cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዝክረ ቅዱስ እስጢፋኖስ

ይህ ቻናል ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን በመዘከር ቃለ እግዚአብሔርን እንድንማማርበት የተከፈተ ቻናል ነው።

Більше
Рекламні дописи
1 062
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...
MK TV || ቅዱስ ቂርቆስ || የቅዱስ ቁርባን ጥቅሞች

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ብዙዎቻችን በምንወዳቸው ሰዎች የልደት ቀን ፍቅራችንን በውብ ቃላት ሰድረን ጽፈን እንልክላቸዋለን፥ መልካም ምኞታችንን እናዥጎደጉድላቸዋለን። ታዲያ የመወለዷ ደስታ ለወላጆቿ እና ለወዳጆቿ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ዘር በሙሉ ለሆነው ለእመቤታችን ልደት ምን ልትጽፉላት አሰባችሁ? ምን ልትሏትስ ትወዳላችሁ? ልደቷ ልደታችን ለሆነው ንጽሕት ምኞታችሁ ምንድነው? እኔ ውለታዋ የከበደኝ ልጇ የተወለደችውን ወላዲተ አምላክ በልደቷ ስዕል ፊት ቆሜ እያየኋት ይህንን ጻፍኩላት: "የተወለድሽ እናት ሆይ ለእኛ የተሾሙልን ብጹዓን ሊቃነ-ጳጳሳት በሥዕልሽ ፊት ቆሙ፥ ለመኑሽም አላፈሩም፤ ቅድስት ሆይ አባቶቻችን ካህናት በሥዕልሽ ፊት መልካም መአዛ ያለውን ዕጣን አጠኑ ፥ ነግህ ሰርክ ሳይሉ ለምሥጋናሽ ተፋጠኑ አላፈሩም፤ ድንግል ሆይ ከእኛ ፊት ሐዘናቸውን እየደበቁ አባቶቻችን በደጀ ሰላምሽ በሥዕልሽ ፊት አነቡ አንቺም አጽናናሻቸው፤ ማርያም ሆይ በእንብርክክ እየዳሁ እጃቸውን ዘርግተው እናቶቻችን በደጃፍሽ ተማጸኑሽ፥ የእናት ሆድ አያስችል ነውና ብሒሉ የለመኑትን ከሆድሽ ፍሬ ዘንድ አሰጠሻቸው፤ እኔም ይኸው በመቅደስሽ በሥዕልሽ ፊት ቆምኩ። የጳጳሳቱ የረቀቀ ክህነት፣ የካህናቱም ትጋት፣ የአባቶቼ ፍቅር፥ የእናቶቼም የዋሃት የለኝም፥ አንቺን ግን ተስፋ አደርጋለሁ። ሕጻን እና ሽማግሌ፥ ድሃና ሀብታም ብሎ የማይለይ የተአምርሽን በረከት ለእኔም ለባርያሽ ታደርጊልኝ ዘንድ በሊቃውንቱ ውብ ዜማ "በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም" ብዬ ዘወትር በመቅደስሽ አውጃለሁ።" ንጽሕት ሆይ ልደት የለንም እኛ፥ ልደትሽ ነው ልደታችን!! ዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ
Показати все...
Repost from ግጻዌ
4.53 KB
#የካቲት_12 መዝሙር ዘዐቢይ ፆም ዘዘወረደ ፩ኛ መዝሙር ተቀነዩ ለእግዚአብሔር፡፡               #ዘቅዳሴ #ዕብራው_13:7-17፡ተዘከሩ መኳንንቲሆሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር #ያዕቆብ_4:6-ፍጻሜ፡ወበእንተ ዝንቱ ይቤ #የሐዋ_ሥራ_25:13-ፍጻሜ፡ወእምድኅረ ኅዳጥ መዋዕል              #ምስባክ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር   #መዝ_2:11-12             #ወንጌል #ዮሐንስ_3:10-25፡ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎ   #ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኩተከ)   @gitsawe
Показати все...
አባቶቻችን በኀዘን ተውጠው ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲያለቅሱ አምነናቸው አብረን ካለቀስን ደስ ሲላቸውና ደስ ይበላችሁ ሲሉንም እንዲሁ ልናምናቸው ይገባል፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት አልቅሰን ከጾምን አንድ ሆነች ሲባል ‘አይዋጥልኝም’ ማለትም ‘ታዲያ የጸለያችሁት ምን ይሁን ብላችሁ ነው?’ ያስብላል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱ ‘አምላካችን ሆይ ስማን በሉ’ ሲሉ እንደተቀበልናቸው ‘ሰምቶናል’ ሲሉንም አብረን ማመስገን የልጅነት ግዴታችን ነው፡፡ ነገሩ ምንም ያልተዋጠልን እንኳን ብንሆን አባቶቻችንን አትንኩብን ስንል በከረምንበት አፋችን ለመሳደብ ብንነሣ እንኳንስ እግዚአብሔር ሶሻል ሚድያውም ይታዘበናል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስን ሌላው ሲያቃልለው ከተቃወምን እኛም የማቃለል መብት የለንም፡፡ ሁሉም ሰው መሪ ሊሆን ስለማይችል ጉዳዩን በትኩረት ለያዙት አባቶች ሥራቸውን እንደ ጀመሩት እንዲፈጽሙ እየጸለይን በምንችለው ማገዝ እንቀጥል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው ጊዜ የተሰበረውን የምንጠግንበት ፣ ቤተሰቦቻቸውን ያጡትን የምንደግፍበት ፣ ሰማዕታቱን የምንዘክርበት ፣ በመከራዋ ቀን ለጮህንላት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሁለንተናዊ ድጋፍ የምናደርግበት ነው፡፡ እስካሁን የገጠሙን ችግሮች ያልተሠሩ ሥራዎች ውጤት መሆናቸውን በማሰብ ሌላ ሰው አጀንዳ እስኪያቀብለን በመጠበቅ ሳይሆን እኛ አጀንዳ ሠጪ እየሆንን የተቀጣጠለውን ፍቅረ ቤተ ክርስቲያን ለወንጌል አገልግሎት የምናውልበት ዕድል አሁን ነው፡፡ መጪው ዐቢይ ጾም ነውና እያበጣበጠ ሲያፌዝብን የከረመውን ዲያቢሎስ በርትተን የምንቀጣበት እድልም ከፊታችን ነው:: አሁንም ደግመን እንላለን :- አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የካቲት 8 2015 ዓ.ም.
Показати все...
ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በታሪክዋ አይታው የማታውቀው ሐዋርያዊ ሰንሰለትዋን የሚበጥስ አንዳች ዱብ ዕዳ ገጥሞአት በብዙ ጭንቀትና መከራ ውስጥ አሳልፋለች፡፡ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ በጉዳዩ ተደናግጦ ለእናት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነት የሚችለውን ሁሉ ለመክፈል ታይቶ በማይታወቅ አንድነት ተረባርቦአል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም እስካይ ድረስ ለዓይኖቼ ዕረፍትን ለሽፋሽፍቶቼ እንቅልፍን አልሠጥም ብላችሁ ስለ ቅድስት ቤተ ክርቲያን በምትችሉት ቆማችኋል ፣ ብርድ ላይ አድራችኋል ፣ ለመሞትም ቆርጣችኋል፡፡ አሁን በሰማያዊትዋ የድል ነሺዎች ቤተ ክርስቲያን ሆናችሁ የምታዩን ፣ ዓይናችን እያየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አትደፈርም ብላችሁ ሰማዕታት የሆናችሁት ልጆችዋም በረከታችሁ ይድረሰን፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ከብባችሁ አካላችሁ የጎደለ ፣ አሁንም ድረስ በአልጋ ላይ ያላችሁ ፣ ቤተሰቦቻችሁን ያጣችሁ ፣ ከቀዬያችሁ የተፈናቀላችሁ እስከ አሁንዋ ሰዓት ድረስ በወኅኒ ቤት ሆናችሁ ከእናንተ መፈታት ይልቅ የችግሩ መፈታት ያስጨነቃችሁ ወንድምና እኅቶቻችን ሥራችሁ በልበ ሥላሴ የተጻፈ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስለተገደሉ ልጆችዋ ስታለቅስና ማቅ ስትለብስም ከዳር ዳር ጥሪዋን ተቀብላችሁ ማቅ የለበሳችሁ ‘ቤተ ክርስቲያን ሆይ ማቅ ልልበስልሽ’ ያላችሁትን በአደባባይ በጥፊ የተመታላት የቤተ ክርስቲያን ራስዋ ክርስቶስ አይቶታል፡፡ ግራ ቀኝ የሚናፈስ ወሬ ነገሩን ሊያደፈርሰው ሲሞክርም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ምእመናን ‘ከሲኖዶስ ሌላ ማንንም አንሰማም’ ብላችሁ ታዝዛችኋል፡፡ ከመቼውም ጊዜ በላይ የቤተ ክርስቲያን ክብርና የቅዱስ ሲኖዶስ ምንነት ሰምተው የማያውቁ ሰዎች ሳይቀር በዚህ የተነሣ የጉዳዩ መሠረታዊነት ግልፅ ሆኖላቸው ፣ ግድ የማይሰጣቸውና ሲኖዶስን ሲሳደቡ የነበሩ እንኳን ‘እኔ ነኝ ያስደፈርኩሽ ቤተ ክርስቲያኔ ይቅር በይኝ’ ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኔን ነገር አደራ ብሎ ያነባው ፣ ንስሓ የገባው ሕዝበ ክርስቲያን እልፍ አእላፍ ነበረ፡፡ መተዳደሪያ ሥራቸውን ፣ ዝናቸውን ፣ ሙያቸውን አደጋ ላይ ጥለው ብዙዎች ለቤተ ክርስቲያናቸው ጮኸዋል፡፡ እምነታቸው ሌላ ሆኖ እንኳን ለቤተ ክርስቲያን የቆሙ ባለውለታዎችም ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ምንም ዓይነት ማስፈራሪያና ጫና ያልበገራቸው ብፁዓን አበው ታሪክ በማይረሳው መንፈሳዊ ጥብዓትና ጽናት በአንድ ልብ ሆነው በመናገር የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠበቆች ሆነዋል፡፡ ሁላችሁም ‘ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ እግዚአብሔር አመጸኛ አይደለም’ ዕብ. 6፡10 ‘ይህ ሁሉ ለምን ሆነ?’ አንድ ፓትርያርክ ፣ አንድ ሲኖዶስ ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን በሚል መርሕ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ለማስከበርና የቅዱስ ፓትርያርኩን አባትነት ለማጽናት ፣ በዚህም በሺህ ለሚቆጠሩ ዘመናት የተሻገረችውን ቤተ ክርስቲያን ሳትፈርስ እንድትቀጥል ለማድረግ ነው፡፡ ያ ሁሉ ዕንባና ልቅሶ ፣ ያ ሁሉ ሰማዕትነት አንድ ፓትርያርክ ፣ አንድ ሲኖዶስ ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ቀኖናዊ ዶግማ (Canonical Doctrine) ለማስከበር ነበር፡፡ በዛሬው ዕለት ከቅዱስ ሲኖዶስ እንደሰማነው በእግዚአብሔር ቸርነት ለሳምንታት ቤተ ክርስቲያንን እስከ ሰማዕትነት ድረስ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው ችግር ተፈትቶ ‘አንድ ፓትርያርክ ፣ አንድ ሲኖዶስ ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን’ የሚለው የቤተ ክርስቲያኒቱ መርሕ ተከብሮአል፡፡ ፓትርያርካችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፤ ሲኖዶሳችን አንድ ፣ ቤተ ክርስቲያናችንም አንዲት ናት የሚለው ጸንቶአል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ስለ ክብሩ መደፈር ተቆርቁረን ብዙ የጮኽንለት ቅዱስ ሲኖዶስን የእውነት ማክበራችንና መውደዳችን በተግባር የሚፈተነው አሁን ነው፡፡ ከአባቶቻችን ጎን እንደነበርን ከዚህ በኋላ በሚመጣው ነገር ሁሉም አብረናቸው እንሆን ይሆን? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ዛሬ በሰማናቸው መግለጫዎች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተከብሯል ፣ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ የነበረው ሹመትም መሻሩን ሿሚዎቹ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረበውን የመመለስ ጥሪ ተቀብለው ይቅርታ ጠይቀውም የተወገዙት ሊቃነ ጳጳሳት ተመልሰዋል፡፡ ልባችንን ያደማው የቤተ ክርስቲያን መከፈል ጉዳይ ባልተጠበቀ ፍጥነት ተፈትቶ እግዚአብሔር ጸሎታችንን እንደሰማ አይተናል፡፡ በሒደቱ ላይ ነገሮች በጣም በፍጥነት ከመለዋወጣቸው የተነሣ ብዙ ጥያቄ የሚፈጥሩ ዝርዝሮችና ከልባችን ገና ያልወጡ ሥጋቶች መኖራቸው ግን የማይካድ ነው፡፡ ክስተቱ ተመለሱ የተባሉ ሰዎች ሲወላወሉ ባየንበት ማግሥት የሆነ ነገር እንደመሆኑም ለማመን የቸገረንና በሙሉ ልብ ለመደሰት የፈራን ብዙዎች ነን፡፡ ቤተ ክርስቲያን በውግዘት የለየቻቸውን አበው መልሳ የምትቀበልበት አካሔድ እንዴት ነው? ፣ ከዚህ በኋላስ ምን ይፈጠር ይሆን? ፣ ወደነበርንበት ለመመለስ የከረምንበት ሁኔታ ይፈቅድልን ይሆን? መንግሥት በቃሉ ባይገኝስ? በፍርድ ቤት የታዩ ጉዳዮችስ? ይቅርታ የሚጠይቁ ሰዎች እያታለሉን ቢሆንስ ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች የቤተ ክርስቲያኑ ነገር እንደ እግር እሳት ሲያንገበግበው ከሰነበተ ምእመን የሚጠበቅ ውስጣዊ ጥያቄ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ተግባራዊ ምላሽ እንደሚሠጥበት እንጠብቃለን:: መንግሥትን እንዴት ማመን እንችላለን? ለሚለው እኛ ሁልጊዜም የምናምነው እግዚአብሔርን ብቻ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ አምነነው አሳፍሮን አያውቅም፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ስለ እግዚአብሔር ብቻ ነው:: በእግዚአብሔር መንፈስ ይመራሉ ብለን የምናምንባቸው አባቶቻችንንም እስከ አሁን ያዘዙንን ስናደርግ ሰንብተን ከዚህ በኋላ አባትነታቸውን ብንጠራጠርና በስሜታዊነት ብንሳደብ ‘ለሦስት ሳምንታት ቅዱስ ሲኖዶስ ክብርና ልዕልና ተነካ ብለን የጮኽነው ለምን ነበረ? ያስብላል፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ከመንግሥት ጋር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ሆነው ‘ቤተ ክህነቱ ሊወረር ነው ፣ አባቶች ሊታፈኑ ነው’ የሚል የሚያሸብር ዜና እየሰሙ በዚያ የጭንቅ ሰዓት ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው የሰነበቱ አባቶች ፣ ጠባቂዎች ቢነሡባቸው እግዚአብሔርን ጠባቂያችን ብለው ስለ ሕገ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ በድፍረት የቆሙ ሊቃነ ጳጳሳት ዋናው ችግር ከተፈታ በኋላ በሚኖረው ሒደት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን አሳልፈው ይሠጣሉ ብሎ መደምደም የሚያሳዝን ነው፡፡ አባቶችን ላታልላቸው ብሎ እንደ ሀናና ሰጲራ መንፈስ ቅዱስን ሊያታልል የሚሞክር ሰው የሚያታልለው ራሱን ነውና ይቀሰፋል፡፡ አርዮስ አባቶችን አታለልኩ ብሎ ሳያምን አምኛለሁ ብሎ የደረሰበትን ስንማር ኖረናልና ቤተ ክርስቲያንን ሊያታልል የሚሞክር ሁሉ በእርሱ እንደሚብስበት እናምናለን፡፡ ስለዚህ ተመለሱ በሚል ዜና እንደጠፋው ልጅ ወንድም አኩራፊ ፣ እንደ ሀናንያ ተጸያፊ ሳንሆን የእውነት ያድርገው ብለን በመጸለይ እንበርታ:: የነነዌ ለቅሶ መልስ ሲያገኝ ካኮረፍን ኩርፊያችን የዮናስ ኩርፊያ ይሆንብንና ትርፉ ቅላችንን ማድረቅና በፀሐይ መለብለብ ይሆናል:: (ዮና. 4:1-11) ልጅ ጠፍቶ ሲገኝ ደስ የሚል ከሆነ አባት ጠፍቶ ሲገኝ እንዴት ደስ አይልም? እንደ ልጅነታችን ዳግም አባት አልባ እንዳንሆን መለመን ነው እንጂ::
Показати все...
Показати все...
EOTC TV | የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ቀጥታ ሥርጭት ከመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ጥቁር መልበስም አትችሉም!! ................................. የጅማ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። ሰይጣን ክርስቲያኖችን ላይ እየጨፈርኩባቸው ነው ብሎ የሚያስብበት ግቢ ነው። ይገርማችኋል ነገ ጾመ ነነዌ ሲገባ የግቢው ካፌ በሬ አርዶ ሥጋ ለእራት ያቀርባል። ተማሪው ጾሙን ላለመግደፍ በበሶ እና በቆሎ በልቶ ያሳልፋል። በግቢው ሂጃብ እስከ ጥግ መልበስ በደምብ የሚቻል ሲሆን ነጠላ ግን አጣጥፈን በትከሻችን መያዝ እንኳን አንችልም። ይሄ ማለት እግዚአብሔር ፈቅዶላቸው ሥጋ ወደሙን የሚቀበሉ ተማሪዎች ወደ ግቢ አይገቡም ማለት ነው። እንደው ከዕለታት በአንድ ቀን ድንገት ደስ ብሎን የሀገር ባህል እንልበስ ካልን እንኳን ልብሱ ላይ የመስቀል ምልክት ካለ ወደ ግቢ መግባት አንችልም። ይኸው በግቢያችን መጾምም፣ መደሰትም፣ ማዘንም አትችሉም ተብለናል። ነጭ ነጠላም ጥቁር ልብስም ከለበሳችሁ ነገ አስራችኋለሁ እያለ ነው። አሁን ኦርቶዶክስ ላይ የተጀመረው ዘመቻ በግልጽ በጦር ነው፤ ግን እዚህ ላይ የደረስነው ለብዙ ዓመታት በጭንቅላታችን ላይ (Subconciously) ካዳከሙን በኋላ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም። ከጾመ ነነዌ በኋላ ግን እግዚአብሔር ያነባነውን ዕንባ ተቀብሎ ሲፈርድ፣ የእኛን መጥፋት ሲተነብዩ የነበሩ ደቂቀ ሰይጣናት ሲያፍሩ ለማየት ግን ቸኩያለሁ! "ለእመ እግዚአብሔር ምስሌነ መኑ ይክለነ?" "እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይችለናል?" ሮሜ 8፥31 ............................... ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ . . #share ካደረጋችሁስ ይህንንም አድርጉልን!! ቅዱስ ሲኖዶስም ጥቁር ልብስ ከገበያ እንዲጠፋ ብቻም ሳይሆን መከልከልም እንደተጀመረ ለብጹዓን አባቶቻችን አድርሱልን!! . #onepatriarch #onesynod #oneorthodox
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
271ሺ ደርሰናል ግማሽ ሚልየን መድረስ አለብን በመንግስት መገናኛ ብዙኅን ድምጿ እንዳይሰማ የታፈነችውን ቤተክርስቲያናችን ድምጽ እናጉላ ላልሰሙት አሰሙ! የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ ➽ የዩቲዮብ ገጻችን http://www.youtube.com/c/eotctv ➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን https://www.facebook.com/eotctvchannel
Показати все...