1 322
Підписники
+124 години
+77 днів
+14530 днів
Архів дописів
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🇪🇹ሕልምዎን እውን ለማድረግ ትክክለኛውን መንገድ ይምረጡ!
በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ሆነው ዓላማዎን ለማሳካት ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይኖርብዎታል።
በርካታ ዜጎች ህጋዊና ደህንነቱ የተጨበቀ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በማግኘታቸው መብትና ደህንነታቸው እንዲሁም ክብርና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ችለዋል።
ህጋዊ ያልሆነ ስምሪት መብትና ደህንነትዎን አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ መንገድ መሆኑን ያስተውሉ።
እርስዎም በህጋዊ የሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ካሰቡ፤ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ፣ ከትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ያግኙ! 9138 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የመረጃ ማዕከል ነፃ የስል መስመር ነው።
☎️ በ9138 ይደውሉ፡-
👉ስምሪቱ ህጋዊ መሆኑን ያረጋግጡ፣
👉ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፣
👉 አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሪፖርት ያድርጉ
#ህጋዊስምሪት #ደህንነቱየተጠበቀሥራ
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
የድሬዳዋ አሰተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በዛሬው ዕለት በቀበሌ 05 አስተዳደር ስር የሚገኙ የሶስት አቅመ ደካማ እናቶችን የፈራረሰ ቤት በአዲስ ገንብቶ አስረከበ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ከሚገኘው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ አቅመ ደካማ የሆኑ ዜጎችን መደገፍ ነው።
በዛሬው ዕለትም በ05 ቀበሌ የሚገኙት እኚህ ቋሚ የገቢ ምንጭም ሆነ በአጠገባቸው የሚረዳቸው የሌለ፤ በፈረሰና ለመኖር እጅግ የሚከብድ ቤት ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ እየኖሩ የሚገኙ እናቶች ናቸው።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ሠራተኞችና አመራሩ ይህን ችግር በመረዳት የሶስቱን እናቶች መኖሪያ ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርቶ በማጠናቀቅ ከአስፈላጊ የቤት ዕቃዎች ጋር የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
ማስታወቂያ ለዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!!
በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካምፓስ በ2018 የትምህርት ዘመን በመደበኛው ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች በተጨማሪ በመጀመርያ ዲግሪ በምሽት (Extension) እና በቅዳሜ እና እሁድ (weekend) መርሃግብር፤ በAutomotive Technology: በConstruction Technology: በElectrical Electronics Technology: በGarment Technology እና በManufacturing Technology የቅበላ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ይገልፃል::
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ዜና|ድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በራስ አቅም ያስጠናው የምሩቃን እና የስራ ገበያና ፍላጎት የጥናት ውጤት ሪፖርት የተለያዩ ባለድርሻ አካላቶች ባሉበት ቀረበ፡፡
ይህ ጥናት እንደ አስተዳደር እንዲሁም በኮሌጅ ደረጃ ያለብንን ክፍተት የለየና በቀጣይ በምን አይነት መልኩ ስራዎችን መስራት እንዳለብን ያሳየ ጥናት ነው ያሉት የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽግግር ምክትል ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ ወጣቶችን አሰልጥኖ ማስመረቅ ብቻ ሳይሆን በሰለጠኑበት ሙያ ለሀገር እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ሰልጣኞችን ወደ ገበያው ማስገባትና ክትትል ማድረግ ይገባናል ሲሉ ም/ዲኗ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በዳሳ ጥናቱ የተገኙ ግብአቶችን እቅድ ውስጥ በማካተት የሚሰራ ይሆናል ።በመጨረሻም ለዚህ ጥናት መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጥናቱን አስመልክቶ የኮሌጁ ጥናትና ምርምር ቡድን መሪ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ አበራ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በኮሌጁ አቅም ተመሳሳይ ጥናት መደረጉን አስታውሰው አሁን የተጠናው ጥናት በራስ አቅም ማስጠናት መቻላችን በወጪ ረገድ ዋጋ ቆጣቢ የሆነና ከመረጃ ጥራት ጋር በትኩረት መስራት እንድንችል ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጃችን ከኢንዱስትሪው ጋር የማስተሳሰር ስራ እንዲሁም ቀሪ ጥናቶችን ደግሞ ሁሉን አሳታፊ አድርገን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም staff exchange የተገኘውን ተሞክሮ በአቶ ሽመክት ክፍሌ የቀረበ ሲሆን ከተሞክሮው አንጻር የተገኘው ልምድ ለድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አካላቶች ተግባራዊ ቢደረግ ብዙ ለውጦች ማምጣት እና ሰልጣኞቻችን ከተለመደው የስልጠና አሰጣጥ በመቀየር ፕሮጀክት ላይ ትኩረት ባደረገ እና ኢንዱስትሪውን መሰረት ባደረገ መልኩ ስልጠናዎችን መስጠት እንድንችል ረድቶናል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይም የሁለቱም ኮሌጆች ዲኖችና ም/ዲኖች እንዲሁም ፤የኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርድ አባላቶች እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡
ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
ለወቅታዊ ትኩስ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መረጃ
You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC)
Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute
Telegram: t.me/Dire Dawa Polytechnic College
TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege
እንደ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተነቃቃ ከመጣው ኢንዱስትሪዎች የተነሳ የነፃ ንግድ ቀጠና፣ ደረቅ ወደብና ትልልቅ አቅም የሆኑ ተቋማት አየተፈጠሩ ስለሆነ ለሀገር ውስጥ ስራ ፈጠራ ትልቅ አቅም ሆኖልናል።
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
የመንግስት ሠራተኞች አዲሱ አዋጅ 1353/2017 ስለ ዲሲፒሊን ቅጣት ምን ይላል? For your understanding.
ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች አንቀፅ 69/5 #አዋጁ እንዲህ አስቀምጦታል።
+++++++++++++++++++++++++
1.ሕጋዊ_ትእዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመልገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤
2. ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤
3. ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤
4. በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤
5. በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነትን መደባደብ፤
6. በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤
7. ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤
8. በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤
9. የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤
10.የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤
11. በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
12. በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም፤
13. በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም እና
14.በዚህ አንቀፅ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈፀም ።
++++++++++++++++++++++++++
ሠራተኛን ከሥራ አግዶ ስለማቆየት
አንቀፅ 72/1 እና 2
++++++++++++++++++++++++++
1.ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ከሥራ አግዶ ማቆየት የሚቻለው
(ሀ)ከተጠረጠረበት ጉዳይ ጋር አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማበላሸት:በመደበቅ ወይም በማጥፋት ምርመራውን ያሰናክላል
(ለ)በመንግስት ንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያደርሳል
(ሐ)ከተከሰሰበት ጥፋት ክብደት አንፃር የሌሎችን ሰራተኞች ሞራል የሚነካ ወይም የተገልጋዩን ሕዝብ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ሊኖረው የሚገባውን እምነት ያዛባል
(መ)ተፈፀመ የሚባለው ጥፋት ከሥራ ያስወጣል ተብሎ ሲገመት ነው
2.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት አንድ ሠራተኛ ከሥራና ከደሞዝ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው ከሁለት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ይሆናል።
የመንግስት ሠራተኞች አዲሱ አዋጅ 1353/2017 ስለ ዲሲፒሊን ቅጣት ምን ይላል? For your understanding.
ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች አንቀፅ 69/5 #አዋጁ እንዲህ አስቀምጦታል።
+++++++++++++++++++++++++
1.ሕጋዊ_ትእዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመልገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤
2. ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤
3. ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤
4. በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤
5. በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነትን መደባደብ፤
6. በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤
7. ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤
8. በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤
9. የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤
10.የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤
11. በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
12. በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም፤
13. በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም እና
14.በዚህ አንቀፅ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈፀም ።
++++++++++++++++++++++++++
ሠራተኛን ከሥራ አግዶ ስለማቆየት
አንቀፅ 72/1 እና 2
++++++++++++++++++++++++++
1.ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ከሥራ አግዶ ማቆየት የሚቻለው
(ሀ)ከተጠረጠረበት ጉዳይ ጋር አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማበላሸት:በመደበቅ ወይም በማጥፋት ምርመራውን ያሰናክላል
(ለ)በመንግስት ንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያደርሳል
(ሐ)ከተከሰሰበት ጥፋት ክብደት አንፃር የሌሎችን ሰራተኞች ሞራል የሚነካ ወይም የተገልጋዩን ሕዝብ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ሊኖረው የሚገባውን እምነት ያዛባል
(መ)ተፈፀመ የሚባለው ጥፋት ከሥራ ያስወጣል ተብሎ ሲገመት ነው
2.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት አንድ ሠራተኛ ከሥራና ከደሞዝ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው ከሁለት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ይሆናል።
በአስተዳደሩ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማትን የሚደግፉ ፕሮጀክቶች ከቢሮውና ብድር ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር ያላቸው ቅንጅታዊ አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡
በዚህም አቶ ተፈሪ ታደሰ የኢኔብሊንግ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ፣ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኢኔብሊነግ ኢትዮጵያ ሲንየር አማካሪ፣ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እንዲሁም የቢሮው ባለሙያዎች በተገኙበት የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ቀርቦ በመስክ ምልከታ የታዩ ጉዳዮችን ጨምሮ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በመስክ ምልከታ አፈጻጸማቸው ከታየ ፕሮጀክቶች ጥላ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የገጠር ወጣት ሴቶች ቀጣይነት ያለው የኑሮ መሻሻል እንዲፈጠር መነሻ ካፒታል የሚሆን የሶስት አመት ከዋስትና ነጻ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እና ቢዝነሶቹን በቅርበት ውጤታማነታቸውን በመከታተል መደገፍ ላይ ያለበት ደረጃ ታይቷል።
ሌላኛው አፈጻጸሙ የታየው ሳፊ ፕሮግራም ሲሆን ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራና መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ብድሮችን በማቅረብ በተለይ ለኢ-መደበኛ ተበዳሪዎች በመታወቂያ ብቻ ብድሮችን ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆነ በAI ታግዘው ብድሮችን ያመቻቻሉ፤ በዚህም በዋናነት 80% ሴቶች፣ 10% ለአካል ጉዳተኞች እና 10% ለተፈናቃዮች ትኩረት አድርጎ የሰራቸው ስራዎች በተጨባጭ ምን ላይ እንደሚገኙ ምልከታ ተደርጎባቸዋል፡፡
በተጨማሪም መስመር ፕሮግራም የብድር አገልገሎት ሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታትና ሥራቸውን ለማስፋፋት የሚሰጠውን የብድር አገልገሎት በአስተዳደሩ የሚገኙ በተለይም በወጣት ሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመጠነኛ ዋስትናና በአነስተኛ የወለድ መጠን እንዲሁም የሸሪአ መርህን የተከተለ ከወለድ ነጻ የብድር አገልገሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ተጠቃሚዎችን በአካል በማነጋገር ያሉበትን ሁኔታ መመልከት ተችሏል፡፡
ቢሮው ከማስተር ካርድ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን የ2025 የመጀመሪያ ሩብ አመት የአምስቱም አጋር ድርጅቶች ሪፖርት በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ዘመን የአዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ምዝገባ ከጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም ድረስ የሚያከናውን መሆኑን እናሳውቃለን::
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
እንቁ ባለሙያዎችን የሚያፈራው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ዘመን የአዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ምዝገባ ከጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚያከናውን መሆኑን እናሳውቃለን::
