uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 317
Підписники
Немає даних24 години
+287 днів
+14730 днів
Архів дописів
ከአፈጻጸም ግምገማ ወደ ውጤት ተኮር አቅጣጫ ክቡር ከንቲባ አብዱላሂ አደን ለድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የሥራ አቅጣጫ አስቀመጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደን የሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅድን በመገምገም ለቀጣይ አፈጻጸም የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ክቡር ከንቲባው በዛሬው ውሎ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ያቀረቡትን የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በዝርዝር በመገምገም፣ የዘርፉ ሥራዎች በተለይም በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አመላክተዋል። በተለይም በአስተዳደሩ የሚገኙ ወጣቶች በ‹‹ብቃት›› የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት በመመዝገብ የሥራ ልምድ፣ የገቢ አቅም እና የኑሮ ሁኔታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ክቡር ከንቲባው አሳስበዋል። በተጨማሪም በአስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ የተደረገበትን የኮሪደር ልማት ሥራ ከገቢ ማስገኛና ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ጥቅም እንዲያስገኝ የግሪነሪ ልማቱን በአግባቡ መንከባከብ እና በዘርፉ የሚሰማሩ ማህበራትን በማደራጀት የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 26/2019 ዓ.ም

የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ አፈጻጸምን ለማሻሻል የተቋማት የጋራ አቅጣጫ ተቀመጠ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስትና የግል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተካሄዱ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን፣ በቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ትኩረት መስኮች አፈጻጸም ላይ የታዩ ክፍተቶችን እና ሊወሰዱ የሚገቡ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በመገምገም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ። መድረኩ በአስተዳደሩ ካሉ የመንግስትና የግል ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዲኖች፣ ምክትል ዲኖች፣ የስልጠናና የእቅድ ክፍል ተጠሪዎች ጋር በቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ላይ ዳሰሳ በማድረግ የተካሄደ ሲሆን፣ ከስትራቴጂ ትኩረት መስኮች (Pillars) አንፃር የተለዩ የአፈጻጸም ክፍተቶች ቀርበው በመፍትሔ አቅጣጫዎቹ ላይ ሰፊና ግልጽ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም የተቋማትን ማህበርና ክላስተር በማጠናከር የተቋማቱን የጋራ አቅም ማሳደግ፣ በተቋማት መካከል የልምድና የሀብት ልውውጥን ማስፋፋት እንዲሁም ከኢንዱስትሪው ጋር ያለውን የትብብርና የአጋርነት ትስስር ማጠናከር የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። ተሳታፊዎቹም የተለዩ ክፍተቶችን በተግባራዊ መፍትሔዎች ለመዝጋት፣ የስትራቴጂ ትኩረት መስኮችን በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር እና የተቋማትን አፈጻጸም በተከታታይ ለማሻሻል በወጣው የድጋፍና ክትትል ፕሮግራም ለመመራት ተስማምተዋል። የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ከስትራቴጂ ወደ ተግባር፣ ከተግባር ወደ ውጤት በመሸጋገር የሚፈለገውን የክህሎት ልማት ለማምጣት የተቋማት ትብብር፣ የኢንዱስትሪ ትስስር እና ተከታታይ የድጋፍና ክትትል ሥርዓት ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል። መድረኩም የተለዩ ክፍተቶችን በመፍትሔ አቅጣጫዎች ለመዝጋት፣ የተቋማትን ትብብር ለማጠናከር እና ከኢንዱስትሪው ጋር ያለውን አጋርነት በውጤታማ ሁኔታ ለማስቀጠል በመስማማት ተጠናቋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 26/2019 ዓ.ም

በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የቅሬታ አፈታት ኮሚቴ (GRM)ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ባለድርሻ አካላትና የኮሌጁ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በተገኙበት በዛሬው እ
+3
በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የቅሬታ አፈታት ኮሚቴ (GRM)ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ባለድርሻ አካላትና የኮሌጁ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በተገኙበት በዛሬው እለት ተከናወነ፡፡ በዛሬው እለት የተከናወነው የኮሚቴው ስብሰባ በዋናነት ከግዥና ከግንባታ ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች በEASTRIP ፕሮጀክት ደረጃ እና በኮንትራክተሩ ደረጃ የተነሱ ቅሬታዎችን መከለስ፣ መከታተል እና የተፈቱበትን ሁኔታ ይፋ ለማድረግ ያለመ ነበር በዚሁ መድረክ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ኢ/ኤ/ቴ/ሽ ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ሲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎች እንዳይከሰቱ በቂ የመከላከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ፣ ቅሬታዎች ከተነሱም በወቅቱ እንዲመዘገቡ፣ እንዲፈቱ እና ለባለድርሻ አካላት ተገቢው ምላሽ እንዲሰጥ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በስብሰባው ወቅት ኮሚቴው በባለድርሻ አካላት የቀረቡ ቅሬታዎችን፣ ቅሬታዎቹን ለመፍታት የተወሰዱ እርምጃዎችን እና የአፈታት ሂደታቸውን ለባለድርሻ አካላት አቅርቦ የተገመገመ ሲሆን የኮሚቴው አባላትም በቀሪው የፕሮጀክት ትግበራ ወቅት የቅሬታ አፈታት ሥርዓቱን በተገቢው ሁኔታ መከታተልና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውጤታማ ተሳትፎና ግንኙነት ማረጋገጥ እንዳለበት አጽንዖት ተሰጥቶት ተወያይተዋል፡፡   በተጨማሪም፣ የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም. የቅሬታ አፈታት ዕቅድ ለኮሚቴው ቀርቦ በዝርዝር ተገምግሟል። ከውይይትና ከግምገማ በኋላ ኮሚቴው ዕቅዱን አጽድቋል።   የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መስከረም 26/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

100 ቀናት፤ ከዕቅድ ወደ ውጤት ከመስከረም 25/2019 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 30/2019 ዓ.ም ባሉት 100 ቀናት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያካተተ የሥራ ዕቅድ ቀርቦ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ማኔጅመንት ውይይት ተካሂዷል። የ100 ቀናቱ ዕቅድ አገራዊ የመንግሥት የሥራ አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚከናወኑ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን በትኩረት ለመፈጸምና የአስተዳደሩን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው። የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ የቢሮው የሥራ አቅጣጫ በተግባር የሚመዘን ውጤትንና የአስተዳደሩን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዋና ትኩረቱ ያደርጋል። “ውጤት ተኮር አሠራርን መከተል ይገባል፤ ትኩረታችንም ‘ምን አደረግን?’ በሚለው ብቻ ሳይሆን ‘ምን ውጤት አመጣን?’ በሚለው ላይ ይሆናል” ብለው ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ተናግረዋል። በመሆኑም በ100 ቀናቱ የሚከናወኑ ተግባራት በግልጽ ዕቅድ፣ በተጠያቂነትና በውጤት መለኪያ እንዲመሩ በማድረግ የሥራና ክህሎት ዘርፉ ለአስተዳደሩ ነዋሪዎች የሚያመጣውን ተጨባጭ ተጠቃሚነት ማሳደግ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ሆኖ ተቀምጧል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 25/2019 ዓ.ም

የሥራ ርክክብ ለተቋማዊ ቀጣይነት   የድሬዳዋ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ የሥራ ርክክብና ከቢሮው ማኔጅመንት ጋር ትውውቅ  አካሄዱ   የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ከቀድሞው የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ጋር የሥራ ርክክብ አካሂደዋል።   የሥራ ርክክቡ የቢሮውን የሥራ አፈጻጸም፣ ቀጣይ ተግባራትና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገቡ የሥራ አቅጣጫዎችን በማስተላለፍ የአመራር ሽግግሩ በተቋማዊ ቀጣይነት እንዲከናወን መሠረት ጥሏል።   ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በርክክቡ ወቅት የቢሮው የቀድሞ የሥራ ልምዶችና የተጀመሩ ተግባራት እንደ መሠረት በመውሰድ የተቋሙን ሥራ በትብብር፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሠራር ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።   በተያያዘም ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ከቢሮው ማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅ በማድረግ የቢሮውን የሥራ አመራር ሂደት ተዋውቀዋል።   የሥራ ርክክቡ በአዲስ አመራር ሥር የቢሮው ተግባራት ያለመቋረጥ እንዲቀጥሉ፣ የተጀመሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩና ተቋሙ የሚያተኩርባቸው ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች በተቀናጀ አመራር እንዲመሩ ያስችላል።   የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 25/2019 ዓ.ም

የ‹‹ብቃት›› የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ 4ኛ ዙር ምዝገባ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ቢሮው ገለጸ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ዙር የሚተገበረውን “ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት በማስመልከት ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመሆኑም እድሜያቸው ከ18–29 ዓመት የሆኑ፣ 12ኛ ክፍልና ከዚያ በታች የትምህርት ደረጃ ያላቸው፣ ፋይዳ፣ የቀበሌ መታወቂያና የንግድ ባንክ አካውንት ማቅረብ የሚችሉ፣ ሥራ የሌላቸውና በፕሮጀክቱ አሠራር ለመመራት ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው። ቢሮው ብቁ የሆኑ የአስተዳደሩ ወጣቶች እስከ መስከረም 28/2019 ዓ.ም ድረስ በወረዳ/ቀበሌ የሥራ ማዕከላት በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አስተላልፏል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 23/2019 ዓ.ም

መልካም ዜና ለድሬዳዋ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች!!! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ዙር ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” በርካታ የከተማችንን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ለ
መልካም ዜና ለድሬዳዋ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች!!! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ዙር ”ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት” በርካታ የከተማችንን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ለማድረግ አስቧል። በዚህም መስፈርቱን የሚያሟሉ 1ኛ. ዕድሜ፡- ከ18 እስከ 29 2ኛ. የትምህርት ደረጃ ፡-12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በታች 3ኛ. ፋይዳ ፣ የቀበሌ መታወቂያ እና የንግድ ባንክ አካውንት ማቅረብ የሚችሉ 4ኛ. ምንም አይነት ስራ የሌላቸው 5ኛ. በፕሮጀክቱ አሰራር ለመመራት ፍቃደኛ የሆኑ ከመስከረም 20-28/2019 ዓ.ም በወረዳ/ቀበሌ ሥራ ማዕከላት በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

#ዜና_ሹመት!!! ዶ/ር ፍቃዱ በየነ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን!!!
#ዜና_ሹመት!!! ዶ/ር ፍቃዱ በየነ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን!!!

የአቶ ሮቤል ጌታቸው የምስጋና መልዕክት ውድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ማህበረሰብ፣ በቢሮው ኃላፊነት ቆይታዬ አብራችሁኝ ለሠራችሁ፣ ለደገፋችሁኝና ለተቋሙ ውጤት ያደረጋችሁትን ያላሰለሰ ጥ
የአቶ ሮቤል ጌታቸው የምስጋና መልዕክት ውድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ማህበረሰብ፣ በቢሮው ኃላፊነት ቆይታዬ አብራችሁኝ ለሠራችሁ፣ ለደገፋችሁኝና ለተቋሙ ውጤት ያደረጋችሁትን ያላሰለሰ ጥረት በልቤ እያደረግሁ ከፍተኛ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የተመዘገቡት ውጤቶች የአንድ ሰው ሳይሆኑ፣ የጋራ ትጋታችን፣ ትብብራችንና የሥራ ባህላችን ውጤት ናቸው። በተለይም በተቋሙ ውስጥ የሚታየው የለውጥ መንፈስ በሁላችሁም ተሳትፎ የተገነባ ነው። የቢሮ ኃላፊነቴን ለማስረከብና ቀጣይ ፓርቲዬ በሚሰጠኝ የስራ መደብ ለመስራት በተዘጋጀሁበት በዚህ ወቅት፣ ለሁላችሁም ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በቀጣይም የጀመራችሁትን ሥራ በተሻለ ትጋትና በተቋማዊ ትብብር እንድታስቀጥሉ አደራ እላለሁ። ከልብ አመሰግናለሁ።

የአራተኛው ዙር የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት የአሰልጣኝ መምህራን ሥልጠና ተጀመረ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአራተኛው ዙር የ“ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ትግበራ ለሚሳተፉ ከሁለቱ የመንግሥት ኮሌጆች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራን የሕይወት ክህሎትና የሥራ አፈላለግ ሥልጠና መስጠት ጀመረ። ሥልጠናው ወጣቶችን ወደ ሥራ ዓለም በተሻለ ዝግጅት ለማስገባት የሚያስፈልጉ የሕይወት ክህሎቶችን፣ የሥራ ፍለጋ ዘዴዎችን፣ የሥራ ዓለም ዝግጅትን እና የሙያ አመራር ችሎታዎችን ለወጣቶች በተግባር ለማስተላለፍ አሰልጣኝ መምህራኑን ለማብቃት ያለመ ነው። የአሰልጣኝ መምህራኑ ሥልጠና በቀጣዮቹ 12 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጊዜ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ምዝገባም የሚካሄድ ይሆናል። ይህ ሂደት ወጣቶችን በክህሎት ብቻ ሳይሆን በሥራ ዓለም የሚያስፈልጉ የግል አቅም፣ የመግባባት፣ የችግር አፈታት፣ የሥራ ፍለጋና የሙያ ዝግጅት ችሎታዎችን በማሳደግ ወደ ሥራ ዓለም በተሻለ ዝግጅት እንዲገቡ የሚያግዝ ነው። በመሆኑም የአራተኛው ዙር የ“ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ከሥልጠና ወደ ተግባራዊ የሥራ ልምድ በመሻገር ወጣቶችን ለሥራ ዓለም የማዘጋጀትና የሥራ ዕድል ተጠቃሚነታቸውን የማሳደግ ዓላማን ያጠናክራል። “ብቃትን ከሥልጠና ወደ ሥራ፤ ወጣቶችን ከእውቀት ወደ ዕድል!” የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት | መስከረም 19/2019 ድሬዳዋ

የሴቶች ተሳትፎን ያጎለበተ የማህበራት ምስረታ በዚህ ዓመት ከሚደራጁ 58 ማህበራት ውስጥ 35ቱ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚደራጁ ይሆናሉ። ኢንጂነር ኢሳም ሁሴን፣ የድሬዳዋ ቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP II) ስራ አስኪያጅ የድሬዳዋ ቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP II) በስራ ፈጠራ፣ በንግድ ልማት፣ በስራ አመራር፣ በቡድን ስራ እና በELMIS አጠቃቀም ዙሪያ ለስራና ክህሎት ባለሙያዎች ስልጠና ጀምሯል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ኢንጂነር ኢሳም ሁሴን እንደገለጹት፣ በዚህ ዓመት የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማጠናከር 58 ማህበራት የሚደራጁ ሲሆን፣ 35ቱ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመሰረቱ ይሆናሉ። ስልጠናው የሚመሰረቱ ማህበራትን በብቃት ለመደገፍና ለመከታተል የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት ያለመ ሲሆን፣ በልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

#ለዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!! በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካምፓስ በ2019 የትምህርት ዘመን በሚከተሉት ሙያዎች በመጀመርያ ዲግሪ በምሽት (NIGHT) ወይም በቅዳሜ እና እሁድ (weekend) መርሃግብር፤ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከ 14/1/2019 እስከ 25/1/2019 በድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት እንድታመለክቱ እያስተወቅን የመግብያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በውስጥ ማስታወቅያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡