cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። " https://t.me/MoaeTewahedoB አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014

Більше
Рекламні дописи
10 925
Підписники
+2024 години
+227 днів
+2730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
❤️
Показати все...
🥰 4
ሰው በግእዝ ሰብእ ይባላል። ይህንን አንዳንድ ሰዎች "ሰብዐ-ሰባት አደረገ" ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ዘር ውስጠዘ ነው ይላሉ። ይኽውም ከሰባቱ ባሕርያት የተገኘ ማለት ሲሆን ሰባቱ ባሕርያት የተባሉትም አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ማለትም ባሕርየ እሳት፣ ባሕርየ ማይ፣ ባሕርየ መሬት፣ ባሕርየ ነፋስ እና ሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ ለባዊነት፣ ነባቢነት እና ሕያውነት የተገኘ ነው ይላሉ። ይህ ግን የተሳሳተ አነጋገር ነው። ሰው ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአንዲት ባሕርየ ነፍስ ተገኘ ይባላል እንጂ ሦስት ባሕርያተ ነፍስ የሚባል የለም። ሰብእ የሚለው ዘር ውስጠ ዘ "ተሰብአ-ሰው ሆነ" ከሚለው ግሥ ይወጣል እንጂ "ሰብዐ-ሰባት አደረገ" ከሚለው አይወጣም። ለባዊነት፣ ሕያውነትና ነባቢነት የነፍስ ግብራተ ባሕርይዎች (መሆኖች) ናቸው እንጂ ባሕርይዎች አይደሉም። ወይም የነፍስን ግብራተ ባሕርያት ከተናገርን የእያንዳንዱን ባሕርያተ ሥጋ ግብራትም ጠቅሰን መቁጠር ነው። የእያንዳንዱን አንድ ብለን ከቆጠርን ደግሞ የነፍስንም አንድ ብሎ መቁጠር ይገባል። በእርግጥ ግብረ ባሕርይን ባሕርይ ብለው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊኖሩ ይችላሉ። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሰው በጠቅላላው ከሰባቱ ባሕርያት የተገኘ ከሚባል ይልቅ የእያንዳንዱን ግብረ ባሕርይ ቆጥሮ ፲፭ ቢል የቀና ይሆን ነበር። ይኽውም       ፩) የመሬት ግብራተ ባሕርይ                  -ደረቅነት                  -ጥቁርነት                  -ርጥብነት       ፪) የውሃ ግብራተ ባሕርይ                  -ብሩህነት                  -ርጥብነት                  -ቀዝቃዛነት       ፫) የነፋስ ግብራተ ባሕርይ                  -ሞቃትነት                  -ቀዝቃዛነት                  -ጥቁርነት       ፬) የእሳት ግብራተ ባሕርይ                  -ብሩህነት                  -ሞቃትነት                  -ደረቅነት ናቸው። የነፍስን ግብራተ ባሕርይ ባሕርይ ብለን ቆጥረን ሦስት ካልን የሥጋን ግብራተ ባሕርይም ቆጥረን ፲፪ ማለት ግድ ይለናል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሰው ከ፲፭ቱ ባሕርያት ተገኘ ያሰኛል። የአራቱን ባሕርያተ ሥጋ ባሕርይን ቆጥረን አራት ብለን ከቆጠርን ደግሞ የነፍስን አንድ ብለን መቁጠር ግድ ይለናል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ከአምስቱ ባሕርያት ተገኘ ያሰኛል እንጂ ከሰባቱ አያሰኝም። ፍርድ:- አንዳንድ መጻሕፍት ላይ ለምሳሌ አክሲማሮስ አንድምታ ላይ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ ሲል ይገኛል። ይህን ጊዜ ሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ ያላቸው ግብራተ ባሕርይ እንደሆኑ ልብ ማድረግ ይገባል። አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ሲል ግን ግብራተ ባሕርይን አይቶ ሳይሆን ባሕርይን ራሱን አይቶ መሆኑን መዘንጋት አይገባም። ግብራተ ባሕርይን ሳይመለከት ቀጥታ ባሕርይን ተመልክቶ በሚታተት ሐተታ ግን ትክክለኛው ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአንዲት ባሕርየ ነፍስ የሚለው መሆኑን መረዳት ይገባል። ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ "አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እም ገነት" ከሚለው የታተተው በዚህ መንገድ ነው። በመምህር በትረማርያም አበባው @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 1
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
3🥰 1
"ከማንም ሰው ጋር ሳልጋጭ የሰላም ሕይወት ለመኖር ብችልና ቢፈቀድልኝ ኖሮ ለእኔ ለግል ሰብእናዬና ጠባዬ በእጅጉ ይሻለኝ ነበር። ነገር ግን አሁን የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጠላት ተከብባ እያለች ፣ ታላቁ የእምነት አጥርና ቅጥር ዙሪያውን በከበቡት የኑፋቄ የጦር መሣሪያዎች እየተመታ ከመሆኑ የተነሣ እየተነቀነቀና እየተናወጸ እያለ ፣ ከዲያቢሎሳዊ ተንኮላቸውና ጥቃታቸው የተነሣ የእግዚአብሔርን ቃል ለጥፋታቸውና ለኑፋቄያቸው ምርኮኛ ሊያደርጉት ቀላል በማይባል ሥጋት ላይ ጥለውት እያየን ፣ በዚህ ሁኔታ ላይ በዚህ የክርስትና ውጊያ አለመሳተፍና ድርሻን አለመወጣት አስጨናቂና አሳዛኝ ነገር እንደሆነ በማሰብ ወደዚህ ሰልፍ ውስጥ ገብቻለሁ። እያንዳንዱ ሰው ሐዋርያው እንዳለ እንደየድካሙ ዋጋውን እንደሚቀበል ሁሉ ከአቅሙ አንጻር መድከም የነበረበትን ያህል ድካም ያልደከመ ሰው ደግሞ ቅጣት ይጠብቀዋልና።" (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ - መድሎተ ጽድቅ ገጽ 16) @MoaeTewahedoB
Показати все...
👍 4🥰 1
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 3
እግዚአብሔር ሲቀጣን "አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡ "እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገጽ 36) @MoaeTewahedoB
Показати все...
4🥰 1
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 5👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#እናቴ_ሆይ "ደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ፤ ባዝንም ባንቺ እፅናናለሁ፤ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ።" (#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ - በመጽሐፈ አርጋኖ)
Показати все...
🥰 11 5👍 1😢 1
🕰🔔 11:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰       @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 3👍 1 1
#ከሐልዮ_ኃጢአት_መጠበቅ ሰይጣን ነቅዓ ሐልዮን መጠበቅ ላልቻለ ወጣት በቀጣይ እርሱን የሚወጋበት ኹለተኛው ጦር ሐልዮ ኃጢአት ነው። “የሐልዮ ኃጢኣት ምን ትጎዳለች?” እያለ እንዲያስብ ያደርገዋል። በሐልዮ ኃጢአት ያዝለዋል። ይኸውም ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃኤልን ከመስማት አልፈው እንዲመለከቷቸው በማድረግ በዝሙት ፍላጻ እንደነደፋቸው ነው። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮችን እንዲመለከት ያደርገዋል። ለምሳሌ ራስን በራስ ስለ ማጎሳቆል፣ ወይም ስለ ምስለ ሩካቤ፣ ወይም ስለሚያውቃት ሴት በዝሙት ሕሊና እንዲያስብ ያደርገዋል። ጓደኞቹ የተናገሩትን ነገር ወይም በመጽሔት ያነበበውን ወይም በተለያየ መንገድ ሲወራ የሰማውን “ይህ ምን ያረክሳል?” እያለ በሕሊናው እንዲያመላልሰው ያደርገዋል። እንደዚህ በሚኾንበት ጊዜ በየትኛውም ቀን ቢሰግድ ፆሩ ይመለስለታል። አንድ ወንድሜ እንደ ነገረኝ፡ እንደዚህ ያለ ፆር ሲመጣበት በሩካቤ አካሉ አከባቢ ካለው ፀጕር የተወሰነውን ይነጫል። በጣም ያማል። በዚያ ሰዓትም ከፆሩ ይልቅ ሕመሙ ስለሚበልጥ ፆሩን ከማሰብ ይመለሳል። ሕሊናው አድርገኝ አድርገኝ ብሎ እንዳይገፋፋው፣ ነጉዶ የመጣውን ፆሩን በተግባር ለመፈጸም ሰይጣንን እንዳይታዘዘው ያደርገዋል። እንደ ነደ እሳት የሚያቃጥለውን የፍትወትን ፆር እንዳያስነሣበት ይከልለዋል። የሐልዮ ኃጢኣት በተነሣ ጊዜ "ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ” እንደ ተባለው፥ ለዚህ ከሚዳርጉን ነገሮች (ቦታ፣ ኹኔታ) መራቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። “ይህ አሳብ የእኔ አይደለም” ብሎ ለመሸሽም የሐልዮ ኃጢአት የምታመጣውን መከራ የሚነግረን መምህር ወይም አበ ነፍስ ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው (2ኛ ጢሞ.2፥22)። መካሪ መምህር ሳናገኝ ቀርተን ካዋልናትና ካሳደርናት ለሰይጣነ ፍትወት እጅ እንደ መስጠትና ወድቀን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ገቢር ልናልፍ እንችላለንና። ከክፉ አሳብ መራቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ክቡር ዳዊት “ከክፉ ሽሽ” ካለ በኋላ በዚያ ሳያቆም ጨምሮ “መልካምንም አድርግ" ይላልና (መዝ.33፥14)። እርስ በእርሳቸው የተያያዙ ናቸው። ስለዚህ አንዲት ሴት ጥሩ ልብሷን ተሸላልማ ተጊያጊጣ እየተኩነሰነሰች ስትሔድ አይቶ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች "ከዚች ክፉ ወጥመድ ሽሹ" እንዳላቸው ሸሽቶ ወደ በጎ ሥራ ፊትን ማዞር ይገባል። ከወደቁ በኋላ ከመጠበብ ሳይወድቁ መጠንቀቅ ይሻላልና። በሌላ መልኩ ደግሞ ተፈጥሮ ስለኾነ እነዚያ ስሜቶች ለምን መጡ ማለት አይቻልም። ስሜቶቹን ግን መቀደስ ስለሚቻል ከክፉ ሸሽቶ መልካም በማድረግ መቀደስ ይቻላል። አንድ ፈረስን የሚጋልብ ሰው፥ ፈረሱ ወደ ገደል ቢያመራ ጋላቢው የሚያደርገው ልጓሙን ማጥበቅ ብቻ አይደለም፤ ፈረሱ በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድም ይመራዋል እንጂ። ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲመጡብን ከመራቅ ባሻገር ወዲያው መንፈሳዊ ተግባር ማከናወንም አስፈላጊ ነው። ጸሎት ሊኾን ይችላል፤ ስግደት ሊኾን ይችላል፤ መጽሐፍ ማንበብ ሊኾን ይችላል፣ መንፈሳዊ አባት ጋር መደወል ሊኾን ይችላል። ከበረኻ አባቶች ከተሰጡት ምክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦“ሌላ እኁም ከሰይጣነ ዝሙት ጋር ይጋደል ነበር። በሌሊት ተነሥቶም ከአረጋውያኑ ወደ አንዱ መጥቶ ስለ ሕሊናው ነገረው። አረጋዊውም ይታገሥ ዘንድ መከረው። በዚህ መንገድ እገዛ አግኝቶም ወደ በዓቱ ተመለሰ። ለኹለተኛ ጊዜም ወደ አረጋዊው መጥቶም እርዳታ አግኝቶ ወደ በዓቱ ተመለሰ። ውጊያው ለሦስተኛ ጊዜ ሲመጣበትም እንደገና  በሌሊት ወደዚያ አረጋዊ ሔደ። አረጋዊውም ወጣቱን አላሳዘነውም፤ እንደሚጠቅመው መክሮ ዘክሮ ነገረው እንጂ፤ እንዲህ ሲል፡- ምንም ዕድል እንዳትሰጠው። ሰይጣነ ዝሙት በፈተነህ በማናቸውም ሰዓት ወደ እኔ ና። ከዚያም ታጋልጠዋለህ። ስታጋልጠው ሸሽቶ ይሔዳል። ሰይጣነ ዝሙት እነዚህን አሳቦች የሚደብቃቸውንና የማይገልጣቸውን ሰው ያህል የሚፈትነው የለምና።" ያ እኁም በዚያች ሌሊት እርዳታ ፈልጎ ዓሥራ አንድ ጊዜ ወደ አረጋዊው እየተመላለሰ አሳቦቹን ተቃወማቸው። አረጋዊውም ሰይጣነ ዝሙቱ ከእርሱ እንደ ራቀ ነገረው። ነገር ግን ወደ በዓቱ በተመለሰ ጊዜ ውጊያው እንደ ገና መጣበት። ከብዙ ጊዜ ምልልስ በኋላም ያ እኁ አረጋዊውን:- አባ! ቸርነትህ ይደረግልኝ፡ እንዴት አድርጌ መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ አለው። አረጋዊውም፡- ልጄ ፥ በርታ! እግዚአብሔር ፈቃዱ ከኾነ የእኔ ሕሊና ወደ አንተ ይመጣል። ከዚያም በኋላ ንጹሕ ሕሊና ይዘህ ትሔዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ አትፈተንም' አለው። ይህን ብሎ ሲጨርስም እግዚአብሔር ሰይጣነ ዝሙቱን እስከ ወዲያኛው ከዚያ እኁ አራቀለት።” ስለዚህ ሰይጣነ ዝሙት መጥቶ ሲያሳስበን ወይም በሌላ መንገድ ያየነውንና የሰማነውን በሕሊናችን እንድናመላልሰው በሚፈልግበት ጊዜ ምንም ሳንሰለችና ዕድል ሳንሰጥ ወደ አበ ነፍሳችን መሮጥ እንዳለብን ያስረዳል። አበ ነፍሶችም በትዕግሥት ልጆቻቸውን የመርዳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። ወላጆቻችንም ሊያግዙን ይችላሉ። የሐልዮ ኃጢአት በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከሚያደርጉ ነገሮች ኣንዱ ለብቻና ሥራ ፈት መኾን ነው። ሥራ ፈትተን ለብቻችን ስንኾን ሰይጣን መጥቶ ያንን ኃጢአት በደንብ እንድናስብበት፣ ተግብረው ተግበረው ይለናል። ልክ ለሔዋን በለስን የምታስጎመጅ አድርጎ እንዳሳያት፥ በእኛም የማስተዋል ሕሊናችንን አጣምሞ ከዚያ ኃጢአት ስለምናገኘው ደስታ ያሳስበናል። “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል” የተባለው መነኰሴ ሥራ ላለመፍታትና ከሓልዮ ኃጢኣት ለመራቅ ሲል ይህን ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህ ዝም ብለን መቀመጥ አይገባንም። ይልቅስ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመሳተፍ፣ ሌሎች በጎ ሥራዎችንም በመሥራት እንጠመድ። በዚህ ከተጎዱት ሰዎች መካከል አንዱ ነቢዩ ዳዊት ነው። ነቢዩ ዳዊት ወጣት ኾኖ በጎችን በሚጠብቅበት፣ ለሳኦል ጋሻ ጃግሬው ኾኖ በገና እየደረደረ በሚያገለግልበት፣ ሳኦል በምቀኝነት ተነሥቶበት በሚያሳድደው፣ ወደ ንግሥናው መጥቶ መንግሥቱ እስከ ተደላደለ ጊዜ ድረስ በዝሙት አልወደቀም ነበር። መንግሥቱ ተደላድሎ ከተመሠረተ፣ ክብሩ ከጨመረ በኋላ ግን ሥራ ፈትቶ በሰገነት ላይ ሲመላለስ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህን ስትታጠብ ተመለከታት። ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ፡- “ሰውነት ሥራ ሲፈታ፥ ሕሊናም ሥራ ይፈታል” እንዳለው፥ ንጉሥ ዳዊት ሥራ ፈትቶ ስለ ነበረም በቀላሉ በነቅዓ ሐልዮ ሳያበቃ ስለ እርሷ በማሰብ ወደ ሐልዮ ኃጢኣት ገባ። ስለዚህም “መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፣ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ" (2ኛ ሳሙ.11፥4)። በመኾኑም ራሳችንን ሰይጣን ወደ ሕሊናችን የሚያስገባውን የሐልዮ ኃጢአትን ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በማራቅ፥ ንጽሕናችንን ጠብቀን ከሴት ከወንድ ርቀን እስከ ጋብቻ ድረስ መጽናት ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በሕልማችን ሩካቤ ስንፈጽም ልናይ እንችላለን። በዚህ ጊዜ እኛ ራሳችን ቀን ላይ ያሰብነው አሳብ አለመኾኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቀን ያሰብነው ሌሊት ቀጥሎ ከኾነ ከአበ ነፍስ ጋር ተነጋግሮ አሳቡን ማራቅ፣ ከዚያ ውጭ ግን ወጣቶች በመኾናችንና “ፒቱታሪ” የተባለው ዕጢ የዘር ፈሳሽ ማመንጨቱና አንዳንድ ጊዜ በራሱ ተስፈንጥሮ ስለሚወጣ በዚህ መነሻነት ወደ ሌላ ኣሳብ እንዳንሔድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ  ከተጻፈው #ትንሿ_ቤተክርስቲያን መጽሐፍ - ገጽ 161-163) @MoaeTewahedoB
Показати все...
🥰 5👍 3