1 325
Підписники
+224 години
+67 днів
+11030 днів
Архів дописів
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
‹‹የSIFA ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ እንደ ሀገር የሚጠቅመው ጥቅም የላቀና ብዙ ወጣቶችን የክህሎት፣የስራ ባለቤት እንዲሁም የስራ ፈጣሪ የሚያደርግ እንደሆነ እና ከተማችንን ደግሞ ዲጂታል አሰራሮች የሚያሳድግ ፕሮጀክት እንደሆነ እተማመናለሁ፡፡›› ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
በAUDA NEPAD እና EU የገንዘብ ድጋፍ እየተተገበረ የሚገኘው የ Skill Initiative For Africa(SIFA) ፕሮጀክት የICT የልህቀት ማእከል የጨረታ ሂደት ለመገምገምና የልህቀት ማእከሉን ግንባታ ሂደት ለማስጀመር ያለመ AUDA NEPAD እና EU የግዢ ስራ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያዎች አቶ ቪንሴንት እና ከSIFA ፕሮጀክት ተወካዮች የተውጣጣ የግምገማ ቡድን በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አደረገ፡፡
በግምገማና ውይይት ሂደቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው ሲሆኑ በንግግራቸውም የSIFA ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ እንደ ሀገር የሚጠቅመው ጥቅም የላቀና ብዙ ወጣቶችን የክህሎት፣የስራ ባለቤት እንዲሁም የስራ ፈጣሪ የሚያደርግ እንደሆነ እና ከተማችንን ደግሞ ዲጂታል አሰራሮች የሚያሳድግ ፕሮጀክት እንደሆነ እተማመናለሁ፡፡ ይህ በጀርምን መንግስት ድጋፍ የሚተገበረው በተጨማሪም በኮሌጁ እየተተገበረ ያለው ይህ የSIFA ፕሮጀክት መሳካት የከተማችን አስተዳደር ፕጀክቱ ከግብ እንዲደርስ ማቺንግ ፈንድ በመመደብ ለሌሎች ከተሞች አርአያ የሆነ ተግባር ፈጽመዋል ይህም ፕሮጀክቱ ከግብ እንዲደርስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በኮሌጁ የሚተገበረው ይህ የSIFA ፕሮጀክት ወጣቶቻችን የሙያና የስራ ፈጣሪ የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ ያሉት የኮሌጁ ዲን ክቡር አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም ዘመኑ የAI ዘመን እንደመሆኑ መጠን ይህ በኮሌጁ የሚገነባው የልህቀት ማእከል ከተማችንን ብሎም ሃገራችንን የICT ማእከል የሚያደርጋት ነው ብለዋል፡፡
በግምገማና ውይይቱ ሂደቱ ወቅት የSIFA ፕሮጀክት እስካሁን የደረሰበት የፕሮጀክት አፈጻጸም በአቶ ሃምዲ ሙሃመድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በስተመጨረሻም በኮሌጁ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋወውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱና በሪፖርቱ መሰረትም ልኡክ ቡድኑ የመሩት አቶ ቪንሴንት እንዳሉት ኮሌጁ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው በቀጣይ በኮሌጁ ውስጥ የሚገነባው የICT ልህቀት ማእከል ሲጠናቀቅ ደግሞ ለኮሌጁ ብሎም ለከተማው እንዲሁም ለሃገሪቱ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም የልህቀት ማእከሉን ግንባታ በፍጥነት ተጀምሮ እንዲያልቅ አስፈላጊውን ስራ በAUDA NEPAD እና EU በኩል እንደሚፈጸም ተናግረዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የንግድ ሃሳብ ያላቸው ዜጎችን መደገፍ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ የ2017 ዓ.ም "ብሩህ" የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር የሽልማትና የእውቅና መርሃግብር ተካሄደ፡፡
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በሀገራችን የሚታየውን ስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የቴክኖሎጂ ፈጠራና የንግድ ሃሳብ ያላቸውን አካላት መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡
ውድድሩ የፈጠራ ስራ ያላቸውን አካላት ሃሳባቸው ተግባራዊ የሚደረግበትን መድረክ ለመፍጠር ከማስቻሉም በላይ ለበርካቶቹ የሥራ ዕድል የመፍጠር ዓላማ እና ግብ አለው።
በመርሃግብሩ ከዚህ ቀደም በተከታታይ አመታት በተደረጉ ውድድሮች ተሳታፊና አሸናፊ በመሆን ሃሳቦቻቸውን ወደ ስራ የቀየሩ ወጣቶች ልምዳቸውን ለተወዳዳሪዎች ማካፈል ችለዋል።
ተወዳዳሪዎችና የውድድሩ አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ውድድሩ በመዘጋጀቱና በመሳተፋቸው የፈጠራ ስራቸውን ለታለመለት አላማ ለማዋል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
#አሁን
#Happening Now
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ የ2017 ዓ.ም ብሩህ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር የሽልማትና የእውቅና መርሃግብር
ረቂቅ አዋጁ ቅንጅታዊ አሰራሮችን የሚያጠናክርና የዜጎችን ደህንነት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ማጎልበት የሚያስችል ነው
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ቅንጅታዊ አሰራሮችን የሚያጠናክርና የዜጎችን ደህንነት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ማጎልበት የሚያስችል መሆኑ ተመላከተ።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሀላፊዎች ጋር ተወያይቷል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዋጁን ማስፈጸም የሚያስችል የሰው ሀይል የማደራጀትና ሌሎች የዝግጅት ስራዎችን ማከናወንን ጨምሮ የአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብና መመሪያዎችን የማዘጋጀት ስራ ከወዲሁ በትኩረት ሊሰራ ይገባል።
አዋጁ በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ስራ የሚፈልጉ ዜጎችን ማካተቱ እንዲሁም፣ ኤጀንሲዎች በማህበር ተደራጅተው እንዲሰሩ የሚያደርግ መሆኑ መልካም ነው ብለዋል።
በረቂቅ አዋጁ ላይ የጤና ምርመራ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ምርጫ፣ የኮሚሽን ድርድር በኤጀንሲዎችና ፌዴሬሽን ብቻ መገደቡና የባህረኞችና የሹፌሮች የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ከቋሚ ኮሚቴውና የህግ ጥናት ዳይሬክቶሬት ቀርበዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሰጡት ምላሽ ረቂቅ አዋጁ ቅንጅታዊ አሰራሮችን የሚያጠናክርና የዜጎችን ደህንነት፣ ብቃትና ተወዳዳሪነት ማጎልበት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ህገወጥነትን ከመከላከል አንጻርም ቀደም ሲል በነበረው አዋጅ ላይ የታዩ ክፍተቶችን መፍታትና ጠንካራ እርምጃዎች መውሰድ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ፣ ሀገሪቱ ከውጭ ምንዛሬ ማግኘት ያለባትን ገቢ፣ በዘርፉ የዳበረ ልምድ ያላቸው ሀገራትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ የኮሚሽን ድርድር በኤጀንሲዎች ብቻ እንዳይደረግ መደረጉን ጠቅሰዋል።
በውጭ ሀገራት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አመራር አባል እና ቤተሰቦች የኤጀንሲ ፍቃድ እንዳያገኙ ክልከላ የተደረገው የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅና የጥቅም ግጭትን ለመከላከል መሆኑንም አንስተዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ስምሪት የሚሄዱ ዜጎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በመዳረሻ ሀገራት ከሚቀያየሩ ሁኔታዎች አንጻር የክለሳ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አንስተዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ በበኩላቸው፤ የዜጎችን ደህነነት ለማስጠበቅና ህገወጥነትን ለመከላከል በማሰብ በረቂቅ አዋጁ ጠንካራ ህጎች መካተታቸውን ገልጸዋል።
በምክር ቤቱ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረው የኤጀንሲዎች መብዛትንም በጋራ ሆነው እንዲሰሩና ለአስተዳዳር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በማህበር እንዲደራጁ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው።
“ዕቅዶቻችን በዋናነት የክህሎት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፉን ግቦች ሊያሳኩና የአስተዳደሩን ነዋሪ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ተግባራትን እንደ ቢሮ ተናብቦ እና ተቀናጅቶ መፈጸም ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡”
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለቀጣይ በጀት ዓመታት ማለትም በመካከለኛ የዕቅድ ጊዜ ከ2018 እስከ 2020 ዓ/ም የሚሰሩ ስራዎችን እንዲሁም ለነዚህ ተግባራት ማስፈፀሚያ ተብሎ በተዘጋጀ የፕሮግራም በጀት ዕቅድ ላይ ውይይት አደረገ፡፡
ቢሮው ከዘርፉ ተግባራት አንፃር አገራዊ የፖሊሲና የትኩረት አቅጣጫዎችን መሰረት ያደረጉ ተግባራት በዕቅዱ ተካተው እንዲዘጋጁ የተደረገበት ሁኔታ በስፋት የገመገመ ሲሆን ለዕቅዱ ተግባራዊነት አስፈላጊ የሆኑ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት ዕቅዱን ማጽደቅ ተችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 17/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+3
#ዜና|የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የGRM ኮሚቴ 4ተኛ ሩብ አመት መደበኛ ስብሰባውን አከናወነ፡፡
በኮሌጁ እየተገነባ ያለው የልህቀት ማእከል ግንባታው ምንም ችግር ሳይፈጠር እና ማህበረሰቡ ላይ ተጽእኖ ሳይኖረው በአግባቡ ተገንብቶ ለሚፈለገው አላማ እንዲውል እንዲሁም ችግር ቢከሰት በተገቢው መንገድ እንዲፈታ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ የGRM ኮሚቴ ምስጋና ያቀረቡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም ባለፉት 3 ሩብ አመታት በኮሌጁ፣ በኮሚቴው እንዲሁም በፕሮጀክቱ በኩል የተሰሩ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን በቀጣይም የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ የማህበረሰቡን፣ የኮሌጁ እንዲሁም የመንግስትን ፍላጎት በተከተለ መልኩ ሊሰራና ችግሮችም በተገቢው መንገድ እንዲፈቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በስብሰባው ላይ በርካታ ባለድርሻዎች እና የማህበረሰቡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በእለቱም በዓመታዊ የግንባታ ሂደት እና የቅሬታ አፈታት ሁኔታ እንዲሁም ቀጣይ የግንባታ ቦታ እና ከማህበረሰቡ የሚጠበቁ ስራዎች ላይ በሰፊው ውይይት የተደረገ ሲሆን ለቀጣይ ስራም አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በትምህርትና ስልጠና ክፍሎች ላይ በኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት እየተካሄደ የሚገኘው የምልከታ መድረክ በተጠናከረ መልኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል::
ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንት በኮሌጁ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች የስልጠና አሰጣጥ ትግበራን በተመለከተ እያካሄደ የሚገኘው የግምገማ መድረክ በዚህ ሳምንትም ቀጥሎ ተካሂዷል::
የምልከታ ቡድኑ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር መሰረት በዚህ ሳምንት የኤሌክትሪካል/ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት እና የቢዝነስ ዲፓርትመትን የተመለከተ ሲሆን በዚህም የትምህርትና ስልጠና ክፍሎቹ በ2017 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ከተቀመጠው ግብ አንፃር ያከናወኗቸውን ዝርዝር ተግባራት መመልከትም ተችሏል::
የቀረቡት የአፈፃፀም ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግም በምልከታ ቡድኑ ሀሳብ አስተያየት የተሰጠባቸው ሲሆን ጥሩ አፈፃፀም በታየባቸው ጉዳዮች ላይ አውቅናን በመስጠት እንዲሁም ዝቅተኛ እፈፃፀም በተስተዋለባቸው ጉዳዮች ላይም ዲፓርትመንቶቹ በቀጣይ ትኩረት ሰጠተው እንዲሰሩ ግብረ-መልስ ተስጥቷል::
በትምህርትና ስልጠና ክፍሎች የሚካሄደው ይህ የግምገማ መድረክ በቀጣይም በተቀረሩት ዲፓርትመንቶች ላይ በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት የሚቀጥልም ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+9
#ዜና| የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር በዘርፉ ላይ ያለውን የግንዛቤ ችግር መፍታት ያስፈልጋቸዋል ተባለ።
ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማህበር ለድሬዳዋ ቅርንጫፍ አባላት በኢንተርፕርነርሺፕ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ም/ ዲን ወ/ሮ ትግስት በዙ እንደ ገለጹት ሃገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላለችብት እድገት እንዲሁም ቀጣይ ለምትደርስበት የእድገት ደረጃ ለመድረስ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነዉ። ስለዚህ ሴቶችን በማብቃትና አካታች እቅዶችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል ይሆንንም ደግሞ ኮሌጁ እየሠራበት ይገኛል ያሉ ሲሆን፡፡
አያይዘውም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር በዘርፉ ላይ ያለውን የግንዛቤ ችግር መፍታት ያስፈልጋቸዋል እንዲሁም ባለሙያዎችን በማብቃት ሴቶችን ወደ አመራር ለማምጣት እድል ልንሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በስልጠናው ላይ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከድሬዳዋ ቅርንጫፍ አባላት የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ በፊት በ ህይወት ክህሎት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መሠጠቱ ይታወሳል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 ዓ.ም "ብሩህ" የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር አካሄደ።
ውድድሩ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች፥ ሀሳባቸውን ወደ ተግባር መለወጥ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው ተብሏል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ ቢሮው የአስተዳደሩን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ ለዜጎች የስራ እድል የመፍጠርና የማመቻቸት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፥ በዚህ ውድድር የተሳተፉ ወጣቶችን በሀሳብ ከመደገፍ በተጨማሪ ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በቢሮው የስራ እድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰኢድ አሊ በበኩላቸው፥ በውድድሩ የተሻለ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ መኖሩን ከማሳየት ባሻገር፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ የሚሆኑ የድሬዳዋ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች እንደሚወጡ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ባዘጋጀው ውድድር ላይ በተሳታፊ ተወዳዳሪዎች አረንጓዴ አካባቢ መፍጠር ፥ ፕላስቲክን መልሶ የመጠቀም ቴክኖሎጂ፥ የዲጂታል ገበያ እና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ጨምሮ በርካታ የፈጠራ ሀሳቦች ቀርበዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 13/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሠራተኞች ይቀነሳሉ በሚል የሚናፈሰውን ወሬ በሚመለከት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ
ለተሟላ ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የስራ ባህልን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ ነው - ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "የስራ ባህልና ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር አብሮ ለመራመድ ከስራ ባህል አስተሳሰብ ጀምሮ እስከ ተግባር መለወጥ ያስፈልጋል።
ለተሟላ ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የስራ ባህልን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው÷ የስራ ባህልን ለማምጣት የአስተሳሰብ እና የእይታ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም በየአካባቢው ያለ ፀጋን መመልከት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስራ መገለጫቸው የሆኑና ኢኮኖሚያዊ ህልውናቸውን ያረጋገጡ ዜጎች አንዲኖሯት የስራ ባህልን እያሳደገች እንደምትገኝ ጠቅሰው÷ ቀጣዩ ትውልድም በዚህ የታነፀ እንዲሆን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው÷ ተቋማቸው የስራ ባህል ሊያሳድጉ የሚችሉ በርካታ ተሞክሮዎችን በማስተላለፍ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
የፓናል ውይይቱም የስራ ባህል ለውጥ ማምጣት ላይ ከባለድርሻ አካላት ለመምከርና የጋራ አቋም ይዘው ለመስራትና ለማገዝ ያለመ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በመድረኩ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ከፌደራልና ከክልል ተቋማት የተውጣጣና ሌሎች ተጋባዥ ተሳታፊዎች እየተወያዩበት ይገኛል፡፡
©️FMC
