1 331
Підписники
Немає даних24 години
+97 днів
+8030 днів
Архів дописів
በገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ በቡድን በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ አንቀሳቃሾች ሙያዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፤
ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉ አንቀሳቃሾች በአስተዳደሩ ወረዳ 2፣ በቢዮ አዋሌ እና ዋሂል ክላስተሮች የሚገኙ አራት ኢንተርፕራይዞችን የሚያንቀሳቅሱ 30 አንቀሳቃሾች ሲሆኑ 90 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
ይህንን ስልጠና ያዘጋጀው የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ስር የሚገኘው የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ነው፤ ፕሮግራሙ የተለያዩ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በሥራ ዕድል ፈጠራው አቅጣጫ ለኢንተርፕራይዞቹ ከስልጠናው ባሻገር 300 እንቁላል ጣይ ዶሮ ለእያንዳዳቸው ለሁለት ወር የሚበቃ መኖ ድጋፍ ያደረገላቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቀን ወደ ሁለት መቶ እንቁላል እየጣሉ ይገኛል፤
ፕሮግራሙ በስልጠናም ሆነ በአይነት የሚደረጉት ድጋፎች የአንድ ጊዜ ብቻ እንዳልሆነ እና በየአመቱ ለተከታታይ ስድስት አመት ለኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለክቡራን ተገልጋዮቻችን በሙሉ
***
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ቅዳሜ ጳጉሜ 02 ቀን 2016 ዓ.ም “ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሪፎርም ቀን አስመልክቶ በዕለቱ ቢሯችን ሙሉ ቀን ለአገልግሎት ክፍት ሆኖ ስለሚውል ክቡራን ተገልጋዮቻችን በዕለቱ መጥተው የአገልግሎታችን ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እናሳውቃለን።
ቢሮው
ለክቡራን ተገልጋዮቻችን በሙሉ
***
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ቅዳሜ ጳጉሜ 02 ቀን 2016 ዓ.ም “ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሪፎርም ቀን አስመልክቶ በዕለቱ ቢሯችን ሙሉ ቀን ለአገልግሎት ክፍት ሆኖ ስለሚውል ክቡራን ተገልጋዮቻችን በዕለቱ መጥተው የአገልግሎታችን ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እናሳውቃለን።
ቢሮው
+2
#ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!!!
#ጳጉሜ 1 "የመሻገር ቀን"፣
#ጳጉሜ 2 "የሪፎርም ቀን"፣
#ጳጉሜ 3 "የሉዓላዊነት ቀን"፣
#ጳጉሜ 4 "የኅብር ቀን"
#ጳጉሜ 5 "የነገው ቀን"
.......
#Danoomni Walabummaa hunda galeessaaf!!
#Qaammee 1 " Guyyaa ''Cehuumsaa"
#Qaammee 2 " Guyyaa "Riifoormii"
#Qaammee 3 " Guyyaa "Walabummaa"
#Qaammee 4 " Guyyaa "Danoomaa"
#Qaammee 5 " Guyyaa "Boruu"
......
#Hal-ku-dhagyada maalmaha Baagume!!
#Maalinta 1 "Ka gudubka caqabada
#Maalinta 2 "Dib uhabaynada"
#Maalinta 3 "Madaxbanaanida"
#Maalinta 4 "Iskaashiga"
#Maalinta 5 "Rajada barri"
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ የጋራ አገልግሎት ሰራተኞች በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አዘገጃጀት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ አካሄደ::
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ያስፈለገበት ዋና አላማ ፈፃሚዎች ላይ ከዚህ ቀደም የሚታየውን የእቅድና ሪፖርት አዘገጃጀትን ክፍተት ለመሙላት እንዲሁም ሰራተኛው የተሰጠውን የስራ ሀላፊነት በዝርዝር ተረድቶ በሀላፊነት ስሜት እንዲተገብርና የሚጠበቅበትን እቅድን ሪፖርት በወቅቱ እንዲያዘጋጅ በማድረግ በሚፈለገው አቅጥጫ ለማስኬድ ታልሞ የተዘጋጀ የግንዛቤ መስጫ ስልጠና ነው::
ኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ነሃሴ 29/2016 ዓ.ም
የውጭ ሃገር የስራ ዕድል ምዝገባን በተመለከተ !
ለሚመለከተው ሁሉ
በውጪ ሃገር የስራ እድል ላይ ለመሳተፍ መመዝገብና የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ በርካታ አመልካቾች እንዳላችሁ ይስተዋላል፤
ምዝገባ በማድረግ የአማራጩ ተጠቃሚ መሆን የምትፈለጉ ዜጎች ምዝገባ ማድረግ የምትችሉበትን ሁኔታ በቅደም ተከተል በተዘጋጀው ቪዲዮ መመልከት ትችላላችሁ።
መልካም ዕድል !
የሥራዎ ባለቤት እርስዎ ነዎት !
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
#ለ2ኛ ዙር የሠመርካምፕ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር ምዝገባ ተጀመረ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ያዘጋጁት በአይነቱ ልዩ የሆነ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ወጣቶች የፈጠራ ሐሳባቸውን እና ችሎታቸውን ወደ ተጨባጭ ሥራ እንዲለውጡ በማስቻል ለአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ አበርክቶ ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ማስገኘት የሚያስችል ነው።
በዚህ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል። ስለሆነም በማንኛውም መስክ የቴክኖሎጂ እና የሥራ ፈጠራ ሐሳብ ያላችሁ በሙሉ ከነሐሴ 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።
https://forms.office.com/r/CNMFUUSZZe
#ማሳሰቢያ
📌 ምዝገባው የሚካሄደው በተቀመጠው ድህረገጽ ብቻ ነው
📌ከምዝገባ በኋላ በሚካሄድ ልየታ መሠረት ለሚመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የሠመር ካምፕ ፕሮግራሙ የሚካሄደው አዲስ አበባ ላምበረት መነሀሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ካምፓስ ነው።
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ
ነሃሴ 27/2016
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
በአገር አቀፍ ደረጃ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና አሰልጣኞችና አስተባባሪዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ማለትም ድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና ኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ላይ የሚያሰለጥኑ አሰልጣኝ መምህራን በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኝ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎን በበጎ አድራጎት ስራዎች የደም ልገሳ መርኃግብር አካሂደዋል፤
ዘርፉን ከስልጠና በላይ በማሰብ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ በምንሰራው ስራ አጠቃላይ ኢኮኖሚውን ትራንስፎርም የሚያደርግ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠርም አልፎ የዘርፉን አቅም በመጠቀም ፈጥነን ከድህነት እንድወጣም የሚያስችል ነው፤ ከዚህ በመነሳት እነዚህን እሳቤዎች የዘርፉ ሁሉም አሰልጣኝ መምህራን በግንዛቤ የጨበጧቸውን ወደ ተግባር በመቀየር በቀጣይም በስልጠና ማዕከሉ አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦችን በበጎ አድራጎት ስራዎች ተደራሽ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የአስተዳደሩን አሰልጣኝ መምህራን በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና እና የዘርፉ እሳቤ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እንዲሁም የአሰልጣኞችን ባህሪያዊና ቴክኒካዊ ብቃት ለማሳደግ ያለመ ስልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ ይገኛል።
በሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ም/ኃላፊ ክብርት ፈጡም ሙስጠፋ ሀሮማያ ዩኒሸርሲቲ በመገኘት የስልጠና ሂደቱን ተመልክተዋል። በምልከታው ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር በስልጠናው የሚሳተፉ አሰልጣኝ መምህራን ጋር በመነጋገር አበረታቸዋል፡፡
የቢሮው ኃላፊዎች በቆይታው ከሰልጣኞችና ከስልጠና አስተባባሪዎች ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን ስልጠናው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሆነ እና እንደ አስተዳደር የተሰሩ ስራዎች በተሞክሮ መቅረባቸው ተጠቁሟል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራንና የስልጠና አስተባባሪዎች ስልጠና ተጀመረ፡፡
በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የአሰልጣኞችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት ማዘጋጀት ዓላማ ያደረገ ሲሆን እንደ አገር 17 የስልጠና ማዕከላት 24 ሺህ የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት ይካሄዳል፡፡
በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ላይ የሚያሰለጥኑ 285 የሚሆኑ አሰልጣኝ መምህራንና የስልጠና አስተባባሪዎች በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ማዕከል ስልጠናውን የሚከታተሉ ይሆናል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ከትምህርት ሚኒስቴርና ከድሬዳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በግብርና ናሙና ቆጠራ ላይ ለተዘጋጀው ስልጠና የመክፈቻና የኦረንቴሽን ፕሮግራም በማዘጋጀት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።
በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በአስተዳደሩ የከተማና የገጠር ወረዳዎች የተመዘገቡ ዜጎችም ተሳታፊ ሆነዋል።
የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ እንደተናገሩት በመንግስትም ይሁን በግል የሚካሄዱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያቤት ጀምሮ በዘመናዊና ዲጂታላይዝ ስርዓቶች የሚመሩ መሆናቸው ውጤት እያስገኙ እንደሚገኝ ማሳያ ይሆናል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 20/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
