uk
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Відкрити в Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

Показати більше
3 614
Підписники
Немає даних24 години
-27 днів
+1330 днів
Архів дописів
በተለያዩ ክፍለከተሞች ለሚከናወኑ ስራዎች የወጣው ጨረታ በዛሬው ዕለት ተከፈተ። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጥር 19/2018 ዓ/ም በአስሩም ክፍለከተሞች ለሚገኙ የመሬት ይዞታ ምዝገባ
በተለያዩ ክፍለከተሞች ለሚከናወኑ ስራዎች የወጣው ጨረታ በዛሬው ዕለት ተከፈተ። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጥር 19/2018 ዓ/ም በአስሩም ክፍለከተሞች ለሚገኙ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ዕድሳት ስራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ መጋበዙ የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎ በዛሬው ዕለት 20 ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት የጨረታ ሰነድ ተከፍቷል። በኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት /EGP/ የተከናወነው ይኸው ጨረታ ተወዳዳሪዎች ካሉበት ሆነው ሂደቱን የሚከታተሉበት ዕድል የፈጠረ ሲሆን በተጨማሪም በጨረታ ሂደት የሚከሰቱ ክፍተቶችንም ማስቀረት ችሏል። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የካቲት 11/2018

ስለ ግምታዊ  ዋጋ አወጣጥ ማዎቅ ይፈልጋሉ? (Approximate) Bill of Quantity – BOQ ‎1.  የቤቱ መጠን (Basic Data) ‎ስፋት፡ 6 m × 8 m = 48 m² ‎ቁመት (Wall height)፡ 3.1 m ‎የግንባታ አይነት፡ Block work ‎1ፎቅ (Single storey) ‎የጣሪያ አይነት፡ ቆርቆሮ (CGI sheet) ‎2. የብሎኬት መጠን (Block Quantity) ‎2.1 የውጪ ግድግዳ ርዝመት ‎Perimeter = 2(6 + 8) = 28 m ‎2.2 የግድግዳ አካባቢ ‎28 m × 3.1 m = 86.8 m² ‎2.3 የብሎኬት ቁጥር ‎1 m² ≈ 12.5 blocks (40×20 cm block) ‎86.8 × 12.5 ≈ 1,085 blocks ‎5% ተጨማሪ (wastage) ≈ 55 blocks ‎ጠቅላላ ብሎኬት ≈ 1,140 ብሎኬቶች ‎3. #የብረት (Reinforcement) መጠን (ግምታዊ) ‎3.1 ኮሎም (Columns) ‎ቁጥር፡ 9 (ኮርነር + መካከለኛ) ‎መጠን፡ 20×20 cm ‎Main bars: 4Ø12 ‎Stirrups: Ø8 @ 20 cm ‎ጠቅላላ ብረት (Columns) ≈ 280 kg ‎3.2 ቢም (Ring beam) ‎ርዝመት = 28 m ‎4Ø12 main bars ‎Ø8 stirrups @ 20 cm ‎ጠቅላላ ብረት (Beam) ≈ 200 kg ‎3.3 ጠቅላላ የብረት መጠን≈ 480 – 500 kg (0.5 ቶን) ‎4. የጣሪያ (ቆርቆሮ) መጠን ‎4.1 የጣሪያ አካባቢ ‎የቤት አካባቢ = 48 m² ‎15% slope + overlap ‎48 × 1.15 ≈ 55 m² ‎4.2 ቆርቆሮ ብዛት ‎√ sheet ≈ 2.5 m² ‎ 55 ÷ 2.5 ≈ 22 sheets ‎ √ ተጨማሪ (wastage) ‎ጠቅላላ ≈ 24 ቆርቆሮ ‎5. አጭር BOQ ማጠቃለያ ‎ንጥል መጠን ብሎኬት≈ 1,140 pcs ‎ብረት≈ 500 kg ‎ቆርቆሮ≈ 24 sheets ‎የግድግዳ አካባቢ86.8 m² ‎የጣሪያ አካባቢ=55 m² ‎      ::::::::::///////::::::::: ‎Via~ tile👷‍♂️ @consite🏗

👉የ 2018 አጋማሽ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ ከላይ በፋይል ተያይዟል። የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16 እስከ 27/2018 እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል። @etconp

👉 INTERCON Construction Chemicals ● Concrete Admixtures ● Bonding Agents ● Waterproofings ● Wall Putty, Prime Coat ● Concret
👉 INTERCON Construction Chemicals  ● Concrete Admixtures ● Bonding Agents ● Waterproofings ● Wall Putty, Prime Coat ● Concrete Repair Mortar ● Floor hardener, Epoxy ● Grout, Self-level mortar ● Quartz paint, Contextra ● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers  ● Geotextiles and other construction chemicals and materials ☎️ Tel: 0961955555 🔹 Address 1: Signal road, around Dinberwa Hospital 🔹 Addres 2: Wellosefer, Infront of Dani Plaza

+3
የዋጋ ማሻሻያ (Price Adjustment) – አስፈላጊነቱ እና ተግባራዊነቱ የዋጋ ማሻሻያ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያለው የኮንትራት መርህ ሲሆን፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ወቅት የሚከሰቱ የዋጋ ግሽበቶች፣ የገንዘብ ዋጋ መቀነስ እና የግብዓት ዋጋ ለውጦች ተፅዕኖ እንዳያስከትሉ የሚረዳ መንገድ ነው። ዓላማው ኮንትራክተሩን እና አሠሪውን ከልክ ያልፈ የፋይናንስ አደጋ መጠበቅ እና ፍትሃዊ ክፍያ ማረጋገጥ ነው። በኢትዮጵያ፣ በተለይም በመንገድ እና በትልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የነዳጅ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ቢቱመን፣ የሰራተኛ ኃይል እና የመሳሪያ ዋጋ ፈጣን መለዋወጥ የዋጋ ማሻሻያን የማይተካ አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል። ይህ መርህ በትክክል ሲተገበር፣ ፕሮጀክቶች እንዳይዘገዩ፣ ኮንትራክተሮች እንዳይጎዱ እና የህዝብ ገንዘብ በአግባቡ እንዲውል ያግዛል። 📎 ለተግባራዊ አጠቃቀም፣ የዋጋ ማሻሻያ ሂሳብ ማስላት የሚያግዝ Excel ፎርማት አብረን አያይዘናል፤ ለወደፊት አጠቃቀምዎ እንዲረዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። If you need advisor on this matter contact @BidHelpbot Read more https://constructionproxy.com/price-adjustment-in-construction-projec-ethiopia/

👉 ለመንገድ የኮሊደር ልማት ግንባታ የስራ ተቋራጮች የወጣ ማስታወቂያ
👉 ለመንገድ የኮሊደር ልማት ግንባታ የስራ ተቋራጮች የወጣ ማስታወቂያ

#የሰምንተኛው ዙር የሊዝ ጨረታ አሸናፊወች ዛሬ ይፋ ሆነ 👉መልካም ሳምንት 📞0931168635 📞0934433939

+7
200_questions_and_answers_on_practical_civil_engineering_wor_1.pdf5.87 KB

🔑 ለጨረታ ማስከበሪያ ከመድን የሚቀርቡ ዋስትናዎች (Conditional Bond) ከዚህ በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ስራ ተቋራጮች ለውል ማስከበሪያ ከመድን የሚያቀርቡት ዋስትና Uncondition
🔑 ለጨረታ ማስከበሪያ ከመድን የሚቀርቡ ዋስትናዎች (Conditional Bond) ከዚህ በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ስራ ተቋራጮች ለውል ማስከበሪያ ከመድን የሚያቀርቡት ዋስትና Unconditional  መሆን ይጠበቅበታል። 📌 በነባሩ የፌደራል ግዥ መመሪያ በግንባታ ስራ ለተሰማሩ የሃገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የመድን ዋስትና (Conditional Insurance Bonds) ለጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የነበረው ቢሆንም አዲሱ መመሪያ ይህንን አማራጭ አላካተተም። 📌 ለውል ማስከበሪያ ደግሞ  ከአገር ውስጥ የግንባታ ዘርፍ ሥራ ተቋራጮች ወይም መድሐኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች አምራች ድርጅቶች ለሚፈጸም ግዥ ከታወቀ የመድን ድርጅት የሚቀርብ በሁኔታ ላይ ተመሠረተ የመድን ዋስትና ቢያቀርቡ ተቀባይነት የነበረው ቢሆንም በአዲሱ የግዥ መመሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ መሆን እንዳለበት ተመላክቷል። N.B. የሃገር ውስጥ መድን ድርጅቶች በብሄራዊ ባንክ በኩል በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional) መስጠት የማይችሉ ከመሆኑ አንጻር ይህ እንዴት ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚችል ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። 📌 የአገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች እንዲሁም የመድሀኒት እና ሕክምና መሳሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional) የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee) ከታወቀ የመድን ድርጅት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የሚገልፀው አንቀፅ ባለበት ፀንቷል። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👵 Discussion: @procinsightet2

ከአቅም በላይ ሁኔታ (Force Majeure) 🟢 በውል አስተዳደር ወቅት የሚያጋጥሙ ከአቅም በላይ ሁኔታ (Force Majeure) በተመለከተ አዲሱ የፌደራል ግዥ መመሪያ አንቀፅ 149 ዝርዝር ጉዳዮ
ከአቅም በላይ ሁኔታ (Force Majeure) 🟢 በውል አስተዳደር ወቅት የሚያጋጥሙ ከአቅም በላይ ሁኔታ (Force Majeure) በተመለከተ አዲሱ የፌደራል ግዥ መመሪያ አንቀፅ 149 ዝርዝር ጉዳዮችን አካቷል። 🔴 ያስታውሱ: ግልጽ የሆነ ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ተደርገው ሊቆጠሩ አይችሉም። 1⃣ ለውሉ አፈጻጸም አስፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶች ዋጋ መወደድ ወይም መርከስ (Increases or decreases in prices of essential supplies for contract performance) 2⃣ ተዋዋይ ያለበትን የውል ግዴታ አፈጻጸም የሚያከብድበት አዳዲስ ህግ መውጣት (New legislation rendering contractual obligations more onerous) ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል☝️ 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👵 Discussion: @procinsightet2

⭐️Variation/ተጨማሪ ስራ/✨ በፌደራል የግዥ መመሪያ መሠረት: 🟢 ያልታሰቡ ሁኔታዎች በማጋጠማቸው ምክንያት በመጀመሪያ ውል ውስጥ ያልተካተቱ ተጨማሪ የግንባታ ሥራዎች ማሠራት አስፈላጊ ሲሆንና
⭐️Variation/ተጨማሪ ስራ/✨ በፌደራል የግዥ መመሪያ መሠረት: 🟢 ያልታሰቡ ሁኔታዎች በማጋጠማቸው ምክንያት በመጀመሪያ ውል ውስጥ ያልተካተቱ ተጨማሪ የግንባታ ሥራዎች ማሠራት አስፈላጊ ሲሆንና በቴክኒክ ወይም በኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ምክንያት እነዚህን ተጨማሪ የግንባታ ሥራዎች ከመጀመሪያው ውል ነጥሎ ማሠራት የማይቻል ሲሆን ተጨማሪ ስራ ማሰራት ይቻላል። 🟣 በተጨማሪነት ወይም በዋናው ሥራ ውስጥ ያልተካተቱ አዲስ የሚሰሩ የግንባታ ሥራዎች የገንዘብ መጠን ከመጀመሪያው ውል ጠቅላላ ዋጋ  ከ30% /ሠላሳ በመቶ/ የበለጠ መሆን የለበትም። 🔴 አሸናፊው ተጫራች በውድድር ከተመረጠ በኋላ ከተፈረመ ውል ውጭ የመጀመሪያው ግዥ የተከናወነባቸው  ከምክር ውጭ የሆነ አገልግሎት ወይም  የምክር አገልግሎት ሥራዎች ወይም  አቅርቦቶች ውል አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ  መጠናቀቁ እና ቁጠባንና ቅልጥፍናን  የሚያስገኝ መሆኑ በመረጋገጡ ቀደም ሲል ውሉን ከፈረመው አቅራቢ እንዲሠራ ወይም እንዲቀርብ ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን፣ በተጨማሪነት የሚታዘዘው ዕቃ፣ የምክር ወይም ሌሎች አገልግሎት ግዥ  መጠን ከውሉ ጠቅላላ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) መብለጥ የለበትም። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👵 Discussion: @procinsightet2

👉 procurement of Building Construction of Residences for Rangers (Chebera churchura) The time zone is: East Africa Time (GMT+3:00) Package Information Invitation Date  Feb 11, 2026, 12:00:00 AM Procurement Reference No  EWCA-NCB-W-0037-2018-BID- Open Procurement Category  Works Market Type  National Object of Procurement  procurement of Building Construction of Residences for Rangers (Chebera churchura) Description  Not Available Lot Number  1 Clarification Request Deadline  Feb 26, 2026, 5:00:00 PM Pre-Bid Conference Schedule  Not Applicable Site Visit Schedule  Not Applicable Bid Submission Deadline  Mar 3, 2026, 10:00:00 AM Bid Opening Schedule  Mar 3, 2026, 10:30:00 AM Financial Resources  The Bidder must demonstrate access to, or availability of, financial resources such as liquid assets, unencumbered real assets, lines of credit, and other financial means, other than any contractual advance payments to meet the cash-flow requirement ETB  5,000,000.00 (Five Million Birr). Annual Turnover  The average annual turnover calculated as total certified payments received for contracts in progress or completed for the last five years in construction sector shall not be less than 18 Million Birr. Testimony of audited report must be attached. Number of staffs  At least 6 staff currently work for the Bidder. Personnel for the key positions  Among the staff mentioned in Sub-Clause 2.1 Bidder must demonstrate that it will have the personnel for the key positions that meet the following requirements; Position , Quantity , Total Work Experience in years, Experience in Similar Works in years are as follows Respectively Site Engineer, 1, 6, 4 Office Engineer, 1, 6, 4 Quantity Surveyor, 1, 4, 2 Sanitary Engineer, 1, 4, 2 Construction Forman, 1, 6, 4 Electrical Engineer, 1, 4, 2 Notice Terms and Conditions  EWCA-has the right to cancel the bid fully or partially. ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ተወዳዳሪ ሳይት ቪዚት ማድረግ አለበት Application online on EGP https://egp.gov.et/egp/bids/all/tendering/6a97ec05-5bb3-4243-8a8b-dba71680c8e4/open

የሚከናወንበት ዋና ምክንያቶች በጥቂቱ ብንመለከት፦ በምሽት ኮንክሪት ሙለት ማከናወን አከባቢዉን ላለመረበሽ ሳይሆን የህንፃውን ጥንካሬ እና ጥራት ለመጠበቅ የሚደረግ ስልታዊ ውሳኔ ነው። ​1. የሙቀት ቁጥጥር (ዋናው ምክንያት) -​ኮንክሪት ዝም ብሎ አይደርቅም፤ ሃይድሬሽን (Hydration) የተባለ ኬሚካላዊ ሂደት ውስጥ ያልፋል። - ይህ ሂደት የራሱን ሙቀት ያመነጫል። የአየሩ ሁኔታ በጣም ሞቃት ከሆነ (ለምሳሌ በቀትር ሰዓት)፣ ኮንክሪቱ ውስጥ ያለው እርጥበት በፍጥነት ሊተን ወይም በጣም ሊሞቅ ይችላል። - Thermal Cracking (በሙቀት ምክንያት የሚመጣ ስንጥቅ): የኮንክሪቱ ውጫዊ ክፍል ቀዝቅዞ ውስጣዊ ክፍሉ አሁንም በጣም ሞቃት ከሆነ፣ በግፊቱ ምክንያት ስንጥቅ ይፈጠራል። - Workability (ለመስራት አመቺነት): የቀዘቀዘ የምሽት አየር ኮንክሪቱ ሳይደርቅ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ ስለሚያደርግ፣ ሰራተኞች ለማስተካከልና ለማለስለስ በቂ ጊዜ ያገኛሉ። ​2. የትራፊክ እና የሎጂስቲክስ ሁኔታ - ​አንድ ትልቅ የኮንክሪት ሙሌት የበርካታ ሚክሰር መኪናዎችን ያልተቋረጠ ጉዞ ይፈልጋል። አንዲት መኪና በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ከዘገየች አጠቃላይ ስራው ይስተጓጎላል። - Cold Joints (የቅዝቃዜ መገጣጠሚያ): አዲስ የሚመጣው ኮንክሪት ገና ሳይደርቅ ቀድሞ ከተፈሰሰው ጋር መዋሃድ አለበት። መኪና ዘግይቶ ቀድሞ የተፈሰሰው መድረቅ ከጀመረ በመካከላቸው ደካማ ስፌት ወይም Cold Joint ይፈጠራል። - ቅልጥፍና: ማታ ላይ የኮንክሪት መኪናዎች ያለ ትራፊክ መጨናነቅ በፍጥነት መመላለስ ስለሚችሉ ስራው ሳይቋረጥ እንዲከናወን ይረዳል። ​3. የተሻለ የጥራት ቁጥጥር - በምሽት የሚፈስ ኮንክሪት የማለስለስ ስራውን ቶሎ ስለማይደርቅ በጥራት ለማከናወን  ያስችላል። - ​ትነት (Evaporation): ለፀሐይ ብርሃን አለመጋለጡ ኮንክሪቱ ላይ ላዩን ብቻ ተንትኖ እንዳይሰነጣጠቅ (Plastic shrinkage cracking) ይከላከላል። - ​Power Troweling (በማሽን ማለስለስ): ቀዝቃዛው የሙቀት መጠን ለማሽን ኦፕሬተሮች ወለሉን እንደ መስታወት ለስላሳ አድርገው ለመስራት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል።

👉በትልልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ኮንክሪት ሙለት በምሽት ለምን ይከናወናል??
👉በትልልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ኮንክሪት ሙለት በምሽት ለምን ይከናወናል??