cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Admas Media - አድማስ ሚዲያ

ይህ Admas Media -አድማስ ሚዲያ - ኦፈሽአል ቴሌግራም ነው። የሚወዱትን Admas Media -አድማስ ሚዲያ ማህበራዊ ገፅ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። This is Admas Media - አድማስ ሚዲያ Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ እና ለማንኛውም አይነት ጥያቄ @Admas_media_bot እንዲሁም ለማስታውቂያ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

Більше
Рекламні дописи
4 119
Підписники
Немає даних24 години
-47 днів
-19130 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Джерела переглядів
  • Підписники 28.78%
  • Канали 0.00%
  • Через посилання 39.07%
  • Групи 7.09%
  • Пошук в Телеграмі 23.12%
  • Персональні повідомлення 0.02%
  • Інші 1.93%
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
Update የህውሃት ሰው የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር ከሳምንታት ጋር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ውስጥ በኢንተርፖል ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።ለኢትዮጵያ መንግስትም ተላልፈው ይሰጣሉ ተብሎ ነበር።ሆኖም በርካታ የትግራይ ተወላጆች ባሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ ኢንተርፖል ሰውየውን ትናንት እንደለቀቃቸው ታውቋል።ቢሊየነሩ አቶ ዳዊት የወ/ሮ ፈትለወርቅ/ሞንጀሪኖ/ወንድም ናቸው።ለመንግስት ተቃዋሚዎችን የትጥቅ ድጋፍ በማጠናከር በተደጋጋሚ ስማቸው ይነሳል።
170Loading...
02
በዓለም አሳሳቢ የሆነው የሞት ፍርድ❗️ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በ2023 ጥፋተኛ በተባሉ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣትን ተፈጻሚ በማድረግ ኢራን እና ሳዑዲ አረቢያ ቀዳሚ አገራት ናቸው ብሏል። የመብት ተሟጋቹ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ተፈጻሚ የሚያደርጉትን የሞት ቅጣት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመራቸው በ2023 የተመዘገበው አሃዝ ከባለፉት 8 ዓመታት ከፍተኛው ነው ብሏል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በ16 አገራት 1ሺህ 153 ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል። ከእነዚህ መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት በኢራን የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ሲሆን 15 በመቶ የሚሆኑት የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ደግሞ በሳዑዲ ነው ተብሏል። በዚህ የአምነስቲ ሪፖርት ላይ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በሞት ከምትቀጣው ቻይና መረጃ ማግኘት ባለመቻሉ ቤይጂንግ በሪፖርቱ አለማካተቱን ገልጿል።
170Loading...
03
Media files
120Loading...
04
በኢትዮጵያ በሰላም ወጥቶ መግባት አጠራጣሪ ሆኗል- ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ በሰላም ወጥቶ መግባት አጠራጣሪ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ። ፓትሪያሪኩ ይህን ያሉት ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባት ለጠቅላላ ማህበረሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሯል ያሉት ፓትሪያሪኩ፥ የቤተክርስቲያኗ ፈተና ምንጭ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱና ዕድል ሰጩው ሁኔታ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው ብለዋል፡፡ በዚህ አለመግባባት ምክንያት መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት፣ ምእመናን፣ አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት እየደረሰባቸውም ቢሆንም “ይህን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም’’ ሲሉ ተናግረዋል። “ባለፉት አመታት በቤተክርስቲያኗ እና በአገልጋዮቿ ላይ የሚደርሱ በደሎች ቀጥለዋል፤ ወደፊትም የሚያስቆም ሁኔታ መኖሩን እንጠራጠራለን” ያሉት አቡነ ማትያስ፥  በደልን በካሣ እና በዕርቅ፣ በይቅርታ እና በምህረት መዝጋት ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቋማስርዓት ማበጀት እንደሚገባ አሳስበዋል። ፓትሪያሪኩ በመክፈቻ ንግግራቸው ከውጫዊ ችግሮች ባሻገር ቤተክርስቲያኗ የገጠማትን ውስጣዊ ፈተና አንስተዋል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሹመት ፈላጊነት እና የገንዘብ ፍቅር መንገሱን፣ መለያየት እና መነቃቀፍ እየሰፋ መምጣቱን በማንሳትም ኃላፊነት የጎደላቸው ንግግሮች “በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነት እና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው” ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፤ በአገልጋዮች እና ምዕመናንን ላይ የሚደርሱ ግድያዎች እንዲቆሙ ቤተክርስቲያኗ በተደጋጋሚ ማሳሰቧ ይታወሳል። ቤተክርስቲያኗ ውስጣዊ አንድነቷን አደጋ ላይ ይጥላሉ ባለቻቸው ጉዳዮች ላይም አቋሟን የሚያንጸባርቁ መግለጫዎችን ስታወጣ ቆይታለች። ባለፈው አመት ጥር ወር ከቤተክርስቲያኗ አፈንግጠው የራሳቸውን ሲኖዶስ አቋቁመናል ካሉ የቀድሞ አባቶች ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት መቋጨቷ የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የተከናወነውን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲቆም ጥረት ስታደርግ መቆየቷና ሹመቱ መካሄዷ በእጅጉ እንዳሳዘናት መግለጿም አይዘነጋም። ቤተክርስቲያኗ ቀኖናዋን ባልጠበቀ መልኩ የኦሮሚያ ሲኖዶስን ከመሰረቱ አባቶች ጋር ስምምነት ላይ መድረሷን ካሳወቀች በኋላም የቤተክርስቲያኗን አንድነት የሚፈታተኑ ድርጊቶች መቀጠላቸውን በመግለጫዎች ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ የጀመረው እና ለቀናት በሚዘልቀው ምልዓተ ጉባኤው ቤተክርስቲያኗን እየፈተኑ በሚገኙ ሀገራዊ ሁኔታዎች እና ውስጣዊ ችግሮች ዙሪያ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ተገልጿል። Via አል አይን
140Loading...
05
የካርድ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  ተጠቃሚዎች በየሱቁ  ካርድ መግዛት የሚችሉበት አሰራር ይፋ ሊሆን ነው የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት 10 ወራት ሚያዚያን ጨምሮ  76 አዳዲስ የገጠር  ከተሞች እና አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታየ  በካርድ እያስሞሉ የሚጠቀሙ ደንበኞች አገልግሎት በተመለከተ ቴክኖሎጂውን ለማዘመን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ። በተጨማሪም  አሁን ላይ በቴሌብር የሚከፍሉ ደንበኞች  የኤሌክትሪክ ካርድ በየሱፐር ማርኬቱ እና በየሱቁ በሞባይል ካርድ ይዘት ባለው መልኩ  የሚያገኙበት  አሰራር  እየተዘጋጀ እንደሚገኝ  እና አፈጻጸሙ  84 በመቶ እንደደረሰ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ባለፈው 10 ወራት ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ  ሶስት መቶ ሁለት አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት ተችሏል ከእቅድ አንጻር 66.5 በመቶ ማሳካት የተቻለበት ዓመት መሆኑንም ገልዋል። በሌላ በኩል ወላይታ ሶዶ ፣ ሻሸመኔ ፣ ሀረር፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር  ከተሞች ላይ የኔትወርክ ማሻሻያ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው የተሰሩባቸው አካባቢዎችም  ናቸው ። የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የአገልግሎቶት ሂሳባቸውን የማይከፍሉ ደንበኞች ፣ እንዲሁም የመስመር ብልሽት እና ማርጀት እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎት  መስመሮች ስርቆት   በበጀት ዓመቱ የነበሩ ተግዳሮች መሆኑም ተነግሯል ።
160Loading...
06
ቲክቶክ በመንግስታት የሚደገፉ የሚዲያ ተቋማት አካውንቶችን ላይ አዲስ ህግ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው። ከዚህ በፊት ቲክቶክ የእነዚህ ተቋማት የቲክቶክ አካውንት "State controlled media" የሚል ታግ ይለጥፍባቸው ነበር። በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደረገው የገለፀው ህግ ጣቢያው ከሚሰራጭበት ሀገር ውጪ ባሉ ቲክቶክ ተጠቃሚዎች ላይ የጣቢያዎች ቪዲዮ for you page ላይ አይመጣም። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ አካውንቶች for you page ላይ አይመጣም ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የእነዚህ ጣቢያዎች የአካውንት ማስታወቂያ ከሀገሪቱ ክልል ዉጭ የማይታይ ይሆናል። ይህ ህግ የወጣበት ምክንያት ሀገሮች በሌሎች ሀገሮች ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ፕሮፖጋንዳ ስለሚነዙ ነው ተብሏል።
220Loading...
07
በመሬት መንሸራተት 300 ሰዎች ተቀበሩ❗️ በፓፑዋ ኒው ጊኒ በተደረሰ የመሬት መንሸራተት 300 ሰዎች መቀበራቸው ተነገረ። በፓፑዋ ኒው ጊኒ አንድ መንደር ባወደመው ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ 300 ሰዎች እና 1100 ቤቶች መቀበራቸውን ሮይተርስ የሀገሪቱን ሚዲያዎች ጠቅሶ ዘግቧል። ከዋና ከተማዋ ሞረስቢ 600 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው የኢንጋ ግዛት ውስጥ የካዎካላም መንደር የመታው የመሬት መንሸራተት አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ሳይቀጥፍ እንደማይቀር ተሰግቷል።
250Loading...
08
ኦሮሚያ ባንክ ለብድር ካቀረበው 43.5 ቢሊዮን ብር 26 በመቶ የሚሆነውን ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በብድር ማቅረብን አስታወቀ! ከተመሰረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ኦሮሚያ ባንክ 54 ቢሊዮን ብር በቁጠባ መልክ ማሰባሰቡን፤ ከዚህ ውስጥም ለብድር ካቀረበዉ 43.5 ቢሊዮን ብር ዉስጥ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ በአማካይ አንድ ተበዳሪ 1.5 ሚሊዮን ብር ከባንኩ ማግኘቱ ተገልጿል።ይህም የብድር ስርጭቱ ከባንኩ ደንበኞች ምጣኔ አኳያ 92 በመቶ ይይዛል እንዲሁም ከተበደሩት ብድር አንፃር ደግሞ 26 በመቶ ይሸፍናሉ ተብሏል። ቀሪው የብድር አቅርቦት ለከፍተኛ ተበዳሪዎች ማቅረብን የገለፀዉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ይህም የብድር አቅርቦት በአማካይ አንድ ተበዳሪ 5 ሚሊዮን ብድር መውሰዱ ተናግረዋል።የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ጨምረዉ እንደተናገሩት የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠኑ ከ1.6 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ እንደሆነ ገልፀዋል። በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የተበላሸ ብድር መጠን ጣሪያ 5 በመቶ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ በዘርፉ ያለው አማካይ የተበላሸ የብድር መጠን 3.6 በመቶ መሆኑን አብራርተዋል።አሁን ላይ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ወደ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ፊቱን ያዞረዉ ባንኩ "ኦሮ ዲጂታል" በተሰኘው አገልግሎት ቴሌግራምን ጨምሮ በ7 አማራጮች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። Via Capital
200Loading...
09
በሱዳን ያንዣበበውን የዘር ማጥፋት ዓለም ችላ እንዳለው የተመድ ባለሙያ ተናገሩ! በሱዳን ዳርፉር ግዛት የዘር ማጥፋት እያንዣበበ ቢሆንም የዓለም ትኩረት ግን የዩክሬን እና ጋዛ ጦርነት ላይ ብቻ እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያ ገለጹ።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊን የዘር ማጥፋትን ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት በተመለከተ የሚያማክሩት ልዩ ልዑክ አሊስ ዋይሪሙ ንደርቱ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በዳርፉት የዘር ማጥፋት የተካሄደበት ወይም ሊካሄድ የሚችልበት ሁኔታ አለ። በሱዳን ኤል ፋሽር ከተማ ውስጥ ሰዎች በጎሳ ማንነታቸው ምክንያት የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን ባለሙያዋ ተናግረዋል።በከተማው የሚገኝ የሕክምና እርዳታ የሚሰጥ ተቋም ባለፉት 10 ቀናት 700 ሰዎች መገደላቸውን መዝግቧል።ከዳርፉር ግዛት በሱዳን ጦር ሥር የሚገኘው ብቸኛ ከተማ ኤል ፋሽር ሲሆን፣ ባለፉት ቀናት ጦርነቱ ተባብሷል። ፈጥሮ ደራሽ ኃይሉ እና የሱዳን ጦር ከአንድ ዓመት በላይ ጦርነት ውስጥ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተድለዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው ተሰደዋል።ኢብራሒም አል-ታይብ አለ-ፋኪ የተባለ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ እህቱ የተገደለችው ቤታቸው ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ነው። ሦስት ልጆቹ ከአያታቸው ጋር እንዲቆዩ ቢልካቸውም ይህ ቤትም በአየር ጥቃት እንደወደመ ገልጿል። አሁን መላ ቤተሰቡ መጠለያ ውስጥ ይገኛል።“በኤል ፋሽር ምንም ደኅንነቱ የተጠበቀ ቦታ የለም” ብሏል።የተመድ ባለሙያ እንደተናገሩት ሁኔታው “እንደ ሩዋንዳ” እየሆነ ነው። “በኤል ፋሽር ጥቃት እየተባባሰ ነው። ግጭቱ አስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል። ድምጼን ለማሰማት ብሞክርም ትኩረት ያለው በዩክሬን እና ጋዛ ጦርነቶች ላይ ስለሆነ ሰሚ አላገኘሁም” ብለዋል።ሂውማን ራይትስ ዋችም በዳርፉር የዘር ማጥፋት ስጋት እንዳለ አስታውቋል። በማሳሊት ብሔር እንዲሁም አረብ ባልሆኑ ማኅበረሰቦች ላይ የዘር ማጽዳትና ሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።የመብት ጥሰቱን እየፈፀሙ ይገኛሉ ያላቸው የፈጥኖ ደራሽ መሪው መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሚቲ)ን ጨምሮ ሌሎችም ኃይሎች ተጠያቂ እንዲደረጉም ጠይቋል። አረብ ያልሆኑ አርሶ አደሮችና አረብ አርብቶ አደሮች መካከል ለረዥም ጊዜ የቆየ ቁርሾ ያለ ሲሆን፣ ጦርነቱ ውጥረቱን አባብሷል።የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከተማዋ ላይ ከበባ ከማድረጉም ባሻገር የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።ተመድ እንደሚለው አምና በዳርፉሯ ኤል ጀኒና ከተማ ወደ 15 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል። Via BBC
220Loading...
10
በ13ተኛው "ለዛ ሽልማት" እነማን አሸናፊዎች ሆኑ?  13ኛው የ "ለዛ ሽልማት" ስነ ሥርዓት ትናንት ግንቦት 16 2016 ዓ/ም በሂልተን ተካሄዷል። 🎞 በዚህም መሰረት በፊልም እና ትወና ዘርፍ ፦ - የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ፦ አርቲስት ግሩም ዘነበ (በዶቃ ፊልም) - የዓመቱ ምርጥ ፊልም፦ ዶቃ ፊልም  - የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት፦ አርቲስት መስከረም አበራ (በ የሱፍ አበባ ፊልም) - የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም፦ በስንቱ  - የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ፦ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ (በስንቱ) - የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት፦ አርቲስት መስከረም አበራ (በስንቱ ) አሸናፊ መሆን ችለዋል። 🎙 በሙዚቃ ዘርፍ የዓመቱ የለዛ አሸናፊዎች እነማን ናቸው ? - የዓመቱ ምርጥ አልበም፦ የግርማ ተፈራ ካሣ " ግን የት ሀገር ?" አልበም - የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ፦ የድምጻዊት ራሔል ጌቱ "ኢትዮጵያዬ" - የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን፦ የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "ናዕት" - የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ)፦ ወግዳይት (አሳላፊ አልበም) - የዓመቱ ምርጥ ዘፈን፦ የድምጻዊት ሔዋን ገ/ወልድ "ሼሙና"   🙏 የህይወት ዘመን ተሸላሚው ደግሞ አንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ መሆን ችለዋል። #LezaAward #Award #Admasmedia1
200Loading...
11
ኤርትራ እንደ ሀገር የተመሰረተችበት 33ኛ ዓመት ዛሬ እያከበረች ነው።ፕሬዝደንት ኢሳያስም ንግግር አድርገዋል።በኢትዮጵያ ከ68 ሽህ በላይ ኤርትራዊያን በህጋዊ መልኩ እንደሚኖሩ አለምአቀፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።57ሺህ የሚሆኑት የሚኖሩት አፋር ክልል ነው ተብሏል።ኢትዮጵያና ኤርትራ የወቅቱ መንግስታዊ ግንኙነታቸው የተቀዛቀዘ እንደሆነ ከሚዲያዎች ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
290Loading...
12
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶስት ዓመት ዉስጥ 5ሺህ የቴሌኮም ማማዎች ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከዉዳ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ 68 የካሞፋላጅ የቴሌኮም ማማዎችን ለመረከብ መስማማቱም ተገልፃል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለነዚህ ማማዎች ለዉዳ ብረታብረት 50 ሚሊዮን ብር መከፈሉን ጣብያችን ሰምቷል። በስምምነቱ መሠረት እስካሁን 13 የቴሌኮም ማማዎችን ተረክቦ በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝ ሁለቱ ድርጅቶች በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ "ይህ ወቅት ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ታሪካዊ ነዉ" ያሉት ሲሆን "የማማዎቹ ጥራት ጥሩ እና ወጪ ቆጣቢ ነዉ" ሲሉ ተደምጠዋል። " እንደዚህ አይነት ስምምነቶች የሀገር ዉስጥ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላችንን አስተዋፅእ የምናደእግበት ነዉ" ብለዋል። "ይህ በኢትዮጵያ ማኑዩፋክቸሪንግ ትልቅ ምዕራፉ ነዉ" ያሉት ደግሞ የዉዳ ብረታብረት ዋና ስራ አስኪያጅ ስቴቨን ኪዩ ናቸዉ። ስራ አስኪያጁ "ለሳፋሪኮም ማማዎችን በማቅረብ የመጀመሪያዉ ሀገር በቀል ተቋም በመሆናችን ኩራት ይሰማናል" ብለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶስት ዓመት ዉስጥ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር የኔትወርክ ማስፋፊያ በማድረግ 5000 የቴሌኮም ማማዎችን ለመገንባት አቅዷል። ተቋሙ በአሁን ሰዓት ከ2,800 በላይ የቴሌኮም ማማዎች አሉት። ዉዳ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ከ18 ዓመታት በላይ ለቴሌኮሙኒኬሽን ፣ለብሮድካስቲንግ እና የቴሌቪዥን ሴክተሮች ማስተላለፊያ ማማዎች አምራች ድርጅት ነዉ።
250Loading...
13
Media files
170Loading...
14
እያንዳንዱ ድሮን ታጥቆ የሚሰማራው ሚሳኤሎች ዋጋ 3.5 ሚሊዮን ብር እንደሚገመት ተጠቆመ! በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ የእርሻ ማሳ ላይ ወድቋል የተባለ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ተንቀሳቃሽ ምሥል እና ፎቶ በስፋት ሲሠራጭ ነበር። የወደቀው ድሮን ባይራክተር ቲቢ 2 የተባለ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውል መሆኑን ቢቢሲ ከጦርነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ከሚተነትኑ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ማረጋገጡን በዘገባው አስነብቧል።ባለሙያዎች ሰው አልባ አውሮፕላኑ በመሳርያ ተመትቶ ስለመውደቁ የሚያሳይ ምንም ፍንጭ በምሥሉ ላይ እንደሌለ አረጋግጠዋል ብሏል። የወደቀው ሰው አልባ አውሮፕላኑ አራት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ወይንም ሮኬቶችን የመታጠቅ አቅምም እንዳለው የጠቆመው ቢቢሲ ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የተተመነለት መሆኑን እና የሚያስወነጭፋቸው ሮኬቶች የእያንዳንዳቸው ዋጋ ከ 60,000 እስከ 100,000 ዶላር አንደሚገመት አመላክቷል። ይህም ማለት እያንዳንዱ ድሮን ታጥቆ የሚሰማራው ሚሳኤሎች ዋጋ 3.5 ሚሊዮን ብር ይገመታል ማለት ነው ብሏል።
190Loading...
15
https://youtu.be/UJIvzaLcoP0?si=T2CIsM_yFlPHlUxS
220Loading...
16
የአሚሶን  ጉዳይ በአሜሪካ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የአፍሪካ ኅብረት ጦር ከሱማሊያ በመውጣት ሂደት ላይ መኾኑ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። ወደ አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት በዚህ ስጋት ዙሪያ ከሱማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር ተነጋግሬበታለኹ ያሉት ሩቶ፣ የኅብረቱ ጦር መውጣት በአገሪቱ ነባራዊ የጸጥታ ኹኔታ ላይ የተመሠረተ አይደለም ብለዋል። አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብታ ሂደቱን እንድታስቀይርም ሩቶ ጠይቀዋል። የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ በሱማሊያ እንዲሠማራ ሥልጣን የሰጠው፣ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ነው።(Wazena) አሚሶን አብዝሃኛው በኢትዮጵያ ወታደሮች የተያዘ ነው።
260Loading...
17
በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ ይሆናሉ ተባለ በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ እንደሚሆን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ 71 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም የሚፈጠረው የስራ እድል ግን ከ50 በመቶ በታች መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ወንድማገኝ ታዬ ለአራዳ ገልጸዋል። በዚህም በየዓመቱ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ዜጋ ስራ አጥ እንደሚሆን የሴንትራል ስታቲስቲክስ ዳታ ጥናት ያመላክታል ነው ያሉት ባለሙያው። የህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር አለመመጣጠን፣ ከማምረቻው ዘርፍ ይልቅ የአገልግሎት ዘርፉ መስፋፋትና የሚቀጥረው ሰው አነስተኛ መሆን የራሱ ድርሻ እንዳለውም ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ከሚፈጠር የስራ እድል ውስጥ 80 በመቶው በመንግስት በኩል መሆኑም ለዚህ የራሱ ድርሻ አለው ነው ያሉት። ይህን ለመቅረፍም የግሉ ዘርፍ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ በስፋት መስራት እንዳለባቸው ባለሙያው አስገንዝበዋል። ከዚህ ባለፈም የመስራት ባህልን ማሳደግ፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትና መሰል የመፍትሄ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባም አስረድተዋል።
260Loading...
18
በቻድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን መልቀቂያ አስገቡ! በቻድ የሁንታ መሪ በሆኑት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢንቶ ከሁለት ሣምንት በፊት በፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰክሰስ ማስራ የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን ዛሬ አስታውቀዋል። የ40 ዓመቱ ማሃማት ዴቢ ምርጫውን 61 በመቶ ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ሲታወቅ፣ ከነገ በስቲያ ሐሙስ በሚደረግ ሥነ ስርዓት ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙ በመጠበቅ ላይ ነው። መሃማት ዴቢ፣ ለ30 ዓመታ ሃገሪቱን የገዙት አባታቸው ከሶስት ዓመታት በፊት በአማጺያን መገደላቸውን ተከትሎ፣ 15 ዓባላት ያሉት ወታደራዊ ሁንታ የሽግግር ፕሬዝደንት አድርጎ ሾሟቸው ነበር። እርሳቸውም የ40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰክሰስ ማስራ፣ ከአራት ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸውም ቀደም ብሎ የዴቢ ጠንካራ ተቃዋሚ የነበሩ መሆናቸው ይነገራል። በፕሬዝደንታዊ ምርጫው 18.5 በመቶውን ድምፅ ብቻ አግኝተዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማስራ የአገዛዙ መጠቀሚያ ናቸው ሲሉ ይከሳሉ። ማስራ ቀድመው አሸናፊነታቸውን አውጀው የነበረ ሲሆን፣ ፓርቲያቸው ምርጫውን “ጭንብል” ሲል ጠርቶታል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቡድኖችም ምርጫው ተአማኝም፣ ፍትሃዊም እንዳልነበር ገልፀዋል። Via VoA
230Loading...
19
በአዲስ አበባ ከተማ በህንፃ መሰረት ግንባታ በደረሰ የድንጋይ እና አፈር መደርመስ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ። ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ  ህንጻ  ለመገንባት  የመሰረት ስራ ላይ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። አደጋዉ የደረሰዉ ሰራተኞቹ  በስራ ላይ እንዳሉ  ስራዉ ከሚከናወንበት አጠገብ የነበረና አፋፍ ላይ ያለ  የግለሰብ መኖሪያ ቤት  የዉሀ ልክና ድንጋይ እ አፈር  በሰራተኞቹ ላይ በመናዱ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ከተጫነበት አፈርና ድንጋይ ስር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በማናቸዉም የግንባታ ስራዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ አለመስራት መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የግንባታ ፈቃድ ሰጪ አካላትም ተገቢዉን ክትትል ቁጥጥር ማድረግ ይገባቸዋል። ቤቶቹ የግለሰብ ቤቶች መሆናውንም ኮሚሽኑ አስታውቃል አስከሬኑን ለማውጣት 1:30 መፍጀቱም ተነግራል።
210Loading...
20
የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ በመሙላቱ ምክንያት ግድቡን ለማስተንፈስ የተለቀቀው ውሃ የጎርፍ አደጋ እንዲከሰት አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ በመሙላቱ ምክንያት ግድቡን ለማስተንፈስ የተለቀቀው ውሃ የኦሞ ወንዝ በከፍተኛ መጠን እንዲሞላ እና ወንዙ ከዚህ ቀደም በጎርፍ ከሚያጥለቀልቃቸው ቦታዎች በተጨማሪ በሌሎች ቦታዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንዲከሰት አስተዋጽዖ ማድረጉ ኮሚሸኑ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ውስጥ ባሉ 12 የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ አግባብነት ካላቸው ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ሕጎችና ሰነዶች አንጻር መገምገሙን አስታወቀ፡፡ በግምገማውም የመፈናቀል መንስኤዎችን፣ በመፈናቀል እና ድኅረ መፈናቀል ወቅት የደረሱ ጉዳቶችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እና አሳሳቢ ሁኔታዎችን መለየቱን ነው ያስታወቀው፡፡ የኦሞ ወንዝን በከፍተኛ ሁኔታ መሙላት እና የዳሰነች ወረዳ በርካታ አካባቢዎችን በጎርፍ መጥለቅለቅ ተከትሎ፣ ሰዎች ለመፈናቀል ከመዳረጋቸው ባሻገር በሕይወታቸውና በንብረታቸው እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በሚያገኙባቸው ተቋሟት ላይ  ጉዳት የደረሰ መሆኑን የክትትል ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ በዚህም መሠረት ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተፈናቃዮችን ቅድሚያ በሰጠ መልኩ ለተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ ሰብአዊ ድጋፍ የማቅረቡ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ ስምምነት (የካምፓላ ስምምነት) አባል ሀገር እንደመሆኗ መንግሥት በስምምነቱ የተጠበቁ መብቶችን በተቻለ መጠን እና ፍጥነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ እንደዚሁም በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰት መፈናቀልን ለማስወገድ እና መፈናቀል ሲከሰትም የሰብአዊ መብቶች መርሖችን የተከተለ ዘላቂ መፍትሔ ለማመቻቸት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሠሩ ይገባል” ብለዋል።
210Loading...
21
https://youtu.be/aBQKbL_8u7Q?si=SYSGVZf2qBjtqdsn
240Loading...
22
https://youtu.be/rGhK-3L8gzM?si=fZ4VEZC5pWJ9uiqI
180Loading...
23
ኤችአይቪ ገዳይነቱ እየጨመረ መሆኑ ተሰማ❗️ ኤችአይቪ ኤድስን ጨምሮ በግብረ ስጋ ግንኝነት የሚተላለፉ በሽታዎች ገዳይነት እየጨመረ ነው ተብሏል። የአለም ድርጅት አዲስ ያወጣው ሪፖርት በብዙዎች ዘንድ ችላ የተባለው ኤቺ አይቪ ኤድስ እና ሌሎች በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለለፉ በሽታዎች በአመት 2.5 ሚልየን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡ ድርጅቱ በተለይ በአሜሪካ እና አፍሪካ የሚገኝውን ከፍ ያለ የበሽታውን ስርጭት ከ7.8 ሚልየን ወደ 0.7ሚልየን ለመቀነስ እቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይሁንና በ2022 ከ15-49 እድሜ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ  አንድ ሚልዮን አዲስ ኢንፌክሽን ተመዝግቧል፡፡
970Loading...
24
አዲስ አበባ‼     አዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ 10:10 ሰዓት አቡኒ የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ፋብሪካ ላይ ተነስቶ በነበረዉ የእሳት አደጋ ፋብሪካዉ በከፊል መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ። የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢፕድ በሰጡት መረጃ እንዳሉት የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ስምንት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የዉሀ ቦታ ከ56 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርቷል። ባለሙያው የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል። በአደጋዉ ለመልሶ መጠቀም ግልጋሎት የሚዉሉ ጥሬ ዕቃዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ፋብሪካዉ በከፊል ወድሟል። በፋብሪካዉ የአደጋ ደህንነትን መስፈርት ያልጠበቁ ያገለገሉ የፕላስቲክ ዉጤቶች ክምችት እንዲሁም ስፍራዉ የአደጋ መቆጣጠር ተሽርከርካሪውችን የማያስገባ መሆኑ ለአደጋዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ አድርጓል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሁለት ሰዓት የፈጀ ሲሆን  በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። (ኢፕድ)
930Loading...
25
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡ ህንጻ ለመገንባት የአፍር ቁፋሮ እያደረጉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች አፈር እንደተናደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ከአፈር ናዳው እስካሁን ድረስ አንድ ሰው ብቻ ማውጣት እንደተቻለ የገለጹት ነዋሪዎቹ በቦታው ያለው ነገር የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሰራተኞች ባሁኑ ሰአት በቦታው መገኝታቸቀው የተነገረ ሲሆን ሰራተኞቹን ለማዳን ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡የአፈር ናዳው የደረሰው ህንጻው ከህንጻው አጠገብ ባሉ መኖርያ ቤቶች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ Via Ethio FM
920Loading...
26
https://youtube.com/shorts/jIyg4ETpBEE?si=9GMqlsnlvaVL6iQN
900Loading...
27
ማስታወቂያ /Advertisment የSpaceX አውቶማቲክ የቁጥር አሰራር ስርዓት ዝቅተኛውን የዲጂታል ምንዛሪ መሸጫ ዋጋ እንደ BTC፣ ETH፣ USDT፣ ወዘተ ባሉ ዋና ዋና ልውውጦች ላይ በመፈለግ በፍጥነት በሰከንዶች ውስጥ መግዛት ይችላል። 1. USDT በቁጥር ይገለጻል፣ እና የገንዘብ ማስቀመጫዎች እና ገንዘቦች ወዲያውኑ ይመጣሉ። 2. መጠናዊ VIP1-VIP10፣ መጠናዊ ገቢ 19%-40% 3. የመልቲ-ምንዛሪ ብልህ የኢንቨስትመንት ገቢ ከ15% -28% 4. መጠኗ በየ24 ሰዓቱ አንድ ጊዜ ይዘጋጃል፣ እና እያንዳንዱ ሰው በቀን አንድ ጊዜ በቁጥር ግብይት ትርፍ መሳተፍ ይችላል። 5. የቁጥር ግብይትን እና የሶስት-ደረጃ ወኪሎችን ያስተዋውቁ (የ13% ሽልማት ለኤ፣ 3% ሽልማት ለቢ፣ 2% ሽልማት ለ C = 18% ሽልማት) የ24-ሰዓት ያልተቋረጠ መረጃ መሰብሰብ፣በእጅ የገበያ ሁኔታን አለመከታተል፣ ቀልጣፋ እና የተረጋጋ ትርፍ። ይህ የSpaceX xAI አውቶሜትድ የቁጥር ስርዓት ነው። የቴሌግራም የደንበኞች አገልግሎት https://t.me/Spacex_XAI SpaceX xAI ኦፊሴላዊ ድር ጣቢያ፡ https://sp-xai.com የአባል ምዝገባ አገናኝ፡ https://sp-xai.com/#/register?i=819346
5190Loading...
28
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠጥል ተነገረ የኢትዮጰያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በቀጣዮቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እንደሚያመላክቱን በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሰፊ ቦታዎችን ያካተተና የተጠናከረ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተስፋፋ ዝናብ የሚኖር ሲሆን እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጲያ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከኢትዮጰያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በአጠቃላይ በሚቀጥሉት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፤ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፤ ነአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች  ላይ የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ ፣ በአዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ እና ሃረር ላይ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጥል ይጠበቃል፡፡
1990Loading...
29
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ፤ የወረዳ ንግድ ቢሮዎች  በከተማዋ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የነበራቸው ሥልጣን ላይ ገደብ ጣለ በአዲሱ አሠራር መሠረት ወረዳዎች በራሳቸው ውሳኔ የንግድ ቦታዎችን ማሸግ የሚችሉት ከንግድ ፈቃድ ጋር በተያያዙ ሁለት ጥሰቶች ፈፅመው ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ይህን አሠራር ያስተዋወቀው አዲስ ባወጣው “በመንደር የንግድ ቁጥጥር የአሠራር ሥርዓት መመሪያ” ላይ መሆኑን  በቢሮዉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡ በመመሪያው መሰረት በወረዳዎች ደረጃ የሚካሄድ የንግድ ቁጥጥርና ክትትል ተግባራት ወረዳዎችን የንግድ ድርጅቶችን ቁጥር፣ የቆዳ ስፋትና የባለሙያዎችን ቁጥር ታሳቢ ባደረገ መልኩ በመንደር ተከፋፍለዋል። በዚህም  ከሁለት እስከ ሦስት የሚደርሱ የወረዳ የቁጥጥር ባለሙያዎችን  በመመደብ የሚተገበር እንዲሆን ማስቀመጡን አቶ ሰውነት ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር መመሪያው የወረዳ የንግድ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከንግድ ጥፋቶች ጋር በተያያዘ ለቅርብ ኃላፊዎቻቸው በፅሁፍ በማሳወቅ ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ማሸግ ድረስ የሚወስዷቸው አስተዳደራዊ እርምጃዎች በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲገደብ ተደርጓል፡፡ እነዚህም የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲነግዱ በተገኙ እና  ባልታደሰ፣ በታገደ ወይም በተሰረዘ የንግድ ፈቃድ ሲነግዱ በተገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ ብቻ እንደሆነ መመሪያው በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ይሁንና የወረዳ የንግድ ቁጥጥር ባለሙያዎች በቁጥጥርና ክትትል ወቅት የሚደርሱባቸውን ሌሎች ጥፋቶች ላይ እምርጃ መወሰድ ሳይኖርባቸው ጥፋቱን በፅሁፍ ለወረዳው ንግድ ፅ/ቤት ኃላፊ ማሳወቅ፣ ኃላፊው ለክፍለ ከተማ ንግድ ፅ/ቤት ጥፋቱን በግልፅ ጠቅሶ ሪፖርት የማድረግ፣ በተመሳሳይም የክፍለ ከተማው ንግድ ፅ/ቤት ለቢሮው በፅሁፍ ሪፖርት በማድረግና ጥፋቱን በማሳወቅ ከቢሮው በሚሰጠው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ተግባሪያዊ እንዲደረግ ለወረዳው የማሳወቅና አፈፃፀሙንም የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዳለበት የሚያሳይ ነው፡፡
1980Loading...
30
#Ethiopia የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃለማርያም ሀገር ጥለው ከወጡ ዛሬ ድፍን 33 ዓመት ሆኗቸዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ/ም ነው ከሀገር የወጡት። የድርግ ውድቀትን እና የ #ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ መቃረብን ተከትሎ ከሀገር እንደወጡ የሚነገርላቸው ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃለማርያም በአንድ ወቅት ፤ " እኔ ኮብልዬ አልወጣሁም " ሲሉ ነበር ቃላቸውን የሰጡት። ኬንያ የሄዱትም ' #አሰብ ' በሻዕብያ በመያዙ ለመልሶ ማጥቃት የሚሆን ሌላ በር እንዲኖር ከኬንያ፣ ከጅቡቲ እና ሰሜን ሶማሊያ መንግስታት ጋር ለመነጋገርና ለመመለስ እንደነበረና ይህም ጥብቅ ሚስጥራዊ ጉዞ እንደሆነ ተናግረው ነበር። ጥዋት 2:20 ወደ ኬንያ ጉዞ እንደጀመሩ እዚህ ስብሰባ መጀመሩና ኬንያ እንዳሉ ከቀን 7:00 ሰዓት ከስልጣን እንደወረዱ እንደሰሙ ገልጸው ነበር። በራሳቸው አንደበትም ፥ ምንም አይነት #ገፊ ምክንያት በሌለበት በአሻጥር ከሀገር እንዲወጡ መገደዱን ነው በአንድ ወቅት ሲናገሩ የተደመጡት። ዛሬ ላይ ሀገር ጥለው ከወጡ 33 ዓመት የደፈናቸው ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም በዚምባቡዬ ውስጥ ይኖራሉ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳት ከዓመታት በፊት  ፦ ° በዘር ማጥፋት ፣ ° በግድያ፣ ° ከህግ ውጪ ሰዎችን በማሰር ° ንብረትን በመውረስ ጥፋተኛ ተብለው በሌሉበት #የሞት ፍርድ ተወስኖባቸዋል።
2000Loading...
31
Media files
1990Loading...
32
ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ  የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡ ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ  ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው  የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የከተማችንን እና የነዋሪዎቿን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ  በከተማችን የተፈጸሙ አንዳንድ ወንጀሎችን መነሻ በማድረግ የበሬ ወለደ ይዘት ያላቸውን የተዛቡ እንዲሁም የተጋነኑ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦችና  ተቋማት መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የከተማችንን የፀጥታ ጉዳይ በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ ምንጭ የማግኘት ልምድን ሊያዳብር እንደሚገባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፎ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ፖሊስ ጨምሮ አሳስቧል።
990Loading...
33
Media files
1000Loading...
34
በሲንጋፖር አየር መንገድ አዉሮፕላን በረራ ላይ ባጋጠመ የአየር ለዉጥ አንድ መንገደኛ መሞቱ ተገለጸ፡፡ ከለንደን ወደ ሲንጋፖር ሲበር የነበረዉ ቦይንግ 777-300 አዉሮፕላን ባጋጠመዉ የአየር ለዉጥ አንድ መንገደኛ ህይወቱ ሲያልፍ ሌሎች 30 መንገደኞች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተገልጿል፡፡ ብዙም በማያግጥም ክስተት የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን እና አዉሮፕላኑም ባንኮክ ላይ ለማረፍ መገደዱን የሲንጋፖር አየር መንገድ አስታዉቋል፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደዚህ ዓይነት አደጋዎች ብዙ ጊዜ የሚከሰቱት ተጓዦች የመቀመጫ ቀበቷቸዉን በማያስሩበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በአየር ሁኔታ መከታተያዉ ላይ ምንም ዓይነት ለዉጥ ባለመታየቱ አብራሪዉ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለመቻሉንም አንስተዋል፡፡ ቦይንግ 777-300 ኢ አር የበረራ ቁጥር ኤስ-ኪዉ 321 አዉሮፕላን በዉስጡ 2መቶ11 ተሳፋሪዎችን እና 18 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነበር ከለንደን ሄዝሮዉ አየር መንገድ የተነሳዉ፡፡ ባለፈዉ ዓመት ግንቦት ወር ላይ ከህንድ ዴልሂ ተነስቶ ወደ አዉስትራሊያ ሲድኒ ሲጓዝ የነበረ የህንድ አዉሮፕላን ላይ እንደዚህ ዓይነት የአየር ለዉጥ ተከስቶ ብዙ ተጓዦች ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ሲኤንኤን አስታዉሷል፡፡
980Loading...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Update የህውሃት ሰው የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር ከሳምንታት ጋር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ውስጥ በኢንተርፖል ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።ለኢትዮጵያ መንግስትም ተላልፈው ይሰጣሉ ተብሎ ነበር።ሆኖም በርካታ የትግራይ ተወላጆች ባሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ ኢንተርፖል ሰውየውን ትናንት እንደለቀቃቸው ታውቋል።ቢሊየነሩ አቶ ዳዊት የወ/ሮ ፈትለወርቅ/ሞንጀሪኖ/ወንድም ናቸው።ለመንግስት ተቃዋሚዎችን የትጥቅ ድጋፍ በማጠናከር በተደጋጋሚ ስማቸው ይነሳል።
Показати все...