uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

The Remedial Tutorials

The Remedial Tutorials

Відкрити в Telegram

To register,use @the_remedial_tutorial_bot For any question contact us @Remedial_admins

Показати більше
2 252
Підписники
-324 години
-257 днів
-7930 днів
Архів дописів
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 19 እና 20 /2019 ዓ.ም እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 19 እና 20 /2019 ዓ.ም እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ የተገለጸው የመግቢያ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል። ቀጣይ የመግቢያ ቀን እስከሚገለፅ ተማሪዎች ገለጽ ድረስ በትዕግሥት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል። @tikvahuniversity

Repost from Tikvah-University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 19 እና 20 /2019 ዓ.ም እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 19 እና 20 /2019 ዓ.ም እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ የተገለጸው የመግቢያ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል። ቀጣይ የመግቢያ ቀን እስከሚገለፅ ተማሪዎች ገለጽ ድረስ በትዕግሥት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል። @tikvahuniversity

በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 23 እና 24/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ ለምዝገ
በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 23 እና 24/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦ ● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ● ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ● ሁለት መጠኑ 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID)፣ ● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡ @tikvahuniversity

በ2019 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተዘዋወራችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአንደኛ ዓመት መደበኛ
በ2019 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተዘዋወራችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአንደኛ ዓመት መደበኛ (Freshman) ተማሪዎች በመመደቡ ምክንያት በትምህርት ሚኒስቴር ዳግም ምደባ ወደ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ መዘዋወራችሁ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የጥሪ ማስታወቂያ በሚያወጣበት ወቅት በጭሮ ከተማ በሚገኘው ዋና ግቢ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። @tikvahuniversity

በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደ ጥቅምት 12 እና 13/2019 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒ
በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደ ጥቅምት 12 እና 13/2019 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ሬጂስትራር ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ (ፍሬሽማን) የምዝገባ ጊዜ ቀድሞ በተገለፀው ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። በተገለጹት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ትምህርት ማስረጃዎችን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ሪሚዲያል ተማሪዎች ወደ ካምፓስ ከመምጣታችሁ በፊት በ https://forms.cloud.microsoft/r/SzXVPsKU9x አማካኝነት በጊዚያዊነት መመዝገብ ይኖርባችኋል ተብሏል። @tikvahuniversity

ለ2019 አዲስ ሪሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ያደረጉ ጊቢዎች:- ✨ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም ✨ዲላ ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም
+1
ለ2019 አዲስ ሪሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ያደረጉ ጊቢዎች:- ✨ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም ✨ዲላ ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም

ለ2019 አዲስ ሪሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ያደረጉ ጊቢዎች:- ✨ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም ✨ዲላ ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም
+1
ለ2019 አዲስ ሪሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ያደረጉ ጊቢዎች:- ✨ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም ✨ዲላ ዩኒቨርሲቲ -ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም

#WoldiaUniversity በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባ
#WoldiaUniversity በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity

Repost from Tikvah-University
#WoldiaUniversity በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባ
#WoldiaUniversity በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity

#MoE የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡ በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወ
#MoE   የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡   በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡   የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇 https://student.ethernet.edu.et/preferences   @tikvahuniversity

የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨ
+1
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። 1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) 2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%) በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ 1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%) 4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

የ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካሌንደር ትምህርት ሚኒስቴር የ2019 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካሌንደርን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል። በትምህርት ሚኒስቴ
+3
የ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካሌንደር ትምህርት ሚኒስቴር የ2019 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካሌንደርን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል። በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በቀን 04/13/2018 ዓ.ም የተፈረመው ካሌንደሩ፤ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም የሁሉም የቅድመ-ምረቃ (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መሆኑን ያሳያል። ካሌንደረሩ፣ የሁሉም የቅድመ-ምረቃ (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ትምህርት መስከረም 11/2019 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልጿል። (ሙሉ የ2019 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካሌንደር ከላይ ተያይዟል።) @tikvahuniversity

photo content

photo content

የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ! በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባ
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!   በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡   የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇 ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም   የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇 https://student.ethernet.edu.et/   የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል። Telegram | TikTok | YouTube | Instagram

Repost from Tikvah-University
#Remedial_Complaint ዛሬ ይፋ ከተደረገው የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ጋር በተያያዘ እጅግ በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል። በርካታ ተማ
+4
#Remedial_Complaint ዛሬ ይፋ ከተደረገው የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ጋር በተያያዘ እጅግ በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል። በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ 'Disqualified' የተባለባቸው መሆኑን በመግለፅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሌሎች በርካታ ተማሪዎች ደግሞ የሂሳብ ትምህርት ውጤታቸው ብቻ 'Disqualified' እንደሚል ገልፀዋል። የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የሆኑት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "በፈተና ወቅት ምንም አይነት የስነ-ምግባር ግድፈት አልፈፀንም" በማለት በእርማት ወቅት ቴክኒካል ችግር ከነበረ እንዲታይላቸው በትህትና ጠይቀዋል። ቅሬታችሁን በኦንላይን አስገቡ 👇 https://result.ethernet.edu.et ከውጤታችሁ ስር መጨረሻ ላይ ያለውን Submit Complaint የሚለውን ይጫኑ፣ Select a category የሚለውን ይክፈቱ፣ My result disqualified without reason የሚለውን ይምረጡ፣ አጠር ያለ መግለጫ ይፃፉ፣ የስልክ ቁጥርዎን ይሙሉ እና Submit Complaint የሚለውን በመጫን ቅሬታዎን ያስገቡ። የሪሚዲያል ፕሮግራም የማለፊያ ነጥብ 250 ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች (5 የትምህርት አይነቶች) እና 200 ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች (4 የትምህርት አይነቶች) መሆኑ ታውቋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎቹ በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ የሚሰጡትን ምላሽ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርሳችሁ ይሆናል። @tikvahuniversity

#RemedialResult በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል። https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Ex
#RemedialResult በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል። https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Examination ከሚለው ስር View Results የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና 53,620 ተፈታኞች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል። @tikvahuniversity

" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የ
+1
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለ
" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል። " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም Telegram | TikTok | YouTube | Instagram

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫው እስካሁን ያልተጀመረ ሲሆን መግለጫው መሰጠት እንደተጀመረ በቀጥታ የምናስተላልፍ ይሆናል። @tikvahethiopia
+1
ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫው እስካሁን ያልተጀመረ ሲሆን መግለጫው መሰጠት እንደተጀመረ በቀጥታ የምናስተላልፍ ይሆናል። @tikvahethiopia