uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 331
Підписники
Немає даних24 години
+97 днів
+8030 днів
Архів дописів
photo content
+9

” የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ቆሟል” ቢሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነታው የራቀ ነው! የሥራና ክህሎት ሚስቴር መቋቋሙን ተከትሎ የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ስምሪቱ በርካታ ህገወጥ አሰራሮች በሰፊው የተንሰራፉበት ነበር፡፡ በመሆኑም ለተሻለ ህይወት እና ሥራ ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎቻችን ላልተፈለገ ወጪ እና እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ከዚህ በላይ በርካቶች ለሞት እና ለከፍተኛ አካል ጉዳት ሲዳረጉ ቆይቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፍልሰት አይቀሬ ነባራዊ ሁኔታ መሆኑን ከግምት በማስገባት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስርዓቱን ለማሻሻል የተለዩ የሪፎርም ሥራዎችን በትኩረት ሰርቷል፡፡ የሪፎርሙ አጠቃላይ መነሻና መዳረሻ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሲሆን ይህንን ዕውን ለማድረግ ሥራውን ጊዜውን በዋጁ ቴክኖሎጂዎች ለመደገፍ ከፍተኛ ሥራ ተሰርቷል፡፡ በውስጥ አቅም በልፅጎ ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን ከማዘመኑም በላይ ዜጎች ከመነሻ እስከ መዳረሻ ሀገራት ድረስ ይገጥማቸው የነበረውን አላስፈላጊ ወጪ እንዲቆምና የነበረው እንግልትም እንዲቀንስ   አድርጓል፡፡ ከመረጃ ጋር ተያይዞ እንደ ሀገር የነበረብንን መሰረታዊ ችግርንም ሙሉ ለሙሉ እንድንሻገር አስችሎናል፡፡ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ዜጎቻችን ሥርዓተ-ትምህርት ተቀርጾ  በመላ ሀገሪቱ በሚገኙና በተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ስልጠና እንዲወስዱና ብቃታቸውንም በምዘና እንዲያረጋግጡ የሚያስችል ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ  ይገኛል፡፡ ይህም  ዜጎች ከሙያ ባለፈ ስለሚሄዱበት ሀገር ባህል፣ ቋንቋና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጭምር በስነ-ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ጆርዳን፣ ኳታር፣ ቤሩት እና ኩዌት የመዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት በተደረገው ጥረት የሁለትዮሽ ስምምነት የተደረገባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ መዳረሻ ሀገራቱን ለማስፋትም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው፡፡ በ2016 በጀት ዓመት ብቻ ከ345 ሺህ ዜጎች በላይ ስምምነት ወደተገባባቸው ሀገራት ህጋዊ በሆነ መንገድ የሥራ ስምሪት አግኝተዋል፡፡ አሁንም በሁሉም መዳረሻ ሀገራት ያለው የሥራ ስምሪት ሥራ ካለምንም ችግር እንደቀጠለ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ በህጋዊ መንገድ የሥራ ሥምሪተ ያገኙት ዜጎቻችን በ2014 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ከነበረው አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ762 በመቶ በላይ እድገት አሳይቷል፡፡ በቀጣይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰለጠነና በከፊል የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካታ ዜጎቻችን የዓለም የሥራ ገበያ በሚያመጣው ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች “የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ቆሟል” የሚል ከእውነታው ፍፁም የሚቃረን መረጃ እየተዘዋወረ ይገኛል፡፡ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ዘመኑን በዋጁ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ እና ፍትሃዊነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ህጋዊ በሆነው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ላይ ማንኛውንም አይነት መረጃ ሲፈልግ አቅራቢያቸው ከሚገኙ ሥራውን ከሚያስተባብሩ ቢሮዎችና ጽ/ቤቶች እንዲሁም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ማግኘት እንደሚችል እንገልፃለን፡፡

photo content

ናፍቆት የድሬደዋ ሳምንት ከሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ በድምቀት ለሚካኼደው 'ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት' በዓል ላይ የሚሳተፉ ወገኖች ወደድሬደዋ መግባት መጀመራቸውን አቶ ሮቤል ጌታ
ናፍቆት የድሬደዋ ሳምንት ከሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ በድምቀት ለሚካኼደው 'ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት' በዓል ላይ የሚሳተፉ ወገኖች ወደድሬደዋ መግባት መጀመራቸውን አቶ ሮቤል ጌታቸው የበዓሉ አቀባበልና መስተንግዶ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተናገሩ። 3ኛው አመት 'ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት' በዓል ከሐምሌ 21 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚከበር ታውቋል። በዓሉ የድሬደዋን ሕዝብ ባሳተፈ መልኩ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ በኪነጥበባዊ ዝግጅቾች ለማክበር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አቶ ሮቤል ጠቅሰዋል። ለበዓሉ አከባበር በወጣው መርሐግብር መሰረት ሐምሌ 21 የሰላም እና የፍቅር ቀን ሐምሌ 22 የባህል እና የስፖርት ቀን ሐምሌ 23 የንግድ ቀን 'ኑ በድሬ እንነግድ' ሐምሌ 24 የቤተሰብ ቀን እንዲሁም ሐምሌ 25 የምስጋና እና የመዘከር ቀን በሚል መጠሪያ እንደሚከበሩም ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በሳምንቱ ቀናት፥ የበጎ ፈቃድ (በጤና፣ በትምህርት እና በማሕበራዊ ዘርፍ) አገልግሎት እንዲሁም ከአስተዳዳሩ ወጣቶች እና አመራሮች ጋር የሚደረግ የልምድ ልውውጥና፥ የዙም ሚቲንግን ጨምሮ የሽልማት መርሐ ግብር እንደሚኖር ታውቋል። Via በድሬቲዩብ

በዘንድሮ አመት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተሳተፉ ፈታኞች እንዲሁም ተፈታኝ ተማሪዎች በጋራ በመሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወኑ፡፡ የዘንድሮ አመት
+8
በዘንድሮ አመት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተሳተፉ ፈታኞች እንዲሁም ተፈታኝ ተማሪዎች በጋራ በመሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወኑ፡፡ የዘንድሮ አመት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በትናንትናው እለት በሰላም መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ከ520 በላይ ተፈታኝ ተማሪዎች በኮሌጁ ተመድበው በኮምፒውተር የታገዘ የፈተና ስርአት ፈተና መውሰዳቸው የሚታወስ ሲሆን እነዚህም ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ተፈትነው እንደጨረሱ ከትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ እንዲሁም ከኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማ እና ከተለያዩ እንግዶች ጋር በመሆን በጋራ በኮሌጁ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምንኬሽን ሀምሌ12/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን በኮሌጁ የነበሩትን እንግዶች በዛሬው እለት የመሸኛ የምሳ ግብዣ አደረገ፡፡ ፈተና ለማስተባበር እንዲሁም ለመፈተን ከ
+4
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን በኮሌጁ የነበሩትን እንግዶች በዛሬው እለት የመሸኛ የምሳ ግብዣ አደረገ፡፡ ፈተና ለማስተባበር እንዲሁም ለመፈተን ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተውጣጡ ፈታኞች በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ በጣም ደስተኛ እንደነበሩና አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴም በአገር ደረጃ ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚገባ ትልቅ ተቋም ነው  ስለዚህ በዚህ ኮሌጅ ውስጥ በቆየንባቸው ቀናቶች ውስጥ በኮሌጁ ያየናቸው ነገሮች እጅግ በጣም ጥሩ ናቸው እንዲሁም ይህን እንደ አገር ጥቂቶች ብቻ  የተወጡትን የፈተና ስርአት  ኮሌጁ በብቃት ያለምንም ችግር ተወጥቶታል ብለዋል፡፡ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በኮምፒውተር የታገዘ የፈተና ስርዓት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚወስዱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በኮሌጁ የተመደቡ የማህበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎችና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአጠቃላይ ከ520 በላይ ተማሪዎች በኮምፒውተር የታገዘ የፈተና ስርዓት እንደተፈተኑ የሚታወስ ነው፡፡ የኮሌጁ ኮምንኬሽን ሀምሌ 11/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን በኮሌጁ የነበሩትን እንግዶች በዛሬው እለት የመሸኛ የምሳ ግብዣ አደረገ፡፡ ፈተና ለማስተባበር እንዲሁም ለመፈተን ከ
+4
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን በኮሌጁ የነበሩትን እንግዶች በዛሬው እለት የመሸኛ የምሳ ግብዣ አደረገ፡፡ ፈተና ለማስተባበር እንዲሁም ለመፈተን ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተውጣጡ ፈታኞች በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ በጣም ደስተኛ እንደነበሩና አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴም በአገር ደረጃ ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚገባ ትልቅ ተቋም ነው ስለዚህ በዚህ ኮሌጅ ውስጥ በቆየንባቸው ቀናቶች ውስጥ በኮሌጁ ያየናቸው ነገሮች እጅግ በጣም ጥሩ ናቸው እንዲሁም ይህን እንደ አገር ጥቂቶች ብቻ የተወጡትን የፈተና ስርአት ኮሌጁ በብቃት ያለምንም ችግር ተወጥቶታል ብለዋል፡፡ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በኮምፒውተር የታገዘ የፈተና ስርዓት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚወስዱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በኮሌጁ የተመደቡ የማህበረሰብ ሳይንስ ተማሪዎችና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአጠቃላይ ከ520 በላይ ተማሪዎች በኮምፒውተር የታገዘ የፈተና ስርዓት እንደተፈተኑ የሚታወስ ሲሆን፡፡ የኮሌጁ ኮምንኬሽን ሀምሌ 11/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሣኒ የተመራ ልዑክ በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ በአለም ባንክ ድጋፍ የተደረገባቸውን ፕሮጀክቶች የስራ አፈጻጸም ጉብኝት አደረገ። በዚህ የጉብኝት መርሃግብር በአስተዳደሩ ወረዳ 3 ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገነባውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እና ለአገልግሎት መስጫ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓት ተሟልተው ለህብረተሰቡ እየሰጡ ያለውን አገልግሎት በስፍራው በመገኘት ተመልክተዋል። በተያያዘ "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ቢሮው ከአስተዳደሩ የኢንዱስትሪዎች ጋር በፈጠረው መግባባት ብዙ ወጣቶችን ተጠቃሚ መሆናቸው ይታወቃል ይህንንም በስራ ላይ የሚገኙ ወጣቶችንና ቅጥር የፈጸሙ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን ከጊዜው ጋር በሚራመድ የስርአት ማዕቀፍ ውስጥ እንዲመሩ የሚያስችል ስራዎችን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸውን የገበያ ተደራሸነትን ለመቅረፍ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚመራው የኢትዬጵያ ሥራ ገበያ  መረጃ ስርአት ፕሮጀክት ለምቶ ተግባራዊ የሆነው  መተግበሪያና ድህረገፅ ላይ በሰፊው እንዲመዘገቡ የንቅናቄ መርሃግብር መጀመሩ ተገለጸ፡፡ ይህም የንቅናቄ ዘመቻ በአስተዳደሩ 01 ወረዳ የተጀመረ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች ላይ በተመሳሳይ የሚቀጥል ይሆናል ምዝገባውን እያካሄደ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እንደተናገሩት ኢንተርፕራይዞች  ምርታቸውን ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገራት  ኦንላይን በማስተዋወቅ የሚሸጡበትና ክፍያ የሚቀበሉበት መሆኑን በማንሳት ሁሉም ኢንተርፕራይዞች በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በ2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር እየተተገበረ የሚገኘው "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡    በመድረኩም የቢሮውና በአስተዳደሩ የሚገኙ አንድ ማዕከላት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በግምገማ መድረኩም አንድ ማዕከላት አሁን ላይ እስከ ደረሱበት የወጣቶቹ በኢንዱስትሪዎች የስራ ላይ ልምምድ ሶስተኛ ወራቸው ያለውን የሥራ አፈጻጸም አቅርበው ባቀረቡት አፈጻጸም ላይ በመነሳት ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶ ያለባቸውን ክፍተትም ለማሟላት ያግዝ ዘንድ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡    የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ተገኝተው በቀጣይ በተለይ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወጣቶች በአግባቡ እና ያለማቆራረጥ የስራ ላይ ልምምዱን እያደረጉ እንደሚገኝ ክትትልና ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ልምምዱን በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ሲያጠናቅቁ ከስራ ጋር የሚተሳሰሩበትን ሁኔታ የማመቻቸት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በማዕድናት፣ በፈጠራዎች፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና አይ ሲ ቲ ዘርፍ  ላይ እየሰራችሁ ላላችሁ ኢንተርፕራይዞች በ3ኛው ዓመታዊ የመካከለኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ/MSME/ መድረክ ላይ በመገኘት ልምድና ተሞክሮአችሁን እንዲሁም ሥራችሁን  ለማጋራት ትልቅ ዕድል ተመቻችቶላችኋል ፡፡ በማዕድናት፣ በፈጠራዎች፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና አይ ሲቲ ዘርፍ  የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ሁለት ዓመትና በላይ የቆያችሁ ኢንተርፕራይዞች ይህ ዕድል እንዳያመልጣችሁ፡፡ ፎረሙ የሚካሄደው በአፍሪካ ናሚቢያ ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ኢንተርፕራይዞች በፍጥነት ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡ ሊንክ   https://msmeforum.africa/ የዚህ የአፍሪካ ኢንተርፕራይዞች አውታረ መረብ ስብስብ ፕሮግራም አባል መሆንም ትልቅ ዕድል ነው፡፡

photo content

የድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ፥ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሠልጣኝ ተማሪዎችን በዛሬው እለት በጋራ በመሆን አስመረቁ። በምረቃ ስነ-ስ
+9
የድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ፥ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሠልጣኝ ተማሪዎችን በዛሬው እለት በጋራ በመሆን አስመረቁ። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሃርቢ ቡህ እንደገለጹት የአንድ አገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት የሚወሰነው በትምህርት የሰለጠነ የሰው ሃይል የዳበረ እውቀትና ክህሎት ባላቸው ዜጓቿ በመሆኑ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል። ምክትል ከንቲባው አክለውም ድሬዳዋ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ያልተቆጠበ ተሣትፎ ቀዳሚውን ድርሻ የሚይዝ ብለዋል። በዚህ የምርቃት ስነ -ስርአት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሃርቢ ቡህ፣ ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የሁለቱም ኮሌጆች ዲኖችና ም/ዲኖች እንዲሁም መምህራን እና ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሠቦች ተገኝተዋል ። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ከድሬዳዋ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ ጋርመንት ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆኑት ሲሳይ ዘውዱ እና በእምነት ጠብቀው 3.91 እኩል ነጥብ በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ፥ ከኢትዮ ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካንፓስ ተማሪ ኤርሚያስ ከፍያለው 3.95 በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል። የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ሀምሌ6/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (SNV) RAYEE ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለተደራጁ 50 ኢንተርፕራይዞች የኢንተርፕሩነርሺፕና የህይወት ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ የሥራ መነሻ ድጋፍ "start up support" ግምቱ 3,869,715 ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ፤ የድጋፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአስተዳደሩ ካቢኔ ባስቀመጠው ውሳኔ የከተማና የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች በአንድ ላይ እንዲመሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ቢሮው የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አንስተው በተለይ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (ኤስ ኤን ቪ) ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት የተደረገው የሥራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለራሳቸውና ለሌሎች እንዲፈጥሩ የሚያስችል ማሳያ ሆኖ የሚቀርብ ነው ብለዋል፡፡ የSNV ድርጅት ተወካይ አቶ ኃይለየሱስ ለምለም በበኩላቸው ድርጅታቸው ከቢሮው ጋር በመተባበር ሥራ የሌላቸው ሴቶችና ወጣቶችን በገጠርና በከተማ በማደራጀት በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮዎች በተለይ በኢንተርፕሩነርሺፕና በህይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት እና ተደራጅተው በሚሰማሩበት ሥራ ዘርፍ ላይ አሰፈላጊው ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው የዛሬው ድጋፍ 41 በገጠር እና 9 በከተማ ለተደራጁ 71 ሴቶች እና 4 ወንዶች በአጠቃላይ 74 ወጣቶች ከሶስት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል ፡፡ በመቀጠል ድጋፍ የተደረገላቸው ተጠቃሚ የተደራጁ ወጣቶች እንደተናሩት በሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮና በSNV የጋራ ትብብር ለተሰጣቸው ስልጠና እና የአይነት ድጋፍ በማመስገን ለበለጠ ሥራ ለመሥራት እንደሚያነሳሳቸው ተናግረው ከዚህ በፊት በዚሁ የዶሮ እርባታ ላይ በአነስተኛ አቅምና እውቀት የጀመሩትን አስፍተውና አጠናክረው ለመስራትም መነሳሳት የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡  በድጋፍ ርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፣ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን እንዲሁም  የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

photo content

የሥራ ማስታወቂያ **** Ethiopian Airlines መረጃውን ሼር በማድረግ ለወጣቶቻችን ተደራሽ እናድርግ!!
+1
የሥራ ማስታወቂያ **** Ethiopian Airlines መረጃውን ሼር በማድረግ ለወጣቶቻችን ተደራሽ እናድርግ!!