uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 322
Підписники
+124 години
+77 днів
+14530 днів
Архів дописів
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ታላቁ የረመዳን ወር ፆምን ምክንያት በማድረግ የኮሌጁ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት የተካፈሉበት የኢፍጣር መርሃ-ግብር በተቋሙ አካሄደ::  ይህን መሰል የኢፍጣር መርሃ-ግብር እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር አብሮነት እና እንድነት የሚፀባረቁበት ልዩ ትዕይንት መሆኑን የተገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም ይህን መደጋገፍና በህብረት መቆምን በሁሉም መስኮች ላይ ጠብቆ ማስቀጠል ይገባል ያሉ ሲሆን ይህን ልዩ የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላዘጋጁ እንዲሁም ለተሳተፉ የኮሌጁ ማህበረሰብና አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል።  በኢፍጣር መርሃ-ግብሩ ላይ የስራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጃችን አመራርና ሰራተኞችን ጨምሮ ሰልጣኝ ተማሪዎችም የተሳተፉበት የአብሮነት መርሃ-ግብርም ነበር ። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 8/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚጾመውን ታላቁን አብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ማህበረሰብ አካላቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በርእሰ አድባራት ወገዳማት
+7
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚጾመውን ታላቁን አብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ ለተለያዩ ማህበረሰብ አካላቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በርእሰ አድባራት ወገዳማት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ለእምነቱ ተከታዮች የማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር በዛሬው እለት አከናወነ ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት በካይዘን ትግበራ ዙሪያ ለኮሌጆች ስልጠና አዘጋጀ። በዚህም ስልጠናውን ከአስተዳደሩ የካይዘን ኢንስቲትዩት በመጡ ባለሙያ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣልያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የካይዘን ትግበራ አፈጻጸም ተሞክሮ ቀርቧል፤ ቢሮው ለሪፎርም ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህም ስራዎች የሆነ ጊዜ ብቻ ተግባር አለመሆኑ በሚያሳይ መልኩ የካይዘን ትግበራውን በሁሉም የግል ኮሌጆች ላይ ተግባራዊ ማድረግ በተለየ መልኩ ቦታ ተሰጥቶታል። በመሆኑም መጀመር ብቻ ሳይሆን ማዝለቅ እንደሚገባና ጥሩ አፈጻጸም የሚያስመዘገቡ ኮሌጆችና የትምህርት ክፍሎችና ሰራተኞችን ቢሮው እንደሚያበረታ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 4/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የኢፍጣር መርሀ-ግብር አካሄዱ፤      መርሃ-ግብሩ በተለይም የቢሮው እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችን አብሮነት እና አንድነት በመፍጠርና በማጠናከሩ ረገድ ሚናው ላቅ ያለ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ  አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረው የዛሬውን የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላዘጋጁና ለተሳተፉ የቢሮው ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።     በዚሁ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላይም የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የኮሌጅ ዲኖች አሰልጣኝ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መጋቢት 4/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በአስተዳደሩ ከአራቱም የገጠር ክላስተሮች ለተወጣጡ ወጣቶች በኮሌጁ ሲሰጥ የቆየው የክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ:: ስልጠናው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ከአራቱም የገጠር ክላስተሮች ለተወጣጡ 20 ለሚሆኑ ሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም በህይወት ክህሎት፣ በመሰረታዊ ቢዝነስ አያያዝ እንዲሁም በካይዘን አተገባበር ላይ የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞችም ላለፉት ሳምንታት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ የተሰጣቸው ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ማጠናቀቅ ችለዋል:: በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በመልዕክታቸውም ይህ ስልጠና ወጣቶቹ ከዚህ በፊት በኮሌጁ የወሰዱትን የMarketing based sanitation concrete slab training በአግባቡ ስራ ላይ እንዲያውሉ የሚያግዛቸው ክህሎት መሆኑን ገልፀው ወጣቶች እዚህ ያገኟቸውን ክህሎቶች በየአካባቢያቸው የሚስተዋሉትን መሰረታዊ ችግሮች በመቅረፍ የሚፈጠርላቸውን የስራ እድል በአግባቡ መጠቀም ይገባቸዋልም ብለዋል:: በአስተዳደሩ የጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዩሱፍ ሰኢድ በበኩላቸው መሰል ስልጠናዎችን ለአስተዳደሩ ወጣቶች አዘጋጅተው ወደ ኮሌጁ ሲመጡ ምንግዜም ፈጣን ምላሽ ከኮሌጁ እንደሚያገኙ አስታውሰው ለዚህ ስልጠና መሳካት ጉልህ ሚና ለተወጡ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን እና አመራሮችም ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለወጣቶቹም የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል:: በመድረኩ ማጠቃለያም ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ላጠናቀቁ ወጣቶች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መጋቢት 3/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ሰልጣኞች በስነ ምግባር የታነጹና አገር ወዳድ እንዲሆኑ እየሰራ እንዳለ ኮሌጁ ገለጸ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሀገር ወዳድ እና በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድን ለመፍጠር ያሰበ
+4
በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ሰልጣኞች በስነ ምግባር የታነጹና አገር ወዳድ እንዲሆኑ እየሰራ እንዳለ ኮሌጁ ገለጸ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሀገር ወዳድ እና በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድን ለመፍጠር ያሰበ ስልጠና ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጋር በመተባበር ለሰልጣኝ ተማሪዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡ ኮሌጁ በቀን በማታ እንዲሁም በአጫጭር ስልጠናዎች ኢንዱስትሪውን ማንቀሳቀስ የሚችሉ ስራ ፈጣሪና የቴክኖሎጂ ባለቤቶች እንዲሆኑ ከሚሰጠው ትምህርትና ስልጠና በተጨማሪ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሰልጣኞችን በስነ ምግባር የማነጹ ስራ መደበኛ ስራ አድርገን እየሰራን ነው ያሉት በስልጠና ማስጀመሪያው እለት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ም/ዲንና የውጤት ተኮር ት/ስልጠና ኃላፊ አቶ ቢቂላ ታደሰ ሲሆኑ አያይዘውም በኮሌጁ በመደበኛነት በስልጠና ስርአቱ ከሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎች በተጨማሪ ወጣቶቹ ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ በስነ ምግባር የታነጹ እንዲሆኑ እንደ ዛሬው አይነት ስልጠናዎችን በተከታታይ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡ ይህ በዛሬው እለት የተጀመረው ስልጠና ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ አካዳሚ በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ሲሆን በቀጣይም በኮሌጁ እየሰለጠኑ ላሉ ሰልጣኞች በተከታታይ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መጋቢት 3/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የማሰልጠን ስነ-ዘዴ/ Training Methodology/ ላይ ስልጠና ላልወሰዱ ከለሁለቱ የመንግስት ኮሌጅ አሰልጣኞችና ከግል ኮሌጅ በተለያዩ ሙያዎች ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው መልክት እንዳስተላለፉት ወቅቱ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ጊዜው በሚጠይቀው ስልጠና ማብቃት ትኩረት የተሰጠው አንደመሆኑ አሰልጣኝ መምህራኑ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዲችሉ ታሳቢ ያደረገ ስልጠና መሰጠቱን አንስተው በተግባርም ውጤታማ ስራ ሰርተው ማሳየት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፤ አቶ ታሪኩ አክለውም ከስልጠና ጥራት ጋር ተያይዞ በሰልጣኞች የምዘና ውጤት ላይ የሚስተዋለው ክፍተት ለመሙላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ተቀራርቦ እየተሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን በዋናነት ግን የአሰልጣኝ መምህሩን አቅም መገንባት የስልጠና ጥራቱን ከማሻሻል አንጻር የሚጫወተው ሚና የላቀ በመሆኑ ትኩረት መሰጠቱን  ጠቅሰው በቀጣይ በክትትልና ድጋፍ ተፈጻሚነቱ አንደሚረጋገጥ ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 30/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በድሬዳዋ የነበረኝ ቆይታ ቅኝት

photo content
+1

የድሬ የኮሪደር ልማት ምቹ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬ እውን እንዲሆኑ አስችሏል። በኮሪደሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች
+9
የድሬ የኮሪደር ልማት ምቹ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬ እውን እንዲሆኑ አስችሏል። በኮሪደሩ ለከተማዋ ነዋሪዎች ገቢ ለማስገኘት የሚያስችሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ ስቴሽን፣ ሱቆች፣ ካፍቴሪያዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ የፓርኪንግ ቦታዎች እንዲካተቱበት ተደርጓል።

ኢፍጣር በድሬደዋ የረመዳን ኢፍጣር ከድሬደዋ ነዋሪዎች ጋር። Iftar in Dire Dawa Breaking bread with the local community during Ramadan. #PMOEthiopia