uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 321
Підписники
+224 години
+87 днів
+15130 днів
Архів дописів
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የፋይናንስ ዘርፉ ግስጋሴ!💰 ****** በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የተዛባውን ኢኮኖሚ ከማረጋጋት ባለፈ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ አዳዲ
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የፋይናንስ ዘርፉ ግስጋሴ!💰 ****** በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የተዛባውን ኢኮኖሚ ከማረጋጋት ባለፈ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ አዳዲስ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። የዘርፉ ዋና ዋና ለውጦች፡- 🔹 ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን እየሆነች ነው፡ የባንክ አሰራርን ዘመናዊና ተደራሽ በማድረግ፣ የገንዘብ ዝውውርና የዲጂታል አገልግሎቶች በከፍተኛ ፍጥነት እንዲስፋፉ አስችሏል። 🔹 ቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ እድገት፡ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለዜጎች ምቾትን ከመፍጠር ባለፈ፣ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት የላቀ አበርክቶ እያደረገ ይገኛል። 🔹 የፋይናንስ አማራጮችና የቦንድ ሽያጭ፡ መንግሥት የቦንድ ሽያጭን እንደ አንድ የፋይናንስ አማራጭ መጠቀሙ፣ ዜጎች በሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ "የእኔነት" ስሜት ኖሯቸው እንዲሳተፉ በር ከፍቷል። ባለሙያዎች ምን ይላሉ? 🎙️ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የፈቃድና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ ኢድሪስ ሰልማን ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ "ዜጎች የመንግሥት ቦንድ በመግዛት ለሀገር ግንባታ የፋይናንስ አቅም ከመፍጠር ባለፈ፣ ገንዘባቸውን አዋጭ በሆነ ኢንቨስትመንት ላይ እያዋሉ መሆኑን መገንዘብ ይገባቸዋል።" በማህበረሰቡ ተሳትፎና በሀገር ውስጥ ሀብት የሚገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ ለሀገር ትልቅ አቅም ከመሆናቸውም በላይ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጡ ናቸው። 🇪🇹

በዛሬው እለት በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የከተራና ጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በጀርባ ሰፈር ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ለምእመናኑ የሚታደል የታሸገ ውሃና ለማእድ ማጋራት
+3
በዛሬው እለት በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የከተራና ጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በጀርባ ሰፈር ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ለምእመናኑ የሚታደል የታሸገ ውሃና ለማእድ ማጋራት የሚሆኑ የተለያዩ ነገሮችን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ ስም ለፖሊስ ጣቢያው አስረክበናል። በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ በዓሉ የፍቅር የአንድነት እንዲሆንላችሁ በኮሌጁና በኮሌጁ ማኔጅመንት ስም መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ጥር 10/2018 ዓ.ም አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን

አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ለከተራና ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። የተከበራችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድ
+2
አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ለከተራና ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። የተከበራችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉ ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር የአብሮነታችን መገለጫ ከመሆኑም በተጨማሪ የሀገርና የህዝብ ሃብት እንዲሁም የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበ ስለሆነ በዓሉን ስናከብር ሀገራዊ ገፅታን በሚያሳድግ መልኩ ማክብር ይገባናል። ህዝበ ክርስቲያኑም በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን በማብላት በማጠጣት እንዲሁም ከሁሉም ህብረተሰብ ጋር ሠላምና አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ ማክበር ያስፈልጋል። በድጋሚ እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ። አደረሰን። መልካም በዓል!                    አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

ኮሌጁ የታዳጊና ወጣቶችን ፈጠራ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአስተዳደሩ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሄደ:: በመድረኩ ለታዳጊዎች መልዕክት ያስተለፉት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ዋና ስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ በንግግራቸውም በቅድሚያ የብቁ ሞያተኞችና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች መፍለቂያ ወደ ሆነው ተቋማችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን እዚህ እንድትገኙ የሆነበት ምክንያት አሁን ላይ በንድፍ ምትማሯቸውን ትምህርቶችን በተግባር ችግሮችን ለመፍታት የምትጠቀሙበትን አግባብ ለማስገንዘብ እንዲሁም ያላችሁን የፈጠራ ሀሳብ ከወዲሁ መሰረት የምታሲዙበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሆነም ገልፀዋል:: ባደጉት ሀገራት ከፍተኛ ተከፋይ መሆን የሚያስችሉት የክህሎት ሙያዎች እንደሆኑ የገለፁት በኮሌጁ የEASE ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢ/ር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ እንደ ፕሮጀክት በነዚህ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ስናስብ አስተዳደሩ ላይ ያሉ ወጣቶች የራሳቸው ሙያ ኖሯቸውና ከስራ ጋር ተገናኝተው እራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን እንዲደግፉ ለማስቻል ነውም ብለዋል:: በመድረኩ የፈጠራ ሀሳብን ወደ ተግባር አሳድጎ ችግር ፈቺ ቢዝነሶችን እውን የማድረግን ፅንሰ ሀሳብ በተመለከት የጥናትና ቴክኖሎጂ ሽግግር አስተባባሪ በሆኑት አቶ ያሬድ ሁሉአለም አማካኝነት ግንዛቤ መፍጠር የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ(STEM) ምንነትና በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለታዳጊዎቹ ግንዛቤ ሰጥተዋል:: በቀጣይም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ታዳጊዎች በመለየት ሀሳባቸው ወደ ችግር ፈቺ ቢዝነሶች መለወጥ የሚያስችላቸውን ክህሎቶች በተቋሙ እንደሚሰጣቸውም ተገልፀዋል:: በእለቱ በተካሄደው የግንዛቤ መድረክም የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህርትና እና ሰልጣኝ ተማሪ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎቹ በዘርፉ ያደረጏቸውን ስኬታማ ጉዞዎች እና የህይወት ልምዳቸውን ማካፈልም ችለዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥር 9/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

"በአስተዳደሩ በስራ እድል ፈጠራ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏ".. ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ በኢፌድሪ የሥራ እና ክህሎት ሚንስቴር የተመራው የድጋፍ እና ክትትል ልዑክ ቡድን በሶማሌ፣በሐረር ክልሎች እና በድሬዳዋ አስተዳደር ያካሄደውን ክትትል እና ድጋፍ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ አካሂዷል። በማጠቃለያ መርሃ ግብሩም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ተገኝተው እንደገለጽት በአስተዳደሩ በገጠር እና በከተማ በተፈጠሩ የስራ እድሎች ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። በተለይም በሁለቱ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ወጣቶችን በማሰልጠን እና በማብቃት በአስተዳደሩ ከሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር በማስተሳሰር ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ የሥራ እና ክህሎት ሚንስቴር በ11 የክልል ከተሞች እና የከተማ አስተዳደሮች የድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን እና የተቋም ግንባታን እና የአሰሪ እና ሰራተኛን ጉዳይ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በባለፉት አራት አመታት ከ16 ሚሊዮን በላይ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው በባለፉት ስድስት ወራት በተቋም ግንባታ፣ ከክህሎት ልማት፣ ከስራ እድል ፈጠራ ከአሰሪ እና ሰራተኛ ዘርፍ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። በመድረኩም በክትትል እና ድጋፍ የተገኙ ጠንካራ እና ምርጥ ተሞክሮች እንዲሁም በዘርፉ የታዩ ማነቆዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በስፋት ተዳስሰዋል። በመርሃ ግብሩም የክልል እና የአስተዳደሩ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ©️DGC ጥር 9/2018 ዓ.ም

photo content
+9

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሚመራ የሱፐርቪዥን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተሰሩ ስራዎችን ጉብኝት ቀጥሎ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። ቡድኑ በዛሬው ዕለት በጠዋቱ መርሃግብር በዋናነት በአሰሪና ሰራተኛው ዘርፍ  በኢንዱስትሪዎች እና በኤጀንሲዎች ያለውን አጠቃላይ የስራ ሁኔታ የጎበኘ ሲሆን በተለይም በፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ እና የመንግስት የልማት ድርጅት በሆነው ኤሌክትሪክ አገልግሎት  የሰራተኛ ማህበራት ከድርጅቶቹ ጋር ያላቸው ግንኙነት እና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ስርዓት ያለበትን ደረጃ ምልከታ አድርጓል። ከኢንተርፕራይዝ ልማት አኳያ በድሬዳዋ የመጀመሪያ የሆነው በዲጂታል ማርኬቲንግ እና የበቃ የሰው ሃይል ለኢንዱስትሪዎች አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ የተተገበሩና የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ያስገኛቸው ውጤቶችና ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎችን ተመልክቷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 8/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በአስተደዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚሰሩ የቀን ሰራተኞች በስራ ቦታ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ ሁለተኛ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ። መድረኩ ኢንዱስት
+8
በአስተደዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚሰሩ የቀን ሰራተኞች በስራ ቦታ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ ሁለተኛ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ። መድረኩ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል ከተለያዩ ቦታዎች በስራ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ከሚያዘጋጃቸው ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች አካል መሆኑ ታውቋል፡፡ ቢሮው የቀን ሰራተኛ ዜጋውን ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ አምራች ሃይል ባለሙያ በማዘጋጀት የሚሰሩበት ኢንዱስትሪ ድረስ በመሄድ ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 7/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊነትን ለመከታተልና ለመደገፍ ባለመውና በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራው ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ድጋፋዊ ጉብኝት ማካሄድ ጀመረ። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የመግቢያ ውይይቱ ላይ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት በአስተዳደሩ በሥራ እና ክህሎት ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተለይም የክህሎት ልማት፣  የአሰሪና ሰራተኛ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎችን  ተመልክቶ ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ የስራ ጉብኝት መሆኑ ለቀጣይ የስራ ዕንቅስቃሴ መነቃቃት የሚፈጥር ነው ብለዋል። የመስክ ምልከታው ዓላማ በዋናነት መልካም አፈፃፀሞችን ማስፋት፣ ማነቆዎችን መፍታት እና ድጋፍ የሚፈልጉ ሥራዎችን ለይቶ በመደገፍ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የኢንዱስትሪ ሰላማዊ ግንኙነት ላይ የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ መደላድል ለመፍጠር የሚያስችል ድጋፋዊ ጉብኝት መሆኑን የልዑኩ ቡድን መሪ አቶ ጥኡመዝጊ በርሔ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም የልዑክ ቡድኑ በዛሬው ዕለት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ልህቀት ማዕከል፣ በአስተዳደሩ የሚገኙ የግልና የመንግስት ኮሌጆች፣ የወረዳ አንድ ማዕከላት እና ከፍተኛ የማደግ አቅም ያላቸው ኢንተርፕራይዞችን ተዟዙሮ የተመለከተ ሲሆን በተጨማሪ በአስተዳደሩ የተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች፣ ኢንተርፕራይዞች ያሉበትን ሁኔታ እና የኢንዱስትሪ ሰላም ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ሥራዎችን ጉብኝት በቀጣይ ቀን ያካሂዳል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 7/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

photo content
+1

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሌጁን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወነ፡፡ የኮሌጁን መደበኛ የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር የንብረት፣የወጪ አስተዳደር እንዲሁም የካይዘን ትግበራ ሂደት ለመገምገም በኮሌጁ ለተገኘው የምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት አጠቃላይ በኮሌጁ ውስጥ የተሰሩትን ስራዎች በተለይም ከዲጂታላይዜሽን፣ኮሌጁን ለስራ ምቹ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ስራዎችን በበቂ ሁኔታ የተብራራ ሲሆን በተለይ ኮሌጁ ከካይዘን ትግበራ አንጻር ያለውን ልምድና የትግበራ ሁኔታ ለኮሚቴው አባላት የተገለጸ ሲሆን እቅዱ ተፈጻሚ እንዲሆንና ስራዎች ዘላቂ እንዲሆኑ ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች ከኮሌጁ ማኔጅመንት ጋር በከፍተኛ ትጋትና የሁሉም ተሳትፎ በጋራ በማካተት እየሰራ እንዳለ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ኮሌጁ በአስተዳደሩ የተጣለበትን ትልቅ ሀላፊነት ለመወጣት ወጪዎችን በመቀነስና በራስ አቅም በመስራትና ምርቶችን በማምረት ሌሎች ተቋማትም ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ እንዳለ ለኮሚቴው አብራርቷል፡፡ የመስክ ምልከታውና ግምገማውን ለማድረግ የተገኘውን ኮሚቴ የመሩት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ አንድነት ሀይሉ እንዳሉት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚሰራቸው ስራዎች በሙሉ በአስተዳደሩ እንደ ሞዴል የሚወሰድ ተቋም ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም ኮሌጁ የመንግስት ወጪን ለመቀነስ የሚሰራቸው ስራዎች ለራሱ አልፎ ለሌሎችም እንደ ተሞክሮ ሊወሰድ ይገባዋል ብለዋል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ አክለውም ስራዎችን ለማዘመን እየተሰራ ያለው የዲጂታላይዜሸን ስራዎች፣ትምህርትና ስልጠናው የተቀላጠፈ እንዲሆን እየሰራ ያለው ስራ እንዲሁም የስራ ቦታው ለሰራተኛውና ለሰልጣኞች ምቹ እንዲሆን ከካይዘን አተገባበር አንጻር እየሰራ ያለው ስራ እጅግ አርኪ በመሆናቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ይህንንም የስራ አፈጻጸም ሌሎች ተቋማት እንደ ልምድ ሊወስዱት ይገባል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ቋሚ ኮሚቴው በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የመስክ ምልከታውንና ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥር 6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከአራቱ የድጋፍ ማዕቀፍ አንዱ የሆነውን የኢንተርፕሩነርሽፕ ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። በተያዘው የበጀት አመት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለአሰልጣኝ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ሲሆን ይህን መሰረት በማድረግ የመንግስት ፖሊ ቴክኒክና የግል ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራኖች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ አዲስ በተዘጋጁ እና ከተከለሱ የስልጠና ሰነዶች አንዱ የሆነውን  Entrepreneurship (Discover yourself and develop an entrepreneurial mind set and design and lunch your vencher) ላይ ስልጠና ወስደዋል፡፡ ስልጠናው ከEDI በመጡ አሰልጣኝ የተሰጠ ሲሆን በመርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ውልታ ትልቅሰው ለመንግስት ፖሊ ቴክኒክና ለግል ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራኖች የኢንተርፕርነርሺፕ ስልጠና መሰጠቱ ስራዎችን በተለይም የሚሰጡ ድጋፎችን በዕውቀትና በክህሎት ለመስራት  የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

በየጊዜው የሚዘረጉ ዲጂታል የአሰራር ሲስተሞችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተቋሙን አጠቃላይ አሰራር በዲጂታል ሲስትም ለመቀየር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል:: ኮሌጁ የአገልግሎት አሰጣጡን ጨምሮ አጠቃላይ የተቋሙን አሰራር በDigital System ለመተካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለአመራር አባላትና ለክፍል ተጠሪዎች የግንዛቤ መድረክ አካሂዷል:: አሁን ባለንበት ዘመን ቴክኖሎጂን መጠቀም ምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ አክለውም እንደ ተቋም ቀጣይነትን ለማረጋገጥ በዲጂታል ሲስተም ጠንካራ ተሳትፎ ማድረግና ምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ማዘመን ይጠበቅብናልም ብለዋል:: የግንዛቤ ስልጠናው ከኢትዮ ቴሌኮም በመጡ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በዚህም አሁን ያለው አሰራር በዲጂታል ሲስተም ሲቀየር በምን መልኩ ይሰራል የሚለውና የስራ ክፍሎች ሲስተሙን የሚያንቀሳቅሱበትን ሂደት በዝርዝር ግንዛቤ መስጠት ችለዋል:: በመድረኩ በተሰጠውን ግንዛቤ ላይ ከተሳታፊዎች በሲስተሙ አተገባር ዙሪያ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ማብራሪያም ተሰጥቶባቸዋል:: በእለቱ ግንዛቤውን የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎች በቀጣይ ቀናትም ሲስተሙ የሚተገበርባቸው በሁሉም ስራ ክፍሎች ላይ በመገኘት የሲስተሙን አጠቃላይ አተገባበርና አጠቃቀምን በተመለከተ የተግባር ስልጠና እንደሚሰጡም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥር 3/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa - Статистика та аналітика Telegram каналу @bolsdd