cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ASD AJ LAH

ካነበብኩት…

Більше
Рекламні дописи
645
Підписники
Немає даних24 години
+467 днів
+5430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የበታቻችሁን ተመልከቱ ሲባል ብዙዋችን የምንዞረው ከኛ ይበልጥ ድሃ ወደሆኑ ሰዎች ነው ። አላህ በአንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ከመዘንጋት ይመስላል ። ይህ ዝንጋቴ ነው ትክክለኛውን ሹክር እንዳናደርግ የሚያግደን ። እዚሁ መንደር እገሌ የተባለ ሰው በዚህ በሽታ ስለተጠቃ ገንዘብ እንርዳው ሲባል እንመለከታለን ። አላህ በታማሚው ቦታ ስላላደረገን ለማመስገን ሁለቴ ማሰብ የሚፈልግ አይደለም ። ጤና ሐብት መሆኑ የሚገለፅልን ሆስፒታሎች ውስጥ ስናዘወትርና እንዲህ ያሉ መሰል ታካሚዎችን ስንመለከት ነው ፣ ዕድሜ ፀጋ መሆኑ የሚገለፅልን መቃብሮችን ስንዘይር ነው ፣ ከሁሉ በላይ ግን «ዛሬ»ን የመሰለ ስጦታ የለም ። ለዚህም ነው ። ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ‹‹ አልሐምዱሊላሂ ለዚ አህያና……›› የምንለው ። አዎ! ትንሿን ሞት አስሙተህ በዚያው ሳታስቀር ህያው ያደረግከን አላህ ሆይ ምስጋና ይገባህ የምንለው ። ቀናችንንም በምስጋና እንድንጀምር የተደረገውም ለዚሁ ነው ። አላህ ‹‹ ዛሬን ›› ሰጥቶሃል ። እርሱ የሚወደው አልያ የማይወደው ማድረግ ግን የኛው ምርጫ ነው ። ከወደደው ጥቅሙ ለኛ ካልወደደው ጉዳቱ ለኛ እንጂ እኛ ቀኑን ሙሉ ብናምፀው አላህን አንጎዳውም ቀኑን ሙሉ ብናመልከው አላህን አንጠቅመው ። ለእኛው ነው ወገን ለእኛው ! አብዱ ረዛቅ
Показати все...
1
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰#አልዓርቢዓዐ 0️⃣7️⃣ #ዙልቀዓዳ 1️⃣4️⃣4️⃣5️⃣ ሂ
Показати все...
👍 1
ከአሳሳ እስከ ሮቤ፣ ከኮኮሳ እስከ አዳማ ፣ ከአርሲ እስከ ባሌ፣ እስከ ሸገርና ጎንደር ድረስ ጭምር ታሪክ አለን ከዚህ ሰው ጋር፡፡ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረ በጎዳና ላይ ደዕዋ ሲያደርግ ታውቁታላታችሁ፡፡ ምንም ማንንም የማይፈራ ሙጃሂድ ነው። ስፒከሩ በተዳጋጋሚ ታስሮበት በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተትም አጋጥሞኛል፡፡ ከልጅነት እስከ ወጣትነትና ጎልማሳነት ምናልባት እስካዛሬዋ እስከመጨረሻዋ የዱንያ ላይ ቀን ድረስ ሐያቱን በሙሉ በደዕዋ አሳልፏል፡፡ አላረፈም። ኢስላምን ለማድረስ ሁሌ እንደተጓዘ ስለማየው ቤት ይገባ ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ ብዙ ጊዜ፡፡ ዛሬ ሻሻመኔ ላይ ድንገት ማረፉን ሰማሁ፡፡ ፈቂ ገለቶ አላህ ይዘንልህ፡፡ ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል፤ በሞተበት ነገር ላይም ይቀሰቀሳል፡፡ ደጋግ ባሮችህ ወዳንተ እየመጡ ነው። አላህ ሆይ! ዐለይከ ረበና ቢሑስኒልኺታሚ እንላለን ። Abx
Показати все...
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
Показати все...
ከቀድሞ ባለቤቱ የተፋታበትን ከትውልድ መንደሩ የተሰደደበትን ምክንያት ሲያስረዳ ወላህ ያስቀና ነበር። የሁሌም አደራው "ውጡ! ወደ አላህ መንገድ ተጣሩ" የሚል ቃል ብቻ ነበር። ከዚህ ንግግሩ የሚገናኝ ቃልን እንጂ ከአፉ ሌላን ቃል አድምጨ አላውቅም።
Показати все...
ይሄ ዛሂድ ይህ መንገደኛ የአላህ ባሪያ አለፈን ሰማሁ😢 ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂ ራጂኡን ! ዱኒያን ለአላህ ብሎ ትቶ በዝህድና የአላህና መልእክተኛውን መልእክት እያስተላሉፉ ኖሮ መሞት ምንኛ መታደል ነው ! እንዳለመታደል ሆኖ ልፋቱን ባናግዘውም ተገቢውን ክብር ባንሰጠውም አላህ ግን አንዱንም መልካም ስራውን ሳያስቀር በብዙ አባዝቶ ትልቅ ደረጃን እንደሚያጎናፅፈው ተስፋ እናደርጋለን ! አላህ ሆይ በራህመትህ ተቀበለው ከዚህች ዱኒያ በበለጠቺዋ ጀነትህም አጣቅመው ! ሰዒድ
Показати все...
😢 2👍 1
ወንድማችን ፈቂ ገለቶ አላህ ይዘንለት። በተለይ መርካቶ አካባቢና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በአደባባይ ዳዕዋው ይታወቃል። ዛሬ ሻሸመኔ ላይ ወደ አኺራህ መሄዱን ሰማን። አላህ ይዘንለት፤ መልካም ሥራውንም ይቀበለው።
Показати все...
😢 2
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #አሱለሳዒ 0⃣6⃣ #ዙልቀዓዳ  1⃣4⃣4⃣5⃣ ሂ
Показати все...
የአብዛኛው ወጣት ጥያቄ ይመስለኛል... "የቱ ጋር ነው የተሳሳትኩት ፈጣሪዬ??.. ለምን እድገቴ እንዲህ የዘገየ መሰለ?.. የቱ ነገር ነው ከህልሜ ጋር ያለኝን ርቀት ያሰፋብኝ?.. የቱ ልምምዴ?.. የትኛውስ ክፉ ስራዬ ነው መንገዴን ያረዘመው?......" ወጣቱ ይጠይቃል.. አሁን ግን የምር ነው የሚጠይቀው.. መልሱ ደግሞ ለአሁን አጥጋቢ ባይመስለንም እንዳንሰላች.. 🙏 የእውነት ፈጣሪያችን የሻትነውን ሁሉ የሚሰጠበት የራሱ የሆነ ፍፁም ትክክል የሆነ ወቅት አለው.. 😊 'ነገርን ሁሉ ውብ አድርጎ የሰራው በጊዜው ነው አዎ በጊዜው!!.. በእርግጥም እኛም ቀን አለን እሺ አህባቢ 👐❤
Показати все...
نذكركم غزة 🇵🇸💣
Показати все...
❤‍🔥 1