cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። " https://t.me/MoaeTewahedoB አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014

Більше
Рекламні дописи
10 914
Підписники
-1124 години
-107 днів
+3530 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
430Loading...
02
የይቅርታ ሂደቶች የሚከተሉት ናቸው።   *በደለኛው በበደሉ መጸጸት አለበት።   *የተበደለ ካሣ ያስፈልገዋል።   *የበደለ ቅጣት ይገባዋል።   *ለቀጣዩ ሕይወት አስተማማኝ ኪዳን ይደረጋል። ቤተክርስቲያን ስለ ይቅርታ ብቻ ሳይሆን ስለፍትሕም ታስተምራለች። ለብዙ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ተጠያቂ የሆኑ አካላት እንዲሁ ይቅርታ ተደርጎላቸው ይኑሩ አይባልም። ፍትሕስ?? ላጠፉት ጥፋት ቅጣት ይገባቸዋል። እነዚህ ሂደቶች የሌሉበት ይቅርታ ግን የወንበዴ ዋሻ፣ የሌባ መነኻርያ፣ የወንጀለኞች መደበቂያ ይሆናል። አዳም ይቅርታ ሲደረግለት እነዚህን ነገሮች አልፎ ነው። መጀመሪያ አዳም በበደሉ ተጸጽቷል። ከዚያ ለበደሉ ቅጣትን ተቀብሏል። ወደ 5000 ለሚጠጉ ዓመታት በሲኦል ኖሯል። በምድርም በታላቅ መከራ ኖሯል። አዳም ለሠራት አንዲት በደል ይህ ሁሉ ቅጣት ተላልፎበት ኖሯል። በኋላ ክርስቶስ ስለ አዳም ቤዛ ሆኖ አድኖታል። ለቀጣዩም አስተማማኝ ኪዳን ተሰጥቶታል። ኪዳኑን የጠበቀ ይድናል። ኪዳኑን ያልጠበቀ አይድንም። ይቅርታን በተሳሳተ መልኩ ባንረዳው መልካም ነው። አንድ ሰው በጣም ክፉ ቢሆንና ብዙ ኃይል ቢኖረው ብዙ ጥፋትን ከሚያጠፋ ያለፈውን ኃጢአቱን እንተውለትና በአብሮነት እንኑር አይባልም። ያጠፋውን ያህል ጥፋት ቢያጠፋ እስከመጨረሻው ድረስ ለፍትሕ እንዲቀርብ ማድረግ ይገባል እንጂ። ፍትሕ ተዛብታ ሚልዮን ሰዎች ከሚኖሩባት ምድር ይልቅ ፍትሕ ጸንታ 10 ሰዎች ብቻ ቢኖሩ የተሻለ ነው። ሀገሪቱ ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ያደረጉ ሰዎችን ምንም ያህል መሥዋዕትነትን ቢጠይቅ ለፍትሕ ማቅረብ ነው። ሰው ፍርሃትን ማሸነፍ አለበት። ለትክክለኛ ነገር እስከሞት ድረስ መታመን አለበት። ሞት ላይቀር መፍራት አይገባም። ፈሪ ሰው አስጠቂ ነው። ፈሪ በዋናነት የሚጎዳው ራሱን ነው። ጀግንነት ድፍረት ይኑረን። ከድፍረት ጋር ጥበብም ሊኖረን ይገባል። በመምህር በትረማርያም አበባው @MoaeTewahedoB
2363Loading...
03
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
1811Loading...
04
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል: “እርሱም፦ ‘መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ’ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።” [ዮሐንስ 21: 6] ጌታችን ጀሞት ከተነሳ በኋላ ደጋግሞ ተገለጠ.. አሁን የተገለጠው በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ነው.. እና እነዚህ አሥ አጥማጅ ሐዋርያትም በዛን ለሊት ብዙ ቢታገሉም ምንም ሊያጠምዱ አልቻሉም ነበር.. እና ጌታችን መጥቶ “መረቡን በስተቀኝ ጣሉት” አላቸው.. እነሱም እንዲሁ አደረጉና ለማውጣት እስኪከብዳቸው መረቡ በዓሣ ተመላ.. ዮሐንስም ይሄኔ “ጌታ እኮ ነው” አለ.. ጴጥሮስም ራሱን ወዳ ባህር ጥሎ ወደ ጌታ ሮጠ.. ድኀነትን የተጠሙ በዓለም ያሉትን ዓሣዎች ወደ መረብ(ቤተ ክርስቲያን) ለማጥመድ የአገልጋይ ድካም ብቻውን ዋጋ የለውም.. የጌታ ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል.. (አኪ) @MoaeTewahedoB
2342Loading...
05
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል። እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ነበረች ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣለች። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች። በውጭም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወገኖቼ  ያለኝን ጨርሻለሁ አሁን ላይ ያለኝን ቀሪ ነገር ኩላሊቴን ልስጠው ነውና ገንዘብ ያለው በገንዘቡ የሌለው በሃሳብና በጸሎት አግዙኝ ወንድሜን አድኑልኝ ስለፈጣሪ ተባበሩኝ የሰው ህይወት በማዳናችሁ በፈጣሪ ታገኙታላችሁ።                    ፍሩታ አሻግሬ              የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ               1000629004045 ለበለጠ መረጃ ➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929 ➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
1030Loading...
06
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
531Loading...
07
“እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” (ዮሐ. 6፥63) *** የክርስትና አስተምህሮ አመክንዮአዊ ቀመር እና የቃላት ብያኔ ብቻ አይደለም። ጌታችን እንደነገረን ከዚያ የሚያልፍ መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው። በመሆኑም አንድ ንባብ በቅዱሳት መጻሕፍት ቢገኝም 'መንፈሱን' ካልተረዳን እንስታለን። ያ አገላለጽ የተነገረው ምንን ለማጠየቅ ነው? ምን ብለን ብንረዳው ደግሞ ስህተት ይሆናል? ብሎ ትውፊታዊ መረዳትን ይጠይቃል። አንዳንዶቹ አገላለጾች ደግሞ እጅግ ትልቅ ቅጥነተ ህሊና ይጠይቃሉ። ከእነዚህ አንዱ 'ፈጣሪ ወፍጡር' የሚለው ትምህርት ነው። ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮች እንኳ ክርስቶስን 'በሥጋው ፍጡር' ማለት በትክክለኛ ዓውዱ ከተነገረ ስህተት ባይሆንም ምእመናን እንዳይደናገሩ በነገረ ሃይማኖት ሐተታዎች ውስጥ በብዛት አንጠቀመውም ይላሉ። (Catholic Encyclopedia) ይህ ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ውስጥም ያለ ነው። እኔ እስከማውቀው በአምልኮ መጽሐፎቻችን ውስጥ አይነገርም። እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኘው በአንዳንድ ሊቃውንት ድርሳናት ውስጥ ነው። ይህ የሚያመለክተው አገላለጹ በቅጥነተ ህሊና ከነሙሉ ዓውዱ ካልተረዱት ምእመናን 'በሥጋው ፍጡር ስለሆነ በሥጋው አናመልከውም' ብለው እንዳይሰናከሉ ነው። 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ሲባል፦ 1. የለበሰው ሥጋ ዘላለማዊ ህልውና ያልነበረው የእኛ የተፈጠረ እውነተኛ ሥጋ ነው ለማለት ነው። 2. የሰው ልጆች ሐዲስ ተፈጥሮ (መታደስ) ከእርሱ የተጀመረበት ዳግማይ አዳም፣ በኲረ ፍጥረታት መሆኑን ለመናገር ነው። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ያልነሳውን አላዳነምና። 3. ሌሎችም። *** ነገር ግን ከነዚህ እሳቤዎች መጠንቀቅ ደግሞ ይገባል፦ 1. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው አምልኮ አይገባውም ማለት አይደለም። የክርስቶስን ሥጋ ከመለኮቱ ለይተን በመለኮቱ ብቻ እናምልክ ካልን የማይከፈለውን አንዱን ክርስቶስን እየከፈልነው ነው፤ ስለ መዳናችን ሰው የሆነውን ክርስቶስን ስለእኛ ሰው በመሆኑ ዝቅ እያደረግነው ነው። ስለ ሕዝቡ ሲል ከአባቱ ዙፋን ወርዶ ሕዝቡ የሚለብሱትን መናኛ ልብስ ለብሶ የሚታደገውን የንጉሥ ልጅ ውለታ ባለመረዳት 'በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሥ አናይህም' ብሎ እንደመሳለቅ ነው። 2. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ማኅየዊ (ሕይወትን የሚሰጥ) አይደለም ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ቅዱስ ቄርሎስ እንዳለው ሥጋውን እና ደሙን መቀበል ከንቱ በሆነ! 3. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ለአብ ይገዛል ማለት አይደለም። አብ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስምን ሰጠው የተባለ በሥጋው ነው። ታዲያ ይህ ከፍታ ከመገዛት የማያወጣ ከሆነ ከቅዱሳን የጸጋ ክብር በምን በለጠ? ቅዱስ አትናቴዎስ እንዳለው ከፍጡራን ግብርናት እስካልወጣ ድረስ ምን ቢከብር ለእርሱ የሚገባ ክብር አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ የተነገሩ የትሕትና ንግግሮች ከማዳን ግብሩ እና አርአያነቱ (economy of salvation) አንጻር የምንረዳቸው ናቸው። ካልሆነ ግን በክርስቶስ ዘንድ ሰው ከመሆኑ የተነሣ ዘላለማዊ ተዋርዶ ገብቷል ያስብላል። በሥላሴ አካላት ዘንድ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈስ ዘላለማዊ ክብርና ምሥጋና አለ። ነገር ግን ሰው ከመሆኑ የተነሣ በወልድ ዘንድ የፍጡር አምልኮ ግዴታ አልወደቀበትም። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ይህን አብም አይፈልግም፤ ወልድም አይሰጥም። Bereket Azmeraw @MoaeTewahedoB
2882Loading...
08
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
3580Loading...
09
ጥበበኛው ሰሎሞን "የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደኾነ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት "(ምሳ ፲፩፥፳፪) እንዳለ በዚህ ዓለም ምንም ዓይነት እንኳ ጌጥ ቢኖራት የውስጥ አስተሳሰቧ ከጎደለ ግን ከእርያ አፍንጫ ላይ የወርቅ ቀለበት አድርጎ ታምርያለሽ እንደ ማለት እንደኾነ ተናግሯል ። እርያ ምንም ቢነጻ ታጥቦ በጭቃ መንከባለል እንደ ኾነ እንዲህ ዓይነት ሰውም ምንም ቢያውቅ ዕውቀቱ ዓለማዊ እስከኾነ ድረስ የእርያ ኑሮ ነው ። ይህ ቃል ለሴት ብቻ ሳይሆን ለወንድም ቢኾን ያው ነው ። ዋናው ሚሥጢሩ ግን ምንም አዋቂ ነኝ ፣ ኹሉንም እመረምራለሁ ፣ እፈላሰፍለሁ ፣ አጽፍለሁ ፣ እናገራለሁ ብትልም እንኳ የፈላስፎች ነፍስ ከስብእና ከሚያወጣውና ከሚጎዳው ፍልስፍና ካልተለየች ራሷን በሚያስጨንቅ ፣ ፈጣሪ የለም በሚል ከንቱ ከኖረች በእርያ አፍንጫ የወርቅ ቀለበት አንደኾነ ፤ ጥበብ የሌላት ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት የተባለች ይቺ ናት ። ሴት ብሎ የጠራት ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች በብዙ መጻሕፍት በሴት አንቀጽ ስለምትጠራ ነው ። ከንቱ እሳቤም ማለት የሚያሳዩትን ኹሉ አንደማያዩ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ፍልስፍና መኖር ነው ። ("ሚሥጢረ ሚሥጢራት" መምህር ገብረ መድኅን እንየው እና መምህር መዝገበ ቃል ገብረ ሕይወት ገጽ-36) @MoaeTewahedoB
3593Loading...
10
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
1241Loading...
11
+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? + ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት:: "ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39 ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ:: "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ:: ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20) እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም? ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3 ረቢ ወዴት ትኖራለህ?  "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥  በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ  "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር:: የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23) ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን?  ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን? ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ:: "ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም:: ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦  ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13) ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ:: ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ::  አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር:: የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 21 2016 ዓ.ም. @MoaeTewahedoB
3092Loading...
12
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
2572Loading...
13
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ … በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት መጽሐፍ #ይቀላቀሉ @MoaeTewahedoB
3295Loading...
14
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
10Loading...
15
ተወዳጆች ሆይ አንድ የልብ ምክር አለኝና አድምጡኝ፦ ወዳጄ የቤተሰብ ሓላፊ ከሆንህ፡- እኔ ለቤተሰቤ እንደ ኢዮብ ካህን ነኝ ስለዚህ በመንፈስ ሁል ጊዜ፤ በአካል ደግሞ እንደ ችሎታዬ መጠን ስለራሴ ምክንያቱም በመልካም ማስተዋል ቤተሰቤን እመራ ዘንድ ስለቤተሰቤ ምክንያቱም ቤተሰቤ በኃጢአት ምክንያት አእምሮው እንዳይቆሽሽ በራስ መተማመን እንዳያጣ በማስተዋልና እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲመላለሱ ስለሀገሬ ሰዎች ደግሞ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ማስተዋልንና እርስ በእርስ መግባባትን እንዲሰጣቸው ፍቅር እንድትነግሥ ስለዓለሙ ሁሉ ደግሞ “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” እንድንል ጌታ እንዳስተማረን የምንኖርባት ዓለም ፈቃዱን ለማድረግ እንደሚተጉ መላእክት ለመልካም ሥራ እንዲበረቱ በጸሎት መትጋት አለብኝ ብለህ ለልብህ ንገረው፡፡ ለቤተሰባቸው እማወራ ለሆኑ እናቶችና ሚስቶች ደግሞ ለልባቸው እንዲህ ብለው ይንገሩ፡- እኔ ለቤተሰቤ አካሉ ነኝ፡፡ በእርግጥም ባለቤቴ ራሴ ነው እኔም አካሉ ነኝ ልጆቼም ከእኔ የወጡ የአካሌ ክፋዮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሳራን “ካንቺ ሕዝብና አሕዛብ ይወጣሉ” እንደተባለች ከእኔ ማኅበረሱ ተገኝቶአል ይገኛልም፡፡ እኔ ለማኅበረሰቡ ፣ እንደ ሀገር ለሚቆጠረው ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ እንደ መሠረት ነኝ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ቡሆው ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ይሆናል” እንዲል የእኔ ቅድስና ለእነርሱ ቅድስና መሠረት ነው፡፡ ይህን ሁሌም ላስበው ይገባል ትበል፡፡ ሁሌም ይህን አስቤ እንደ ተምሳሌቴ እንደ ቤተ ክርስቲያን ማስተዋልን ያድለኝ ዘንድ ስለሀገሬ ስለ ዓለሙ ሁሉ ሰላም በመንፈስ ሁልጊዜ ፤ በአካል እንደ ችሎታዬ መጠን በጸሎትና ራሴን በማስተዋል ለማነጽ ልተጋ ይገባኛል ትበል፡፡ ልጅም እንደ ክርስቶስ በመንፈስም በአካልም በጥበብም በእግዚአብሔርም በሰው ፊት ሊያድግ እንዲገባው ዘወትር ያስብ የእርሱ ወጣትነት ዘመን ክርስቶስ ዓለምን ለማስተማር በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተመላለሰበት ዘመን እንደሆነ ያስብ፡፡ ስለዚህም ሰውነቱን በኃጢአት ሳይተደደፍ ወጣትነቱን በንጽሕና ይጠብቃት ዘንድ ክርስቶስን ማወቅ ከቅዱሳን ጋር ማኅበርተኛ መሆንን ሊለማመድ እንደሚገባው ቆጥሮ በጸሎትም በምንባብም በተመስጦም ሊተጋ እንዲገባው ለልቡ ይንገረው፡፡ ሁሉ ነገር ከራስ ሲጀመር እጅግ መልካም ነው፡፡ የቅድስና መንገዱም ይህ ነው፡፡ ጌታስ ቢሆን ያስተማረው ይሄንኑ አይደለምን? አንተ ግብዝ አስቀድመህ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ በኋላ የወንድምህን ጉድፍ ማየት ይቻልሃል” ብሎ አላስተማረንምን? ወገኖቼ በጸሎት አንዳችንለአንዳችን እንትጋ፡፡ (ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ) @MoaeTewahedoB
3733Loading...
16
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
5021Loading...
17
#ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን? ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ @MoaeTewahedoB
1802Loading...
18
🕰🔔 11:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
4491Loading...
19
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ግንቦት 22 እና 23 ከ72ቱ አርድእት ውስጥ አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ ዐረፈ፡፡ ዳግመኛም በማግሥቱ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስን ገንዞ የቀበረውና ወዳጁ የሆነ ሌላኛው ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስ ዐረፈ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ፡- ይኽንንቅ ቅዱስ በመጀመሪያ የክብር ባለቤት ጌታችን መረጠው፡፡ እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታችን ከመከራው በፊት ከላካቸው ከ72ቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው፡፡ በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከከበሩ ሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ የከበረች ወንጌልን በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ፡፡ ብዙዎችንም አስተምሮ በማሳመን አጠመቃቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ በኒውብያ አገር ላይ ሐዋርያት በአብሮተ እድ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት፡፡ በውስጧም የከበረች ወንጌልን በሰበከ ጊዜ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙ አረማውያንን የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደጌታችን ሃይማኖት አስገባቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ ሐዋርያውን ዮልዮስን ወሰደውና አብረው በአንድነት በብዙ አገሮች ዞረው በማስተማር አልጫውን ዓለም በወንጌል ጨውነት አጣፈጡት፡፡ ብዙዎችንም በእጆቻቸው አጠመቁ፡፡ ተአምራትንም በማድረግ ከብዙ ሰዎች ላይ አጋንንትን አስወጡ፡፡ በርካታ ድውያንንም ፈወሱ፡፡ ሙታንንም አስነሡ፡፡ የጣዖታት ቤቶችን አፍርሰው በምትካቸው በጌታችን ስም አብያተ ክርስቲያናትን አነጹ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስና ወዳጁ የሆነ ሐዋርያው ዮልዮስም አገልግሎታቸውን በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ፡፡ ወዲያውም ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ ታመመና በዚኽች ዕለት ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ፡፡ ቅዱስ ዮልዮስም በክብር ገንዞ ከቀበረው በኋላ ከእርሱ እንዳይለይ ጌታችንን ለምኖት ዮልዮስም በቀጣዩ ቀን ዐረፈ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስን ገንዞ የቀበረው ሌላኛው ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስ ግንቦት 23 ቀን ዐረፈ፡፡ ይኽም ቅዱስ ትውልዱ ከይሁዳ ነገድ ከእስራኤል ልጆች ወገን ነው፡፡ ጌታችን ከረጣቸው ከ72ቱ አርድእት ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመርጦ ከሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበለ በኋላ የከበረች ወንጌልን ዞሮ ሰብኳል፡፡ በዚህም ታላቅ መከራ ተቀብሏል፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾመውት ከቅዱስ እንድራኒቆስ ጋር በተለያዩ አገሮች ውስጥ የከበረች ወንጌልን እንዲሰብክ ላኩት፡፡ ቅዱስ እንድራኒቆስም ከአንድ ቀን በፊት በሞት ባረፈ ጊዜ ይህ ቅዱስ ዮልዮስ ገንዞ በክብር ቀበረው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮልዮስ ከጓደኛው ከቅዱስ እንድራኒቆስ እንዳይለይ ጌታችንን በጸሎት ቢጠይቀው ጌታችንም ፈቃዱን ፈጸመለትና በማግሥቱ ዐረፈ፡፡ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም እነዚኽን የከበሩ ሐዋርያት በሮሜ ክታቡ ‹‹እንድራኒቆስንና ዮልዮስን ሰላም በሏቸው›› ሲል አስታውሷቸዋል፡፡ የእነዚኽ የከበሩ ሐዋርያት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ + ዳግመኛም በዚኽች ዕለት (ግንቦት 23) ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነው አፍሮዲጡ፣ ዮልያኖስና እናቱ እስክንድርያ፣ ቅዱስ ኤስድሮስና ሚስቱ ሰማዕት ከሆነው ከ2 ወር ልጃቸው ጋር በዓመታዊ በዓላቸው ታስበው እንደሚውሉ ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ https://t.me/MoaeTewahedoB
5401Loading...
20
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
5881Loading...
21
✝ቅንነት|| ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ውጡ✝ Size:-29.9MB Length:-1:25:53     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
6252Loading...
22
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
6030Loading...
23
#በእምነት መዳን በእምነት መዳን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ሲሆን "በእምነት ብቻ" መዳን የሚለው ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም ። ይህ የፕሮቴስታንቶችና የልጆቻቸው የተሐድሶዎች የፈጠራ ትምህርት ነው ። መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ስለመዳን እንጂ በእምነት ብቻ ሰለመዳን አንድም ቦታ አይናገረም ። "ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና" በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ "በእምነት ብቻ እንዲጸድቅ" በማለት "ብቻ" የሚለውን አፍራሽ ቃል በራሱ ደፍርነት የጨመረው በ16ኛው መቶ ዓመት የተነሣው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር ነው ። ሮሜ 3፥28 "በእምነት መዳን" በሚለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ "ብቻ" የሚል ቃል በድፍረት የጨመረው በሰው መዳን ውስጥ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ፣ የመጽናትንና የተጋድሎን አስፈላጊነት ሁሉ ከንቱ ለማድረግና እንዲሁ "ድኛለሁ" እያሉ በመፎከር  እንዳሻቸው ኃጢአትን ለመሥራት ለራሳቸው ይለፍ ለመስጠት የፈጠሩት ሰፊ መንገድ ነው ። ቅዱስ መጽሐፍ መሠረታዊ ነገር ስለ ሆነው በእምነት ስለ መዳን ጉዳይ ደጋግሞ ይናገራል ። ለአብነትም "እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደውም የሆነ ማስተሰሪያ አድርገን አቆመው" ይላል። ሮሜ 3፡25 እንዲሁ "እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርሰቶስ ሰላምን እንያዝ " ፤ " በእርሱም ደግሞ ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል ። ፤ "ይህስ ስለ ምንድር ነው ?በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው " ይላል ። ሮሜ 5፥1፣ 5፥2 ፣ 9"፥30 ( መድሎተ ጽድቅ ቅ.፩ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ገጽ-188 ) https://t.me/MoaeTewahedoB
7938Loading...
24
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
8180Loading...
25
"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡"                 ቅዱስ ፓትርያርኩ        በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ            ምልዓተ ጉባኤ የተናገሩት              ግንቦት 21/2016 ዓም
9800Loading...
26
🕰🔔 11:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
9070Loading...
27
🥰
9642Loading...
28
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
1 2133Loading...
29
ይሁንና ሰው እናትና አባቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር አንድ የሚሆነው ለምንድ ነው ? በክርስቶስ በኩል ከጌታ የተቀበላት ቅዱስ አካሉ ሆና ለእርሱ እንደ ቤተክርስቲያን ስለሆነችለት ነው ። "እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናቹሁ ። 1ኛ ቆሮ 12፥27 ( "የክርስቶስ ስሞች" ዲ/ን በረከት አዝመራው ) https://t.me/MoaeTewahedoB
9887Loading...
30
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
9720Loading...
31
አንድ አረጋዊ እንዲህ አሉ ፦”ልጆቼ ሆይ፦ ራሳችሁን መለወጥ ሳትችሉ የሌላን ሰው ነፍስ ማዳን ወይንም ሰወችን መርዳት አትችሉም፤ ነፍሳችሁ በልዩ ልዩ ምስቅልቅል ውስጥ ሆናም የሌላውን ሰው መንፈሳዊነት ስርአት ማስያዝ አይቻላችሁም፤ እናንተ ራሳችሁ የውስጥ ሰላም ከሌላችሁ ለሌሎች ሰላምን ማስገኘት አትችሉም ፤ ብዙውን ጊዜ የሰወችን በኛ ምክንያት ለበጎ ነገር መነሳሳትና ነፍሳቸውም ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምናየው ወደ በጎ ይቀርቡ ዘንድ በአፍ በምንነግራቸው ነገር ሳይሆን በእኛ ላይ በተግባር በሚገለጥ የመንፈስ ፀጋና ስጦታ ነው፡፡ ሌሎች ሰወችም ህይወታቸው ለበጎ ነገር እንዲነሳሳና እንዲለወጥ በእኛ ህይወት ሲማሩ እኛ እንኳን ላናየውና ላንረዳው እንችላለን፡፡" @MoaeTewahedoB
95910Loading...
32
“#በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ"መዝ.፻፪፥፳፬ #ሊቀ ዲያቆናት ዘማሪ ይገረም ፀጋዬ  ደግ ትሁት ሽቁጥቁጥ ሰው አክባሪ  ምን አጋጠመህ ወንድም? በቅዱሳኑ ጎን ያሳርፍህ። 😭 “#በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።” መዝሙር 102፥24
1 0511Loading...
33
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
1 0090Loading...
34
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡  ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ  በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል፤ በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው፤ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ ‹‹እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት… የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል፤ በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፤ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል፤  ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡ ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት! የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው፤ በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡ በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው፤ ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል፤ ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በመጨረሻም ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡ መልካም ጉባኤ ያደርግልን! እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፩ ቀን !፻0፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ @MoaeTewahedoB
1 0775Loading...
35
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! - ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!     እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን! ‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤  ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡ https://t.me/MoaeTewahedoB
1 0154Loading...
36
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
1 2081Loading...
37
ጌታችን በተገረፈበት ልክ በ6666 ድንጋይና በእመቤታችን የዕድሜ መጠን 64 መስኮት እንዲኖረው አድርገው ዐፄ ኀይለ ሥላሴ በ1951 ዓ.ም ያሠሩት የእመቤታችን ቤተ መቅደስ!!! በ2010 ግንቦት 21 ቀን በዓመታዊ ክብረ በዓል ወቅት አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን በዚህ ገዳም ውስጥ ለ45 ደቂቃ ያህል ተገልጣ መታየቷን በገዳሙ ያሉና መገለጧን ያዩ አባቶች ነግረውናል፡፡ ይኽም እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ክርስቲያኑም እስላሙም በግልጽ እያዩአት ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 24 ትገለጥ በነበረበት ሁኔታ ነው፡፡ (በወቅቱ የተቀረጸውን ምሥል-"ቪዲዮ" ከላይ ይመልከቱ።) አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ይኽን የከበረ ገዳሟን ለመሳለምና በረከቷን ለመቀበል ታብቃን!!!
1 12315Loading...
38
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
1 1291Loading...
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 3
የይቅርታ ሂደቶች የሚከተሉት ናቸው።   *በደለኛው በበደሉ መጸጸት አለበት።   *የተበደለ ካሣ ያስፈልገዋል።   *የበደለ ቅጣት ይገባዋል።   *ለቀጣዩ ሕይወት አስተማማኝ ኪዳን ይደረጋል። ቤተክርስቲያን ስለ ይቅርታ ብቻ ሳይሆን ስለፍትሕም ታስተምራለች። ለብዙ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ተጠያቂ የሆኑ አካላት እንዲሁ ይቅርታ ተደርጎላቸው ይኑሩ አይባልም። ፍትሕስ?? ላጠፉት ጥፋት ቅጣት ይገባቸዋል። እነዚህ ሂደቶች የሌሉበት ይቅርታ ግን የወንበዴ ዋሻ፣ የሌባ መነኻርያ፣ የወንጀለኞች መደበቂያ ይሆናል። አዳም ይቅርታ ሲደረግለት እነዚህን ነገሮች አልፎ ነው። መጀመሪያ አዳም በበደሉ ተጸጽቷል። ከዚያ ለበደሉ ቅጣትን ተቀብሏል። ወደ 5000 ለሚጠጉ ዓመታት በሲኦል ኖሯል። በምድርም በታላቅ መከራ ኖሯል። አዳም ለሠራት አንዲት በደል ይህ ሁሉ ቅጣት ተላልፎበት ኖሯል። በኋላ ክርስቶስ ስለ አዳም ቤዛ ሆኖ አድኖታል። ለቀጣዩም አስተማማኝ ኪዳን ተሰጥቶታል። ኪዳኑን የጠበቀ ይድናል። ኪዳኑን ያልጠበቀ አይድንም። ይቅርታን በተሳሳተ መልኩ ባንረዳው መልካም ነው። አንድ ሰው በጣም ክፉ ቢሆንና ብዙ ኃይል ቢኖረው ብዙ ጥፋትን ከሚያጠፋ ያለፈውን ኃጢአቱን እንተውለትና በአብሮነት እንኑር አይባልም። ያጠፋውን ያህል ጥፋት ቢያጠፋ እስከመጨረሻው ድረስ ለፍትሕ እንዲቀርብ ማድረግ ይገባል እንጂ። ፍትሕ ተዛብታ ሚልዮን ሰዎች ከሚኖሩባት ምድር ይልቅ ፍትሕ ጸንታ 10 ሰዎች ብቻ ቢኖሩ የተሻለ ነው። ሀገሪቱ ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ያደረጉ ሰዎችን ምንም ያህል መሥዋዕትነትን ቢጠይቅ ለፍትሕ ማቅረብ ነው። ሰው ፍርሃትን ማሸነፍ አለበት። ለትክክለኛ ነገር እስከሞት ድረስ መታመን አለበት። ሞት ላይቀር መፍራት አይገባም። ፈሪ ሰው አስጠቂ ነው። ፈሪ በዋናነት የሚጎዳው ራሱን ነው። ጀግንነት ድፍረት ይኑረን። ከድፍረት ጋር ጥበብም ሊኖረን ይገባል። በመምህር በትረማርያም አበባው @MoaeTewahedoB
Показати все...
👍 2🥰 2
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
2👍 1🥰 1
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል: “እርሱም፦ ‘መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ’ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።” [ዮሐንስ 21: 6] ጌታችን ጀሞት ከተነሳ በኋላ ደጋግሞ ተገለጠ.. አሁን የተገለጠው በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ነው.. እና እነዚህ አሥ አጥማጅ ሐዋርያትም በዛን ለሊት ብዙ ቢታገሉም ምንም ሊያጠምዱ አልቻሉም ነበር.. እና ጌታችን መጥቶ “መረቡን በስተቀኝ ጣሉት” አላቸው.. እነሱም እንዲሁ አደረጉና ለማውጣት እስኪከብዳቸው መረቡ በዓሣ ተመላ.. ዮሐንስም ይሄኔ “ጌታ እኮ ነው” አለ.. ጴጥሮስም ራሱን ወዳ ባህር ጥሎ ወደ ጌታ ሮጠ.. ድኀነትን የተጠሙ በዓለም ያሉትን ዓሣዎች ወደ መረብ(ቤተ ክርስቲያን) ለማጥመድ የአገልጋይ ድካም ብቻውን ዋጋ የለውም.. የጌታ ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል.. (አኪ) @MoaeTewahedoB
Показати все...
8👍 4🥰 1
09:23
Відео недоступнеДивитись в Telegram
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል። እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ነበረች ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣለች። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች። በውጭም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወገኖቼ  ያለኝን ጨርሻለሁ አሁን ላይ ያለኝን ቀሪ ነገር ኩላሊቴን ልስጠው ነውና ገንዘብ ያለው በገንዘቡ የሌለው በሃሳብና በጸሎት አግዙኝ ወንድሜን አድኑልኝ ስለፈጣሪ ተባበሩኝ የሰው ህይወት በማዳናችሁ በፈጣሪ ታገኙታላችሁ።                    ፍሩታ አሻግሬ              የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ               1000629004045 ለበለጠ መረጃ ➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929 ➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
Показати все...
😢 3
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 1
“እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” (ዮሐ. 6፥63) *** የክርስትና አስተምህሮ አመክንዮአዊ ቀመር እና የቃላት ብያኔ ብቻ አይደለም። ጌታችን እንደነገረን ከዚያ የሚያልፍ መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው። በመሆኑም አንድ ንባብ በቅዱሳት መጻሕፍት ቢገኝም 'መንፈሱን' ካልተረዳን እንስታለን። ያ አገላለጽ የተነገረው ምንን ለማጠየቅ ነው? ምን ብለን ብንረዳው ደግሞ ስህተት ይሆናል? ብሎ ትውፊታዊ መረዳትን ይጠይቃል። አንዳንዶቹ አገላለጾች ደግሞ እጅግ ትልቅ ቅጥነተ ህሊና ይጠይቃሉ። ከእነዚህ አንዱ 'ፈጣሪ ወፍጡር' የሚለው ትምህርት ነው። ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮች እንኳ ክርስቶስን 'በሥጋው ፍጡር' ማለት በትክክለኛ ዓውዱ ከተነገረ ስህተት ባይሆንም ምእመናን እንዳይደናገሩ በነገረ ሃይማኖት ሐተታዎች ውስጥ በብዛት አንጠቀመውም ይላሉ። (Catholic Encyclopedia) ይህ ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ውስጥም ያለ ነው። እኔ እስከማውቀው በአምልኮ መጽሐፎቻችን ውስጥ አይነገርም። እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኘው በአንዳንድ ሊቃውንት ድርሳናት ውስጥ ነው። ይህ የሚያመለክተው አገላለጹ በቅጥነተ ህሊና ከነሙሉ ዓውዱ ካልተረዱት ምእመናን 'በሥጋው ፍጡር ስለሆነ በሥጋው አናመልከውም' ብለው እንዳይሰናከሉ ነው። 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ሲባል፦ 1. የለበሰው ሥጋ ዘላለማዊ ህልውና ያልነበረው የእኛ የተፈጠረ እውነተኛ ሥጋ ነው ለማለት ነው። 2. የሰው ልጆች ሐዲስ ተፈጥሮ (መታደስ) ከእርሱ የተጀመረበት ዳግማይ አዳም፣ በኲረ ፍጥረታት መሆኑን ለመናገር ነው። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ያልነሳውን አላዳነምና። 3. ሌሎችም። *** ነገር ግን ከነዚህ እሳቤዎች መጠንቀቅ ደግሞ ይገባል፦ 1. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው አምልኮ አይገባውም ማለት አይደለም። የክርስቶስን ሥጋ ከመለኮቱ ለይተን በመለኮቱ ብቻ እናምልክ ካልን የማይከፈለውን አንዱን ክርስቶስን እየከፈልነው ነው፤ ስለ መዳናችን ሰው የሆነውን ክርስቶስን ስለእኛ ሰው በመሆኑ ዝቅ እያደረግነው ነው። ስለ ሕዝቡ ሲል ከአባቱ ዙፋን ወርዶ ሕዝቡ የሚለብሱትን መናኛ ልብስ ለብሶ የሚታደገውን የንጉሥ ልጅ ውለታ ባለመረዳት 'በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሥ አናይህም' ብሎ እንደመሳለቅ ነው። 2. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ማኅየዊ (ሕይወትን የሚሰጥ) አይደለም ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ቅዱስ ቄርሎስ እንዳለው ሥጋውን እና ደሙን መቀበል ከንቱ በሆነ! 3. 'ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው' ማለት በሥጋው ለአብ ይገዛል ማለት አይደለም። አብ ከፍ ከፍ አደረገው፣ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስምን ሰጠው የተባለ በሥጋው ነው። ታዲያ ይህ ከፍታ ከመገዛት የማያወጣ ከሆነ ከቅዱሳን የጸጋ ክብር በምን በለጠ? ቅዱስ አትናቴዎስ እንዳለው ከፍጡራን ግብርናት እስካልወጣ ድረስ ምን ቢከብር ለእርሱ የሚገባ ክብር አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ የተነገሩ የትሕትና ንግግሮች ከማዳን ግብሩ እና አርአያነቱ (economy of salvation) አንጻር የምንረዳቸው ናቸው። ካልሆነ ግን በክርስቶስ ዘንድ ሰው ከመሆኑ የተነሣ ዘላለማዊ ተዋርዶ ገብቷል ያስብላል። በሥላሴ አካላት ዘንድ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈስ ዘላለማዊ ክብርና ምሥጋና አለ። ነገር ግን ሰው ከመሆኑ የተነሣ በወልድ ዘንድ የፍጡር አምልኮ ግዴታ አልወደቀበትም። ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ እንዳለው ይህን አብም አይፈልግም፤ ወልድም አይሰጥም። Bereket Azmeraw @MoaeTewahedoB
Показати все...
👍 4 4🥰 2
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 5👍 2 1
ጥበበኛው ሰሎሞን "የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደኾነ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት "(ምሳ ፲፩፥፳፪) እንዳለ በዚህ ዓለም ምንም ዓይነት እንኳ ጌጥ ቢኖራት የውስጥ አስተሳሰቧ ከጎደለ ግን ከእርያ አፍንጫ ላይ የወርቅ ቀለበት አድርጎ ታምርያለሽ እንደ ማለት እንደኾነ ተናግሯል ። እርያ ምንም ቢነጻ ታጥቦ በጭቃ መንከባለል እንደ ኾነ እንዲህ ዓይነት ሰውም ምንም ቢያውቅ ዕውቀቱ ዓለማዊ እስከኾነ ድረስ የእርያ ኑሮ ነው ። ይህ ቃል ለሴት ብቻ ሳይሆን ለወንድም ቢኾን ያው ነው ። ዋናው ሚሥጢሩ ግን ምንም አዋቂ ነኝ ፣ ኹሉንም እመረምራለሁ ፣ እፈላሰፍለሁ ፣ አጽፍለሁ ፣ እናገራለሁ ብትልም እንኳ የፈላስፎች ነፍስ ከስብእና ከሚያወጣውና ከሚጎዳው ፍልስፍና ካልተለየች ራሷን በሚያስጨንቅ ፣ ፈጣሪ የለም በሚል ከንቱ ከኖረች በእርያ አፍንጫ የወርቅ ቀለበት አንደኾነ ፤ ጥበብ የሌላት ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት የተባለች ይቺ ናት ። ሴት ብሎ የጠራት ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች በብዙ መጻሕፍት በሴት አንቀጽ ስለምትጠራ ነው ። ከንቱ እሳቤም ማለት የሚያሳዩትን ኹሉ አንደማያዩ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ፍልስፍና መኖር ነው ። ("ሚሥጢረ ሚሥጢራት" መምህር ገብረ መድኅን እንየው እና መምህር መዝገበ ቃል ገብረ ሕይወት ገጽ-36) @MoaeTewahedoB
Показати все...
2🥰 2

🥰 2