በጋራ ያወጡት ድርጅቶች ደረሰብን ባሏቸው "ጫናዎች ምክንያት የሲቪል ምኅዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ ይገኛል" ብለዋል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#AddisAbaba " ... የቤት አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ ነው " - ቤቶች ልማትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። ቢሮው ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ120 ወረዳዎች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጿል። በቀሪ የ15 ቀናት ጊዜ ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ወረዳዎች በማቅናት ምዝገባ እንዲያካሂዱ አሳስቧል። አከራዮች የውል ስምምነቱን ሳይፈጽሙ እስከ 3 ወር ድረስ ከቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ ይደረጋል ተብሏል። ይህንን ስራ ብቻ የሚያከናውን ቡድን መቋቋሙንም ቢሮው ገልጿል። የውል ምዝገባው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በምሽት ጭምር እየተሰጠ እንደሆነ ያመለከተው ቢሮው ፥ " የተሰጠው የምዝገባ ጊዜ በቂ በመሆኑ የቀን ጭማሪ ላይኖር ይችላል " ሲል አሳውቋል። ቢሮው በመግለጫው ከመጋቢት 24 ጀምሮ የሚደረግ የቤት ኪራይ ጭማሪ እና ውል ማቋረጥ ክልክል እንደሆነ እና ተቀባይነትም እንደሌለው አመልክቷል። መንግስት ጥናት በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ አሳውቋል። አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ እንደሚሆን አስገንዝቧል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ethiotelecom #Oromia በኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን በጸጥታ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ 87 የሞባይል ጣቢያዎች ተጠግነው በ42 ወረዳዎች የሚገኙ 83 ቀበሌዎችና ከተሞች ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት እንዳገኙ ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል። ተቋሙ ፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት በምዕራብ እና በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሩ ጉዱሩ እንዲሁም ቄለም ወለጋ ዞኖች የሚገኙ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራ ሲሰራ እንደነበር ገልጿል። የኃይል አቅርቦትን ባላገኙ አካባቢዎች ላይ ጀነሬተር ፣ ነዳጅና አስፈላጊ ግብዓት በማሟላት የጥገና እና የማሻሻያ ስራዎች በማጠናቀቅ  87 የሞባይል ጣቢያዎችን አገልግሎት ዳግም በማስጀመር በ42 ወረዳዎች የሚገኙ 83 ቀበሌዎች እና ከተሞች አገልግሎት እንዳገኙ አሳውቋል። እስካሁን በተከናወኑ ስራዎች ፦ - በሆሩጉዱሩ 18 የሞባይል ጣቢያዎች፣ - በምዕራብ ወለጋ 19 ጣቢያዎች፣ - በቄለም ወለጋ 17 ጣቢያዎች፣ - በምስራቅ ወለጋ 12 ጣቢያዎች - በምዕራብ ሸዋ 1 ጣቢያ ጥገና ተደርጎ አገልግሎት ማስጀመር እንደተቻለ አመልክቷል። በተጨማሪ ከዚህ በፊት በተሟላ መልኩ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ አጠቃላይ 20 የሞባይል ጣቢያዎች አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን በተቀሩት አካባቢዎችም ላይ ጥገናው እንደሚቀጥል አሳውቋል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከእንግዲህ መንግስት እንደፈለገ ገንዘብ አይወስድም‼️ ብሄራዊ ባንክ ለመንግስት ቀጥታ ብድር እንዳይሰጥ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ ባለፉት ዓመታት በመቶ ቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ከብሄራዊ ባንክ የወሰደው መንግስት ከዚህ በኋላ እንደፈለገ የሚበደርበትን አሰራር የሚከለክል አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው መንግስት የከፋ ችግር ካልገጠመው በቀር ከብሄራዊ ባንክ ያለገደብ የሚበደርበት አሰራር ከዚህ በኋላ በህግ የተከለከለ ይሆናል። ይህ ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተካቶ የቀረበ ሲሆን በረቂቅ አዋጁ ክፍል አምስት በብሔራዊ ባንክ እና በመንግስት መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ባተተበት ምእራፍ ውስጥ ተካቷል። “በአዋጁ በግልጽ ካልተፈቀደ በስተቀር ብሔራዊ ባንክ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለፌዴራል ; ለክልል ; ለማንኛውም የታችኛው የመንግስት የአስተዳደር እርከን ፣ የከተማ አስተዳደር ወይም የመንግስት ተቋም ብድር መስጠት አይችልም ” ይላል። (ዋዜማ)
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በቤት ኪራይ ውድነት የተቸገሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ በተማሪዎች ዶርም “በጊዜያዊነት” እየኖሩ ነው ተባለ ትግራይ ክልል በሚገኘው መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑን ገለጹ። የዩኒቨርስቲው መምህራን በክልሉ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል።    የዩኒቨርሲቲው መምህራን “የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል” የሚሉ ማመልከቻዎችን ለተቋሙ ማስገባት የጀመሩት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ቢሆንም፤ ካለፈው ሶስት ወር ወዲህ ግን በርካታ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለተቋሙ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ ማቅረባቸው ተነግሯል። መምህራኑ ለዩኒቨርሲቲው ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተገደዱት፤ በጦርነት ወቅት ሳይከፍሉ የቀሩትን “ውዝፍ የቤት ኪራይ” አሁን እንዲያመጡ እየተጠየቁ በመሆኑ እና በክልሉ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ነው ብለዋል።
Показати все...
💯 2👍 1😱 1😘 1
የፐርፐዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ የመንግስት አካል ባሏቸው ሰዎች 200 ሚሊየን ብር ጉቦ መጠየቃቸውን ተናገሩ። የደረሰብንን በደል ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ እንዲያዩልን እና ይህንን ገንዘብ አልከፍልም በማለቴ በደረሰብኝ ማስፈራሪያ  ተገድጄ ከሀገር ወጥቻለው ብለዋል ፐርፐዝ ብላክ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዉስጥ የተቋሙ ሁሉም የባንክ ሂሳቦች መዘጋታቸውን ባለፈው ሳምንት በሰጠው መግለጫ መግለፁ ይታወሳል።የፐርፐዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ በኦንላይን ከአሜሪካ በሰጡት መግለጫ በመንግስት በደረሰባቸው ግፍ ከሀገር መሰደዳቸውን  እና እንደሌባ ያልፈፀሙት ክስ እንደተመሰረተባቸው አስታውቀዋል። እንደ ዶክተር ፍሰሀ ማብራሪያ የተከፈተባቸው ክሶች ውስጥ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ፅንፈኛ ቡድንን በመደገፍ፣በወንጀል የተገኘን ገንዘብ በማዘዋወር፣ሙስና እና በዘር እና በሀይማኖት ሽፍን የሚሉ ክሶች አንደሚሉ ገልፀዋል። ይህክስ የተመሰረተብኝ ያሉት አቶ ፍሰሀ ከመንግስት ካላቸው አካላት 200 ሚሊየን ብር ጉቦ ተጠይቄ አልከፍልም በማለቴ ነው ብለዋል።የተጠየቁትን ጉቦ ከሰጠው በባንክ አካውንታቸው ላይ የተጣለው እግድ እንደሚነሳ ምንም አይነት ስራ መስራት ቢፈልጉ ከመንግስት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም ቁጭ ብለው እንዲወያዩ እንደሚያመቻቹላቸው እና አብረዋቸው እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል። ጉቦ እንድከፍል የተጠየኩበት የስልክም ሆነ የተለያዩ ማስረጃዎች እጃቸውም ላይ እንዳለ ገልፀዋል።ዶክተር ፍሰሀ አሁን ከሀገር የወጣሁትም እስርንም ፈርቼ ሳይሆን በህይወቴ ዛቻ እና ማስፈራራት ስለደረሰኝ ህግ በሚከበርበት ሀገር ሆኜ እታገላለው ብዬ ነው ብለዋል።ዶክተር ፍሰሀ የዚህ ዋና መነሻ ብለው የሚያስቡት ተቀማጭ ገንዘባችን የነበረበት አዋሽ ባንክ በቂ ወለድ ሊሰጠን ባለመቻሉ ገንዘባችንን የተሻለ ወለድ ሊሰጠን ወደተዋዋልነው ሕብረት ባንክ ለመዘዋወር ጥረት ስናደርግ መሆኑን እና ገንዘባችንን አግተው ማስፈራራት መጀመረቻውን ጨምረው ተናግረዋል። ዶክተር ፍሰሀ አሁንም በሀገሬ ተስፍ አልቆርጥም ለሀገሬ እና ለወገኔ መስራቴን አላቆምም ተስፍም አልቆርጥም ከአላማዬም ዝንፍ አልልም ብለዋል።ዶክተር ፍሰሀ በማጠቃለያቸው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይን ለማግኘት ከዚህ በፊት ጥረት ቢያደርጉም አለማሳካቱን አስታውሰው አሁንም ይህ የተጠየቅነውን ጉቦ እርሳቸው ያቁታል ብለው እንደማያስቡ ሆኖም እርሳቸው በሾማቸው ሰዎች መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የደረሰብንን ግፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተረድተው እንዲያነጋግሩን የደህንነት የሰላም እና ሰባአዊ መብታችንን እንዲከበር እንዲያደርጉ ለዚህ መፍትሄ ከእሳቸው ውጭ ማንም እንደማይፈታው ገልፀው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።ዶክተር ፍሰሀ ከአሁን በፊት የዩኒቲ ዩንቨርስቲ ባለቤት በነበርኩበት ግዜ ተመሳሳይ የጉቦ ጥያቄ ገጥሞኝ ተማርሬ ከሀገር ብወጣም የአሁኑ ግን በብዙ መንገድ ግፍ የበዛበት እንደሆነ ተናግረዋል። ፐርፐዝ ብላክ በእስካሁን በታገቱባቸው የባንክ አካውንቶች የተነሳ 1 ሺህ 600 ገደማ ለሚደርሱ የቋሚ ሰራተኞቹ ደሞዝ የመክፈል አቅም እንዳጣ አስታውቋል።ዶክተር ፍስሃ የአክስዮን ባለቤቶችን እና ለሰራተኞቻቸው ባስተላለፍት መልክት ይህን ግዜ እናልፈዋለን ከዛሬ ጀምሮ ፍትህ ለፐርፐዝ ብላክ የሚል ዘመቻ የተጀመረ ሲሆን ሰራተኞች ያለደመወዝ መቆየት ስለሚቸገር መርዳት የሚፈልግ በኪዋር ኮድ እርዳታ በመላው አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መሰብሰብ መጀመሩን ፐርፐዝ ብላክ ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። via:ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👌 2👍 1😱 1💯 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.