uk
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Відкрити в Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service

Показати більше
3 587
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
+4830 день
Архів дописів
+2
Construction Law and Dispute (Nov. 2024).pdf5.60 KB

Share የግንባታ ስራ ተቋራጮች ማህበራት መረጃ 2017 Latest.pdf

🤚ሰላም እንዴት ናችሁ! እስኪ የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/ በሰፊው እንመልከት:-👇 ➡️ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው። ➡️የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት /resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል። ➡️ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል። እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል። የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? 1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/ 2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን? - በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ። እነዚህም:- 1. Slump test 2.Compacting factor test 3.Veebee test እና 4.Vibro workability test ናቸው። ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት/Slump test/Cone test/Sand test/ ➡️የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት (Consistency) ለመለካት ይጠቅማል። ➡️ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል። ➡️ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው። በዚህ ምክንያት ከ1922GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል። የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች (Factors influencing slump test result) 1- ለኮንክሪቱ  የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ። ለምሳሌ:  ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም 2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር. 3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም። 4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ 5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/ 6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን 7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው? ➡️ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/ - ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm  የታችኛው ዲያሜትር 20 cm  የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው ➡️Plate/መደብ/ -ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/ የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው? 1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት። 2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ። 3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት። 4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት። 5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን። 6ኛ. በርጋታ  ቅርፅ ማውጫውን (mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት። 7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።
ማስታወሻ:
- ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን። - ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች:/Results to be/[ ➡️True Slump: - ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው። - ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው። ➡️Zero Slump: - ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና ሲሚንቶ /water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል። ➡️Collapsed Slump: - ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል።የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል። ➡️Shear Slump - ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ እንዳልሆነ ይነግረናል። @consite💠 እናመሰግናለን! -------------------------------------------- ለወደፊት ሌሎች የኮንክሪት ለስራ  ያለው ምቹነት ላይ ያለውን ደረጃ የምንመዝንባቸው የቴስት ዓይነቶች የምናቀርብ ይሆናል።

🌐 Civil Engg Free Tutorials👇 🌐 Linktr.ee/TsOnlineAcademy #civilengineering #tsonlineacademy #civilengineeringstudents

Alemayehu Ketema General Contractor Needed! General Structure Forman Full Time Yerer Ber LEKA Building , 4th floor , Human Resource Development & Adminsration Department Addis Ababa Project  February 17, 2025 - February 28, 2025  Job Requirement Qualifications : TVET/LEVEL (10+4)/(10+3) /(10+2) OR LEVEL IV/III/II in road construction or other relevant field of study. Total work experience (years):  10 Experience with similar works:  8 Qty: 2 Duty  Station: Different Projects
How to Apply
Date of Registration : 10 Consecutive working days from the first date of announcement. Note:- Interested applicants are invited to send their non-returnable application with CV and copies of relevant documents through the following Address Address: Alemayehu Ketema General Contractor Tel: +251 – 0116-47-77-95 Yerer Ber LEKA Building , 4th floor , Human Resource Development & Adminsration Department Incomplete application will not be considered.

Junior Engineer- Homa Construction Plc engineering Addis Ababa BSc Degree in Civil Engineering, COTM or in a related field of study Duties and Responsibilities: - Apply engineering knowledge in a vast array of projects, from the construction of infrastructure for transportation, housing projects, and luxury buildings, to the construction of natural sites. Quanitity Required: 2 Minimum Years Of Experience: 0 years Deadline: February 27, 2025
How To Apply:👇
Submit your non-returnable application and CV along with supporting documents in person to the office located at 22 Mazoria Yeka Sub-city Near to Nayal Insurance Head Office Telephone +251911936957

Site_Engineer_Hand_book_1737216513.pdf17.20 MB

As a site engineer, your role is critical in ensuring the successful execution of construction projects. Here are the key res
As a site engineer, your role is critical in ensuring the successful execution of construction projects. Here are the key responsibilities and important points to follow: General Responsibilities 1. Planning and Execution: • Understand project plans, specifications, and drawings. • Plan daily and weekly activities and allocate resources accordingly. 2. Site Supervision: • Monitor construction activities to ensure work aligns with drawings and specifications. • Ensure quality control at every stage of the project. 3. Coordination: • Liaise with architects, consultants, subcontractors, and suppliers. • Coordinate with the project manager for smooth progress. 4. Safety Compliance: • Ensure workers follow safety protocols and wear PPE (Personal Protective Equipment). • Identify and mitigate site hazards. 5. Material Management: • Monitor material usage and minimize wastage. • Ensure timely procurement and delivery of materials. 6. Documentation: • Maintain daily progress reports, site logs, and inspection records. • Record as-built drawings and changes made during execution. Important Points to Follow Before Starting Work 1. Site Preparation: • Conduct a site survey to understand existing conditions. • Clear site obstructions and ensure necessary utilities are available. 2. Review Plans: • Carefully review drawings and specifications. • Identify discrepancies or conflicts and raise RFIs (Request for Information). 3. Understand Project Scope: • Be familiar with the schedule, milestones, and deliverables. During Construction 1. Quality Control: • Conduct inspections for reinforcement, formwork, concrete pouring, and other key activities. • Follow approved methods and standards (e.g., ASTM, ACI, or BS standards). 2. Time Management: • Ensure activities are completed on time without compromising quality. • Track progress and address delays promptly. 3. Resource Management: • Ensure efficient use of manpower, machinery, and materials. 4. Communication: • Clearly communicate instructions to workers and subcontractors. • Address issues or conflicts immediately. 5. Monitoring: • Keep an eye on weather conditions that could affect construction. • Check for deviations from specifications or drawings. After Construction 1. Inspection and Handover: • Ensure all works are completed as per specifications. • Conduct final inspections with the client and consultants. 2. Documentation: • Prepare and submit handover documents (e.g., as-built drawings, test reports, warranties). • Document lessons learned for future projects. Additional Tips for Success 1. Stay Updated: • Stay informed about construction techniques, software, and materials. 2. Be Proactive: • Anticipate potential issues and address them early. 3. Focus on Safety: • Conduct regular safety meetings and toolbox talks. 4. Maintain Good Relations: • Build a positive relationship with workers, contractors, and stakeholders. ➡️To these principles, you can effectively manage site activities, ensure quality construction, and complete projects successfully.
Any comments? Or Questions? t.me/Consitesolutionbot 👌
➡️@Consite🏗💠 🤝🤝🤝🤝

ስለ አፈር ጥቅጠቃ ስራ /Soil Compaction/ በጥቂቱ🤚🚧 Soil Compaction: - በሜካኒካል መንገድ የአፈርን የመሸከም አቅምን የምንጨምርበት መንገድ ነው።
➡️እንዴት? 👇
አፈሩን ስንጠቀጥቅ የአፈር ፓርቲክሎች  ጥግግቶሽ ወይም ትፍፍግ/density/ እንዲጨምር እናደርጋለን።ይህም በአየርና ውሃ የተያዙ ቦታዎች /water and air voids/በአፈር እንዲተኩና እየዲቀንሱ ማድረግ ማለት ነው። ➡️ይህም በመሆኑ:- - የአፈሩን የመሸከም አቅም/Load bearing capacity of soil/ ከፍ እናደርጋለን። - በውስጡ የውሃ ማንሸራሸር አቅሙን/permeability/ እንቀንሳለን። - ስምጠት እንዳይኖር ያደርጋል/reduce future settlement/ - የደረቅ አፈር ከፍተኛ እፍግታ መጠን/Maximum dry density of soil/ - የደረቀ አፈር /ከድንግል መሬት/ ከፍተኛ እፍግታ መጠን/density/=1900kg/m3 ነው። - በሰው ሰራሽ ጥቅጠቃ/Artificial Compaction/ በላቦራቶሪ ሙከራ  የምናገኘው እፍግታ /Proctor density/ ደግሞ ቢያንስ 95% እንዲመጣ ይጠበቃል።ከ95% በታች ከመጣ ወዳቂ ሆኖ የጥቅጠቃ ስራው እንደገና መሰራት ይኖርበታል። 👆ማስታወሻ:- ደረቅ አፈር ስንል በማድረቂያ ማሽን/Oven/ ውስጥ የደረቀ ማለታችን ነው። ➡️የአፈር እፍግታ ማወቂያ መንገዶች/methods of testing soil density/ በዋናነት በሁለት ይመደባሉ:- 1). በሳይት ላይ የሚተገበሩ /Field test/: Sand cone test, Rubber balloon method, Nuclear density, Time domain reflectometry, Shelby tube/ባብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል/ናቸው። 2). በቤተ ሙከራ የሚተገበሩ/Laboratory tests/: Proctor test, Modified proctor test...  ለዛሬ በሳይት ላይ የአፈርን እፍግታ ስለምንፈትሽበት መንገድ እናያለን። 🚧Field density of soil/Cone test/Sand replacement test/:- - ተጠቅጥቆ የተጠናቀቀውን አፈር በሳይት ላይ እፍግታውን የምንፈትሽበት መንግድ ነው። የሚያስፈልጉ እቃዎች/Apparatuses/:- - የአሸዋ እቃ/ክብ ጀሪካን መሳይ/Sand pouring cylinder equipment/: ዲያሜትሩ 15cm ቀመቱና 45cm የሆነ ጃር - መቆፈሪያ፣ ማፅጃና ማስተካከያ እቃ/Tools for levelling and excavation/ - ማንኛውም ማጠራቀሚያ ሰሃን ወይም ሳጥን/Container/: - ንፁህ አሸዋ - ወንፊት - ሚዛን/Balance/ - ዳታ መመዝገቢያ ቅጽ የስራ ቅደም ተከተል/Procedure/:- 1ኛ.የአሸዋ ጃሩንና አፈር ለማውጫ የተዘጋጀውን ሰሃን ባዶውን መመዘንና መመዝገብ። 2ኛ. ጃሩን አሸዋ መሙላትና ከነአሸዋው መመዘንና በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ መሙላት። 3ኛ. በ15cm ዲያሜትርና በ20cm ጥልቀት የተጠቀጠቀውን ሙሊት አፈር በጥንቃቄ መቆፈርና ሳይባክን እያወጡ በተዘጋጀው ሰሃን ላይ በማድረግ መመዘንና መመዝገብ።
ማስታወሻ:-
የጉድጓዱን ልክ ለመወሰን በልክ የተዘጋጀ ፕሮፋይል ልንጠቀም እንችላለን። 4ኛ. የአሸዋ ጃሩን ከታች በምስል 1 ላይ በተቀመጠው መሰረት በማድረግ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ላይ በማድረግና መዝገያውን በመክፈት አሸዋው ጉድጓዱን እስኪሞላ ጠብቆ መዝጊያውን በመቆለፍ ጃሩን ማንሳትና ቀሪውን መመዘንና መመዝገብ። 5ኛ. አሸዋውን ደግሞ ለመጠቀም ካስፈለገ ከጉድጓዱ ጠርጎ ማውጣትና በወንፊት እየነፉ በስቀመጫው እቃ ማከማቸት።

Intercon Construction Chemicals 👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber ● Concrete Admixtures ● Bonding Agents ● Wat
Intercon Construction Chemicals       👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber ● Concrete Admixtures ● Bonding Agents ● Waterproofings ● Concrete Repair, Grouting    ● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers  ● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat ● Quartz, Contextra ● Floor hardener, Epoxy               ● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials Tel: 0961955555 or 0944774267 Address: Signal, around signal mall

#ADVERTISEMENT 🔧📐📐ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት 📐📐 መማምረቻ ድርጅት⚙🔧🛠 🛠🛠🛠የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🛠🛠🛠 1 መገለጫችን የሆነው የሞደፊክ ስራዎች 2 እዲሁም ፕሌት ከ 1
#ADVERTISEMENT 🔧📐📐ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት 📐📐                    መማምረቻ ድርጅት⚙🔧🛠 🛠🛠🛠የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🛠🛠🛠 1 መገለጫችን የሆነው የሞደፊክ ስራዎች 2 እዲሁም ፕሌት ከ 1ሚሊም እስከ 30 ሚሊም እንቆርጣለን እበሳለን 3 በመቀጠል ጄቦልት 12ሚ እስከ 32ድረስ ጥርስ አውጥተን አጥፈን እናቀርባለን 4 የተለያዩ ቦልቶች በፈለጉት መጥን                 መገኛችን ቁ1በእጆት ባለ ስልክ ለናተ ቅርብ ቁ2 በታታሪዎች መገኛ ኮርቻ ተራ ቁ3 አየር ጤና ኪዳን ምህረት ጊቢ ማንኛውም ልሜራ          እዛው በዘመናዊ ማሽን እቆርጣለን ቁ  4 ሴሚት ፍየል ቤት በቅርባ ባራቱም አቅጣጫ ማሳሰብያ ከጊዜው አንፃር የዋጋ ንረት ካሳሰቦት እኛጋ እሚገርም መፍትሄ አለ በማያስቡት መልክ ስራዎን ይሰራሉ ይደውሉ ስልክ ቁጥር 0912492727 0913061530 0923764834 መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ ፀግሽ    ፕሌት እና ጄቦልት!

#ADVERTISEMENT 🔧📐📐ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት 📐📐 መማምረቻ ድርጅት⚙🔧🛠 🛠🛠🛠የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🛠🛠🛠 1 መገለጫችን የሆነው የሞደፊክ ስራዎች 2 እዲሁም ፕሌት ከ 1
#ADVERTISEMENT 🔧📐📐ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት 📐📐                    መማምረቻ ድርጅት⚙🔧🛠 🛠🛠🛠የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🛠🛠🛠 1 መገለጫችን የሆነው የሞደፊክ ስራዎች 2 እዲሁም ፕሌት ከ 1ሚሊም እስከ 30 ሚሊም እንቆርጣለን እበሳለን 3 በመቀጠል ጄቦልት 12ሚ እስከ 32ድረስ ጥርስ አውጥተን አጥፈን እናቀርባለን 4 የተለያዩ ቦልቶች በፈለጉት መጥን                 መገኛችን ቁ1በእጆት ባለ ስልክ ለናተ ቅርብ ቁ2 በታታሪዎች መገኛ ኮርቻ ተራ ቁ3 አየር ጤና ኪዳን ምህረት ጊቢ ማንኛውም ልሜራ          እዛው በዘመናዊ ማሽን እቆርጣለን ቁ  4 ሴሚት ፍየል ቤት በቅርባ ባራቱም አቅጣጫ ማሳሰብያ ከጊዜው አንፃር የዋጋ ንረት ካሳሰቦት እኛጋ እሚገርም መፍትሄ አለ በማያስቡት መልክ ስራዎን ይሰራሉ ይደውሉ ስልክ ቁጥር 0912492727 0913061530 0923764834 መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ ፀግሽ    ፕሌት እና ጄቦልት!

በሥራ ላይ! መልካም ቀን!🤚
ቻናሉን አጋሩ!➡️Share ይደረግ!
➡️https://t.me/consite 🏗💠 🤝🤝🤝🤝

🔺ለዛሬ ከውል ማፈገጥን በተመለከተ እናያለን!👇 ከውል የማፈንገጥ ሂደት የሚያስከትላቸው ችግሮችና፣ የመፍትሄ ስርዓቶች/Damage, Breach of Contract and Remedies/?? 1.ከውል ማፈንደጥ ስንል ምን ማለት ነው? 🚧በመካከላቸው ህጋዊ የውል ስምምነት ካደረጉ ተዋዋይ አካላት መካከል አንደኛው ወገን በውሉ የተቀመጡ መሠረታዊ  ግዴታዎችን ሆነ ብሎ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያለምንም የህግ ድጋፍ ወይም ማብራሪያ በሌለው ምክንያት አለመፈጸም ወይም በውል በተቀመጡ የውል ሁኔታዎች መሠረት መስራት አለመቻልን ከውል ማፈንገጥ /breach of contract/ ይባላል፡፡ 🚧ይህ ከውል የማፈንገጥ ሁኔታ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖቸ መካከል ግጭት እንዲነሳ የሚያደርግ ነው፡፡እነዚህን ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሱ ግጭቶች በፍርድ ቤት የመፍታት ሂደት ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅና ጊዜ አባካኝ ከመሆኑም ባሻገር ጉዳዩ እስኪቋጭ አዕምሮን ዕረፍት ሊነሳ የሚችልና የሚያስጨንቅ ነው፡፡ 2.ከውል በማፈንገጥ የተጎጂው አማራጭ መብቶች 🚧በአንድ ተዋዋይ ወገን ከውል ማፈንገጥ ምክንያት ውል ያልተፈጸመለት ወገን ራሱን ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጭ መንገዶች ሊጠቀም ይችላል፡፡ (ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1771) -ለደረሰበት ጉዳት ተመጣጣኝ የጉዳት መቀጮ (ፍብሕቁ 1771(2) -ውል አስገድዶ ማስፈጸም (ፍብሕቁ 1771(1) -ውል እንዲፈርስለት መጠየቅ (ፍብሕቁ 1771(1) 3.የጉዳት መቀጮ (ፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጠር 2360) 🚧የጉዳት መቀጮ ተጎጂው በድርጊቱ የደረሰበትን የጥቅም መቅረት ወይም መቀነስ ለማመዛዘንና ለጉዳቱ መነሻ የሆነው ተግባር ባይፈጸም ኖሮ ተጎጂ ያገኝ የነበረውን ኢኮኖሚያዊ አቋም ለመጠበቅ በታቀደ ዓላማ የሚተገበር አሰራር ነው፡፡ከውል ማፍረስ ጋር ተያይዞ የሚታየው የጉዳት መቀጮ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ካለው ተነጻጻሪ ግዴታ አኳያ የአንደኛው ወገን ግዴታውን አለማክበር በሌላው ተዋዋይ ወገን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከሚያመጣው አሉታዊ ውጤት አንጻር ነው፡፡ይህ ከውል አፈንጋጩ ግዴታውን በተፈለገው ጊዜና በሚፈለገው አኳኆን አለመፈጸም ለተጎጂው ተመጣጣኝ የሆነ የጉዳት መቀጮ የመጠየቅ መብት ያስፈልገዋል፡፡ 🚧ምንጊዜም ቢሆን የተጎጂ ኪሳራ ውሉ በተፈለገው ጊዜና አኳኋን ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ተጎጂው ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅም የሚያሟላና የሚያካክስ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ከውል በማፈንገጥ ምክንንት የሚነሱ ግጭቶችን ለማርጋት የሚኬድባቸው የተለያዩ ዓይነት የመፍትሄ ስርዓቶች አሉ፡፡ ከውል በማፈንገጥ ምክንያት የሚነሳ ቅሬታ የህግ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ በህግ ኪሳራን የማስመለስ ሂደቱ ለሚደርሰው ጉዳት ካሳ የማስከፈል ሂደቱ ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጡ መንገዶች መሠረት ይሆናል፡፡                                                                         ⭐️እነዚህም ፡-  i. የተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራ መቀጮ/Compensatory Damages/ ➡️በተመጣጣኝ ካሳ የኪሳራን መቀጫ፣ ከውል ያፈነገጠው ወገን ለተጎጂው የሚከፍለው መቀጫ የደረሰው ኪሳራ መጠን ተለክቶ ለደረሰው ኪሳራው ልከኛ የሆነ ካሳ በመክፈል የሚደረግ የመቀጫ ዓይነት ነው፡፡ ➡️በዚህ ሂደት የሚደረግ የኪሳራ ወይም የጉዳት መቀጮ በተለካው ጉዳት ልክ ስለሚፈጸም ልከኛ መቀጮ/   actual damages/ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡ ii. በአስተማሪ የቅጣት ርምጃ የሚደረገረግ የጉዳት መቀጮ/Punitive Damages/