1 321
Підписники
+224 години
+87 днів
+15130 днів
Архів дописів
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ሴቶችን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እንዲበቁ ማስቻል ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት የሴቶችን የአመራር ክህሎት፣ በራስ መተማመን እና የውሳኔ አሰጣጥ ችሎታን ማሳደግ ላይ ያተኮረ የLeadership ስልጠና ሰጥቷል።
በEASE ፕሮጀክት በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በትኩረት ከሚያከናወኑ ተግባራት መካከል ሴቶችን በልዩ ሁኔታ የማብቃትና በሁሉም ዘርፎች የመሪነት ሚና ላይ በንቃት እዲሳተፉ ማስቻል እንደሆነ የገለፁት በኮሌጁ የEASE ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ አክለውም ወቅቱ ሴቶችን ለማብቃት ዘርፈ ብዙ ስራዎች የሚከናወኑበት ጊዜ በመሆኑ ሴት እህቶቻችን አቅማቸውን ለማሰየት ጥሩ መደላድል የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ገልፀዋል::
በእለቱ የተዘጋጀው የLeadership ስልጠና በኮሌጁ ለሚገኙ ሴት አሰልጣኝ መምህራን እና ከየዲፓርትመንቱ ለተወጣጡ ሴት ሰልጣኝ ተማሪዎች ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በመጡት ዶ/ር ፈትያ አማካኝነት ስልጠናውን በጥሩ ሁኔታ መስጠት የተቻለ ሲሆን በቀጣይም መሰል ስልጠናዎችን በተከታታይ በማዘጋጀት ሲቶችን የማብቃት ተግባራት እንደሚከናወኑም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም
ባሉበት የሒሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ!
****
ውድ የባንካችን ደንበኞች፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሠረት፤ ሁሉም ደንበኞች የባንክ አገልግሎቶች ለማግኘት እና ሒሳብ ለማንቀሳቀስ የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
በዚህ መሠረት ባንካችን ደንበኞች ወደቅርንጫፍ ቀርበው የሒሳብ ቁጥራቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ከሚያጣምሩበት አሠራር በተጨማሪ ባሉበት አገልግሎቱን የሚያገኙበትን አማራጭ አመቻችቷል።
በመሆኑም ከታች በተቀመጠው የአሠራር ቅደም ተከተል መሠረት የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (16 አሀዝ-FAN Number) በማስገባት የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያጣምሩ::
1. ይህን ማስፈንጠሪያ 👉 https://cbefayda.cbe.com.et/ በመጫን/ በማስገባት ገፁን ይክፈቱ፣
2. የሂሳብ ቁጥርዎን አስገብተው ‘Get OTP’ የሚለውን ይጫኑ፣
3. ሒሳብ ሲከፍቱ ያስመዘገቡትን የስልክ ቁጥር በሚጠቀሙበት የተንቀሳቃሽ ስልክ የተላከልዎትን የአንድ ጊዜ የሚስጥር ቁጥር (OTP) አስገብተው “Verify OTP” የሚለውን በመጫን ያረጋግጡ፣
4. “Log with OTP” የሚለውን ይጫኑ፤
5. የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን (16 አሀዝ-FAN Number) አስገብተው ‘Get OTP’ የሚለውን ይጫኑ፣
6. በድጋሚ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ የተላከልዎትን የአንድ ጊዜ የሚስጥር ቁጥር (OTP) አስገብተው “Verify” የሚለውን በመጫን ያረጋግጡ፣
7. “Allow” የሚለውን ይጫኑ፣
8. “Accept and Update” የሚለውን ሲጫኑ “Update complete. Pending Approval” የሚል መልእክት ይመጣልዎታል። ጨርሰዋል።
+4
የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፍኬሽን ሥራ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጅታል ሥርዓት ሊገባ ነው
የሙያ ብቃት ምዘና ሰርተፍኬሽን አሰራር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና አሰራሩን ለማዘመን፤ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት አካል ሆኖ የለማውን ዲጂታል የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፍኬሽን ስርዓት ን ወደ ተግባር ማሸጋገር የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ለዘርፉ አስፈጻሚ አካላት መስጠት ተጀምሯል፡፡
በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የምዘና ማዕከላት መረጃ ያካተተው ይህ ስርዓት የሙያ ብቃት ምዘናንም ጭምር ከማንዋል በተላቀቀ መልኩ መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከብቃት ምዘና ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚቀርፍ አሰራር በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በኩል ለምቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህም ባለፉት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በማንዋል በታገዘ መልኩ ሲሰጥና ለተለያዩ ብልሹ አሰራሮች ተጋላጭ የነበረው የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፍኬሽን ሙሉ በሙሉ ወደ ድጅታል ስርዓት ማሸጋገር ያስችላል ብለዋል፡፡
በመድረኩ የለማውን ሲስተም ለመተግበር ዋነኛ ሚና ያላቸው የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሙያ ብቃት ምዘና ኤጀንሲ የሥራ ሃላፊዎች እና የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ባለሙያዎች ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ወጣቶችን በዲጂታል ክህሎት ማስታጠቅ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ግንባታ በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግ እደሚረዳ ተገለፀ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች የ"5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" (5 Million Ethiopian Coders) ስልጠና እንዲወስዱ ለማስቻል የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሄደ::
የ5 ሚልዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ስልጠና ዋና አላማ ወጣቶች የኮዲንግ ክህሎት በመማር የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ስራዎችን እንዲያገኙ ወይም የራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም ሀብት እንዲፈጥሩ ለማስቻል እንደሆነ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ አክለውም የICT ዘርፉ የሀገራችን ኢኮኖሚ ሙሰሶ ተደጎ በትኩረት እየተሰራበት በመሆኑን ጭምር ወጣቶች በቀጣይ ህይወታቸው ለውጥ ሊያመጡ የሚያስችሉ መሰል ክህሎቶች ላይ ትኩረት አድርገው ቢሰሩ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋልም ብለዋል::
ሰልጣኞች ከመደበኛ ትምህርትና ስልጠናቸው ጎን ለጎን ጊዜው የሚሰጠንን ዲጂታል ክህሎቶች መቅሰም ተፈላጊነታቸውን ይበልጥ ያሳድጋል ያሉት ደግሞ የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስራ ሂደት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ መንግስት በነፃ ለዜጎቹ ያመቻቸውን ይህን የ"5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" ስልጠና በአግባቡ በመጠቀም የክህሎት ባለቤትና ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችሉም አስገንዝበዋል::
ሰልጣኞች የ"5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" (5 Million Ethiopian Coders) ስልጠናውን ሲወስዱ ከምዝገባው ጀምሮ ስልጠናውን ተከታትለው ሰርተፊኬት እስከመውሰድ ድረስ ያለውን ሂደት በቅደም ተከተል ግንዛቤ የሰጡት በኮሌጁ የICT ዲፖርትመንት ተጠሪ የሆኑት አሰልጣኝ መ/ር አቤል ፉንታሁን ሲሆኑ በቀጣይም ለዚሁ አላማ በተዘጋጁ የዲፖርትመንቱ Labና በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት ሰልጣኞች የኮዲንግ ስልጠናውን በኮሌጁ እንደሚወስዱ ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሥራና ክህሎት ቢሮ ብልጽግና ህብረት የሴቶች ክንፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።
የጥያቄና መልሱ መርሃግብር አላማም የብልፅግና ፓርቲ ሴት አባላትን ለማብቃት ሲሆን በዚህም በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የፓርቲውን ዕሳቤ የተከተለ ተሳታፊነትን ማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የጥያቄና መልስ ውድድሩ ጥያቄዎች በዋነኝነት በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ሴቶች ክንፍ መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ ላይ ሲሆን ሰፊ ሀገራዊ ጉዳዮችንም የዳሰሰ ሆኗል።
ለጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊዎች ማበረታቻ ሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቷል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሥራና ክህሎት ቢሮ ብልጽግና ህብረት የሴቶች ክንፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።
የጥያቄና መልሱ መርሃግብር አላማም የብልፅግና ፓርቲ ሴት አባላትን ለማብቃት ሲሆን በዚህም በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የፓርቲውን ዕሳቤ የተከተለ ተሳታፊነትን ማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የጥያቄና መልስ ውድድሩ ጥያቄዎች በዋነኝነት በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ሴቶች ክንፍ መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ ላይ ሲሆን ሰፊ ሀገራዊ ጉዳዮችንም የዳሰሰ ሆኗል።
ለጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊዎች ማበረታቻ ሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቷል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአስተደዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚሰሩ የቀን ሰራተኞች በስራ ቦታ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።
መድረኩ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል ከተለያዩ ቦታዎች በስራ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ከሚያዘጋጃቸው ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች አካል መሆኑ ታውቋል፡፡
ቢሮው የቀን ሰራተኛ ዜጋውን ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ አምራች ሃይል ባለሙያ በማዘጋጀት የሚሰሩበት ኢንዱስትሪ ድረስ በመሄድ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለዩኒቨርስቲ እና ኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች የኢንተርፕርነርሺፕ እና የማይንድ ሴት ስልጠና በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ስልጠናው በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ስራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ስራ እንዲፈጥሩ በሚያነሳሳ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተናግረዋል።
በዚህም ተሳታፊ የሆኑ የዩኒቨርስቲ እና የኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ይጠብቁ የነበሩ ከስልጠናው በሚያገኙት ግንዛቤ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለመስራት መነሳሳት እንዲፈጠርባቸው ታሳቢ ያደረገ ሆኗል።
ቢሮው በአስተዳደሩ ትኩረት የተሰጠውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የተጀመሩ የተለያዩ ስራዎችን በተለይም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ተመራቂዎች ተደራጅተው ወደ ሰራ እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ከቀበሌ አንድ ማዕከላት ባለሞያዎች ጋር የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ፡፡
በዚህም ቅድመ ሞዴል፣ ሞዴል፣ እድገት ሽግግርና ከምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ጋር በተያያዘ ኢንተርፕራይዞችን የመለየትና ለሞዴልነት የሚበቁ ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍና ክትትል በሰፊው ለማካሄድና በኢንተርፕራይዞች መረጃ ምዝገባ (LMIS) ዙሪያ የተሰሩትንና በቀጣይ ክፍተትን በመለየት መሰራት የሚገባቸውን ስራዎች የገመገመ ሆኗል፤
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ከአስተዳደሩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ከፍተኛ የማደግ አቅም ያላቸውን ኢንቸርፕራይዞች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አቅማቸውን የሚያሳድግ ስልጠና ተሰጠ።
ይህም ስልጠና ኢንተርፕራይዞቹ ስራቸውን ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለመስራት እንዲችሉና በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እና ሌሎች የተሻሉ አሰራሮችን እዲያውቁና እንዲተገብሩ ያስችላቸዋል።
በዚህም ዶት ኢትዮጵያ የተሰኘ ድርጅት ከድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በኮምፒውተር የታገዘ ስልጠና ለ60 ኢንተርፕራይዞች መሰጠት ተችሏል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
በምርት ማእከላችን የምናመርታቸው ምርቶች
ዘመናዊ አልጋዎች፣የምግቤት እቃዎች፣ዘመናዊ የመመገቢያ ወንበሮች፣የህጻናት አልጋዎች፣ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች፣ዘመናዊ የዶሮ ቤቶች
በጣም በተመጣጣኝ ዋጋን በተሸለ ጥራት እናመርታለን
#ይምጡ ይዘዙን
አድራሻችን፡ ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወደ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን
