1 326
Підписники
+224 години
+87 днів
+9730 днів
Архів дописів
በአስተዳደሩ የገጠር አራቱም ወረዳዎች ስር የሚገኙና በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ ምልከታና ልየታ ቀጥሎ በአሰሊሶ ወረዳ ተካሄደ።
በዛሬው ዕለትም በአሰሊሶ ወረዳ የተለዩ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምልከታ የተደረገ ሲሆን ቀሪ የአስተዳደሩ ገጠር ወረዳዎች ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በተመሳሳይ ምልከታ እና ልየታ የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በፊት ይነሳ የነበረውን የተደራሽነት ጥያቄዎች ለመመለስ የቢሮው አቅጣጫ አካል መሆኑም የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሀ/ማርያም አስታውቀዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ወጣቶች የፈጠራ ሃሳባቸውን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ እንዲያዳብሩ በማድረግ በክህሎት የዳበረ ዜጋ የማፍራት ተገባርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ::
የሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ትምህርቶችና ፈጠራ ላይ ዝንባሌ ያላቸው የ STEM ክበብ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ጉብኝት በኮሌጁ አካሄዱ::
ኮሌጁ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ የፈጠረውን ግንዛቤ በተጠናከረ መልኩ ውጤታማ ለማድረግ በት/ቤቶች ላይ የቴክኒክና ሙያ ክበብ እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በዚህም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ክበቡን እንዲቀላቀሉ ማድረግ መቻሉም ተገልፇል::
ለተማሪዎቹ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በመልእክታቸውም በቅድሚያ በቀጣይ የክህሎት ባለቤት ወደ ምትሆኑበት ኮሌጃችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ኮሌጁ ት/ቤቶች ላይ በስፋት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተማሪዎችን በዘላቂነት በክህሎት ለማብቃት ታሳቢ በማድረግ ይህን የቴክኒክና ሙያ ክበብ በየት/ቤቶች እንዲቋቋም አድርገናልያሉ ሲሆን ተማሪዎች በቀጣይም በኮሌጁ የሚኖራችሁን ቆይታ በምትፈልጉት ሙያ መስክ ራሳችሁን ለማብቃት ልትጠቀሙበት ይገባልም ብለዋል::
ተማሪዎች ኮሌጁ ያለውን የማሰልጠን አቅም ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላም በቀጣይ ለክበብ አባላቱ የህይወት ክህሎትና STEMን መሰረት የደረጉ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ የገለፁት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም የSTEM አባላቱ ከመደበኛ ትምህታቸው ጎን ለጎን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ምቹ አጋጣሚ ይፈጠርላቸዋልም ብለዋል::
በተጨማሪም ተማሪዎቹ በኮሌጁ ቆይታቸው የጥናት፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ አስተባባሪ በሆኑት አሰልጣኝ መ/ር ያሬድ ሁሉአለም አማካኝነት ስለ STEM power ፅንሰ ሀሳብ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በተጨማሪም በክፍሉ አስተባባሪነት በኮሌጁ የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን ለተማሪዎቹ እስጎብኝተዋል::
የSTEM ክበብ አባላት በተቋሙ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ወርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በየዲፖርትመንቶቹ ስለሚገኙ የሙያ ስልጠናዎች በተመለከተም በአሰልጣኝ መምህራ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ተደርጎላቸዋል::
በቀጥይ የቴክኒክንይ ሙያ STEM ክበብ አባላት በኮሌጁ በሚዘጋጅላቸ የሙያ ስልጠናዎችን የሚወስዱ ሲሆን ይህም የ2ኛ ደረጃ ትምህታቸውን ከማጠናቀቃቸው አስቀድሞ ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑም የሚያስችላቸው እንደሚሆን ተግልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ዜና| በኮሌጁ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ግንባታ ሂደት ተጠናቆ በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡
በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር መተግበር ላይ ያለው የEASTRIP ፕሮጀክት ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ፣ከEASTRIP National Project Coordinator ቢሮ በተውጣጣ የSupervision team የልህቀት ማዕከሉን የህንጻው ግንባታ አፈጻጸም ገመገሙ፡፡
በኮሌጁ እየተተገበረ ያለው ይህ የ EASTRIP ፕሮጀክት መሳካት በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም በኮሌጁ ማኔጅመንት ትልቅ ድጋፍና ክትትል እየተደረገበት አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ያሉት ልኡክ ቡድኑን የተቀበሉትና የግንባታውን ሂደት ያስጎበኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም ይህ የልህቀት ማእከል ግንባታው እንዲጠናቀቅና ለታለመለት አላማ መዋል እንዲችል አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮ፣ለኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት፣ለ EASTRIP ፕሮጀክት ሰራተኞች እንዲሁም ለኮሌጁ ሰራተኞች ከልብ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ከሪፖርቱና ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ በቀረበው አፈጻጸም ላይ ልኡክ ቡድኑ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ፕሮጀክቱ ውጤታማ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱን ያረጋገጡ ሲሆን በቀጣይ ወር በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እንዲመረቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+7
#ዜና|ድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የፖሊስ አባላት በመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ፡፡
ኮሌጃችን የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በትምህርትና ስልጠና ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሰራን እንገኛለን ያሉት የኮሌጁ ም/ዲን እና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ በሆኑት በአቶ አብዱልፈታህ አፈንዲ ሲሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድግ የሚችሉ ከ42 በላይ የአጫጭር ስልጠናዎችን እንዲሁም ከ12 በላይ ትምህርት ክፍሎች የተለያዩ የሞያ ትምህርቶችን አዘጋጅቶ ስልጠናዎችን በመስጠት የስራ ባለቤት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ይህ በዛሬው እለት የተጠናቀቀው የ2ተኛ ዙር ስልጠናም በተለያዩ ዙሮች የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡
በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት የፖሊስ አባላትም በስልጠናው ያገኙትን ችሎታ በስራ ቦታቸው ላይ ተግባራዊ እንደሚያደርጉትና በቀጣይም በኮሌጁ በሚሰጡ የተለያዩ ሞያዎችን እንደሚሰለጥኑ ተናግረዋል፡፡ስልጠናውም ላመቻቹት ለጠቅላይ መምሪያውና ለኮሌጁ እንዲሁም ስልጠናውን ለሰጧቸው መምህራን ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም በስልጠናው ላይ ተሳታፊ የሆኑት የፖሊስ አባላት በኮሌጁ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም የተለያዩ ትምህርት ክፍሎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ ላይም ስለኮሌጁ እንቅስቃሴ በICT ትምህርት ክፍል ተጠሪ አቶ ቴዎድሮስ አስፋው እና በሬጅስትራር ኃላፊ አቶ ፋሚ ኑረዲን ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የመጋቢት 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የፈጠራ ሃሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየር በስፋት እየተከናወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የሚመራ የኮሌጁ የቦርድ አባላት በተቋሙ የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችና ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
በቦርድ አባላቱ የተጎበኙት የፈጠራ ውጤቶችና ፕሮጀክቶች በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ከፍተኛ ጥረትና በኮሌጁ ያልተቋረጠ ድጋፍ የተሰሩ ሲሆን የማህበረሰቡን ችግር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚፈቱ ታምኖባቸው የተሰሩ እንደሆነም ተገልፇል::
በኮሌጁ ችግር ፈቺ ተብለው ከተሰሩ የፈጠራ ስራዎችና ፕሮጀክቶች መካከልም......
1.በአንድ በሬ ማረስ የሚያስችል የእርሻ ማረሻ ፈጠራ፣
2. የዘር ብክነትን የሚያስቀር ዘር መዝርያ ማሽን፣
3. በአንድ ጊዜ 500 እቁላሎችን ማስፈልፈል የሚችል ማሽን፣
4. እፅዋትን ጨምሮ ከተለያዩ ግብአቶች የተመረተ የነዳጅ ዘይት፣
5. ዘመናዊ የመንገድ ዳር ቁሻሻ ማጠራቀሚያ፣
6. ለኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ውበት የሚያጎናፅፍ ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ሼድ፣
7. የመንገደኞች ማረፊያ አግዳሚ ወንበር... የሚገኙበት ሲሆን በቀጣይ በስፋት ተመርተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ እንደሚደረግም ተገልፇል::
ኮሌጁ የፈጠራ ሃሳብ ማበልጸጊያ ማዕከል እንዲሁም የኢንተርፕራይዞች መፍለቂያ ተቋም መሆኑን በተግባር እያሳየ እንደሆነ ተመልክተናል ያሉት የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አክለውም በቀጣይ የተጀመሩ ስራዎችን በፍጥነትና በጥራት በማከናወን የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ከመፍታት በተጨማሪ ተቋሙም የራሱን ገቢ ማሳደግ ያስችለዋልም ብለዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአብይ ፆምን እና የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ::
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የታላቁን አብይ ፆምን እና የታላቁን ረመዳን ወር ጾምን ወቅትን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ማህበረሰብ አካላቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንና በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ማዕድ አጋርቷል።
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመማር ማስተማር ሂደቱ በዘለለ ማህበረሰባዊ እሴቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ባህልን ለማጠናከር ይሰራል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም በጾሙ ወቅት ስንሰራቸው የነበሩ በጎቶች ከጾሙ ውጪም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ለዚህ መርሃ ግብር መሳካት አስተዋጽኦ ላላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት አካላቶች ለታላቁ የረመዳን ወርና ለአብይ ፆም እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመዳጋገፍ ባህልን ማዳበር እንደሚገባና ይህንንም ተግባር የኮሌጁ ማህበረሰብ ማስቀጠል እንደሚገባቸው እንዲሁም ይህንን ተግባር ሌሎችም አካላቶች ሊከተሉትና እንደ አርአያ ወስደው ሊተገብሩት እንደሚገባ ተናግረዋል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአብይ ፆምን እና የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ::
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የታላቁን አብይ ፆምን እና የታላቁን ረመዳን ወር ጾምን ወቅትን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ማህበረሰብ አካላቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንና በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ማዕድ አጋርቷል።
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመማር ማስተማር ሂደቱ በዘለለ ማህበረሰባዊ እሴቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ባህልን ለማጠናከር ይሰራል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም በጾሙ ወቅት ስንሰራቸው የነበሩ በጎቶች ከጾሙ ውጪም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ለዚህ መርሃ ግብር መሳካት አስተዋጽኦ ላላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት አካላቶች ለታላቁ የረመዳን ወርና ለአብይ ፆም እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመዳጋገፍ ባህልን ማዳበር እንደሚገባና ይህንንም ተግባር የኮሌጁ ማህበረሰብ ማስቀጠል እንደሚገባቸው እንዲሁም ይህንን ተግባር ሌሎችም አካላቶች ሊከተሉትና እንደ አርአያ ወስደው ሊተገብሩት እንደሚገባ ተናግረዋል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ላይ ያተኮረ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተካሄደ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በዘርፉ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን እና ባለሙያዎች እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡
በዚህም በዘርፉ ላይ በተለይም በኮሌጆች ላይ በአሰልጠኝ መምህሩ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በሰልጣኝ ተማሪዎች ላይ የሚስተዋሉ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮች ማለትም አውቶሜትድ የተማሪዎች አቴንዳንስ ማኔጅመንት ሲስተም፣ ከጤና እና ደህንነት አጠባበቅ፣ የቢዝነስ ፕላን ጥራትና ውጤት ማሻሻል፣ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ(ቦሎ) እና የማህበረሰብ ድጋፍ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ጥናቶች ቀርበው ውድድር የተካሄደ ሲሆን ከተወዳዳሪዎችም አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ድሬዳዋን ወክሎ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡
ይህም ውድድር በዋነኛነት ለዘርፉ ችግር ፈቺ የሆኑ ሃሳቦች በማፍለቅ አሰራሮችን ለማሻሻል እና ለመከለስ በግብዓት የሚየገለግሉ እንደሚሆኑና ተወዳዳሪዎች በኮሌጆቻቸው በተግባር ፈትነው ያቀረቧቸው እነዚህ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮች ለዘርፉ መሻሻልና ማደግ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 18/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የብልፅግና ህብረት አባላት የውይይት መድረክ አካሄዱ።
በለውጡ ሂደት ውስጥ የተሰሩ ሰው ተኮር ስራዎች፣ የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን፣ የልማት ስራዎች ውጤታማነት እና ሌሎችንም መሰል ዝርዝር ሀሳቦችን በመድረኩ ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
የመጋቢት ወር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ኩነቶችን ያሳለፈ እንደሆነና ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ አበይት ጉዳዮች የተከናወኑበት መሆኑን የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመግለፅ በኢትዮጵያ ራስን የመቻል ልዕልና ውሳኔ ማሳያ የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበትና የማጠናቀቂያ ዋዜማ ታሪካዊ ወር መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩ "የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች" ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 18/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
