uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Відкрити в Telegram
925
Підписники
Немає даних24 години
+37 днів
+730 днів
Архів дописів
ህዳር 08/2018 ዓ.ም "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የ20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል አስመልክቶ ለፐብሊክ ሰርቫንቱ ስልጠና እየተሰጠ ነው። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ ጨምሮ የጉራጌ ዞን የስራ ኃላፊዎችና የመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። 20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ቀን በክልሉ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን በተለይ በወልቂጤና በሆሳና ከተማ በልዩ ዝግጅት የሚከወን መሆኑ ይታወቃል። ይህንን አስመልክቶ ከፌደራልና ከተለያዩ ክልሎች በርካታ እንግዶች ወደ ክልሉ የሚገቡ በመሆኑ እነዚህ እንግዶች በአግባቡ ተቀብሎ ለማስተናገድ በሁሉም ዘርፎች ስራዎች እየተሰሩ ነው። ፐብሊክ ሰርቫንቱም ለዚህ ተግባር ግንባር ቀደም ሆኖ መስራት እንደሚጠበቅበት የተገለጸ ሲሆን ለፕሮግራሙ እቅዶች ታቅደው ወደ ስራ መገባቱና ለሚመለከታቸው አካላት መሰል አይነት ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑ ለአብነት ተመላክቷል።

ህዳር 07/2018 ዓ.ም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል። የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጥን ከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ:- 👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ፣ 👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣ 👉 የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣ 👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣ 👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ ናቸው። የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች 👉 ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣ 👉 በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች (እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች) ጋር በሚኖር ንክኪ፣ 👉 በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል። የበሽታው መከላከያ መንገዶች 👉 የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣ 👉 ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ካለዎት እና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣ 👉 ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣ 👉 ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣ 👉 ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣ 👉 እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል። FMC

+8
FB_IMG_17632881605575536.jpg1.42 KB

ህዳር 07/2018 ዓ.ም ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በተጨባጭ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ስንዴ በኩታገጠም በማልማታቸው ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ እንደሆነ በኦቼና አንቀዲን ቀበሌ በግብርናው ዘርፍ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ጠቁመዋል። የጉደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ እንዳሉት በወረዳው የሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች እንዲሰማሩ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በተጨባጭ እያረጋገጡ ይገኛል። በ2017/2018 የምርት ዘመን ከ261 ሄክታር በላይ መሬት በ32 የገጠር ቀበሌዎች ወጣቶች ተደራጅተው ገብስ ፣ባቄላ ፣ስንዴና የተለያዩ ሰብሎች እያለሙበት እንደሆነም አብራርተዋል። በኦቼና አንቀዲ ቀበሌ አራት ኢንተርፕራይዞች 42 ወጣቶች በማህበር በማደራጀት ከ14 ሄክታር በላይ መሬት ስንዴ በኩታገጠም እያለሙ እንደሆነም አስረድተዋል። ከወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል ለዳቦ የሚሆን የስንዴ ዘር ድጋፍ የተደረገላቸው እንደሆነም አብራርተው ወጣቶች ያመረቱት ምርት ወደ ገበያ እንዲያጡና የገበያ ትስስር እንደሚፈጠርላቸውም አመላክተዋል። በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች በሶስቱም የእድገት ዘርፎች በግብርና በኢንደስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ወጣቶችን በማደራጀት ሰፊ ስራ እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል። በ2018 በጀት አመት በአንደኛ ሩብ አመት 6804 ስራ አጥ ወጣቶች ለመለየት ግብ ይዘው በዚህም 6842 ወጣቶች ተለይተው ወደ ስራ ለማስገባት የአጫጭር ጊዜ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ስራ ለማስገባት ሰፊ ርብርብ እያደረጉ እንደሆነም ተናግረዋል። በበጀት አመቱ 5 ሺህ 4 መቶ 60 ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እስካሁን ባለው 1 ሺህ 6 መቶ 95 ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ለማረጋገጥ አጽዕኖት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በበጀት አመቱ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ለማስመለስ ጥረት ተደርጎ እስካሁን ባለው 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ማስመለስ መቻሉም ያስታወሱት ሀላፊው ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ለማሰራጨት አቅደው እስካሁን 4 ሚሊየን ብር ብድር የማሰራጨት ስራ መሰራቱም አስረድተዋል። በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በኦቼና አንቀዲ ቀበሌ አዳር ገበያ ልማት የወጣቶች ማህበር አባላት መካከል ወጣት ሚፍታ ስራጅና ታለግን መሀመድአማን እንዳሉት ቀደም ሲል ስራ አጥተው ተቀምጠው እንደነበረና አሁን ላይ መንግስት በግብርና ስራ አደራጅቷቸው ወደ ስራ በመግባት ውጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። የወረዳው መንግስት አራት ሄክታር መሬት አመቻችቶላቸው ስንዴ በኩታገጠም እያለሙ እንደሆነ አመላክተው በዚህም የተሻለ ውጤት እየጠበቁ እንደሆነም አብራርተዋል ። የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል የተሻሻለ የስንዴ ዘር ደጋፍ አድርጎላቸው በማሳቸው በመዝራታቸው ምርትና ምርታማነታቸው ማሳደግ የሚያስችላቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ህዳር 07/2018 ዓ.ም 👉🏼‌‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ''ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ቃል 20ኛው የብሄር ብሔረሰቦች ቀን በዓል የወረዳው ፐብሊክ ሰርቫንት በዛሬው ዕለት በድምቀት አክብረው ዋሉ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ የሐይማኖት ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ መንግስት ባለሀብቱና ማህበረሰቡን በማስተባበር በተለያዩ ቀበሌዎች ከ90 ሚሊየን ብር በለይ ወጪ የሚደረግባቸው የጠጠር መንገድ ለመገንባት ግብ ጥሎ እየሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። 👉🏼‌‎ በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘር ከተሸፈነው 13 ሺህ 8 መቶ 89 ሄክታር መሬት ማሳ 795 ሺህ 426 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገለጸ። 👉🏼‌‎የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ ዓላማ ተኮር የህዝብ ግንኝነት በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብ/ፓርቲ ከባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄዷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እየተገነባ ያለው ከሼሽት ማዴ- አዳዘር ት/ት ቤት ባለው መንገድ ላይ የዳገት ቆረጣ ስራ እና የጠጠር ምርት ስራዎችን አስመልክቶ ከወረዳው ተወላጅ ባለሃብቶችና አመራሮች ጋር የመስክ ምልከታ በዛሬዉ ዕለት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎የዜጎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ህዝቡ ለሚጠይቀው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው ምላሽ ለመስጠት የገቢ አሰባሰብ ስራችን ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨

‎ህዳር 05/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ''ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ቃል 20ኛው የብሄር ብሔረሰቦች ቀን በዓል የወረዳው ፐብሊክ ሰርቫንት በዛሬው ዕለት በድምቀት አክብረው ዋሉ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎በዚህ ወቅትም የወረዳው ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ጫሉ ከድር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሀገራችን የብሔር ብሄረሰቦች መገኛ እንደመሆኗ መጠን አብሮ የመኖር የመቻቻል ባህል የዳበረበት  መግባባት የሰፈነበት ሀገር ናት ብለዋል። የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ዘሃራ ከድት ስለፌደራሊዝም ጽንሰ ሀሳብ አስመልክቶ ለበዓሉ የተዘጋጀ መወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስልጣን በህዝብ ፈቃድ የሚረጋገጥበት ስርዓት መሆኑን አብራርተዋል። ‎ዴሞክራሲ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተግባራዊ የሚደረግበት መሆኑንም አክለው አስረድተዋል። ‎ወይዘሮ ዘሃራ ከድር ከነጠላ ትርክት በመውጣት የወል ትርክት ላይ ማተኮር ለሀገር እድገትና ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ‎ ‎በአሉን አስመልክቶ የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሀገራችን ዴሞክራሲ የሰፈነባት ብሔር ብሔረሰቦች አብረዉ የሚኖሩባት እንደመሆኗ መጠን መቻቻል የሚታይባት ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። በአንድ ሀገር የዲሞክራሲ ስርዓት የዳበረ ማለት መብትና ግዴታው እንዲሁም ሀላፊነቱ የሚወጣ ዜጋ ተፈጥሯል። ‎ፐብሊክ ሰርቫንቱ አገልጋይ መሆን አለበት ለሀገር እድገትና ብልጽግና ለማሻሻል ማገዝ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል። ‎

ህዳር 05/2018 ዓ.ም በፖለቲካው ዘርፍ ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ውጤቶች ተመዝግበዋል - ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ናቸው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)። በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ ማሳያ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ በተለይም በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ናቸው ብለዋል። በፖለቲካው መስክ የነበረውን አግላይነት በማስቀረት ሁሉንም አሳታፊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል። ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በኋላ በመንግሥት ምስረታ ሂደት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በካቢኔ ውስጥ በማሳተፍ በጋራ እንዲሰሩ መደረጉ አስታውሰው፤ የተለያዩ አመለካከቶች የያዙ የኢትዮጵያ ልጆች በሀገራዊ ጉዳዮች በጋራ መስራት ችለዋል ብለዋል፡፡ ይህ ሂደት መግባባት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲ ለመገንባት ጅማሮ እንደሆነም ተናግረዋል። ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በፖለቲካው ዘርፍ እየተገኙ ከሚገኙ ስኬቶች መካከል አንዱ መሆኑን አንስተዋል። ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ አቅጣጫ ተቀምጦ ትጥቅ ያነገቡ ቡድኖች ሰላማዊ ፖለቲካ እንዲያራምዱ በሩ ክፍት መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ሀገራዊ የፖለቲካ ባህል መቀየሩን ያሳያል ብለዋል፡፡ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የመንግሥት ጥረት ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌና በሌሎችም ክልሎች የነበሩ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ በመፍታት በክልሎቹ ሰላማዊ የልማት እንቅስቃሴ መካሄድ መጀመሩን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ከታጠቁ አካላት ጋር በመነጋገር ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ተደርጓል ነው ያሉት። አሁን ላይ በክልሎቹ የሰላም በር ተከፍቶ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። መረጃው ኤፍ ኤም ሲ

ህዳር 05/2018 ዓ.ም መንግስት ባለሀብቱና ማህበረሰቡን በማስተባበር በተለያዩ ቀበሌዎች ከ90 ሚሊየን ብር በለይ ወጪ የሚደረግባቸው የጠጠር መንገድ ለመገንባት ግብ ጥሎ እየሰራ መሆኑን በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ረጋ ሸሪፍ እንዳሉት በ2018 በጀት አመት በወረዳው ህብረተሰቡን፣ ባለሀብቱንና መንግስት በማሳተፍ በመንገድ ዘርፍ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። በወረዳው መንግስትና ህብረተሰቡ በማቀናጀት 57 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገዶችና 46 የስትራክቸር ስራዎ፣ ትልልቅ ድልድዮች፣ የቱቦ ስራዎች ለመስራት ግብ ጥለው እየሰሩ እንደሆነም አመላክተው ለዚህም ስኬት መንግስት 49 ሚሊየን ብር በመመደብ እንዲሁም ከማህበረሰቡ 45 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ በተለያዩ ቀበሌዎች መንገድ እንደሚሰሩም አመላክተዋል። ባለፉት አራት ወራት 6 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ጠጠር የማንጠፍ ስራ ፣ሁለት ድልድዮች ኮንኪሪት የመሙላት፣ ወደ ስድስት ቱቦዎች የመትከልና ሌሎችም ተግባራት እያከናወኑ እንደነበር አመላክተው ማሽን በማንቀሳቀስ የዳገት ቆረጣ በሰፊው እያከናወኑም እንደሆነ አብራርተዋል። መንገድ ሰፊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያው እድገት የሚረጋገጥበት እንደሆነ የተናገሩት ሀላፊው መንገድ ወላድ እናቶችን ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱና የግብርና ስራዎች የሚያሳልጥ እንደሆነም አብራርተዋል። በአምና ደረጃ አንድ ባለሀብት 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ 6 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ሰርቶ ያስረከ ሲሆን በዘንድሮ በጀት አመት 10 ኪሎ ሜትር እንዲሁም 8 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ በባለሀብት ደረጃ በተለያዩ ቀበሌዎች እየተከናወ ይገኛልም ብለዋል። በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኦቼና አንቀዲ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ደምበል ሸሪፍ እንዳሉት ቀደም ሲል በመንገድ እጦት ምክንያት ለተለያዩ እንግልት ይዳረጉ እንደነበረ ተናግረዋል። ወላድ እናቶች በቃሬዛ ተሸክመው ያወጡ እንደነበረና አሁን ላይ በቀበሌያቸው መንገድ በመሰራቱ ወደ መንደራቸው አምፑላንስ የሚመጣና የሚያመርቱት ምርት ለገበያ ለማውጣት ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸውም አመላክተዋል።