cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 መታረም ያለበትን ወይም አስተያየቶች @Ortodoxawi04 በዚህ ይንገሩኝ::

Більше
Рекламні дописи
505
Підписники
+124 години
+137 днів
+4030 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
Media files
350Loading...
02
#ግንቦት_24 ግንቦት ሃያ አራት በዚች ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ከዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ፣ ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ #ነቢይ_ዕንባቆም አረፈ፣ የእንጽና አገር የከበረ #ቀሲስ_አብቍልታ በሰማዕትነት አረፈ፣ ዳግመኛ በዚህች ቀን የአሮን ልጅ የ #አልዓዛር ዕረፍቱ ሆነ ደግሞ የ #አርከሌድስ የ #ቴፍላስ የ #ማርዩ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ስደት ግንቦት ሃያ አራት በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ። ያን ጊዜም እርሱ ጌታ የሁለት ዓመት ሕፃን ነበር። ወንጌላዊ እንዳለ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ምድር ሽሽ ተመለስ ብዬ እስከምነግርህም በዚያው ኑር። የጌታችንም ወደ ግብጽ መምጣት ሰለ ሁለት ሥራዎች ነው አንዱ ኄሮድስ ቢያገኘው ሊገድለው እንደአይችል። ስለዚህ ሌሎች ትስብእቱ ምትሐት ነው ብለው እንዳያስቡ። ሁለተኛው የግብጽ ሰዎች በመካከላቸው በመመላለሱ ጸጋውን እንዲያገኙ ጣዖታትንም ቀጥቅጦ ለማጥፋት እነሆ አግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ጣዖታትም በፊቱ ይወድቃሉ ያለው የነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ። የክብር ባለቤት ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ ሸሸ በመጀመሪያም የደረሱበት አገር ስሙ በስጣ ይባላል አልተቀበሏቸውም በዚያም የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ ያቺም ውኃ ለሩቆች ፈዋሽ ስትሆን ለዚያች አገር ሰዎች ግን መራራ ሆነች። ከዚያም በገምኑዲ መንገድ ተጉዘው ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ ደረሱ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ተረከዙን በአለት ላይ አደረገ በተረከዙም አምሳል በአለቱ ላይ ተቀረጸች እስከ ዛሬ ያም ቦታ የጌታችን የተረከዝ ቅርጽ ተባለ። ጌታችንም እመቤታችን ድንግል ማርያምን እናቴ ሆይ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ይሠራ ዘንድ እንዳለው ዕወቂ። በውስጡም ድንቅ ተአምራትን አደርጋለሁ ስሙም ደብረ ምጥማቅ ይባላል አላት። ከዚያም ወደ ፀሐይ መግቢያ ወዳለ ባሕር ሔዱ የአስቄጥስንም በረሀ ዱር ከሩቅ አዩ። ጌታም በላዩ ባረከ እናቱንም እናቴ ማርያም ሆይ በዚህ ዱር ውስጥ ብዙዎች ሰዎች መነኰሳትን ሁነው በገድልም ተጸምደው በመላእክት አምሳል ያገለግሉኛል። ከዚያም በፀሐይ መውጫ በኲል ወደአለ ተራራ ሔዱ ዮሴፍም የሚመረኰዘው በትር በእጁ ነበር ጌታችንም ይህ ቦታ የሚያቃጥል በረሀ ነውና እንቀመጥ አለ። ጌታችንም የዮሴፍን በትር አንሥቶ ሰበራት ጥቃቅን ስብርባሪዎች አድርጎ በዚያ ቦታ ተከላቸው። በከበሩ እጆቹ ጉድጓድ ማሰ መዓዛው የሚጣፍጥ ውኃ ፈልቆ ፈሰሰ ከእዚያ ውኃም በመሐል እጁ እየዘገነ የተከላቸውን ስብርባሪዎች አጠጣቸው። ወዲያውኑ በቀሉ አድገውም ታላላቅ ዛፎች ሆኑ ከእርሳቸውም ጣፋጭ ሽታ ሸተተ። እርሱም ከሽቱዎች ሁሉ እጅግ የሚጣፍጥ ነው በለሳንም ብሎ ጠራቸው። እናቱን ድንግል እመቤታችንንም እናቴ ሆይ ይህ የተከልኩት በለሳን እስከ ዓለም ፍጻሜ ከዚህ ይኖራል የክርስትና ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለሚጠመቁ ከእርሱ ቅባት ይገኛል አላት የዚያም ስም መጣሪያ ነው። ከዚያም ብህንሳ ወደሚባል አገር ሔዱ ትርጓሜው ቤተ ኢየሱስ የሆነ በይሱስ ወደሚባልም ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሽታውን ደዌውን ሁሉ የሚፈውስ የጒድጓድ ውኃ አደረገ። ሁለተኛም በአንዲት የጕድጓድ ውኃ ምልክትን በየዓመቱ አደረገ ይኸውም ከቀኑ እኲሌታ በማዕጠንትና በጸሎት ጊዜ ለእግዚአብሔር በዚያች የውኃ ጕድጓድ ዕጣንን ሲያሳርጉ የከበረ የወንጌል ንባብም ሲፈጸም በዚያች ጉድጓድ ውስጥ ያለ ውኃ ወደ ላይ ወጥቶ እስከ ጉድጓዱ አፍ ይደርሳል። ከእርሱም ይባረካሉ ከዚያም በኋላ እንደ ቀድሞው ወደ ቦታው ይመለሳል። ውኃው ከነበረበት እስከ ደረሰበት ይሰፍሩታል። ሃያ ክንድ የሆነ እንደሆነ የጥጋብ ዘመን ይሆናል ዐሥራ ሰባት ክንድ ከሆነ ግን በግብጽ አገር ታላቅ ረኃብ ይሆናል። ከዚያም ወደ እስሙናይን አገር ሔዱ በዚያ ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ። እነርሱም ስሙ አፍሎን ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጡ። በዚያም የእሸ እንጨት ዛፎች አሉ ለጌታችንም ሰገዱ እስከ ዛሬም እንደ ሰገዱ ናቸው። ከዚያም ወደ ደብረ ቍስቋም ሔደው በውስጧ ስድስት ወር ተቀመጡ በዚያም በሽታን ሁሉ የሚያድን የጉድጓድ ውኃ አደረገ። ጌታችንም የፈቀደውን በግብጽ የሚኖርበት ወራት በፈጸመ ጊዜ ይኸውም ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው። ኄሮድስም ከሞተ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሙተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ተመለስ አለው። ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚወጣው ነው። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከብርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው። በጌታችን መመለስም ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ያለው የኦዝያን ትንቢት ተፈጸመ። ስለዚህም ተአምራትን በግብጽ ድንቅ ሥራንም በጣኔዎስ በረሀ ያደረገ በማለት እየዘመርን በዚች ዕለት መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ስለ እኛ ለተሰደደ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ምሕረቱ ይሁን። አምላክ የወለደች የተባረከች የድንግል እመቤታችን #ማርያም በረከቷ የዮሴፍና የሰሎሜም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ዕንባቆም_ነቢይ በዚህችም ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነቢይ ዕንባቆም አረፈ። ይህም ቅዱስ በአንዲት ዕለት እህሉን ለሚያጭዱለት ምሳቸውን አዘጋጅቶ ተሸክሞ ሲሔድ መልአክ ተገልጾለት ይህን መብል በባቢሎን አገር በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ላለ ለነቢዩ ዳንኤል ውሰድ አለው። ዕንባቆምም ጌታዬ ሆይ ባቢሎንን አላየኋት ጉድጓዱንም አላውቀው አለው። የእግዚአብሔር መልአክም በራሱ ጠጉር ያዘው ምግቡን በእጁ እንደያዘ ወሰደውና ጉድጓዱ እንደተዘጋ አስገባው ምግቡንም ሰጥቶ መገበው ወዲያውኑ ዕንባቆምን ወደ ይሁዳ አገር መለሰው። በአረጀና በሸመገለም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ከተማረኩበት ተመልሰው ቤተ መቅደስን ሠሩ። ዕንባቆምም ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በታላቅ ደስታም ተቀበሉት ትንቢቱንም ሊሰሙ ወደርሱ ተሰበሰቡ አፉንም ከፍቶ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ። አቤቱ ድምፅህን ሰማሁ ሰምቼም ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ አለ። ስለ መድኃኒታችንም መውረድና በይሁዳ ክፍል በሆነች በቤተ ልሔም ስለመወለዱ ሲናገር የተመሰገነ እግዚአብሔር ግን ከፋራን ተራራ ከቴማን ከይሁዳ አውራጃ ይመጣል ብሎ እስከ መጨረሻው ተናገረ ከነቢያት መጻሕፍትም ጋራ ደመርዋት።
320Loading...
03
ከዚህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች አንዲት ሴት ወደርሱ መጣች እያለቀሰችም እንዲህ አለችው። ሁለት ልጆች ነበሩኝ ጣዖት እንዲአመልኩ ፈለጉአቸው እምቢ በአሉ ጊዜም ገድለው በጐዳና ላይ ጣሉአቸው። ተገድለው ወደ አሉበትም አብሮዋት ሔደ ነፍሳቸውንም ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው ልመናውንም ተቀበሎ በሕይወት አነሣቸው። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ዘመዶቹን ጠራቸው። እንደሚሞትም ነገራቸውና አንዲት ሰዓት ያህል ወደላይ እየተመለከተ ተቀመጠ። እነሆ እንደ ሰው ክንድ ያለች ታላቅ ክንድ የቤቱን ጣሪያሠንጥቃ ወረደች ወደ አፉም ተዘርግታ ነፍሱን ወሰደች ያን ጊዜም አረፈ። በክርስቲያናዊ ንጉሥ በአንስጣስዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ ገድሉን በአነበበ ጊዜ አድንቆ በግብጽ ደቡብ ቀርጣስ በሚባል ቦታ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሠራለት እርሷም በዚች ቀን ከበረች። #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቀሲስ_ቅዱስ_አብቍልታ በዚህችም ዕለት የእንጽና አገር የከበረ ቀሲስ አብቍልታ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ባለ መድኃኒት ነው ለበሽተኞች በጎ ሥራ በመሥራት ያለ ዋጋ ያክማቸዋል ደግሞም የሚበሉትን የሚጠጡትን የሚለብሱትን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል ። በዚያም ወራት ወደ ሰዒድ አውራጃ ወደ መኰንኑ አርያኖስ ዲዮቅልጥያኖስ ላከ የዚያቺን አገር ሰዎች ለጣዖታት እንዲሰግዱ ያስገድዳቸው ዘንድ። በዚያንም ጊዜ ይህን ቅዱስ ያዙት ወደ እስሙናይንም ወስደው በመኰንኑ ፊት አቆሙት መኰንኑም ወደርሱ ይመልሰው ዘንድ በጎ ቃልን ተናገረው ሊመልሰውም ባልቻለ ጊዜ ቆዳው እስቲሠነጣጠቅ እንዲገርፉት አዘዘ ከዚህም በኋላ በሕይወት እያለ በእሳት አቃጠሉት። ገድሉንም በዚህ ፈጸመ ምእመናንም መጥተው በድኑን ወሰዱ ከከተማው ደቡባዊ በሆነ ተራራ ላይ ገንዘው በክብር ቀበሩት። #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት_24)
350Loading...
04
Media files
390Loading...
05
Media files
891Loading...
06
#ግንቦት_21_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ማቴዎስ 18 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር። ⁷ ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት። ⁸ እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ⁹ ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ¹⁰ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና። ¹¹ የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና። ¹² ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን? ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የ #ሚቀደሰው_ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የደብረ ምጥማቅ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
871Loading...
07
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_21_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ቆሮንቶስ 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ። ¹⁰-¹¹ ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥ ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፥ እኔ ግን አላዝም፥ ጌታ እንጂ። ¹² ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤ ¹³ ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው። ¹⁴ ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። ¹⁵ የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። ¹⁶ አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ? ¹⁷ ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ። እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ። ¹⁸ ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። ¹⁹ መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ። ²⁰ እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር። ²¹ ባሪያ ሆነህ ተጠርተህ እንደ ሆነ አይገድህም፤ አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል። ²² ባሪያ ሆኖ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው። ²³ በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። ²⁴ ወንድሞች ሆይ፥ እያንዳንዱ በተጠራበት እንደዚሁ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር። ²⁵ ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥ ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ ከጌታ ምሕረትን የተቀበልሁ እንደ መሆኔ ምክር እመክራለሁ። ²⁶ እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር መልካም ነው። ²⁷ በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ። ²⁸ ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር። ²⁹ ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ ³⁰ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ ³¹ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። ³² ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ³³ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል። ³⁴ ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች። ³⁵ ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም። ³⁶ ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ። ³⁷ ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም፥ የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል፤ ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ። ³⁸ እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ። ³⁹ ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። ⁴⁰ እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ራእይ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። ² እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች። ³ ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥ ⁴ ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ። ⁵ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁴ እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤ ⁴⁵ አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። ⁴⁶ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ። ⁴⁷ ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት። ⁴⁸-⁵⁰ ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም። ⁵¹ እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_21_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ሰወረከኒ በዕለተ ቀትል መልዕልተ ርእስየ። ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን። ተማከሩ ላዕሌየ ኢትኅድገኒ ከመ ኢይዘኀሩ"። መዝ 139፥7-8 አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጕልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ። አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለኃጢአተኞች አትስጠኝ፤ በላዬ ተማከሩ፤ እንዳይጓደዱ አትተወኝ። መዝ 139፥7-8 ወይም👉ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር። ጻድቅ በምሕረት ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የኃጢአተኛ ዘይት ግን ራሴን አይቅባ፤ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና። መዝ.104÷4-5 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
791Loading...
08
#ግንቦት 21 "እናቴ _ማርያም _ደጓ_እናቴ" እንኳን _ለደብረ _ምጥማቅ _አመታዊ _የመገለጥ _በዓል _በሰላም _በጤና _አደረሳችሁ_አደረሰን። #OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ #ማርያም #ግንቦት21  #profile #timline #post #story On Telegram👇          • t.me/winagfx2          • t.me/winaGraphics Share 🙏 https://t.me/winaGraphics
731Loading...
09
https://t.me/Gedilatwedirsanat
1402Loading...
10
ቅዱሳን አባቶቻችን ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን። ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፏል። ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው። አረጋዊ ታዴዎስ በተመሳሳይ ኃጢአት በተደጋጋሚ ብትወድቁም በወደቃችሁበት ቦታ ሳትቆዩ ወደ እግዚአብሔር ሩጡ፡፡ አብዛኛዎቹ የቀደሙት ኃጢአቶች በእኛ ላይ የሚበረቱት ልምድ ሆነውብን ስለኖሩ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉት ኃጢአቶችም ከጊዜና ከፅኑ ፍላጎት ጋር ብቻ ነው ድል የሚነሱት።  ቅዱስ ኔክታሪዮስ @Orthodox_tewahdo_1
1110Loading...
11
Media files
1170Loading...
12
Media files
1351Loading...
13
https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_5533540596 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
1390Loading...
14
#ግንቦት_16 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ስደስት በዚችም ቀን #ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ መታሰቢያው ነው፣ ዕውቀትን ከልቡ ያፈለቀ የኢየሩሳሌሙ ሰው #ቅዱስ_ኢያሱ_ሲራክ_ነቢይና_ጠቢብ አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #ለአቡነ_ሐዋርያ_ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ከሞት ተሰወሩ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ ግንቦት ዐሥራ ስደስት በዚችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው #እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት #ጌታችን በእጆቹ ላይ የሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው። በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን። ከዚህ በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ። ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው። (ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት 16) ተጨማሪ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡ እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ ‹‹በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን›› እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም ‹‹አይዞሽ አትዘኚ›› አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ ‹‹ #እግዚአብሔር የሚሉት #አምላክ አንተ ነህን›› ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹በፍጹም እኔ #አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ›› አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡ በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስታል፡፡ ዛሬ ግንቦት 16 ቀንም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡ ይኸውም በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸውም ባሉ አገሮች ሁሉ ወንጌልን ስለመስበኩና ስለደረሰበት መከራ ስላደረጋቸውም ብዙ ተአምራት ነው፡፡ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡ #ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በ #እግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…›› ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ ‹‹ምን ማድረግህ ነው›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው›› ሲለው ዮሐንስም መልሶ ‹‹ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹አዎን›› አለው፡፡ ዮሐንስም ‹‹በከንቱ ደከምክ›› አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ ‹‹አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ ‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በ #እግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..› ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ›› አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ ‹‹ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…›› ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ #ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ #እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለ #እመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን #እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ #ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የ #ጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የ #ጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም #ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ #ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የ #ጌታችን
1560Loading...
15
Media files
1010Loading...
16
Media files
1110Loading...
17
#አቡነ_ሐዋርያ_ክርስቶስ በዚህች ቀን ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ከሞት ተሰወሩ፡፡ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ መርሐ ቤቴ ነው፡፡ እንደ እነ ኤልያስና ሄኖክ ተሰውረዋል እንጂ በምድር ላይ ሞትን አልቀመሱም፣ ገና ወደፊት መጥተው በሰማዕትነት ይሞታሉ፡፡ ልደታቸው ሐምሌ 16 ቀን ነው፡፡ የነበሩበት ዘመንም በጻድቁ ንጉሥ በዐፄ ገብረ ማርያም ሐርበይ ዘመን ነው፡፡ ጻድቁን መልአኩ ከሚያገለግሉበት ከወሎ የህላ ሚካኤል ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ወስዷቸው እንዲመነኩሱ አድርጓቸዋል፡፡ የቆረቆሩት ‹‹አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ገዳም›› ወሎ መሐል ተከዜ ውስጥ ይገኛል፡፡ የበዛው ገድላቸው በዝርዝር ተጽፎ አይገኝም፡፡ ተከዜ በረሃ ላይ እጅግ አስደናቂ ትልቅ የአንድነት ገዳም አላቸው፡፡ 12 ክንፍ የተሰጣቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ በዛሬዋ ዕለት ነው የተሠወሩት፡፡ #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። #ግንቦት_16_ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 4. አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ከሞት የተሰወሩበት #ወርኀዊ_በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ   (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ 📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" (ዮሐ. 19:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት እና #ከገድላት_አንደበት)
1030Loading...
18
#ግንቦት_15 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ አምስት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሐዋርያ ስምዖን ምስክር ሆኖ አረፈ፣ በላይኛው ግብጽ ውስጥ በደንደራ ከተማ በሰማዕትነት ለዐረፉ #ለአራት_መቶ_ሰዎች ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ፣ በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ #ከባሕታዊ_ሚናስ፣ #ከዲያቆንና_ከአባ_ሐርበጥላክያ ሰማዕታት ከሆኑ #ከኤስድሮስም_ማኅበር ከሆኑ #ቀርጢኖስና_ሚስቱ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ናትናኤል_ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን) ግንቦት ዐሥራ አምስት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሐዋርያ ስምዖን ምስክር ሆኖ አረፈ፣ እርሱም ናትናኤል ተብሎ ይጠራል በገሊላ አውራጃ የቃና ሰው ነው የኦሪትና የነቢያትንም መጻሕፍት ተምሮ ያወቀ ነው። መንፈሳዊ ቅንዓትም በውስጡ አለበት ስለዚህም ቀናዒ ተባለ እርሱም ንጹሕ ፊት አይቶ የማያደላ በሃይማኖቱ ዕውነተኛ ነው። ስለዚህም ፊልጶስ ስለርሱ ሙሴ የጻፈለትን የዮሴፍ ልጅ የሚሉትን የናዝሬቱን ክርስቶስን አገኘነው ባለው ጊዜ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻላልን አለው እንጂ አላደላለትም ፊልጶስም ታይ ዘንድ ና አለው። በመጣም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ይህ በልቡ ሽንገላ የሌለበት ዕውነተኛ እስራኤላዊ ነው አለው። አሁንም ምስጋና ወደመቀበል አልተመለሰም በየት ታውቀኛለህ አለው እንጂ ልብንና ኵላሊትን የሚመረምር ጌታችንም ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት በበለስ ዕንጨት ሥር አየሁህ አለው። ያን ጊዜም የተሠወረውን የሚያውቅ አምላክ መሆኑን ተረድቶ ጌታዬና ፈጣሪዬ በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ አለው እንደ አይሁድ መምህራንም አልተቃወመም እነርሱ ከዚህ የሚበልጥ ድንቅ ተአምራትንና ኃይሎችን አይተው ለዕውነት አልተገዙምና። ስለርሱ እንዲህ ተብሏል ጐልማሳ ሁኖ ሳለ ከአሕዛብ ወገን ከሆነ ጐልማሳ ጋራ ተጣልቶ አንዲት አመታትን መትቶ ገደለው በቤቱ ዐፀድም በአለ ዕፀ በለስ በሥሩ ቀበረው ይህንንም ማንም አላወቀበትም። ሁለተኛም በሕፃናት ዕልቂት ጊዜ እናቱ በአገልግል ውስጥ አድርጋ በበለስ ዕንጨት ላይ ሰቅላ ትሸሽገው እንደ ነበር በጭልታም አውርዳ አጥብታ መልሳ ትሰቅለዋለች የከመራውም ጊዜ ጸጥ እስከ አለ ድረስ እንዲህ ታደርግ ነበር። መድኃኒታችንም በምልክት ከእርሱ የሆነውን በገለጠለት ጊዜ የተሠወረውን የሚያወቅ ሁሉንም የሚመረምር በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተረዳ። ያንጊዜም ራሱን ዝቅ አድርጎ ለመድኃኒታችን ተገዛለት። ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ተከተለው ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያትም ጋራ ተቈጠረ። አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በተቀበለ ጊዜ የሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተገለጠለት መለኮታዊ ምሥጢርንም አወቀ ወደ ኵርጅ አገርና ወደ እልብጅህ ከተማ ከሀድያን በድንቁርና ወደሚኖሩበት ሁሉ ገብቶ የሃይማኖትን ብርሃን አበራላቸው። ከተራቃቂዎችና ከሰነፎችም ብዙዎችን መልሶ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሃይማኖት ልባቸውን አበራላቸው። የክርስትና ጥምቀትንም አጥምቆ ነጣቂዎች ተኵላ የነበሩትን የዋሃን በጎች አደረጋቸው። ሁለተኛም ወደሌሎች የከሀድያን አገሮች ወደ በራንጥያ ደሴትም ሒዶ በውስጣቸው ሰበከ። ይዘውም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃዩት እርሱ ግን ኃይልና ብርታትን ተጨመረ በእግዚአብሔርም ኃይል ሙታንን አስነሣ እንዲአጠምቃቸውም ለመኑት የክርሰትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ብዙ ዘመንም ኖረ። ከዚህም በኋላ ከሀድያን ይዘው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት በዚህም ምስክርነቱን ፈጽሞ ከወንድሞቹ ሐዋርያት ጋራ የማይጠፋ መንግሥትን ወረሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ናትናኤል ጸሎት ይማረን ለሁላችን የክርስቲያን ወገኖችም በረከቱ ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። "#ሰላም_ዕብል_ብእሴ_ምሁር። ዘመጽሐፈ ኦሪት ሕገ ወዘነቢያት መዝሙረ። አመ ውእቱ ወሬዛ ታሕተ ዕፀ በለስ ዘገብረ። #ወልደ_ማርያም_አምላክ ሶበ ኅቡአቶ አእመረ። ለትእዛዘ #ጽድቁ_ናትናኤል_ገረረ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_15። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አራት_መቶ_ሰማዕታት፦ ብዙ ሥቃንም ሲያሠቃዩአቸው ከኖሩ በኋላ የምስክርነታቸው ፍጻሜ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት መጨረሻ ራስን በመቆረጥ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት_15)
1290Loading...
19
ሴትና መላ በመካከለኛው ዘመን በፈረንሳይ አነስተኛ ከተማ ሚስቶች እንግዳ የሆነ ልማድ ነበራቸው። ይህም ጠዋት ላይ ሚስት ባል ሳያውቅ በቁርሱ ላይ አነስተኛ መጠን ያለው መ*ር*ዝ ትጨምራለች ፤ እናም በ12 ሰዓታት ውስጥ ካልተመለሰ እንደ ማቅለሽለሽ፣ ራስ ምታት፣ ድብርት፣ ማስታወክ፣ ህመም ወይም የትንፋሽ ማጠር ወዘተ ያሉ ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል። ምሽት ላይ ባሏ ወደ ቤቱ ሲመለስ የመ*ር*ዙ*ን ማርከሻ በምግብ ወይም በመጠጥ አድርጋ (እሱ ሳያውቅ) ትሰጠዋለች ፤ ከዚያን ያገግማል። ይህንንም በየቀኑ ታደርግበታለች ፤ ባልየው ጠዋት ከቤት ወጥቶ ወደ ሚስቱ ለመመለስ በዘገየ ቁጥር ህመሙ እየባሰበት ይሄዳል። እናም ማታ ቤት ገብቶ ማርከሻውን ሳያውቅ ሲወስድና በፍጥነት ሲሻለው ፣ ቤት ተመልሶ ከሚስቱ ጋር ስለሆነ የተሻለው ይመስለዋል። በዘመኑ ሚስቶች ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለባሎቻቸው ከቤት ርቆ መሄድ ወደ ህመም እና ድብርት እንደሚመራ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው። ስለዚህ በጊዜው ባሎች ከሚስቶቻቸው መራቅ ይፈሩና ቤት ቁጭ ይላሉ:: መ*ር*ዙ ምን እንደሆነ የፈረንሳይ እናቶች ስላልተናገሩ የኛዎቹ አገኘን ብላቹ የአይጥ መርዝ ተጠቅማችሁ ልጅን ያለ አባት እንዳታስቀሩ 😂🙌 ሁሌም ቤት-ቤቱን እንዲያሰኘው፣ ቢያንስ በትንሹ፣ በ*መ*ር*ዝ የተለወሰ ቃላት ሳይሆን በፍቅር በተሞላ ሰላምታ ተቀበይው ቤት ሲገባ። [ተጓዥ ልቦች] ማምሻዎች
1733Loading...
20
Media files
1701Loading...
21
አንድ ቀን ሚስት ለባሌ ሳልነግረው አንድ ቦታ ብሄድ ምን ሊሰማው ይችላል የሚለውን ማወቅ ፈለገችና እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈች,… " ካንተ ጋር መኖር ሰልችቶኛል እናም ከዚህ በኋላ አብሬህ መኖር አልፈልግም መልካም ህይወት " ብላ ፅፋ የመኝታ ክፍል ጠረጴዛ ላይ ደብዳቤውን በማስቀመጥ የባሏን ሁኔታ ለማየት አልጋ ስር ተደበቀች ። ባል ቤት ሲመለስ ያንን ደብዳቤ ያየውና አንስቶ ያነበዋል ። እናም እዛው ወረቀት ላይ ለደብዳቤው ምላሽ ፅፎ ልብሱን እየቀየረ መዳነስ ፣ መዝፈን ጀመረ ። ስልኩንም አንስቶ በመደወል " የኔ ውድ ልብሴን እየቀየርኩ ነው ወዳንቺ እመጣለው ከሚስቴ ጋር ተለያይተናል እስከዛሬ ከሷ ጋር በመቆየቴ እሷን አግብቼ በመኖሬ ስህተት ሰርቻለው አንቺን ቀደም ብዬ ባውቅሽ ጥሩ ነበር " አሁን መጣሁ በቃ ብሎ ስልኩን ዘግቶ ከክፍሉ ወጣ ። ሚስት በዕንባ እና በንዴት ከአልጋው ስር በመውጣት ባሏ መልሶ የፃፈላትን ለማንበብ ወሰነች ። ደብዳቤውንም አንስታ አነበበችው እንዲህ ይላል ፦ " ከአልጋው ስር እግርሽን አይቼዋለው ለማንም ሰው ስልክ አልደወልኩም ዳቦ ገዝቼ መጣሁ,…ተነሽ የሞኝ ጨዋታሽን ትተሽ ርቦኛል እባክሽ ምግብ ስሪልኝ " 😉
1851Loading...
22
Media files
2400Loading...
23
ግንቦት ፩ ልደታ ለማርያም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች! እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በሰላም አደረሠን!!! #ድንግል_ሆይ_ልደትሽ_ልደታችን_ነው፡፡ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ On Telegram👇          • t.me/winagfx2          • t.me/winaGraphics Share 🙏 https://t.me/winaGraphics
2643Loading...
24
እንኳን ለጌታችንና ለመድኅኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ። ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤   አሰሮ ለሰይጣን፤    አግዐዞ ለአዳም፤    ሠላም፤    እምይዕዜሰ፤     ኮነ፤    ፍስሐ ወሰላም፡፡ መልካም የትንሣኤ በዓል!✨❤️👏     
2370Loading...
25
#ተነስቷል በድንገት እየሩሳሌምን ከወደ ጎሎጎታ አካባቢ አስደንጋጭ ድምፅ አናወጣት ክርስቶስም በራሱ ሐይል እና ስልጣን በታላቅ ክብር ፈጥኖ ተነሳ። ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ... በተወለደ ጊዜ የእናቱን መሀተመ ድንግልና እንዳለወጠ ሁሉ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በመላእክት ታጅቦ በክብር ተነሳ። እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓለ ፋሲካ ይሁንልን!! እንደተናገረ ተነሥቶአል በዚህ የለም። ማቴ 28፡6 #OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ #profile #timline #post #story On Telegram👇          • t.me/winagfx2          • t.me/winaGraphics Share 🙏 https://t.me/winaGraphics
2270Loading...
#ግንቦት_24 ግንቦት ሃያ አራት በዚች ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ከዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ፣ ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ #ነቢይ_ዕንባቆም አረፈ፣ የእንጽና አገር የከበረ #ቀሲስ_አብቍልታ በሰማዕትነት አረፈ፣ ዳግመኛ በዚህች ቀን የአሮን ልጅ የ #አልዓዛር ዕረፍቱ ሆነ ደግሞ የ #አርከሌድስ የ #ቴፍላስ የ #ማርዩ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ስደት ግንቦት ሃያ አራት በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ። ያን ጊዜም እርሱ ጌታ የሁለት ዓመት ሕፃን ነበር። ወንጌላዊ እንዳለ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ምድር ሽሽ ተመለስ ብዬ እስከምነግርህም በዚያው ኑር። የጌታችንም ወደ ግብጽ መምጣት ሰለ ሁለት ሥራዎች ነው አንዱ ኄሮድስ ቢያገኘው ሊገድለው እንደአይችል። ስለዚህ ሌሎች ትስብእቱ ምትሐት ነው ብለው እንዳያስቡ። ሁለተኛው የግብጽ ሰዎች በመካከላቸው በመመላለሱ ጸጋውን እንዲያገኙ ጣዖታትንም ቀጥቅጦ ለማጥፋት እነሆ አግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ጣዖታትም በፊቱ ይወድቃሉ ያለው የነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ። የክብር ባለቤት ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ ሸሸ በመጀመሪያም የደረሱበት አገር ስሙ በስጣ ይባላል አልተቀበሏቸውም በዚያም የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ ያቺም ውኃ ለሩቆች ፈዋሽ ስትሆን ለዚያች አገር ሰዎች ግን መራራ ሆነች። ከዚያም በገምኑዲ መንገድ ተጉዘው ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ ደረሱ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ተረከዙን በአለት ላይ አደረገ በተረከዙም አምሳል በአለቱ ላይ ተቀረጸች እስከ ዛሬ ያም ቦታ የጌታችን የተረከዝ ቅርጽ ተባለ። ጌታችንም እመቤታችን ድንግል ማርያምን እናቴ ሆይ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ይሠራ ዘንድ እንዳለው ዕወቂ። በውስጡም ድንቅ ተአምራትን አደርጋለሁ ስሙም ደብረ ምጥማቅ ይባላል አላት። ከዚያም ወደ ፀሐይ መግቢያ ወዳለ ባሕር ሔዱ የአስቄጥስንም በረሀ ዱር ከሩቅ አዩ። ጌታም በላዩ ባረከ እናቱንም እናቴ ማርያም ሆይ በዚህ ዱር ውስጥ ብዙዎች ሰዎች መነኰሳትን ሁነው በገድልም ተጸምደው በመላእክት አምሳል ያገለግሉኛል። ከዚያም በፀሐይ መውጫ በኲል ወደአለ ተራራ ሔዱ ዮሴፍም የሚመረኰዘው በትር በእጁ ነበር ጌታችንም ይህ ቦታ የሚያቃጥል በረሀ ነውና እንቀመጥ አለ። ጌታችንም የዮሴፍን በትር አንሥቶ ሰበራት ጥቃቅን ስብርባሪዎች አድርጎ በዚያ ቦታ ተከላቸው። በከበሩ እጆቹ ጉድጓድ ማሰ መዓዛው የሚጣፍጥ ውኃ ፈልቆ ፈሰሰ ከእዚያ ውኃም በመሐል እጁ እየዘገነ የተከላቸውን ስብርባሪዎች አጠጣቸው። ወዲያውኑ በቀሉ አድገውም ታላላቅ ዛፎች ሆኑ ከእርሳቸውም ጣፋጭ ሽታ ሸተተ። እርሱም ከሽቱዎች ሁሉ እጅግ የሚጣፍጥ ነው በለሳንም ብሎ ጠራቸው። እናቱን ድንግል እመቤታችንንም እናቴ ሆይ ይህ የተከልኩት በለሳን እስከ ዓለም ፍጻሜ ከዚህ ይኖራል የክርስትና ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለሚጠመቁ ከእርሱ ቅባት ይገኛል አላት የዚያም ስም መጣሪያ ነው። ከዚያም ብህንሳ ወደሚባል አገር ሔዱ ትርጓሜው ቤተ ኢየሱስ የሆነ በይሱስ ወደሚባልም ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሽታውን ደዌውን ሁሉ የሚፈውስ የጒድጓድ ውኃ አደረገ። ሁለተኛም በአንዲት የጕድጓድ ውኃ ምልክትን በየዓመቱ አደረገ ይኸውም ከቀኑ እኲሌታ በማዕጠንትና በጸሎት ጊዜ ለእግዚአብሔር በዚያች የውኃ ጕድጓድ ዕጣንን ሲያሳርጉ የከበረ የወንጌል ንባብም ሲፈጸም በዚያች ጉድጓድ ውስጥ ያለ ውኃ ወደ ላይ ወጥቶ እስከ ጉድጓዱ አፍ ይደርሳል። ከእርሱም ይባረካሉ ከዚያም በኋላ እንደ ቀድሞው ወደ ቦታው ይመለሳል። ውኃው ከነበረበት እስከ ደረሰበት ይሰፍሩታል። ሃያ ክንድ የሆነ እንደሆነ የጥጋብ ዘመን ይሆናል ዐሥራ ሰባት ክንድ ከሆነ ግን በግብጽ አገር ታላቅ ረኃብ ይሆናል። ከዚያም ወደ እስሙናይን አገር ሔዱ በዚያ ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ። እነርሱም ስሙ አፍሎን ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጡ። በዚያም የእሸ እንጨት ዛፎች አሉ ለጌታችንም ሰገዱ እስከ ዛሬም እንደ ሰገዱ ናቸው። ከዚያም ወደ ደብረ ቍስቋም ሔደው በውስጧ ስድስት ወር ተቀመጡ በዚያም በሽታን ሁሉ የሚያድን የጉድጓድ ውኃ አደረገ። ጌታችንም የፈቀደውን በግብጽ የሚኖርበት ወራት በፈጸመ ጊዜ ይኸውም ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው። ኄሮድስም ከሞተ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሙተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ተመለስ አለው። ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚወጣው ነው። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከብርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው። በጌታችን መመለስም ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ያለው የኦዝያን ትንቢት ተፈጸመ። ስለዚህም ተአምራትን በግብጽ ድንቅ ሥራንም በጣኔዎስ በረሀ ያደረገ በማለት እየዘመርን በዚች ዕለት መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ስለ እኛ ለተሰደደ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ምሕረቱ ይሁን። አምላክ የወለደች የተባረከች የድንግል እመቤታችን #ማርያም በረከቷ የዮሴፍና የሰሎሜም በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ዕንባቆም_ነቢይ በዚህችም ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነቢይ ዕንባቆም አረፈ። ይህም ቅዱስ በአንዲት ዕለት እህሉን ለሚያጭዱለት ምሳቸውን አዘጋጅቶ ተሸክሞ ሲሔድ መልአክ ተገልጾለት ይህን መብል በባቢሎን አገር በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ላለ ለነቢዩ ዳንኤል ውሰድ አለው። ዕንባቆምም ጌታዬ ሆይ ባቢሎንን አላየኋት ጉድጓዱንም አላውቀው አለው። የእግዚአብሔር መልአክም በራሱ ጠጉር ያዘው ምግቡን በእጁ እንደያዘ ወሰደውና ጉድጓዱ እንደተዘጋ አስገባው ምግቡንም ሰጥቶ መገበው ወዲያውኑ ዕንባቆምን ወደ ይሁዳ አገር መለሰው። በአረጀና በሸመገለም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ከተማረኩበት ተመልሰው ቤተ መቅደስን ሠሩ። ዕንባቆምም ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በታላቅ ደስታም ተቀበሉት ትንቢቱንም ሊሰሙ ወደርሱ ተሰበሰቡ አፉንም ከፍቶ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ። አቤቱ ድምፅህን ሰማሁ ሰምቼም ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ አለ። ስለ መድኃኒታችንም መውረድና በይሁዳ ክፍል በሆነች በቤተ ልሔም ስለመወለዱ ሲናገር የተመሰገነ እግዚአብሔር ግን ከፋራን ተራራ ከቴማን ከይሁዳ አውራጃ ይመጣል ብሎ እስከ መጨረሻው ተናገረ ከነቢያት መጻሕፍትም ጋራ ደመርዋት።
Показати все...
ከዚህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች አንዲት ሴት ወደርሱ መጣች እያለቀሰችም እንዲህ አለችው። ሁለት ልጆች ነበሩኝ ጣዖት እንዲአመልኩ ፈለጉአቸው እምቢ በአሉ ጊዜም ገድለው በጐዳና ላይ ጣሉአቸው። ተገድለው ወደ አሉበትም አብሮዋት ሔደ ነፍሳቸውንም ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው ልመናውንም ተቀበሎ በሕይወት አነሣቸው። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ዘመዶቹን ጠራቸው። እንደሚሞትም ነገራቸውና አንዲት ሰዓት ያህል ወደላይ እየተመለከተ ተቀመጠ። እነሆ እንደ ሰው ክንድ ያለች ታላቅ ክንድ የቤቱን ጣሪያሠንጥቃ ወረደች ወደ አፉም ተዘርግታ ነፍሱን ወሰደች ያን ጊዜም አረፈ። በክርስቲያናዊ ንጉሥ በአንስጣስዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ ገድሉን በአነበበ ጊዜ አድንቆ በግብጽ ደቡብ ቀርጣስ በሚባል ቦታ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሠራለት እርሷም በዚች ቀን ከበረች። #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቀሲስ_ቅዱስ_አብቍልታ በዚህችም ዕለት የእንጽና አገር የከበረ ቀሲስ አብቍልታ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ባለ መድኃኒት ነው ለበሽተኞች በጎ ሥራ በመሥራት ያለ ዋጋ ያክማቸዋል ደግሞም የሚበሉትን የሚጠጡትን የሚለብሱትን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል ። በዚያም ወራት ወደ ሰዒድ አውራጃ ወደ መኰንኑ አርያኖስ ዲዮቅልጥያኖስ ላከ የዚያቺን አገር ሰዎች ለጣዖታት እንዲሰግዱ ያስገድዳቸው ዘንድ። በዚያንም ጊዜ ይህን ቅዱስ ያዙት ወደ እስሙናይንም ወስደው በመኰንኑ ፊት አቆሙት መኰንኑም ወደርሱ ይመልሰው ዘንድ በጎ ቃልን ተናገረው ሊመልሰውም ባልቻለ ጊዜ ቆዳው እስቲሠነጣጠቅ እንዲገርፉት አዘዘ ከዚህም በኋላ በሕይወት እያለ በእሳት አቃጠሉት። ገድሉንም በዚህ ፈጸመ ምእመናንም መጥተው በድኑን ወሰዱ ከከተማው ደቡባዊ በሆነ ተራራ ላይ ገንዘው በክብር ቀበሩት። #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት_24)
Показати все...
#ግንቦት_21_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ማቴዎስ 18 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር። ⁷ ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት። ⁸ እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ⁹ ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ¹⁰ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና። ¹¹ የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና። ¹² ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን? ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የ #ሚቀደሰው_ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የደብረ ምጥማቅ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Показати все...
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_21_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 1ኛ ቆሮንቶስ 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹ ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ። ¹⁰-¹¹ ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥ ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፥ እኔ ግን አላዝም፥ ጌታ እንጂ። ¹² ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤ ¹³ ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው። ¹⁴ ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። ¹⁵ የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። ¹⁶ አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ? ¹⁷ ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ። እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ። ¹⁸ ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። ¹⁹ መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ። ²⁰ እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር። ²¹ ባሪያ ሆነህ ተጠርተህ እንደ ሆነ አይገድህም፤ አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል። ²² ባሪያ ሆኖ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው። ²³ በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። ²⁴ ወንድሞች ሆይ፥ እያንዳንዱ በተጠራበት እንደዚሁ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር። ²⁵ ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥ ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ ከጌታ ምሕረትን የተቀበልሁ እንደ መሆኔ ምክር እመክራለሁ። ²⁶ እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር መልካም ነው። ²⁷ በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ። ²⁸ ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር። ²⁹ ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ ³⁰ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ ³¹ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። ³² ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ³³ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል። ³⁴ ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች። ³⁵ ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም። ³⁶ ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ። ³⁷ ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም፥ የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል፤ ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና፥ መልካም አደረገ። ³⁸ እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ። ³⁹ ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። ⁴⁰ እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ራእይ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። ² እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች። ³ ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥ ⁴ ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ። ⁵ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁴ እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤ ⁴⁵ አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። ⁴⁶ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ። ⁴⁷ ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት። ⁴⁸-⁵⁰ ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም። ⁵¹ እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_21_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ሰወረከኒ በዕለተ ቀትል መልዕልተ ርእስየ። ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን። ተማከሩ ላዕሌየ ኢትኅድገኒ ከመ ኢይዘኀሩ"። መዝ 139፥7-8 አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጕልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ። አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለኃጢአተኞች አትስጠኝ፤ በላዬ ተማከሩ፤ እንዳይጓደዱ አትተወኝ። መዝ 139፥7-8 ወይም👉ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር። ጻድቅ በምሕረት ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የኃጢአተኛ ዘይት ግን ራሴን አይቅባ፤ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና። መዝ.104÷4-5 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Показати все...
👍 1
#ግንቦት 21 "እናቴ _ማርያም _ደጓ_እናቴ" እንኳን _ለደብረ _ምጥማቅ _አመታዊ _የመገለጥ _በዓል _በሰላም _በጤና _አደረሳችሁ_አደረሰን። #OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ #ማርያም #ግንቦት21  #profile #timline #post #story On Telegram👇          • t.me/winagfx2          • t.me/winaGraphics Share 🙏 https://t.me/winaGraphics
Показати все...
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቅዱሳን አባቶቻችን ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን። ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፏል። ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው።
አረጋዊ ታዴዎስ
በተመሳሳይ ኃጢአት በተደጋጋሚ ብትወድቁም በወደቃችሁበት ቦታ ሳትቆዩ ወደ እግዚአብሔር ሩጡ፡፡ አብዛኛዎቹ የቀደሙት ኃጢአቶች በእኛ ላይ የሚበረቱት ልምድ ሆነውብን ስለኖሩ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉት ኃጢአቶችም ከጊዜና ከፅኑ ፍላጎት ጋር ብቻ ነው ድል የሚነሱት። 
ቅዱስ ኔክታሪዮስ
@Orthodox_tewahdo_1
Показати все...