Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
Відкрити в Telegram
Показати більше
2 318
Підписники
+2124 години
+817 днів
+36330 днів
Архів дописів
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ የሚተገብራቸው ዋና ዋና ተግባራት ጥራት ላይ ያተኮረ ነፃ የውይይት መድረክ አካሄደ::
ኮሌጁ በ2018 በጀት ዓመት የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርና እንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ትግበራን በተሻለ ጥራት ለመተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ ለማሰባሰብ የሚያረዳ ነፃ የውይይት መድረክ ከተቋሙ አመራር አባላትና ከስልጠና ክፍሎች ከተወጣጡ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ነፃ የውይይት መድረክ አካሂዷል::
የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማ ኮሌጁ በ2018 ዓ.ም በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ የተቃኘ መሪ እቅድ ማዘጋጀቱን ታሳቢ በማድረግ በእቅዱ የተቀመጡ ተግባራትን በተሻለ መንገድ ለመፈፀም ችግሮችን በመለየትና አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማሰባሰብ ከመግባባት ላይ የተደረሰበትን ጭብጥ ይዞ በአዲሱ በጀት ዓመት ወደ ተግባር ለመግባት በማስፈለጉ እንደሆነም ተገልፇል::
በኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ እንዲሁም በኮሌጁ የቴ/ሽ/ኢ/ኤ አገልግሎት ዋና ስራ ሂደት ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ አማካኝነት የተመራው ነፃ የውይይት መድረክ በአራት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተካሄደ ሲሆን እነርሱም:-
1. የአሰራርና የአደረጃጀት ሁኔታዎች በምን መልኩ መሆን እንዳለባቸው...
2. በኮሌጁ የሚከናወኑ ተግባራት መነሻና መድረሻ የት ድረስ መሆን እንዳለበት....
3. በኮሌጁ ከአመራር እስከ ፈፃሚ ያለው ሚና ምን ምን መሆን እንደሚገባው...
4. ከአሁናዊ ፖሊሲና ስትራቴጂካዊ ሁኔታዎች አኳያ(ከ11 ዘረመሎች አንፃር) እንደ ተቋም በምን አግባብ መንቀሳቀስ ይኖርብናል በሚሉ ነጥቦች ላይ ውይይት ማድረግም ተችሏል::
ለውይይት ይተቀመጡ የመወያያ አጀንዳዎችን መነሻ በማድረግም በመድረኩ ተሳታፊዎች በጥልቅ በነፃነት ሀሳቦች ተነስተው ውይይት የተካሄደ ሲሆን ኮሌጁ ለ2018 በጀት ዓመት የያዛቸውን ተግባራት በተሻለ መንገድ እንዲተገብር የሚያስችለውን በርካታ ግብዓቶችን ከመድረኩ ማግኘትም ተችሏል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ነሃሴ 30/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል::
#መልካም_በዓል!!
Repost from Ethiopian Technical Excellence Institute- ITE
በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ያለው የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ስልጠና ምልከታ ተካሄደ፡፡
ከነሃሴ 15/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተሰጠ የሚገኘው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በተግባር ላይ የተመሰረተው በተለያዩ ማዕከላት ውስጥ በተዘጋጁ ወርክሾፖች በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ስልጠናው የሚገኝበት ሁኔታ የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር፣ የድሬዳዋ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸውና የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ አመራሮች በጉብኘቱ ወቅት ተገኝተዋል፡፡
Website: http://www.ftveti.edu.et/
Youtube ; http://www.youtube.com/fdretvtinstitute
facebook https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/@fdretvtistitute
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት አመት የተቋሙ መሪ እቅድ ለኮሌጁ ፑል አመራር አባላት አስተዋወቀ::
ኮሌጁ የ2018 በጀት አመት እቅዱን ከዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት ሲዘጋጅ የቆየው መሪ እቅድ ተጠናቆ በኮሌጁ ለሚገኙ ስራ ሂደቶችና ስራ ክፍሎች ቀርቦ እቅዱን ማስተዋወቅ ተችሏል::
የእቅድ ትውውቅ መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ የተዘጋጀው የኮሌጁ የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ እዳለፉት ጊዜያት የውጤት አመላቾች ላይ ያተኮረ ሳይሆን ዋናው ውጤት ላይ ያተኮረና ተጠያቂነትም ያለበት እንደሆነ የገለፁ ሲሆን አክለውም እንደ ተቋም በተቻለ መጠን ከመንግስት የተሰጠንን ተልእኮ ሊያስፈፅም የሚያስችል እቅድ ማዘጋጀት ላይ ትኩረት ሰጥተን ሰርተናልም ብለዋል::
የኮሌጁ የ2018 በጀት አመት እቅዱን ለመድረኩ ተሳታፊዎች ያቀረቡት የኮሌጁ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ስራ ክፍል ሀላፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ሲሆኑ ከአዲሱ የዘርፉ እሳቤ አንፃርና የተቋሙ ነባራዊ ሁኔታን መንሻ በማድረግ በእቅዱ የተካተቱ ተግባርና ሀላፊነቶችን በዝርዝር ገለፃ በማድረግ አስተዋውቀዋል::
በተጨማሪም ለኮሌጁ ዋና ስራ ሂደቶችና ደጋፊ ስራ ሂደቶች ካስኬድ ተደርጎ የሚወርደው እቅድ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎችም አጠቃላይ በቀረበው እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች ለእቅዱ አዘጋጆች ምክረ ሀሳቦችን መስጠትም ችለዋል::
መድረኩ በቀጣይ ቀናትም የሚቀጥል ሲሆን በኮሌጁ የሚገኙ የስራ ሂደቶችና ክፍሎች ከዋናው የኮሌጁ እቅድ ላይ የራሳቸውን እቅድ ካስኬድ በማዘጋጀት የእቅድ ስምምነት የሚፈራረሙ መሆኑም ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ነሀሴ 27.2017ዓ.ም
ድሬዳዋ
አድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት ለኮሌጁ የፑል አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት በGreen TVET እሳቤ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት አድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) በኮሌጁ ትግበራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በGreen Energy ዙሪያ በርካታ ስራዎችን በኮሌጁ እንዲሁም በአስተዳደሩ ማከናወኑን አስታውሰው ፕሮጀክቱ ያስቀመጠውን ግብ ከማሳካት አንፃር ብዙ ተግዳሮቶችን አልፎ አሁን ላይ ከሌሎች የፕሮጀክት ሳይቶች አንፃር የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገብ እንደሚገኝም ገልፀዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ይህን በ Green TVET እሳቤ ላይ ያተኮረ የግብዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ያስፈለገው በቀጣይ ኮሌጁ በትኩረት ከሚሰራባቸው ተግባራት ውስጥ የGreen TVET አንዱ በመሆኑ ከወዲሁ በዘርፉ እሳቤ ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲኖር ለማስቻል ያለመ እንደሆነው ገልፀዋል::
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ በቅድሚያ የአድራ ኢትዮጵያ(ADRA Ethiopia) ፕሮጀክት ዋና አላማ ግብን አስመልክቶ በፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ በየነ አማካኝነት ለመድረኩ ተሳታፊዎ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ዋና አስተባባሪው አያይዘውም ፕሮጀክቱ ከጅምሩ እንስቶ በኮሌጁ በቆየባቸው አመታት ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ያከናቸውን ዋና ዋና ቁልፍ ተግባራትና ያስመዘገባቸውን አመርቂ ውጤቶች በዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል::
የGreen TVET እሳቤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ሰነድ በኢንጂነር ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን Green Energy ከTVET ዘርፍ ጋር ያለውን ቁርኝትና ከቅርብ አመታት ወዲህም በዘርፉ ተቀዳሚ ትኩረት እያገኘ እንደሆነ በሚያመላክት ሁኔታ የግንዛቤ ስልጠናውን መስጠት ችለዋል::
የመድረኩ ተሳታፊዎች በተሰጣቸው የግንዛቤ ስልጠና መነሻነት ሀሳቦችን በማንሳት በግሩፕ የተወያዩ ሲሆን Green Energy ከትምህርትና ስልጠና አኳያ፣ ከቴክኖሎጂ አኳያ እንዲሁም አጠቃላይ ከኮሌጁ እንቅስቃሴ አኳያ በምን መልኩ አቀናጅቶ ለመተግበር ያስችላል የሚሉ ጉዳዮችን በዝርዝር አስቀምጠዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ነሃሴ 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+9
በIOM የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም በEDI የስልጠና ሰጭነትና አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው የቴክኒክ እና ሙያ ሰልጣኞችና ምሩቃን የንግድ ሃሳብ pitching ስልጠና እና ውድድር ተጠናቀቀ።
በአስተዳደሩ ከሚገኙ ሁለቱ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የተመረጡና የንግድ ሃሳብ ላላቸው ወጣቶች ከነሀሴ 14/2017 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 18/2017 ዓ.ም ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ስልጠና እና የንግድ ሃሳብ ውድድር ፍፆሜውን አግኝቷል::
በእለቱ በነበረው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የIOM ተወካይ አቶ ዘሪሁን እንደገለፁት ይህን መሰል ፕሮግራሞች ወጣቶች የተሻለ የንግድ ሃሳብ እንዲያጎለብቱ እና የንግድ ሃሳባቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው የሚረዱበት እንዲሁም የቢዝነስ አጋር የሚያገኙበትን አጋጣሚን የሚፈጥር ነው ያሉ ሲሆን አክለው በውድድሩ ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡትን ወጣቶች በሀገር አቀፍ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ የሚደረግ ይሆናልም ብለዋል::
በተጨማሪም በውድድሩ አሸናፊ የሆኑት ወጣቶች የንግድ ሃሳባቸውን ወደ መሬት የሚያወርዱበትን እና ንግዳቸውን የሚያስፋፉበት መንገድ እንደሚመቻችላቸውም በመድረኩ ማወቅ ተችሏል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ነሃሴ 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎፈቃድ ስራዎች ማስጀመሪያ እና የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በኮሌጁ ተካሄደ።
በዘንድሮ ክረምት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ይህን ምክንያት በማድረግም በተቋም ደረጃ በኮሌጁ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩን በዛሬው ዕለት ማከናወን ተችሏል::
በዛሬው ዕለት በኮሌጁ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በተቋሙ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ስፍራ ላይም አሻራቸውን እኑረዋል::
በቀጣይም በኮሌጁ የክረምት የበጎፍቃድ ስራዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚያከናውኑ ሲሆን በዚህም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ፣ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ መሰል ማህበረሰብ ተኮር ንቅናቄዎች ላይ እንደሚሰራ ተገልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ነሃሴ 9/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+9
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለኮሌጁ የቦርድ አባላት አቀረበ፡፡
በበጀት አመቱ የተቋሙን አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለቦርዱ የቀረበ ሲሆን በዚህም ኮሌጁ ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ በበጀት አመቱ የነበረውን የእቅድ አፈፃፀምና አጠቃላይ በኮሌጁ የተሰሩ የለውጥ ስራዎችን እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን ለቦርዱ ሪፖርት አቅርበው ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ በተቋሙ ሊሰሩ በእቅድ የተያዙ ዘርፈ ብዙ ስራዎችንም ለቦርድ አባላቱ በዝርዝር አመላክተዋል፡:
በመድረኩ የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግም የቦርድ አባላቱ ግብረ- መልሳቸውን የሰጡበት ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በቀጣይ በሚኖረው የስራ እንቅስቃሴ ላይ ምክረ-ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል::
በመጨረሻም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በቀረበው የኮሌጁ አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ማጠቃለያ እንዲሁም የቀጣይ ስራ አቅጣጫና መመሪያን በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ነሃሴ 7/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
