Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗
Відкрити в Telegram
Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service
Показати більше3 590
Підписники
Немає даних24 години
+37 днів
+4830 день
Архів дописів
ጊዜያዊ የረዥም ጊዜ (የኮንትራት) ቅጥር ማስታወቂያ
በዚህ ሊንክ ገብተው ይመዝገቡ
https://forms.gle/oqbteUcWuRneaMGE6
🔵እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Baga ayyaana Irreechaan isingahe!Baga Ayyaana Irreecha Hora Finfinnee Baara 2018 tiin Isin Gahe!🤚 Ayyaana gaarri~ መልካም በዓል! ዩኒቲ-ኮንስትራክሽን ካታሎግ🏗
🔵እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Baga ayyaana Irreechaan isingahe!Baga Ayyaana Irreecha Hora Finfinnee Baara 2018 tiin Isin Gahe!🤚 Ayyaana gaarri~ መልካም በዓል! መልካም በዓል! ዩኒቲ-ኮንስትራክሽን ካታሎግ🏗
👉 INTERCON Construction Chemicals
● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Wall Putty, Prime Coat
● Concrete Repair Mortar
● Floor hardener, Epoxy
● Grout, Self-level mortar
● Quartz paint, Contextra
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers
● Geotextiles and other construction chemicals and materials
Tel: 0961955555
Address 1: Signal road, around Dinberwa
Addres 2: Wellosefer, around Dani Plaza
🔷invitation for National Competitive Bid
Development Bank of Ethiopia!
👉የቅድመ ክፍያ እና በኮንትራክተሩ ሚሰጥ ማስያዥያ:-
💫ቅድመ ክፍያ ማለት ምን ማለት ነው?
-አንድ ተቋራጭ የግንባታ ሥራ ለማከናወን ዉል ከገባ በዉሉ ሰነድ ላይ በተቀመጠው መሰረት ቅድመ ክፍያ ይከፈለዋል ያው ወለድ የሌለው ብድር አሰሪው ለ ሥራ ተቋራጩ ይሰጠዋል ማለት ነው።
- ይህ ቅድመ ክፍያ የሚከፈለው ተቋራጩ ስራዉን ለመጀመር እንዲረዳው ነው።
- ስቶር ለመስራት ማሽነሪ እና የሰው ሃይል ሞቢላይዝ ለማድረግ ለግንባታ ስራ የሚረዱ አስፈላጊ የሆኑ ማቴርያል እንዲገዛ እና ወዘተ ለሆኑ እንቅስቃሴዎች ተቋራጩ ቅድመ ክፍያ ይከፈለዋል።
🏷በአብዛኛው የ ሃገራችን የዉል ሰነድ ላይ የምንመለከተው ቅድመ ክፍያ የዉሉን ዋጋ 20 ወይንም 30% ነው።
ለ ምሳሌ ፕሮጀክቱ 100,000,000 ከሆነ
እንዴት አሰሪው 20,000,000 ብር አምኖ ለተቋራጩ ዉል ስለገቡ ብቻ ይሰጠዋል።
እንግዲህ የኮንስትራክሽን ዉሎች መሰረት ተደርገው የሚዘጋጁት የሃገሪቱን ህግ መሰረት በማድረግ ነው የሃገሪቱ ህግ ደግሞ አለማችን ላይ በሰፊው ከምንጠቀመው የኮንስትራክሽን ህግ የወጣ ነው።
አንዳንዴ ቀጥታም ልንጠቀመው እንችላለን። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ scc & gcc የሚባሉ ህጎች ዉላችን ላይ አሉ።
- So ተቋራጩ ለሚወስደው ቅድመ ክፍያ እኩል የሆነ ማስያዥያ ለ አሰሪው ማቅረብ ይኖርበታል።
- FIDIC RED book 2017( GCC )የምንለው ከዚህ የተቀዳ ነው። በአንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ስለ ቅድመ ክፍያ ማስያዝያ እንዲህ ይላል።
- ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው የቅድመ ክፍያ በወሰደው መጠን ልክ ማስያዝያ ለ አሰሪው ማቅረብ ዪጠበቅበታል ኮፒ ደግሞ ለ እንጂነሩ/ ሳይተ ሱፐርቪሶሩ መስጠት ግዴታ አለበት
- ይህ የቅድመ ክፍያ ማስያዝያ የሚቀርበው ሃገር ውስጥ ህጋዊ ሰዉነት ካለው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን እና አሰሪው የተስማማበት መሆን ይጠበቅበታል። ይህ የፋይናንስ ተቋም ዋስትናውን የሚሰጠው የዉሉ ወይንም የጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ናሙና ቅጽ መሰረት ዪሆናል አንዳንዴም ባንኩ በራሱ ቅጽ አቅርቦ አሰሪው የተስማማበት ከሆነ its okay።
- ስራ ተቋራጩ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው ቅድመ ክፍያውን ከፍሎ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተቀባይነት እና ተፈፃሚ ያለው መሆኑን ያረጋግጣል ነገር ግን ያስያዘውን የገንዘብ መጠን ተቋራጩ በከፈለው መጠን ደረጃ በደረጃ ሊቀንስ ይችላል።
የከፈለው መጠን እና የሚቀረው መጠን በክፍያ የምስክር ወረቀት ላይ ይገለጻል።
- የቅድመ ክፍያ ዋስትናው የሚያበቃበት ጊዜ ተጠቅሶ ከሆነ እና ተቋራጩ የወሰደውን ቅድመ ክፍያ ዋስትናው ከመጠናቀቁ 28 ቀን በፊት አጠናቆ ሳይከፍል የሚቀር ከሆነ
1. ተቋራጩ ቅድመ ክፍያው እስኪከፈል ድረስ የዚህን ዋስትና ትክክለኛነት ያራዝማል ቀኑን ያራዝመዋል ማለት ነው።
2. ተቋራጩ ይህንን የማራዘምያ ማስረጃ ወዲያውኑ ለአሠሪው ያቀርባል ለኢንጅነሩ ወይንም ሱፐርቫይሰሩ ግልባጭ ይዞ
3. አሠሪው ይህንን ማስረጃ ዋስትና ከማለቁ ከ7 ቀናት በፊት ካልተቀበለ፣ አሠሪው ያልተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ መጠን በዋስትናው መሠረት የመጠየቅ መብት አለው።
- ተቋራጩ የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና በሚቀርብበት ጊዜ ማመልከቻ ወይንም በደብዳቤ መልክ ለወሰደው ቅድመ ክፍያ ማስያዣ እንዳቀረበ መግለጽ ይጠበቅበታል።
#ነዳጅ
ከዛሬ መስከረም 21 ቀን 2018 ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ፦
- የቤንዚን
- የነጭ ናፍጣ
- የኬሮሲን
- የቀላል ጥቁር ናፍጣ
- የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በመስከረም ወር ሲሸጥበት በነበረው እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።
የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ በሊትር 120 ብር ከ10 ሳንቲም እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራት ያላቸውን እና ለተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የቀይ ሸክላ ጡቦችን እናመርታለን።
🧱 ለሙሉ የቤት ግንባታ፣
🧱ለባንክ ቤት ካዝና፣
🧱 ለግቢ አጥር ማጠሪያ፣
🧱 ለመንገድ ዳር ጠርዞች፣
🧱 ለሆቴሎች፣ሬስቶራንት፣እና ካፌዎች ማሳመሪያ ፣
🧱 ለx-ray ክፍሎች፣
🧱 ለፍሳሽ ማንዋሎች፣
🧱 ለኪችን ሲንክ ማስቀመጫ ፣
🧱 ለሻወር ገንዳ ማሰቀመጫ፣
🧱 የPBC ፍሳሽ ማስወገጃ ለመሸፈን፣
🧱 ለአበባ መትከያ
🧱 ለብረት ማቅለጫ ፈርኒስ፣
🧱 ለፒዛ ኦቭን፣
🧱 ለምድጃ፣
🧱 ለቆሻሻ ማቃጠያ፣
NEW POINT BRICK FACTORY
*We produced best quality clay bricks for various construction purposes.
🧱 For building construction,
🧱 For bank vaults,
🧱 Fence for the yard,
🧱 For road edges,
🧱 For Hotels,Restaurants,and Cafes decoration,
🧱 For x-ray rooms,
🧱 For manuals,
🧱 For kitchen,
🧱 For shower tray
🧱 To cover PBC drains,
🧱 For garden,
🧱 Furnace For steel factory,
🧱 For pizza oven,
🧱 For waste incinerator, 🧱 For more information join our telegram channel 🧱Order now 📲0912854327,0902378888 🧱"Quality is our first priority 🧱Thank you 谢谢
🇱🇷✈️አሜሪካ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክትን እንደምትደግፍ በይፋ አስታወቀች።
የኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት ዘዴዎች እና መሣሪያዎች
የኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት፣ የአንድን ፕሮጀክት ዲዛይን እና ሃሳብ በመቅረጽ ሥራውን ከማስጀመር አንስቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያስፈልገውን ግብዓት፣ የሙያ ዕውቀት እና መሣሪያ የሚያካትት የሙያ ዘርፍ ነው፡፡
ይህንን በአግባቡ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚቻለው የሚከተሉትን አራት የተለያዩ ሂደቶችን በመከተል ነው እነርሱም፡-
መነሻ ሃሳብየዚሀ ሂደት ዋና ግብ የኘሮጀክቱን አስፈላጊነት እና አይነት ለይቶ ማስቀመጥ ነው፡፡
እቅድ መንደፍበኘሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎችን እያንዳንዱን የሚመለከታቸውን ክፍሎች ወይም ግለሰቦች ለይቶ ማስቀመጥን የሚመለከት ነው፡፡
መተግበር እና መቆጣጠርየኘሮጀክቱ ማኔጅመንት ኘሮጀክቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ሥራዉን በዕቅዱ መሠረት በተያዘለት በጀት በአግባቡ እየተጠቀመ መጓዙን የሚከታተልበት ሂደት ነው፡፡
ማጠናቀቅኘሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ ለሚፈለገው ወይም ለሚመለከተው አካል ማስረከብን የሚመለከት ሂደት ነው፡፡ እነዚህን አራት የተለያዩ ሂደቶችን መነሻ በማድረግ የኘሮጀክቱ ማኔጀር ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት ከሚያስችሉት አሠራሮች የሚከተሉት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ዕቅዱን /ኘላኑን/ በጥልቀት በመረዳት የአሠራር ሂደትን ማደራጀት በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በዚህም፣ የኘሮጀክቱን የክንውን ሂደት እና ዘርፎችን ማዘጋጀት አስፈላጊውን ቡድን ማዋቀር እና ቡድኑን መምራት የተመለከተ ይሆናል፡፡ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልገውን በጀት ዕቅዱን እና ክንውኑን ተከትሎ በአግባቡ ወጪ መሆኑን መከታተል ሌላኛው ሃሳብ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚተገበረው ኘሮጀክት በሽርክ እና ወይም በዋናነት በሚገነቡ እና በሥራው ከሚሳተፉ የባለድርሻ አካላት ጋር ውል መፈጸም እና የገቡትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣታቸውን መከታተል ናቸው፡፡
የኘሮጀክት ማናጀሩ ከላይ የተጠቀሱትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ከሚያስችሉት መሣሪያዎች ውስጥ፣ የሚፈልገውን የጽሑፍ መረጃ በፍጥነት የሚያገኝበትን የሶፍትዌር ኘሮግራም መጠቀም እና በየትም ቦታ ሆኖ የሥራውን ሂደት የሚከታተልበትን ዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም ይገባዋል፡፡
የኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት ዘዴዎች እና መሣሪያዎች
የኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት፣ የአንድን ፕሮጀክት ዲዛይን እና ሃሳብ በመቅረጽ ሥራውን ከማስጀመር አንስቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያስፈልገውን ግብዓት፣ የሙያ ዕውቀት እና መሣሪያ የሚያካትት የሙያ ዘርፍ ነው፡፡
ይህንን በአግባቡ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚቻለው የሚከተሉትን አራት የተለያዩ ሂደቶችን በመከተል ነው እነርሱም፡-
መነሻ ሃሳብየዚሀ ሂደት ዋና ግብ የኘሮጀክቱን አስፈላጊነት እና አይነት ለይቶ ማስቀመጥ ነው፡፡
እቅድ መንደፍበኘሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎችን እያንዳንዱን የሚመለከታቸውን ክፍሎች ወይም ግለሰቦች ለይቶ ማስቀመጥን የሚመለከት ነው፡፡
መተግበር እና መቆጣጠርየኘሮጀክቱ ማኔጅመንት ኘሮጀክቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ሥራዉን በዕቅዱ መሠረት በተያዘለት በጀት በአግባቡ እየተጠቀመ መጓዙን የሚከታተልበት ሂደት ነው፡፡
ማጠናቀቅኘሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ ለሚፈለገው ወይም ለሚመለከተው አካል ማስረከብን የሚመለከት ሂደት ነው፡፡ እነዚህን አራት የተለያዩ ሂደቶችን መነሻ በማድረግ የኘሮጀክቱ ማኔጀር ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት ከሚያስችሉት አሠራሮች የሚከተሉት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ዕቅዱን /ኘላኑን/ በጥልቀት በመረዳት የአሠራር ሂደትን ማደራጀት በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በዚህም፣ የኘሮጀክቱን የክንውን ሂደት እና ዘርፎችን ማዘጋጀት አስፈላጊውን ቡድን ማዋቀር እና ቡድኑን መምራት የተመለከተ ይሆናል፡፡ለኘሮጀክቱ የሚያስፈልገውን በጀት ዕቅዱን እና ክንውኑን ተከትሎ በአግባቡ ወጪ መሆኑን መከታተል ሌላኛው ሃሳብ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚተገበረው ኘሮጀክት በሽርክ እና ወይም በዋናነት በሚገነቡ እና በሥራው ከሚሳተፉ የባለድርሻ አካላት ጋር ውል መፈጸም እና የገቡትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣታቸውን መከታተል ናቸው፡፡
የኘሮጀክት ማናጀሩ ከላይ የተጠቀሱትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ከሚያስችሉት መሣሪያዎች ውስጥ፣ የሚፈልገውን የጽሑፍ መረጃ በፍጥነት የሚያገኝበትን የሶፍትዌር ኘሮግራም መጠቀም እና በየትም ቦታ ሆኖ የሥራውን ሂደት የሚከታተልበትን ዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም ይገባዋል፡፡▪️▫️▪️ ኢንፍራኮን ሚዲያን ፎሎው እና ሼር ያድርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ t.me/infraconmedia
♦️Construction Error ♦️
የግንባታ ስህተቶችን የማረሚያ ዘዴዎች
➖
በኮንትራክተሮች ወይም በዘርፉ ባለሙያዎች ያልተገነቡ ህንፃዎች ወይም መኖሪያዎች ጣሪያቸው ቢያፈስ ወይም ውሃ ሊያሰርግ እና ግርግዳው ቢሰነጠቅ ከሚገባው በላይ ሊያስጨንቅዎ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ የአለም መጨረሻን የማያስከትል፣ የሚታረም እና ሊያጋጥም የሚችል ክስተት በመሆኑ ነው፡፡
ዋናው ጉዳይ ችግሩ ቢከሰት በምን አይነት የአሠራር እና የህግ አግባብ ችግሩን መፍታት ይቻላል የሚለውን ማወቅ ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ይረዳሉ ከተባሉ ዘዴዎች ውስጥ ስህተቶችን ከስር ከስሩ መከታተል በቀዳሚነት ይቀመጣል።
የግንባታውን መዋቅር በዲዛይኑ መሠረት መገንባቱን፣ ለግንባታው የሚያስፈልገው ኮንክሪት ጥራቱን እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እየተዘጋጀ ሥራ ላይ መዋሉን፣ የጣራው ኮንክሪት ውኃ አለማስገባቱን፣ የውጭ ግድግዳዎች አለመሰንጠቃቸውን፣ የኤለክትሪክ መስመሮች በዲዛይኑ መሠረት መዘርጋታቸውን፣ ጥራቱን የጠበቀ የኤክትሪክ ገመድ መጠቀማቸውን፣ የበር እና የመስኮት፣ የአደጋ ጊዜ መጥሪያ ደውሎች በአግባቡ መሰቀላቸውን ከሥር ከሥሩ መከታተል ይገባል፡፡
ይህንን በአግባቡ ለመከታተል የሚችሉ ኢንስፔክተሮች ቀጥሮ ማሠራት፣ ልምድ እና ታማኝነትን በተላበሱ ባለሙያዎች ግንባታውን ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ ሌላው ችግሩን በህግ አግባብ ለመፍታት ከኮንትራክተሮቹ ጋር የሚደረግ የውል ሥምምነት በህግ ባለሙያ ድጋፍ መፈጸም በየጊዜው የሚታደስ የውል ሥምምነት መፈጸም /እንደ ሥራው ሂደት/ የኮንስትራክሽን የህግ ባለሙያዎችን ቀደም ብሎ ማማከር ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ የመጨረሻው መስፈርት ችግሩን ለመቅረፍ እና ለማስተካከል በሚሠራው ሥራ ላይ በቀላል ወጪ የዲዛይን ለውጥ ለማረም የሚረዱ የፈጠራ እና የግንባታ ባለሙያዎችን በሥራው ማሳተፍ ይገባል፡፡
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
