ኪያ Online እቁብ
Відкрити в Telegram
በቀላሉ የተለያዩ ሽልማት እና ትንሽ የትኬት ቁጥር ያላቸው እቁቦች ላይ ይሳተፉ። እጣው ከወጣልዎት ከየትም ሆነው መልዕክት ይደርሶታል። ትኬት ለመቁረት @Kiya_ekub_bot
Показати більше2 540
Підписники
-124 години
-177 днів
-2030 днів
Архів дописів
2 540
ትላንት ምሽት ሪያል ሶሴዳድ አልሜሪያን 1-0 በረታበት ምሽት የቀድሞ የክለባችን ተጨዋች የሆነዉ ጃፓናዊዉ ታኬ ኩቦ ጎል አስቆጥሮ የቪኒ ዡኒየርን ዳንስ ደንሷል።
ታኬ 😘
2 540
ሁሉም የሚገርመዉ የዘረኝነት ጥቃቱን በቪኒ ላይ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች መልካቸዉ እንደዚህ በግልፅ እስከሚታይ ድረስ ድርጊቱን መፈፀም መቻላቸዉ አቤቱታ ተቀባይ ተቋም አለመኖሩን በሚገባ በማወቃቸዉ ነዉ። 😢
2 540
ቪኒሲ ዡኒየር በ IG ገፁ ላይ የምትመለከቱትን ቪዲዮ በማያያዝ የለቀቀዉ አዲስ ፖስት ፦
"ከእኛ ስታዲየም ውጭ ባሉት ሁሉም ዙርያ አንድ ደስ የማይል ድንገተኛ ነገር እናያለን ፣ እናም በዚህ ሰሞን ብዙ ብዙ ነገሮችን አይተናል። ብዙዎች ለእኔ ሞት ተመኝተውኝ ነበር ፣ ደም በላያቸው ላይ የነካቸዉ አሻንጉሊቶችንም ይዘዉ ታይተዋል ፣ ብዙ የዘረኝነት ጩኸቶችንም ሲያሰሙብኝ ነበር ሁሉም ነገር ተመዝግቧል። ነገር ግን ክስተቶቹ "በተረሱ ጉዳዮች" ምድብ ውስጥ ተቀምጠዋል። እነዚህ ሊረሱ የማይገባቸው ጉዳዮች ናቸዉ። በስፔን ውስጥ ባሉ በርካታ ከተሞች እና በቴሌቪዥን ትእይንት ውስጥ እንኳን መስፋፋታቸውን የሚቀጥሉ ክፍሎች ናቸው።
"ማስረጃው ሁሉ ከላይ በለቀኩት ቪዲዮዎች ውስጥ አለ። አሁን በድፍረት እጠይቃለዉ ከእነዚህ ውስጥ ምን ያህሉ ኦፕሬተሮች በድረ-ገፃቸዉ ላይ ድርጊቱን ሲያስፋፉ የነበሩ ስሞችን እና ፎቶዎችን ለህዝብ ይፋ አድርገዋል ? ቀለል ለማድረግ እኔ እመልስላችሁ "0 ሰዉ" ማንም አሳዛኝ ታሪክ በድፍረት ሚዲያ ላይ ወጥቶ አይናገርም ወይም እነዚያን የውሸት ህዝባዊ ይቅርታ አይጠይቅም። በማስረጃነት ከተጠቀሱት እነዚህ ቪዲዮዎች ላይ ይህን የዘረኝነት ስድብ ሲያስፋፉ ነበበሩ ሰዎች ወንጀለኛ በማድረግ እና ክለቦቻቸዉን በስፖርታዊ ጨዋነት ለመቅጣት ምን የጎደለ ነገር አለ ? ስፖንሰሮችስ ለምን ከስፔን ሊግ የካሳ ክፍያ አይወስዱም ? ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ለምን ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በየሳምንቱ መጨረሻ በማሰራጨታቸዉ አይፀፀቱም ? ችግሩ በጣም አሳሳቢ ነው። የወንጀል ድርጊቶችን በይፋ በማሳየቴም አትወቀሱኝ። ይህ እግር ኳስ ሳይሆን ኢሰብአዊ ነው።"
2 540
ትንሽ MG ከፍ ሊልባችሁ ይችላል ግን WIFI ያላችሁ ይህን ዋነኛዉን የዘረኝነት ጥቃት ተመልከቱት።
ቪኒ ወደ ተጨዋቹ እየጠቆመ "አንተ ነህ አንተ" ሲለዉ ይስተዋላል። በተቃራኒዉ የቫሌንሲያዉ ተጨዋች ደግሞ ወደ ደጋፊዎቹ ቀርቦ ተረጋጉ 1 ለ 0 እየመራን ነዉ የሚል ምልክት በእጁ ሲሰጥ ታይቷል።
2 540
ምንድነዉ ይሄ አሁን ዳኛዉ እና VAR ስክሪን ላይ የተቀመጡት ረዳት ዳኞች ይህ ሁኔታ ሲከሰት የት ነበሩ።
ነገሩ እንዴት ነዉ 🤷♂
