925
Підписники
Немає даних24 години
+37 днів
+730 днів
Архів дописів
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
ወንጀልን አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የመንግስት ተቋማት የጥበቃ፣የሰው ሀብት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ተወካይ ኢንስፔክተር ጀማል አስፍር እንደገለፁት ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል እና የጎላ ችግር ሳይፈጠር በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
የዕለቱ የመወያያ ሰነድ ያቀሩቡት የገ/ጉ/ወ/ወ/ፖሊስ ፅ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ ም/ኢንስፔክተር በመሀመድ አባተ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረጓል።
በውይይቱ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች የመንግስት ተቋማት የግቢ ውስጥ ማብራት አለመኖር፣የተቋማት ጥበቃዎች ሰራተኝነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ እና ባጅ አለመኖሩን የተቋማት አጥር አስተማማኝ አለመሆኑ የተለያዩ የጥበቃ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች አለማሟላት ፣በተቋማት በቂ ጥበቃ አለ መኖር ፤የተቋማት የሰው ሀብቶች ጥበቃዎች የመከታተል እና የመቆጣጠር ሁኔታ አናሳ መሆን እና በተራቸው ቀን አለመገኘት ከመድረኩ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች ናቸው።
ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄና አስተያየት ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ም/ኢንስፔክተር መሀመድ አባተ የመድረኩ አላማ በየተቋማት ያሉ የሰው ሀብቶች የጥበቃ ሰራተኞቻቸው ማረም እና ከማወቅም ሆነ ካለማወቅ ለሚፈጠሩ ወንጀሎች ተቋሞች ተጠያቂ መሆናቸው ገለፀው የሚያነሷቸው የግብዓት ጥያቄ የተቋም የሰው ሀብት ግብዓት የማሟላት ስራ መስራት እንዳለበት ገልፀው የመሳሪያ አያያዝ እና አጠቃቀማቸው ክትትል ማድረግ እንደ ሚገባ፣ በተጨማሪ ተሽከርካሪዎች ወደ ተቋም ሲገቡ መረካከቢያ በማዘጋጀት መረከብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በመጨረሻም የገ/ጉ/ወ/ወ/ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ተወካይ ኢንስፔክተር ጀማል አስፍር ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ባለድርሻ አካል ከጊዜ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሱን በማዘጋጀት የተጣለበትን አደራ መወጣት እንደሚገባው ጠይቀው የሚያጋጥሙ ችግሮች ካለ በማሳወቅ መፍትሄ መስጠት መቻል እንዳለባቸው ጠቅሰው ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር የጥበቃና የፖሊስ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ህዳር 14/2018 ዓ.ም
👉🏼 የህፃናት መብት እና ደህንነት ለመጠበቅ የህፃናት ፓርላማ አደረጃጀቶች ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 የማር ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የአርሶአደሩ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ያልተከፈለ ተጨማሪ ክፍያ መክፈሉን የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አስታውቀዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 በመብራት በንጹህ መጠጥ ውሃ እና በመንገድ መሰረተ ልማቶች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ያለውን ሰላምና ጸጥታ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በተጨባጭ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ህዳር 13/2018 ዓ.ም
የህፃናት መብት እና ደህንነት ለመጠበቅ የህፃናት ፓርላማ አደረጃጀቶች ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ፅ/ቤት የ2018 ዓ.ም አንደኛ ዙር የህፃናት ፓርላማ በዛሬው ዕለት አካሄደ።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሴቶችና ህፃናትጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ መይሙና ሙዘይን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ራሳቸውን ከጥቃት እንዲከላከሉና ህገመንግስታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ፓርላማው ሚናውን እንዲወጣ እንደሚያግዝ ተናግረዋል
በህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት መደገፍ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የዕለቱ የመወያያ ሪፖርት እና ዕቅድ በህፃናት ዋና አፈጉባኤ በተማሪ ሱላይማን አ/ፈታ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።
በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች በየ ትምህርት ቤቱ የሚገኙ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፣በህፃናት ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ አካላትን አስተማሪ የሆኑ እርምጃዎችን አለመወሰዱ ፤ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መቅረፍ አለመቻላቸውን በህፃናት ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ አካላት ላይየተሰጠ ቅጣት ለሌሎች መማሪያ እንዲሆን መረጃዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ አለማድረጋቸው እንዲሁም ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ግንዛቤ እና ክትትል ከማድረግ ፣ወላጆች ልጆቻቸውን ከትምህርት ገበታቸው አውጥተው ወደ ከተማ በመላክ ለፆታዊ ጥቃት እና ለጎልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆናቸው ከመድኩ የተነሱ ሀሳቦች ናቸው።
የህፃናት ፓርላማ ዋና አፈጉባኤ ተማሪ ሱላይማን አ/ፈታ ባስተላለፈው መልዕክት በየ ትምህርት ቤቱ የተወከሉ የህፃናት አፈ ጉባኤዎች የተፈጠረላቸው ግንዛቤ መነሻ በማድረግ በአካባቢያቸው የሚፈፀሙ የህፃናት ጥቃቶች መረጃዎች በየደረጃው ለሚገኙ አካላት በጊዜ መረጃ መስጠት እንዳለባቸው እና በፓርላማው የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ለሚመለከተው ተቋም ተደራሽ ማድረግ አንደሚገባም አሳስበዋል፣
በመጨረሻም የፅ/ቤቱ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ መይሙና ሙዘይን ከመድረኩ ለተነሱ አስተያየትና ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በህፃናት ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች በህግ ጉዳዩ ከተያዘ በኋላ ሽምግልና በሚል የሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት ትልቅ ችግር እየሆባቸው መምጣቱን ጥቃት ፈፃሚው በተለያየ ጥረት እና ክትትል ለህግ ከቀረበ በኋላ ጥቃት የሚፈፀምባቸው አካላት የሀሳብ ለውጥ እንደሚያደርጉ ጠቅሰው ከመድረኩ የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች የቀጣይ የዕቅዳቸው አካል አድርገው እንደሚሰሩ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ለመከላከልና ለመቀነስ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
መድረኩን አስመልክቶ የተለያዩ ትምህርት አዘል ግጥሞች በተሳታፊ ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን የሃይማኖት አባቶች የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል።
ህዳር 12/2018 ዓ.ም
የማር ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የአርሶአደሩ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ከድር መርጋ እንዳሉት ባህላዊና ዘመናዊ የንብ ቀፎ በመጠቀም በወረዳው በማር ምርት ላይ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አብራርተዋል።
በ11 ቀበሌዎች ላይ በተፋሰስ ልማት በለሙ ቦታዎች ወጣቶች በ22 ማህበራት በንብ ማነብ ስራ ተደራጅተው እየሰሩ እንደሚገኝ ያመላከቱት ሀላፊው የሚመረተው የማር ምርት ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ እንደሆነ አስረድተዋል።
ዞንን በመወከል በዘንድሮ አመት በጅማና በዱራሜ በተዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች ምርታቸውን ይዘው መቅረብ የቻሉበት ሁኔታ መኖሩም አመላክተዋል።
የእንስሳት ዝርያ በማሻሻል ረገድ ሴት ጥጃ የማስወለድ ቴክኖሎጂ በዘንድሮ አመት በተሻለ መንገድ መፈጸም እንደተቻለም አስረድተዋል።
ጽህፈት ቤቱ ከኢንተርፕራይዝ ተቋም ጋር በመሆን በወተት ምርት የሚፈለገው ውጤትና ለውጥ እንዲመጣ አጽኖት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ፈድሉ ኡስማን እንዳሉት በወረዳው በሌማት ትሩፋት ላይ በዶሮ ፣በስጋ፣ በንብ ማነብና እንዲሁም በወተት ሀብት ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በአመት ሁለት ጊዜ የማር ምርት የሚሰበሰብ እንደሆነ አመላክተው በወረዳው 80 የዶሮ መንደር ፣ 28 የወተት መንደሮች እንደሚገኙና እነዚህም ውጤታማ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
በወረዳው በዘሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በማር ምርት ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ አርሶአደር አለም ሸምሱ እንዳሉት ከ2015 ዓመተ ምህረት ጀምሮ 20 ዘመናዊ የንብ ቀፎ በመጠቀም የንብ ማነብ ስራ መጀመራቸው አስታውሰው በአምና ደረጃ በአራት ቀፎ ብቻ 47 ኪሎ ግራም ማር መቁረጥ እንደቻሉም አስታውሰዋል።
በዚህ ዘርፍ በአካባቢያቸው ያሉ አርሶአደሮች ላይ መነቃቃት ተፈጥሮ በግል የንብ ቀፎ በመግዛት ወደ ስራ የገቡና ለመጀመር ያቀዱ ብዙ አርሶአደሮች መኖራቸውም ተናግረዋል።
በማር ምርት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ የግብርና ባለሙያተኞች እያደረጉላቸው ያለውን ድጋፍና ክትትል የሚበረታታ እንደሆነና ቀይጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም ተናግረዋል።
በቀጣይ ባላቸው ቀፎ ላይ ተጨማሪ የንብ ቀፎዎችን በመጨመር የማር ምርትና ምርታማነት በተጨባጭ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩም አመላክተዋል።
ህዳር 11/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ያልተከፈለ ተጨማሪ ክፍያ በዛሬው እለት መክፈሉን የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አስታውቀዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
መንግስት የደመወዝ ጭማሪ ከመስከረም ጀምሮ ተግባራዊ አደርጋለው ባለው መሰረት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመስከረም እና የጥቅምት ወር ያልተከፈለ ተጨማሪ ክፍያ ዛሬ ህዳር 11/2018 ዓ.ም ተግባራዊ ማድረጉን የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጉዳዩን አስመልክቶ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ወሃብ ኸሊል እንደገለጹት ከመስከረም ወር 2018 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገውን አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ እንደሀገር መንግስት የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን ኃላፊው አስታውሰው ይህንኑ የወረዳው መንግስት በዛሬው እለት ተግባራዊ ማድረጉን ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም በተለየ መልኩ አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ስኬል ያልወረደላቸው ተቋምት የተሻሻለው ስኬል ወረዶ ተግባራዊ እስከሚደረግ በትእግስት እንዲጠብቁ በመግለጽ የተሻሻለው ስኬል ሲወርድ በአፋጣኝ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አስታውቀዋል።
በመጨረሻም አቶ አ/ወሃብ ባስተላለፉት መልእክት
የመንግስት አገልግሎት አሰጠጥ የሚያፋጥን የደሞዝና የአበል ማስተካከያ የተደረገው መንግስት የመክፈል አቅም ኖሮት ሳይሆን የመንግሥት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ስለሚያውቅ ትልቅ ዋጋ ተከፍሎ ይህ ጭማሪ መደረጉን አስታውሰው
ሰራተኛው ይህን ተረድቶ ህዝቡን በቅንነት በታማኝነት ማገልገል አለበት ያሉት ኃላፊው ተገልጋዩን ሳያጉላላ ስራውን ማከናወን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
#የመደመር_አንቀጽ
ትናንት ላይ ቆሞ የቀረና በመደመር መንግሥት መዋቅራዊ መሻሻል ያላሳየ ሀገር፤ መሠረታዊ ፍላጎቶችን በሟሟላት አዙሪት የተጠመደና የብልጽግና በር የተቆለፈበት ነው። ዕድገትና ብልጽግናን ቀጣይና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመምራት ውጤታማ መዋቅራዊ ሽግግር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ይሄንን ለማሳካት የኢኮኖሚውን ዋና መሠረት እንደ ግብርና ካሉ መሠረታዊ ዘርፎች በፍጥነት ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ወደሚጠቀም ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ማሸጋገር፣ ብሎም የኢንዱስትሪ ልማትን ወደሚደግፍ የአገልግሎት ዘርፍ ማሸጋገር ይገባል። ኢኮኖሚው በብዝኃ ዘርፍ ዕይታ ማዋቀር ያስፈልጋል፡፡
(#የመደመር_መንግሥት_ገጽ_144)
ህዳር 09/2018 ዓ.ም
"በመደመር መንግስት እይታ ፣የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ቃል የጉራጌ ዞን የብልጽግና አመራሮች ስልጠና በወልቂጤ ከተማ መስጠት ተጀመረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በመክፈቻ መድረኩ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ዲን ዶ/ር አብድላዚዝ ሙሰማ፣የዞን፣የከተማ አስተዳደርና የወረዳ የስራ አመራሮች ተገኝተዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል በመክፈቻ ንግግራቸው ስልጠናው በአመራሩ ዘንድ መቀራረብን በመፍጠር ተመሳሳይ አመለካከት እንዲኖር በማድረግ ተልእኮን በብቃት የሚፈጽም አመራር ለመፍጠር ያለመ ነው።
የብልጽግና አመራሩ በሁሉም ዘርፎች በቂ እውቀት፣ግንዛቤና ክህሎት ኖሮት በብቃት የሚመራ መሆን ይጠበቅበታል ያሉት አቶ አለማየሁ ስራዎች በቅንጅት በመስራት በሁሉም ዘርፎች ውጤታማነትን ማረጋገጥ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
መርሐ ግብሩ የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም የሚገነቡ ልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት ነው።
ስልጠናው ለ9 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በማጠቃለያውም የመስክ ጉብኝት እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ህዳር 08/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ያለውን ሰላምና ጸጥታ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም ተግባር አፈጻጸም የጸጥታ ምክር ቤት የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ነዉ።
በዚህ ወቅትም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን መንግስት የሰላም መዋቅሩን በማቀናጀትና በማደራጀት የወረዳውን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ ባደረገው ጥረት የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ መቻሉን ጠቅሰው አሁን ላይ ያለውን ሰላምና ጸጥታ ባስተማማኝ መልኩ ለማስቀጠል የሚደረገውን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
የወረዳዉ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሰማ በድሩ የመድረኩን ዋና ዓላማ አስመልክተው እንዳሉት በየቀበሌው የቅድመ ጸጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች መለየት፣ ለወረዳው የጸጥታ ሀይል ተልዕኮ መስጠት፣ ሚሊሻ ማጥራት፣ ማደራጀት እና የመከላከያ ሀይል ምልመላ ስራ ዋና ዓላማ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አቶ ሙሰማ በድሩ የ2017 ዓ/ም ተግባር አፈጻጸም አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
አንዳንድ የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ከሰጡት ሃሳብና አስተያየቶች መካከል ለወሰን ግጭት ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚገባ፣ ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ጉዳዮች መለየት ላይ በአጽንኦት መሰራት እንደሚገባ፣ ከወንጀል መከላከል ስራ ጋር በተያያዘ የተቋማት ጥበቃ መጠናከር እንሚኖርበት ያነሱት ተሳታፊዎቹ ለዘማች ቤተሰብ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ማጠናከርና ህግ የማስከበር ስራ ላይ ተቋማት በባለቤትነት ወስደው ሊሰሩ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም የሚሊሻ አባላትን በአልባሳትና በግብዓት ማሟላት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
አቶ ሙሰማ በድሩ ለተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ግጭቶችን አስቀድሞ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ስለመሆኑ ጠቅሰው የሚሊሻ ስልጠና ማጠናከር እንዲሁም የወሰን ግጭቶችን አስቀድሞ ከመከላከል ረገድ የጸጥታ መዋቅሩ ተቀናጅቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
