cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Admas Media - አድማስ ሚዲያ

ይህ Admas Media -አድማስ ሚዲያ - ኦፈሽአል ቴሌግራም ነው። የሚወዱትን Admas Media -አድማስ ሚዲያ ማህበራዊ ገፅ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። This is Admas Media - አድማስ ሚዲያ Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ እና ለማንኛውም አይነት ጥያቄ @Admas_media_bot እንዲሁም ለማስታውቂያ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

Більше
Рекламні дописи
4 116
Підписники
-124 години
-57 днів
-23530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአየር ትርዒት የተጋጩት ጄቶች❗️ በፖርቹጋል የአየር ትርዒት ላይ በተፈጠረ ግጭት የስፔን ዜግነት ያለው ፓይለት ህይወቱ ማለፉን የፖርቹጋል አየር ሀይል አስታውቋል፡፡ እንደ አየር ሀይሉ መረጃ፤ ከፖርቹጋል መዲና ሊዝበን ከተማ በ178 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምተገኘው የቤጃ ከተማ ላይ እየተካሄደ በነበረው የአየር ትርዒት ላይ አውሮፕላኖች ተጋጭተው አደጋ ተከስቷል፡ በግጭቱ አንደኛው አውሮፕላን ከቤጃ አየር ማረፊያ ክልል ውጭ ሲከሰከስ ሌላኛው አውሮፕላን ደግሞ በአየር ማረፊያው አቅራቢያ መከስከሱ ተገልጿል፡፡በአደጋው አንድ ፓይለት ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ፖርቹጋላዊ ፓይለት ክፉኛ ተጎድቶ ወደ ቤጃ ሆስፒታል መግባቱ ነው የተገለፀው፡፡ የፖርቹጋል አየር ሀይል በተፈጠረው ክስተት ማዘኑን ገልፆ በአደጋው ሕይዎቱን ላጣው አብራሪ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቻይና መንኮራኩሯ ማንም ሞክሮ በማያውቀው የጨረቃ ክፍል ማረፉን አስታወቀች ቻይና ቻንግ 6 የተበለው መንኮራኩሯ እሑድ ጥዋት ማንም ሞክሮ በማያውቀው በደቡብ ዋልታ-አይትከን ማረፉን የሀገሪቱ ብሔራዊ የጠፈር አስተዳደር (ሲኤንኤ) አስታውቋል። የዛሬ ወር ገደማ ጉዞ የጀመረው መንኮራኩር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድ ድንጋይ እና አፈርን ለመሰብሰብ ያለመ ሲሆን በደቡብ ዋልታ ላይ ካለው ግዙፍ ጉድጓድ ውስጥ የተወሰኑትን የጨረቃን ጥንታዊ አለቶች ማውጣት እንደሚችል ተነግሯል። መንኮራኮሩ ምቹ የሆነ ቦታ ለማረፍ በሚያደርገው ጥረት መሰናክሎችን በመለየት መንቀሳቀስ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ እና እንደጨለማው ሁኔታ የሚቀያየር ብርሃን የተገጠመለት መሆኑን ተዘግቧል። Credit: Xinhua
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ልዩ መረጃ‼️ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች የሰላም ድርድር ሂደት መጀመሩ ታውቋል   እስክንድር ነጋ የፋኖ ታጣቂዎችን ወክሎ ከመንግስት ድርድር መጀመሩ ተገልጿል። በ3ኛ ወገን አመቻችነት እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ የድርድር ሂደት መጀመሩ ተጠቁሟል። መንግስት ከእስክንድር ጋር እያደረገ ያለው ድርድር የሚሳከ ከሆነ ከእስክንድር ቡድን ጋር ከሸዋ የሻለቃ መከታው ቡድን፣ ከወሎ የምሬ ወዳጆ እና የኮ/ል ፈንታሁን ቡድኖች፣ ከጎጃም የማስረሻ ሰጤ እና የማንችሎት ቡድኖች፤ ከጎንደር በሻለቃ ሀብተ ወልድ የሚመራ ቡድን ወደ በድርድርሩ  እንዲሳቱፉ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ መንገድ የለም! ሰላም ለኢትዮጵያ
Показати все...
ክላውዲያ ሺንባም በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ ድምጽ በማሸነፍ የሜክሲኮ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ክላውዲያ ሺንባም በፈረንጆቹ ጥቅምት 1 ቀን 2024 ላይ ፕሬዚዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶርን ይተካሉ ተብሏል። የቀድሞ የኢነርጂ ሳይንቲስት ሺንባም በሎፔዝ ኦብራዶር የተሰሩትን ስራዎች እንደሚያስቀጥሉ ቃል ገብተዋል
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ትራምፕ ቲክቶክ ከፈቱ❗️ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው እንዲታገድ የወሰኑበትን ቲክቶክ ተቀላቅለዋል። ትራምፕ ትናንት ምሽት የቻይናውን ባይትዳንስ ኩባንያ የቪዲዮ ማጋሪያ መቀላቀላቸውን የሚያበስር ቪዲዮ በአዲሱ አካውንታቸው ለቀዋል። ቪዲዮውን ከ30 ሚሊየን በላይ ሰዎች የተመለከቱት ሲሆን፥ አዲሱ አካውንት በስአታት ውስጥ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተከታይ ማፍራት ችሏል። በህዳር ወር በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የሚፎካከሩት ትራምፕ ቲክቶክን መቀላቀላቸው ወጣት መራጮችን ለማግኘት እንደሚያግዛቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
Показати все...
በቻይና የ35 ዓመቱ ወጣት በኃይለኛ ማስነጠስ የጭኑ አጥንቶች መሰበራቸው ተሰማ የጭን አጥንት በሰው ልጅ የሰውነት አካል ውስጥ ካሉት አጥንቶች ሁሉ በጣም ጠንካራ ወይም ሁለተኛው በጥንካሬ የሚገለፅ አጥንት ተብሎ ይታሰባል፣ ነገር ግን በቻይና የሚኖር የ35 አመቱ ወጣት በሳል ወቅት አጥንቱ መስበሩ ተሰምቷል። በቻይና ፉጂያን ግዛት የህዝብ ሆስፒታል እንዳስታወቀው ዬ በመባል የሚታወቁት የ35 አመቱ ወጣት በአስደንጋጭ ሁኔታ በከባድ ሳል የተነሳ የአካል ጉዳት ደርሶበታል። በሆስፒታሉ የአጥንት ህክምና ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ዶንግ ዞንግ እንደገለፁት ያልተለመደው ክስተት ያጋጥመው በሳል ወቅት ሲሆን ይህ ዓይነቱ የአጥንስት ስብራት በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ወንዶች እንደ መኪና አደጋ ወይም በመሳሰሉት ከባድ የአካል ጉዳቶች ሳቢያ የጭን ስብራት ይደርስባቸዋል እንጂ በሳል ምክንያት የሚፈጠር አልነበረም ብለዋል። ዬ በተለይ ካጋጠመው ጠንካራ ሳል በኋላ ወዲያውኑ ኃይለኛ ህመም እንደተሰማው ለዶክተሮች ተናግሯል። ነገር ግን በቀላሉ የምወጣው ቢመስለኝም እየቆየ በህመሙ ምክንያት በእግሬ መሄድ አስቸጋሪ ሆኖብኝ ሕክምና ዕርዳታ ለማግኘት ወሰንኩኝ ሲል ተደምጧል። በኤክስሬይ ምርመራ ወቅት ዬ የጭኑ ስብራት እንደደረሰበት አሳይቷል፣ ነገር ግን በሳል ምክንያት ተፈጠረ መባሉ ለህክምና ቡድኑ ምንም ትርጉም አልሰጠም። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም አይነት የአካል ጉዳት ምልክት ያልታየበት መሆኑ ሀኪሞችን ግራ አጋብቷል። ዦንግ እና የህክምና ቡድናቸው ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ወስነው ፤ ስለ ታማሚው አጠቃላይ ጤንነቱ፣ የአመጋገብ ልማዱ እና አኗኗሩ ጠይቀዋል፣ በተጨማሪም የአጥንት ጥንካሬ ምርመራ አድርገዋል። በዚህም አሳሳቢ ውጤቶችን አግኝተዋል። የአጥንት ጥንካሬው የ35 ዓመት ወጣት ሳይሆን ከ 80 አመት ሰው ጋር ተመሳሳይ ነበር።  አብዝቶ ለስላሳ መጠጦችን የመጠጣት ባህሪ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለማድረግ ምክንያት በቀላሉ በማይታመን ሁኔታ የሚሰባበር አጥንቶች እንዳሉት ዶክተሮች ደምድመዋል። የ35 አመቱ ሰው ለሀኪሞች እንደተናገረው ከውሃ ይልንቅ በጣፋጭ እና ካርቦን ይዘት ያላቸው የሶዳ መጠጦች በመተካት ሰውነቱ ካልሲየም በትክክል እንዳይወስድ ማድረጉን ገልጿል። በዚህን የአጥንቱን ጥንካሬ ጎድቷል።ዶ/ር ዶንግ ዦንግ ኮላ ላይ የተመሰረቱ መጠጦች ፎስፎሪክ አሲድ ከካልሲየም ጋር በመዋሃድ ወደ ሰውነታችን ከገቡ በኋላ ካልሲየም ፎስፌት እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ይህ ደግሞ ከሰው አካል ጋር ለመዋሃድ በጣም ከባድ ነው።ስለዚህ ለረጅም ጊዜ እንዲህ አይነት መጠጦችን በተደጋጋሚ መጠጣት በአጥንት ጥንካሬ ላይ አስከፊ መዘዝ ያስከትላል ሲሉ ተናግረዋል።
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው። በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦ ✔ የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣ ✔ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ #በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ #ተካቷል፡፡ ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል አለባበስን እና የተማሪዎች አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል። አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡
Показати все...
የህዳሴ ግድብን ግንባታ የሚቃወሙ አካላት በኮንትራክተሮች ላይ ማስፈራሪያ እየላኩ መሆኑ ተሰማ ከዛሬ 13 ዓመታት በፊት የተጀመረውና በመሃል  የግንባታ ሂደቱ ተቋረጦ የነበረዉ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በተሳተፉት ኮንትራክተሮች ላይ ከፕሮጀክቱ እንዲወጡ የማስፈራራት እና የማባበል ዛቻዎች እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል። ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚገኙ ተቋሬጭ ኮንትራክተሮች ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ይህም ቢሆን ግን ግንባታው በታቀደለት ጊዜ ይጠናቀቃል በማለት ተናግረዋል ። የፕሮጀክቱን ሂደት የሚቃወሙ እና አንዳንድ ተቀናቃኞች ሲሏቸዉ የጠሯቸው አካላት ማንነት ከመግለፅ የተቆጠቡት ኢንጅነር ክፍሌ ግንባታው የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ቆሞ በነበረበት ወቅት ፀጥ ብለዉ እንደነበር አስታዉሰዋል። ግድቡ መሰራት ሲጀምር ዝም ብለዉ ነበር ያሏቸው ተቃዋሚዎች ፕሮጀክቱ የታቀደለትን ግብ ይመታል ሲባል የዲፕሎማሲ ጦርነትን ጨምሮ የማስፈራራት እና የተለያዩ ክሶችን ክፍተዋል ማለታቸዉን ዳጉ ጆርናል ከካፒታል ዘገባ ተመልክቷል። ነገር ግን ይሄ ሁሉ ደረጃ ላይ ታልፎ ነዉ ግንባታው አሁን ለደረሰበት አፈፃፀም መድረስ የቻለው ሲሉም ተደምጠዋል ። ኢንጂነር ክፍሌ እንደተናገሩት እነዚሁ አካላት ኮንትራክተሮችን ያባብላሉ ፣ ፕሮጀክት አታገኙም በሚል የተለያዩ ማስፈራሪያዎች አሁንም ድረስ እያደረጉ ይገኛሉ ። የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ይህን የተናገሩት የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አሁን የደረሰበትን የግንባታ ሂደት በተመለከተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈትቤትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ለግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚያደርጉበትን መተግበሪያ ባስተዋወቁበት መድረክ ላይ ነዉ። የፕሮጀክቱ ግንባታ ከዛሬ 5 ዓመታት በፊት ተቋርጦ በነበረበት ጊዜ ተቃዉሞ ያልነበረበት ቢሆንም ነገር ግን ይህ ግድብ መሰራት መጀመሩ በታወቀበት ወቅት እየደረሱ ይገኛሉ ከተባሉት ተግዳሮቶች ዉስጥ ለግድቡ ብቸኛዉ ሲሚንቶ አቅራቢ በሆነዉ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካን ከማቃጠል ጀምሮ ጥሬ እቃዎች እንዳይደርሱት መንገዶችን መዝጋት እና ግብዓቶች ወደ ሳይት እንዳይደርሱ መንገድ ላይ የተልዕኮ ጦርነቶች ይገኙበታል ። ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ ይህ ሁሉ ፈተና እያለበት አጠቃላይ አፈፃፀሙ 96 በመቶ መድረሱንና ቀሪዉ እስከ መጪዉ ጥር ወር ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል። Via ካፒታል ጋዜጣ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Update የህውሃት ሰው የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር ከሳምንታት ጋር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ውስጥ በኢንተርፖል ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።ለኢትዮጵያ መንግስትም ተላልፈው ይሰጣሉ ተብሎ ነበር።ሆኖም በርካታ የትግራይ ተወላጆች ባሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ ኢንተርፖል ሰውየውን ትናንት እንደለቀቃቸው ታውቋል።ቢሊየነሩ አቶ ዳዊት የወ/ሮ ፈትለወርቅ/ሞንጀሪኖ/ወንድም ናቸው።ለመንግስት ተቃዋሚዎችን የትጥቅ ድጋፍ በማጠናከር በተደጋጋሚ ስማቸው ይነሳል።
Показати все...