Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Відкрити в Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
Показати більше3 589
Підписники
+224 години
-17 днів
+4230 день
Архів дописів
እንኳን ለደብረ ታቦር(ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🤚🏗መጣና ባመቱ፤ ኧረ እንደምን ሰነበቱ ክረምቱ አልፎ ወደ ብርሃን መሻገራችንን በሚያበስረው፤ በህጻናት ውብ ዜማ እና የጅራፍ ድምጽ ለሚደምቀው ቡሄ እንኳን በሠላም አደረሳችሁ ብለናል🤚🤚 እንዲሁ እንዳለን አይለየን! ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን! መልካም ቡሄ!!
UNITY - CoN Catalogue Official's(1) t.me/UnitySupplierdb1 ☜|]ገፃችን
በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ ኢንጅነሮች ሊያውቃቸው የሚገቡ:-1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል። ከታች የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል የኮንክሪት ፍተሻ (Concrete Test): •Slump test, •compression test (cubic or cylindrical test), •split tensile test, soundness etc. የአፈር ፍተሻ (Soil Test): •Core cutter test, •compactiontest,sand replacement test, triaxial test, consolidation test etc. Bitumen Test: •Ductility test, softening point test, gravity test, penetration test etc. (በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ አንማር ይሆናል ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ መማር ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው :: 2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL) የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም አቅም እና ርጉእነት (settlement and stability) የምንገነባው አካል ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን። እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው። 3)የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF SURVEYING INSTRUMENTS) በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ መሳሪያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ ! 4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES USED IN CONSTRUCTION) ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካምድራቸው የአየር፣ የንፋስ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ (Construction codes) አላቸው። አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው። 5) BAR BENDING SCHEDULE ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ የሆነው የግንባታ አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል። ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል 6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN) አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል ማለት ነው። ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት ነው:: 7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS) ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው። 8 )የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL) ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው። ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው። አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩ ኢንጂነሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን አደጋ ለመከላከል። 9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT) እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣ ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን ነው 10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ (COORDINATION) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ ሊኖረን ይገባል። ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል። ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና ወሳኝ ነገር ነው።
4.የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡ በተለይም ከላይ ስለዋና ገንዘብ መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡ በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
የጥገና እና ብልሽጽ አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡-በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ዐ.ነገር ይነበባል፡-
"ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡ ”
በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
ሆኖም~ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የለውም::
የውጭ ምንዛሪ ተመን ተጀምረው የቆሙ ፕሮጀክቶች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ስላለው የሚመለተው አካል ቶሎ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል?
+5
ሴራሚክ ቴራዞ መግዛት ስትፈልጉ ጥሩ አቅም ያላቸው ደንበኞች አቅራቢዎች ስላሉን አድራሻቸውን ልንሰጣችሁ እንችላለን
📞+251-908280208 | +251- 707999001 ይደውሉልኝ ቴሌግራም/ጥያቄም ሆነ ሀሳብ ካለችሁ በቀጥታ ከስር /ያለውን: t.me/UnitySupplydbot ☜|] ለመልዕክት ይጠቀሙ, ይደርሰናል
3.የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee)
የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ሲባል ሥራ ተቋራጩ ጨረታውን አሸንፎ ውል ተፈርሞ ወደ ሥራው ሊገባ ሲል የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሥራ ተቋራጩ የተወሰነ የቅድሚያ ገንዘብ በመስጠቱ ምክንያት ሥራ ተቋራጩ በአንጻሩ ለወሰደው ገንዝብ የሚያቀርበው ዋስትና ነው፡፡
በመሰረቱ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ጅማሮ የቅድሚያ ክፍያ መኖር በአንድ በኩል ሥራ ተቋራጩ ያለምንም የገንዘብ ችግር ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች መግዣ ይሆነዋል፡፡ ወይም ደግሞ ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ከፍሎ ለንዑስ ተቋራጮች በሚሰጥበት ጊዜ እንደ ሥራ ማስጀመሪያ (mobilization commission) ይሆናቸዋል፡፡
ስለ ቅድሚያ ክፍያ አስፈላጊነት ታዋቂው የኮንስትራክሽን ክሌም ጸሀፊ ጆን ስካይስ እ.ኤ.አ 1999 በወጣው መጽሀፋቸው እንዳብራሩት ቅድሚያ ክፍያ መኖር ለሥራ ተቋራጮች ከመጥቀሙ ባሻገር የጨረታ ወጥ መለኪያ (tender standardization) ተድርጎ ስለሚወሰድ ጭምር ነው፡፡
የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና መኖረን አስመልክቶ የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁ.649/2001 በአንቀጽ 48 እንደተመለከተው የቅድመ ክፍያ ሊፈጸም የሚችለው ሥራ ተቋራጩ በቅድሚያ ክፍያ መልክ ከሚወስደው ገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቀርብ እንደሆነ ይናገራል፡፡
የመንግስት የኮንስትራክሽን ውሎችን የቅድሚያ ክፍያ መጠንን በተመለከተ እኤአ በ2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ የግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.26 ላይ የቅድመ ክፍያ መጠን የውሉን 30(ሰላሣ) ፐርሰንት መብለጥ የለበትም፡፡ ሆኖም ግን በአገር በቀል የሥራ ተቋራጮች የሚሰራ የመንገድ ግንባታ ሲሆን ግን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ እስከ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት ይደርሳል፡፡
ዝርዝር ሁኔታው በእያንዳንዱ ጨረታ ይገለጻል፡፡
በሥራ ተቋራጩ የሚቀርበው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው መጠን የተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ የዋትናው አቀራረብም በቼክ፣ ያል ቅደመ ሁኔታ የሚቀርብ የባንክ ዋስትና ወይም በቅድመ ሁኔታ የሚዘጋጅ የመድን ዋስትና ሊሆን ይችላል፡፡
ሌላው የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ለምን ዓላማ መዋል እንደለበትና በምን አግባብ ሊሰጥ እንደሚችል መመሪያው በአንቀጽ 16.26.7 ተመልክቶታል፡፡ በተለይም የመንገድ እና ህንጻ ግንባታ የሚሰሩ ሥራ ተቋራጮች በቅድሚያ ክፍያው ገንዘብ ስለሚገዙት የማሽነሪ ዝርዝር በመመሪያው መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡
በበርካታ የግንባታ ቦታዎች የውጭ የግንባታ ተቋራጮችን የምንመለከተው የአገር ውስጥ ተቋራጮች የት ሄደው ነው ?!
የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የግንባታ ተቋራጮች ማህበርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርን አነጋግሬያለሁ።
አለምአቀፋዊ ጨረታ የሚወጣው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ፕሮጀክት ነው። ማህበሩ ወደ 2 ቢሊዮን ማደግ አለበት የሚል ጥያቄ ለመንግሥት አቅርቧል.. .
Via~ኤርሚያስ
ማስታወቂያ:- ለ7ተኛ ዙር ሰልጣኞች በሙሉ!🚧የሰባተኛ ዙር የHealth and Safety in Construction እንዲሁም Ethics in Construction (Code of Conduct for Members of CCAE) ስልጠና ከ CMI ጋር በመነጋገር የሚሰጥበትን ቀን የወሰንን ሲሆን ስልጠናው ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለሦስት ሙሉ ቀናት ቦሌ ሜጋ ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው ሀንሰም ህንፃ ላይ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት 8ተኛ ፎቅ ላይ ባለው የስልጠና አዳራሽ ይሰጣል፡፡ ስልጠናውን ለመውሰድ የማኅበራችን አባል መሆን ስለሚያስፈልግ የሰልጣኞች የመጨረሻ ስም ዝርዝር የሚገለጸው የማኅበራችን አባል የሆኑት ድርጅቶች ብቻ ይሆናል፡፡ አባል ያልሆናችሁ ድርጅቶች የ7ኛ ዙር ስልጠናውን ለማከናወን እስከ ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016ዓ/ም ጠዋት ድረስ ባንቢስ ኃይለገብርኤል ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የማህበሩ ፅ/ቤት በአካል በመምጣት የአባልነት ምዝገባችሁን እንድትጨርሱ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያማኅበራችን ስልጠናውን ለማስተባበር ለሚያወጣቸው ወጪዎች 2,500.00 ብር ክፍያ እንደሚጠይቅ ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ 🏗👷"Think safety, work safely."ደህንነትን አስብ ፤ በጥንቃቄ ስራ" የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማኅበር
✨ https://addiscostestimator.com/
አስደሳች ዜና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች፡፡ አዲስ ኮስት ኤስቲሜተር ይባላል፡፡
ዌብ ሳይቱ ይግንባታዎትን መረጃ ከእርስዎ በመዉሰድ ጥንቅቅ BOQ በኤክሴል አዘጋጅቶ ይሠጥዎታል፡፡
አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋችሁ፣ የኢሜል አድራሻ ብቻ ነዉ፡፡
አሁኑኑ በነጻ ይሞክሩት፡፡
✨ጥቅሞቹ
📌የተሟላ የዋጋ ዝርዝር
📌ፈጣን እና ቀላል
📌ቶሎ ቶሎ የሚሻሻል የገበያ ዋጋ
💥ስራዎትን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ደንበኛዎትን ያስደስቱ፡፡https://youtu.be/llCVWy7fWTE?si=mVhMe81grc1Uc31f
For more information call 0909068750
✨ https://addiscostestimator.com/
አስደሳች ዜና በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ለተሰማራችሁ ባለሙያዎች፡፡ አዲስ ኮስት ኤስቲሜተር ይባላል፡፡
ዌብ ሳይቱ ይግንባታዎትን መረጃ ከእርስዎ በመዉሰድ ጥንቅቅ BOQ በኤክሴል አዘጋጅቶ ይሠጥዎታል፡፡
አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋችሁ፣ የኢሜል አድራሻ ብቻ ነዉ፡፡
አሁኑኑ በነጻ ይሞክሩት፡፡
✨ጥቅሞቹ
📌የተሟላ የዋጋ ዝርዝር
📌ፈጣን እና ቀላል
📌ቶሎ ቶሎ የሚሻሻል የገበያ ዋጋ
💥ስራዎትን በጥራት እና በፍጥነት በማጠናቀቅ ደንበኛዎትን ያስደስቱ፡፡https://youtu.be/llCVWy7fWTE?si=mVhMe81grc1Uc31f
For more information call 0909068750
በዚህ ድረ-ገፅ ለሚቀርቡ ወይም ይጥቅማል የምትሉት ሃሳብ ካለ በቀጥታ ከስር ባለው ማስፈጠሪያ ቦቱ ሊንክ ያጋሩን:
t.me/UnitySupplydbot ☜|] መልዕክቶን ይላኩልን, ይደርሰናል
የኮንስትራክሽን ዋስትና አይነቶች:-የቀጠለ.. .) 2.የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Contract security/ Performance የውል ማስከበሪያ ዋስትና (contract security) ወይም የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (performance bond) የሚባለው አንድም ግራ ቀኙ ለገቡት ውል መልካም አፈጻጸም ሲባል በአንድ ሦስተኛ ወገን የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም ሥራ ተቋራጮች ለፕሮጀክት ባለቤቶች ወይም ንዑስ ተቋራጮች ለዋናው ሥራ ተቋራጭ ውል ለመፈጸም ብለው ከአንድ የፍይናንስ ተቋም ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን አማካኝነት የሚቀርብ ዋስትና ነው፡፡ ሁኖም ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ተፈጻሚ የሚሆነው ዋናው ባለዕዳ(ለምሳሌ፡-ሥራ ተቋራጭ) ግዴታውን ባይወጣ ነው፡፡ "ከመንግስት አስተዳደር መ/ቤት ጋር የሥራ ውል ያደረገ ወገን እንደውሉ መፈጸም ባልቻለ ጊዜ የአስተዳደር መ/ቤቱ ተዋዋዩ የውል ማስከበሪያ (contract security) በሚል ካስያዘው ገንዘብ ላይ ውል ባለመፈጸሙ የደረሰበትን የጉዳት ኪሣራ መቀነስ ይችላል፡፡ ” በፌደራል የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁ.649/2001 አንቀጽ 47 ላይ በግልጽ እንደተመለከው በተለይም የመንግስት ግንባታ ውሎች ላይ አቅራቢ (ውል ተቀባይ) ሆኖ የሚቀርብ ወገን ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት በውል ሰጪው መንግስት መ/ቤት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ መጠኑን በተመለከተም የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡ እኤአ በ ሰኔ ወር 2010 የወጣው የገ/ኢ/ል/ሚ መመሪያ አንቀጽ 16.25 ላይ እንደተመለከው አሸናፊው ሥራ ተቋራጭ ጨረታውን አሸንፎ ውል በተዋዋለ በ 15 ቀናት ውስጥ ቢያንስ የውሉን 10ፐርሰንት እንደ ውል ማስከበሪያ(Performance security) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የዋስትናው መክፈያ መንገድም በመመሪያው አንቀጽ 16.16.4 በተመለከተው መሰረት በተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ፣ የባንክ ዋስትና ሰነድ፣ ክሬዲት ወይም በቅድመ ሁኔታ በሚዘገጅ የመድን ቦንድ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም መመሪያው በአንቀጽ 16.25.3 ላይ ውል ሰጪው የመንግስት መ/ቤት አቅራቢው (ሥራ ተቋራጩ) በውሉ በተቀመጠው መሰረት ግዴታውን መወጣት ካልቻለ የያዘውን ውል ማስከበሪያ ገንዘብ እንደነገሩ ሁኔታ መጠቀም ወይም መውረስ ይችላል፡፡ እንዲሁም ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ሥራ ተቋራጩ ውሉን በተወጣ ጊዜ ያስያዘው ገንዘብ ይመለስለታል፡፡ /የመመሪያው አንቀጽ 16.25.7 ይመለከተዋል፡፡ ሌላው ጉዳይ #የመልካም_ሥራ_አፈጻጸም ዋስትና (Performance bond) በመድን ድርጅቶች መውጣታቸው የዋሱን እና ባለገንዘቡን ግዴታ የሚገዛውን የሕግ ማዕቀፍ ይቀይራል ወይስ አይቀይርም? የሚለው ነጥብ ነው፡፡ ሲጠቃለልም የውል ማስከበሪያ ዋስትና ስለፕሮጀክቱ መልካም አፈጻጸም ውል ተቀባዩ ከአንድ ከሌላ ሦስተኛ ወገን ጋር በሚደርገው ግንኙነት ሊቋቋም ይችላል
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
