cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሱላማጢስ ማርያም

You tube ላይ ሙሉ vidio አለ subscribe በማድረግ ሰላም የተዋህዶ ልጆች ሱላማጢስ (የሰላም መገኛችን )ማርያም tube የንግስ መዝሙሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቤተሰብይሁኑአመሰግናለው

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
179
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Watch "ሰላምለኪ_እያለ_ ሰላም_ሰላም_ለኪ_ማርያም_ሰላምለኪ" on YouTube https://youtube.com/clip/UgkxFHjGRttdDvTle5WiuPKxwQlgCTUFDpft
Показати все...
✂️ ሰላም ሰላም ለኪ ♥♥♥ ሱላማጢስ ማርያም ልዩ የንግስ ዝማሬ subscribe like and share

60 seconds · Clipped by ሱላማጢስ ማርያም sulamaxis maryam · Original video "ሰላምለኪ_እያለ_ ሰላም_ሰላም_ለኪ_ማርያም_ሰላምለኪ" by ሱላማጢስ ማርያም sulamaxis maryam

​[ ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ] ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው። መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል። [አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ]
Показати все...
Watch "ሰላምለኪ_እያለ_ ሰላም_ሰላም_ለኪ_ማርያም_ሰላምለኪ" on YouTube https://youtube.com/clip/UgkxFHjGRttdDvTle5WiuPKxwQlgCTUFDpft
Показати все...

+ አይዞህ አልነካህም + ይህ የብዙዎቻችን የልጅነት ታሪክ ነው:: ጥፋት አጥፍተሃል:: ወላጆችህን በጣም የሚያስቆጣ ጥፋት ነው:: ወይ ውድ ዕቃ ሰብረሃል:: ወይ አንዳች በጣም የሚጠሉትን ነገር ሠርተሃል:: አለዚያም አድርግ ተብለህ ሳታደርገው የቀረኸው ነገር አለ:: ወላጆችህ ያጠፋኸውን ቢያውቁ ምን ሊያደርጉህ እንደሚችሉ እያሰብህ ተጨንቀሃል:: "አባዬ ዛሬ ገደለኝ" "እማዬ በጥርስዋ ነው የምትዘለዝለኝ" "ዛሬ መሞቴ ነው" እያልህ በፍርሃት ውስጥ ነህ:: ስለዚህ ተደብቀሃል:: መደበቅህን ሲያውቁ ወላጆችህ የሆነ ነገር ጠረጠሩ:: "ምን ሆነህ ነው አንተ?" "ምንም" "ታዲያ ምን ያርበተብትሃል" "ምንም" "ተናገር እንጂ" ራስህን ወዘወዝህ እንጂ አልተናገርክም:: አባት ቀረብ ይልና "አይዞህ የኔ ልጅ ምንም አልልህም አልገርፍህም ንገረኝ" እያለ ማባበል ይጀምራል:: ይሄን ጊዜ ለመናገር እያመነታህ ትቁለጨለጫለህ:: አባትም ነገሩ ይገባውና :- "እኔ እኮ እውነት እንድትነግረኝ ብቻ ነው የምፈልገው:: ሐቁን ከነገርከኝ አልነካህም:: እኔ የማልወደው ውሸት ብቻ ነው" ይልሃል:: ይሄን ጊዜ እየተቅለሰለስክ በሹክሹክታ ጥፋትህን ትናዘዛለህ:: "አያትህ የሠጡህን የሸክላ ጌጥ እኮ ሰበርኩት" "ለትምህርት ቤት ክፈል ብለህ የሠጠኸኝን ብር ጣልኩት" ወዘተ ብለህ ትዘረግፈዋለህ:: ተናግረህ ስትጨርስና ፊትህ ላይ የመብረቅ ድምፅ ስትሰማ እኩል ይሆናል:: የአባትህ ጥፊ ነው:: "ሥራህን አውቀህ ነዋ የተደበቅከው!? ኸከከከከ" ሌላ ቀን ከተገረፍከው የላቀ ግርፊያ ይወርድብሃል:: "አይዞህ ያጠፋኸውን ንገረኝ አልነካህም" የሚል ቃል ዋጋ እንደሌለው ትረዳለህ:: ያጠፋኸውን ንገረኝ ብሎ ስትናዘዝ የሚምርህ አባት እግዚአብሔር ብቻ ነው:: "በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው" 1 ዮሐ. 1:9 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 15 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29) ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Показати все...
Henok Haile

Henok Haile, Addis Ababa, Ethiopia. 229,385 likes · 36,318 talking about this. Henok Haile ሄኖክ ኃይሌ

Показати все...

❤ ፍቅር ይዞኛል ለምትሉ ሁሉ ❤ .......................................................... አንተ ፍቅር ይዞኛል የምትለው፤ አዎ አንተ በፍቅሯ አብጃለው፣ ስነሳም ስተኛም ስለእርሷ ነው የማስበው የምትለው! በዓይኗ ሰረቅ አድርጋ ድንገት ስታየኝ ልቤ ቀጥ ይልብኛል የምትለው፤ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አያድርገውና በመጀመሪያ ያየሃት ቀን ያፈዘዘህ ዓይኗ ቢፈስ፣ ቀልብህን ስቦ ያስደነገጠክ መልኳ ቢጠቁር እና ቢጠፋ፣ እስከ ወገቧ የረዘመው ፀጉሯ ቢቆረጥ፣ አቅርበሃት ጓደኛህ ካደረካት በኋላ የወደድክላት ፀባዩዋ እና ሥርዓቷ ተለውጦ ክፉ እና ደረቅ ብትሆንብህ፣ አንጀትህን ያርሰው የነበረው አረማመዷና ቅልጥፍናዋ በበሽታ ተቀምቶ አልጋ ላይ ሆና ብታቃስት አሁንም ከእርሷ ጋር ትሆናለህ? እንደ ድሮ ከእርሷ ጋር ለመሆን ትሽቀዳደማለህ? ሁሌ እንደምታፈቅራትና እንደምትሳሳላት መንገርህን ትቀጥላለህ? ለእርሷ የምታሳየው ትህትናና ክብር ይቀንስብሃል? አንቺስ ብትሆኚ? መጀመሪያ ያየሽው ዕለት ደስ ያለሽ መልኩና ቁመናው እንዳልነበረ ቢሆን፣ ሁሌ አንቺን ለማስደሰት ብሎ አንቺን በመጋበዝ እና በማዝናናት ያጠፋው የነበረው ገንዘብና ሀብት ጠፍቶ ፍጹም ደሃ ቢሆን፣ መጀመሪያ የተዋወቃችሁ ሰሞን ሲያሳይሽ የነበረው ፍጹም ትህትና እና አክብሮት ተለውጦ በትዕቢት አንቺን መማታት ቢጀምር፣ ጤንነቱን አጥቶ በበሽታ ቢንከራተት፣ በመጀመሪያ ወደ እርሱ ስቦ ያመጣሽ ነገሮቹ ሁሉ ቢጠፉ አሁንም ከእርሱ ጋር ትሆኚያለሽ? አሁንም እርሱ ጋር ስልክ መደወልሽን ትቀጥያለሽ? እህቴ ሆይ እስቲ ንገሪኝ፤ ፍቅርሽ ከአፍሽ ነው ወይስ ከልብሽ? ወንድሜ ሆይ ልጠይቅህ፤ ፍቅርህ በመናገር ነው ወይስ በተግባር? መልሳችሁ " ይህ ቢፈጠር አብሬ አልቀጥልም" ከሆነ ከመጀመሪያውም ፍቅር እንዳልያዛችሁ ላርዳችሁ እወዳለሁ፡፡ ስትተያዩ እወድሃለሁ፣ እወድሻለሁ ከምትባባሉ ባየሁሽ/ ባየሁህ ቁጥር በውስጤ ያሉት ንጥረ ነገሮች (hormones) ይንተከተካሉ ብትባባሉ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ትርጉም ይህ አይደለምና፡፡ ፍቅርማ ምን እንደሆነ ራሱ ፍቅር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገባ አስተምሮናል፡፡ እርሱ ከምድር አፈር ካበጃጀን በኋላ የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ ካለብን በኋላ ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ያኔ አምሮብን፣ ተከብረን ሳለ ወዶናል፡፡ እፀ በለስን በልተን ያበራ የነበረው የጸጋ ልብሳችን ተገፎ ራቁታችንን ስንሆን፣ ደዌ የማያውቀው ሥጋችን በከንቱ ፍትወታት ሲታመምም በፍጹም ፍቅሩ አፍቅሮናል፡፡ ይተወንም ዘንድ ስላልቻለ ፍቅርን ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ስለእኛ እስከ ሞት አደረሰው፡፡ ታመን በኃጢአት አልጋ ተኝተን ሳለ ከጎናችን ሳይለይ ያሳታመመን አምላካችን ነው፡፡ እስከመጨረሻው ድረስ በኃጢአት የከረፋነውን ሳይጸየፈን ተጠግቶን ቁስላችንን በቁስሉ ያከመን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሊያክመን መጥቶ እንኳን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ቁስላችንን ሳይጸየፍ የቀረበንን ፈጣሪያችንን መታነው፡፡ ኑ ላድናችሁ ሲለን በመስቀል ላይ ሰቀልነው፡፡ ሐኪሙን የሚሳደብና የሚማታ በሽተኛ እንደምን ያለ ነው? የበሽተኛውን ስድብ እና ድብደባ ታግሶስ በትጋት የሚያክም ሐኪም እንደምን ያለ ነው? ለዚህስ አንክሮ ይገባል!! ወዳጄ ሆይ ፍቅር በደስታ ጊዜ ኖሮ በኃዘን ጊዜ የሚጸና፣ በጤናው ጊዜ አብቦ በደዌ ጊዜ የሚፈካ፣ በሰላም ጊዜ ተኮትኩቶ በጭንቅ ጊዜ የሚበቅል ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ታድያ ወዳጄ ሆይ በፍቅርሽ ተይዣለሁ ያልካት ሚስትህን ያማረው መልኳ በድንገት ቢጠፋስ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ እንዴት እወዳታለሁ ልትል ትችላለህ? ጤናዋን አጥታ አልጋ ላይ ብትተኛ ጥለሃት ለመሄድ የምታስብ ከሆነ እንዴት እወድሻለሁ ልትላት ትችላለህ? አንቺስ ብትሆኚ፤ ፀባዩ እንዳለ ተለውጦ ቢንቅሽና ቢያቃልልሽ ትተሽው ለመሄድ የምታስቢ ከሆነ እንዴት ዓይኑን እያየሽ እወድሃለሁ ትይዋለሽ? ቢመታሽም እንኳን እንደ አምላክ ምቱን ታግሰሽ እርሱን ለማከም ካልፈቀድሽ እንዴት አፈቅርሃለሁ ትይዋለሽ? " ፍቅር ያስታግሳልና"(1ኛ ቆሮ 13÷4) የማትታገሱ ከሆነ እንዴት ፍቅር ይዞኛል ትላላችሁ? አምላክ ያሳየንን ፍቅር ለሌሎች በመስጠት ክርስቶስን ልንመስለው ይገባናል፡፡ እህቴ ሆይ ወዳጅሽ በክፉ ሱስ ተጠምዶ፣ በትዕቢትና በንቀት ልቡ ተነድፎ ገብቶ ቢያንቋሽሽሽ ለእርሱ የምትሰጪው ፍቅር እንዲጎድል አትፍቀጂ፡፡ የፈለገ ተለውጦ የማታውቂው ሰው ቢሆንብሽም ለእርሱ የምትሰጪውን እንክብካቤ በትጋት ፈጽሚ፡፡ ያለንግግር ፍቅርሽን የሚነግሩትን ዓይኖችሽን ከዓይኖቹ አታንሺ፡፡ ወንድሜ ሆይ የሚስትህን የምትወድላት ፀባዩዋን ረስታ ደረቅና የምታውክ ብትሆንብህ እንኳን በስስት የምታያትን የፍቅር መመልከት አትንፈጋት፡፡ አምላክስ በሕመማችን ጊዜ ዓይኑን ከእኛ ድንገት ቢያነሳ ኑሮ ወድቀን እንደምንቀር ሁሉ አንተም ዓይንህን ከሚስትህ ላይ አታንሳ፡፡ ጌታ በፍጹም ፍቅር ወዶናልና እርስ በርሳችሁ በሚያስታግሰው እውነተኛው ፍቅር ተዋደዱ፡፡ በፍቅርም ቃል ተነጋገሩ እንጂ አትቆጡ፡፡ ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ የአፍ ብቻ ሳይሆን የልቡና፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የምንገልጠው እውነተኛውን ፍቅር ስጠን፡፡ ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ ግንቦት/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ https://t.me/dnJohannes
Показати все...
የዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ መጣጥፎች

ይህ ቻናል የተለያዩ የድምጽና የጽሑፍ ትምህርቶች ይተላለፉበት ዘንድ በባለቤቱ የተከፈተ ቻናል ነው።

አረሳሽም አልከዳሽም ዝማሬሽን አላቆምም በልቤ ሰሌዳ በንፅህና በንፅህና ተፅፈሻልና |2| ስለሚገባቸው ለቅኖች ምስጋና ብፅዕት ቅድስት መባል ይገባሻልና የአባ ሕርያቆስ ጥዑመ ቅዳሴ በልቤ ተፅፏል የኤፍሬም ውዳሴ |2| አዝ...... ማርያም ማርያም ስልሽ የአዩኝ በትዝብት ለጨለመባቸው ቢሆንም ግርምት አይጠፋኝም ላፍታ ድንግል ሆይ መልክሽ እንባዬ ይፈሳል ዝወትር ሳስብሽ |2| አዝ...... ሰላም እልሻለሁ በገብርኤል ሰላምታ ይወገድ በምልጃሽ የአፌ ዝምታ አሸበሽባለው እጆቼን ዘርግቼ እንደቀደሙት ልክ እንደ አባቶቼ |2| አዝ...... ሰላም እልሻለሁ በገብርኤል ሰላምታ ይወገድ በምልጃሽ የአፌ ዝምታ አሸበሽባለው እጆቼን ዘርግቼ እንደቀደሙት ልክ እንደ አባቶቼ |2|
Показати все...
አረሳሽም አልከዳሽም.mp36.73 MB
መ. የቅዱስ ያሬድ ዜማ ጥቅም ሀ. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በመጠበቅ፤ በየትኛውም አካባቢ የምትኖር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መዝሙር፣ አንድ ዓይነት ቅዳሴ፣ አንድ ዓይነት ማኅሌት፣ አንድ ዐይነት ሥርዐት በአንድ ዓይነት ጊዜ በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፡፡ ለ. በነገረ መለኮት ትምህርት፤ ሊቁ የትርጓሜ መምህር ስለሆነ ከብዙ መጻሕፍት ስለሚጠቅስና የሃይማኖት ትምህርቱትንም በዜማ አቀነባብሮ መድረሱ በጣም ተወዳጅ ትምህርት እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ሐ. በሥርዓተ ጸሎት፤ ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወኑ (የዘመናትና የሳምንታትን ጨምሮ) ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው፡፡ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ፍትሐቱ፣ ጥምቀተ ክርስትናው ሁሉ በዜማው መሪነት የሚከናወኑ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ መ. ለቱሪዝም ሀብት (መስህብነት)፤ ክርስቲያናችን በየወሩና በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው:: •✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥• ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቢራ ወይስ ሰማዕት? የቅዱሳን ስዕል አድህኖ በክብር መቀመጥ ሲገባው የቅዱስ ገዮርጊስ ስዕል ግን 1/ በየጠርሙሱ ተለጥፎ የሰካራም እጅ ያለ ንጽህና በድፍረት ይጨብጠዋል። 2/ ስዕል አድህኖው በየመጠጥ ቤቱ እየወደቀ ይረገጣል። ከቆሻሻ ጋር ተጠርጎ ይጣላል። 3/ በስሙ ታቦት መቀረጽ ሲገባው የሚያሰክር መጠጥ ሆኖ ስሙን ለማርከስ ተሰርቷል 4/ ኢትዮጵያ ከሰማዕቱ የምታገኘውን ክብርና ጥበቃ ለማሳጣት በ1915 ዓ.ም ጣሊያኖች አቅድው አቋቋሙት። የሚገርመው መጠጡን የሚጠጣው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዩ ነው። አንዳዴ እንደቀላል የምናያቸው ነገሮች ከፍተኛ የሆነ ጥፋቶች ናቸውና እንንቃ። ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!
Показати все...
+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! + እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡ ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ ‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6 ‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10 ‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7 እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡ ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡ ‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12 ‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5 ‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31 የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24 አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ] ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18 ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡ የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡ ’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጋቢት 18 2012 ዓ ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፎቶ :- CMC ሚካኤል ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4 Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Показати все...
Henok Haile

Henok Haile, Addis Ababa, Ethiopia. 227,791 likes · 37,084 talking about this. Henok Haile ሄኖክ ኃይሌ

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.