cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

Більше
Рекламні дописи
1 458
Підписники
-124 години
-17 днів
-2930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ክርስትያን ወገኖቼ ሆይ ከእሳት መዳን ከፈለጋችሁ እሥልምናን ተቀበሉ። ወላሂ ሙሥሊም ሆኖ የሞተ ሰው እንጂ ገነትን አይገባም። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተረከው "ነቢዩ(ﷺ)እንዲህ ብሏል "እነሆ  ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም"። (ሰሒህ ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212) ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/wada_islam
Показати все...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

Фото недоступнеДивитись в Telegram
وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا [ ሱርቱ መርየም፣ - 95 ] ሁሉም በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነው ወደርሱ መጪዎች ናቸው፡፡ ወዳጄ በዚህች አለም ብዙዎች ልወዱህም ልጠሉህም ሊያሞግሱህም ሊተቹህም ይችላሉ! ብዙ ተከታይ ብዙ አድናቂ ሊኖርህ ይችላል የቅርድም የሩቅም ዘመድ ልጅና ሚስት በጣም የተዋቡ ቤትና መኪናም ሊኖርህ ይችላል ግና ምን ዋጋ አለው? ያቺ መራራ ሞት የመጣች ጊዜ ተከታዮችህም ወዳጆችህም የቅርብም ሆነ የሩቅ ዘመዶችህ የምትወዳቸው ወላጆችህና ልጆችህ ሚስህም ከአንተ ይነጠላሉ ጌታ አሏህ በከበረው ቃሉ እንዳለው ብቻህን ሆነህ ጌታህን ትገናኘዋለህ! ታዲያ ለዚያች ብቻህን ሆነህ ጌታህን ለምትገናኝባት ቀን መልካም ሰርተህ ከሆነ ምን የምያምር መገናኘት ነው? ከዚህ ውጭማ ከሆነ ምን የሚያስጠላ መገናኘት ነው? አላህ በእዝነቱ መልካም ሰርተን እርሱን የምንገናኝ ያድርገን አሚን ያረብ🤲 وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ اللَّهُ ۗ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ [ አል-በቀራህ - 197 ] ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا (ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 110) «የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ ✍ሙከሚል https://t.me/mukamil12
Показати все...
👍 2
ውይይት በጨዋ ደንብ🙂 ነቢዩ ሙሐመድን እንዴት አምነህ ተቀበልካቸው? 🎙 Nahom 🎙ሙከሚል 📲https://t.me/mukamil12
Показати все...
record.ogg19.65 MB
record.ogg21.59 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ይህን ምስል ከዛሬ አንድ አመት በፊት ሼር ሳደርገው ብዙዎቻችሁ ይህማ እብድ ነው ብላችሁ ነበር አይደል? በሚያሳዝን መልኩ ግን በክርስትና በባዶ እግር ራቁቱን መራመድ እንደ ተአምር ነው የሚቆጠረው😅 :-ማስረጃ ከፈለጋችሁ እነሆበዚያ ዓመት እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፦ ሂድ፥ ማቅህን ከወገብህ አውጣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፥ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ።”   — ኢሳይያስ 20፥2 “እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥”   — ኢሳይያስ 20፥3 ባልጠፋ ተአምር እንደ እብድ ለሦስት አመት ሙሉ ራቁቱን ሲንከባለል አስባችሁታል?🙊 ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/mukamil12
Показати все...
👍 2 2
“በከንቱ የሚመኩ በዓይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ "ክፉ "አድራጊዎችን" ሁሉ "ጠላህ"።”   — መዝሙር 5፥5 እግዚአብሔር "ሐጢያትን" እንጂ "ሐጢያተኛን" አይጠላም የሚለውን የክርስትያኖችን ስብከት ራቁቱን የሚያስቀራ ጥቅስ!😌 ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/wada_islam
Показати все...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

👍 3
የእየሱስ ፍጡርነት በቁርኣን እና በባይብል [],አቅራቢ 🎙በወንድም ሙከሚል
Показати все...
record.ogg11.41 MB
ነገረ ክርስቶስ ክፍል 4 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው። በባለፈው ቅኝታችን ፈጣሪ የኢየሱስን ሥጋ ፈጥሮ ከዛም ለፈጠረው ሥጋ ሕይወት እንደሰጠው አይተን የኢየሱስን "ፍጡርነት" አረጋግጠናል። ኢየሱስን ፈጣሪ ያለ አባት "ኹን" በሚለው ቃሉ ከማርያም ማህጸን "ከፈጠረው" በኋላ ኢየሱስ እንደ ማነኛውም ሰው "ተገርዟል"። “ሊገርዙት" ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።”   — ሉቃስ 2፥21 ኢየሱስ ከተገረዘም ቦኋላ እንደ ማነኛውም ሰው በሰው እና "በፈጣሪ" ፊት በጥበብ በቁመትና በሞገስ "አደገ"። “ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።”   — ሉቃስ 2፥52 ኢየሱስ እንደ ማነኛውም ሰው በፈጣሪ እና በሰው ፊት ፈጣሪ ያሳድግህ እየተባለ በሚያድግበት ጊዜ እንደ ማነኛውም ሰው መንገድ ሲሄድ አምልጦ "ሲጠፋ" እናቱ ማርያም እና ዮሴፍ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥተው "ያፈላልጉት" ነበር። “ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።”   — ሉቃስ 2፥43 “ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤”   — ሉቃስ 2፥44 “ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።”   — ሉቃስ 2፥45 “ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤”   — ሉቃስ 2፥46 “ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።”   — ሉቃስ 2፥48 [ ]ሦስት የህሊና ጥያቄዎች []¹ እንደ ክርስትያኖች አባባል ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ብለው ያምናሉ። እስቲ አስታውሉ ይህን ግዙፍ ፍጥረት የፈጠረውን ፈጣሪ ራሱ የፈጠራቸው ሰዎች ሸለፈቱን ሲቆርጡለት(ሲገርዙት?) []²  ልብ በሉ እስቲ እንደ ክርስትያኖች አባባል ኢየሱስ ፈጣሪ ነው አስቡት እስቲ ፈጣሪ በሰው እና በፈጣሪ ፊት በቁመት በጥበብና በሞገስ ሲያድግ? ኢየሱስ ፈጣሪ ከሆነ ታዲያ ኢየሱስ በየትኛው ፈጣሪ ፊት ነበር ሲያድግ የነበረው? ስንት ፈጣሪ ነው ያለው? []³ አሁንም ልብ በሉ እስቲ ይህን ግዙፍ ፍጥረት የፈጠረው ፈጣሪ መንገድ ሲሄድ ጠፍቶ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቶ ሲያፈላልጉት? ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ https://t.me/wada_islam
Показати все...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

3👍 1
የነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ነቢይነት! ክፍል 5 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው። لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ {📗57:25} ወዳጄ ሁሌም እንደምለው አሁንም ላስታውስህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ነቢይነት ለማጥናት ከፈለክ በመጀመሪያ እነዚያ በነቢዩ ጥላቻ የተሙሉ ሰባኪዎችህ ያጠለቁልህን የውሸት ካባ አውልቅህ በመጣል ረጋ ሰከን ባለ መንፈስ ለመረዳት ጥረት አድርግ። ከዚህ በፊት ባሳለፍናቸው ክፍሎች አሳማኝ በሆኑ ማስረጃዎች የነቢዩ ሙሐመድን እውነተኛ ነቢይነት አይተናል። አንድ ነቢዩ እውነተኛ ነቢዩ መሆኑ ከሚታወቅባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ ተአምር መስራት እንደሆነ የሁሉም እምነት ተከታዮች በሚባል መልኩ ይስማማሉ። ታዲያ ነቢዩ ሙሐመድም እውነተኛ ነቢይ እንደመሆናቸው መጠን የተሰጣቸው ታላላቅ ተአምራት አሉ ከእነዚያ ተአምራት ውስጥ ለምሳሌ ያህል ቁርአን እንዲሁም የጨረቃን መሰንጠቅ አይተን ነበር። ዛሬም የምንመለከተው ለነቢዩ ሙሐመድ ከተሰጣቸው ታላላቅ ተአምራት ውስጥ ሦስተኛውን ተአምር ነው። አምላካችን አሏህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ለነቢይነታቸው ማስረጃነት ከሰጣቸው ተአምራት ውስጥ አንዱ ነቢዩ ከእጃቸው ውሃን ማፍለቃቸው ነው። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ عَطِشَ النَّاسُ يَوْمَ الْحُدَيْبِيَةِ، وَالنَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم بَيْنَ يَدَيْهِ رَكْوَةٌ فَتَوَضَّأَ فَجَهَشَ النَّاسُ نَحْوَهُ، فَقَالَ ‏مَا لَكُمْ ‏" قَالُوا لَيْسَ عِنْدَنَا مَاءٌ نَتَوَضَّأُ وَلاَ نَشْرَبُ إِلاَّ مَا بَيْنَ يَدَيْكَ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي الرَّكْوَةِ فَجَعَلَ الْمَاءُ يَثُورُ بَيْنَ أَصَابِعِهِ كَأَمْثَالِ الْعُيُونِ، فَشَرِبْنَا وَتَوَضَّأْنَا‌‏ قُلْتُ كَمْ كُنْتُمْ قَالَ لَوْ كُنَّا مِائَةَ أَلْفٍ لَكَفَانَا، كُنَّا خَمْسَ عَشْرَةَ مِائَةً‌‏ ጃቢር ኢብኑ አብድሏህ{ ረ•ዐ} እንደተረከው በሑደይቢያ ዘመቻ ጊዜ ሰዎች በውሃ ተጠምተው ነቢዩ በእጃቸው ላይ በነበረ ውሃ ዉዱዕ እያደረጉ አይተው ወደ እርሳቸው ተቿከሉ ነቢዩም ምን አላችሁ? አሉ ሰዎቹም ከፊትህ ካለው ውሃ ውጭ የምንጠጣውም ሆነ ውዱዓ የምናደርግበት ውሃ የለም አሉ። እርሳቸውም ከመታጠቢያው ቀድተን ጠጥተን ውዱዕ እስከምናደርግ ድረስ ከእጃቸው እንደ አይኖች ውሃ ፈለቀ። ከነቢዩ እጅ በፈለቀው ውሃ የታጠባችሁትና የጠጣችሁት ስንት ነበራችሁ ብየ ስጠይቀው መቶ ሺህ ብንሆን እንኳን ይበቃን ነበር። ያኔ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበርን። {📚ቦኻሪ መጽሐፍ,61 ሐዲስ 8] ، عَنْ قَتَادَةَ، عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ أُتِيَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم بِإِنَاءٍ وَهْوَ بِالزَّوْرَاءِ، فَوَضَعَ يَدَهُ فِي الإِنَاءِ، فَجَعَلَ الْمَاءُ يَنْبُعُ مِنْ بَيْنِ أَصَابِعِهِ، فَتَوَضَّأَ الْقَوْمُ‏.‏ قَالَ قَتَادَةُ قُلْتُ لأَنَسٍ كَمْ كُنْتُمْ قَالَ ثَلاَثَمِائَةٍ، أَوْ زُهَاءَ ثَلاَثِمِائَةٍ‏.‏ ቀታዳ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው ለነቢዩ(ﷺ) የውሃ እቃ መጣላቸው ነቢዩም እጃቸውን በእቃው ላይ ጫኑት ያኔም ከጣታቸው መሃል ውሃ ፍለቅ ሰዎችም በዚያ ውሃ ውዱዕ አደረጉ። ቀዳታ አነስን እንዲህ ብየ ጠየኩት ያኔ ከነቢዩ እጅ በፈለቀው ውሃ ውዱዕ ስታደርጉ ስንት ሰው ነበራችሁ? አልኩት እርሱም ሦስት መቶ ነበርን አለኝ። {📚ቦኻሪ መጽሐፍ 61, ሐዲስ 81} ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለክ ከታች ያሉትን ሐዲሳት ተመልከት። [📗Sahih al-Bukhari, 3572] [📗Sahih al-Bukhari, 3573] [📗Sahih al-Bukhari, 3574] [📗Sahih al-Bukhari, 3575] [📗Sahih Muslim, 2279] [📗Sunan an-Nasa'i, 76] [📗Muwatta malik Book 2, Hadith 33] [📗Jamiat Tirmidhi Book 49, Hadith 27] :-ይህን የነቢዩ ሙሐመድን አስደናቂ ተአምር ማንም ሊያስተባብለው የማይችለው በዛን ጊዜ የነበሩ ከሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በሥጋ ዓይናቸው የተመለከቱት እውነተኛ የነቢዩ ሙሐመድ(ﷺ) ተአምር ነው። ይህም የሚያሳየው የነቢዩ ሙሐመድን እውነተኛ ነቢይነት ነው። እናንተ የውሸት ሰባኪዎች እንደምትሉት ነቢዩ ሙሐመድ ሐሰተኛ ነቢይ ቢሆኑ ኖሮ እንደዚህ ያለን አስደናቂ ተአምር መስራት ይችል ነበር? መልሱን ለራስህ። وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا ۚ قُلْ كَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ  [ 📗ሱረቱ አል- ረዕድ፥ - 43 ] እነዚያም የካዱት ሰዎች «መልክተኛ አይደለህም» ይላሉ፡፡ «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ በላቸው። ✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/wada_islam
Показати все...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

👍 7 2
:-አምላኬ ሞተልኝ ብየ በዓሉን የማከብርለት አምላክ ስለሌለኝ አልሐምዱሊላህ። :-እኔ የማመልከው አምላክ የማይተኛ የማያንቀላፋ ነው። [📗 2:255] የማይደክም ነው። [2:129] የማይራብ የማይጠማ ነው። (📗6:14 ) {📗22:37} {📗51:57} የማይሞት ሕያው አምላክ ነው። {📗2:255} {📗3:2} {📗25:58} وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ  :-በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ [25:58] አልሐምዱሊላህ! ዓላ ኒዕመተል ኢሥላም😊 ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/wada_islam
Показати все...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

👍 15 1
ነገር ክርስቶስ ክፍል 3 ባለፈው ቅኝታችን ጠቅለል ባለ መልኩ ኢየሱስን ፈጣሪ ያለ ወንድ ጣልቃ ገብነት ከሴት ብቻ እንደፈጠረው አይተን እንደነበረ ታስታውሳላችሁ ዛሬ ደግሞ ዝርዝር ውስጥ ገብተን የኢየሱስን ፍጡርነት እንቃኝ። “ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤”   — ዕብራውያን 10፥5 በዚህ አንቀጽ ላይ እንደምንመለከተው ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ስገባ ሥጋን አዘጋጀህልኝ ብሎ እንደተናገር ልብ በል! ሥጋን አዘጋጀህልኝ ሲል ሥጋን ፈጠርከልኝ እያለ እንደሆነ ልብ ይላል! ምክንያቱም በባይብል አዘጋጅ የሚለው ቃል ፈጠረ በሚል ተለዋዋጭ ሆኖ ይመጣል! “ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።”   — መዝሙር 74፥16 ፈጣሪ በዘፍጥረት 1:14 እና በዘፍጥረት 1:16 እንዲሁም በመዝሙር 136:7 ላይ  ፀሓይንና ጨረቃን ፈጥሮ እያለ አዘጋጅ በሚል የተቀመጠው አዘጋጅ የሚለውን ቃል ፈጠረ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ እንደሆነ ልብ ይላል! ታዲያ የኢየሱስ ሥጋው ፍጡር መሆኑን ከተመለከተን ሥጋ ብቻውን ግዑዝ ነገር እንጂ ሕያው አይደለምና የግድ ሕይወት ያስፈልገዋል ስለዚህም ነው ኢየሱስም ሕይወት የተቀበለው። “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”   — ዮሐንስ 5፥26 ኢየሱስ ከፈጣሪ ሕይወትን ሳይቀበል በፊት ምን ነበረ? ግልጽ ነው ግዑዝ ሥጋ ብቻ ነበር ለዛውም ነው እንደ ማነኛውም ሰው ከፈጣሪ ዘንድ ሕይወት ተቀብሎ ሕያው የሆነው። ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ለምትሉ በሙሉ ግልጽ ጥያቄ! :-አንደኛ ለኢየሱስ ሥጋን የፈጠረለት ፈጣሪ ማን ነው? ኢየሱስ ራሱ ፈጣሪ ከሆነ የኢየሱስን ሥጋ የፈጠረው ማን ነው? ፈጣሪን ፈጣሪ ፈጠረው እያላችሁን ነው?? :-ሁለተኛ ለኢየሱስ ሕይወትን የሰጠው ፈጣሪ ማን ነው? ፈጣሪ ጥንትም ዘልዓለምም ሕያው ነው እንጂ ከጊዜ ቦኋላ ሕይወት ይቀበላልን?? []]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]] [ይቀጣላል ___ኢንሻ አሏህ] []]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]] ✍ ሙከሚል ሙሥሊም  ልጅ https://t.me/wada_islam
Показати все...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

👍 2 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.