cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ማኅበረ አቤኔዘር መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዞ ማኀበር

✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ፅሁፎች ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞ https://t.me/Mahebare_Abenzer ሁሉም እንዲያነበው Share ያድርጉ ለማንኛውም መረጃዎች ለመጠየቅ @kedusurael22 ማናገር ይችላሉ 🇪🇹 ✝✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹 Join Us Today And Lets learn Together ✝✝✝

Більше
Рекламні дописи
198
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

''ስትጸልይ በማክበር ውስጥ መሆንን ተለማመድ፣ የልብና የሥጋ ማክበር ይኑርህ፣ የስሜቶች ሰላምም እንዲሁ። ቀስ በቀስ መዝሙራትን፣ ወንጌላትንና የዘወትር ጸሎቶችን አጥና። በሁሉም ጊዜ ውስጥ ጸሎት መጸለይን ተለማመድ፣ ስትሠራ፣ ስትራመድና ከሌሎች ሰዎች ጋር ስትቀመጥ እንኳ፣ ዘወትር ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ኃጢአተኛውን ማረኝ እያልህ መጸለይን ተለማመድ። በማንኛውም ጊዜ ለሌሎች ሰዎች መጸለይን ተለማመድ፣ ለሁሉም ሰዎችም ፍቅር አሳይ፣ ለጠላቶችህና አንተን ለሚሰድቡህ ሰዎች እንድትጸልይ የሚያዝህን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ተለማመድና ተግባራዊ አድርግ።" #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
Показати все...
ምሳሌ 31 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል። ¹¹ የባልዋ ልብ ይታመንባታል፥ ምርኮም አይጐድልበትም። ¹² ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም። ¹³ የበግ ጠጕርና የተልባ እግር ትፈልጋለች፥ በእጆችዋም ደስ ብሎአት ትሠራለች። ¹⁴ እርስዋ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ ከሩቅ አገር ምግብዋን ትሰበስባለች። ¹⁵ ገና ሌሊት ሳለ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለገረዶችዋም ተግባራቸውን ትሰጣለች። ¹⁶ እርሻንም ተመልክታ ትገዛለች፤ ከእጅዋም ፍሬ ወይን ትተክላለች። ¹⁷ ወገብዋን በኃይል ትታጠቃለች፥ ክንድዋንም ታበረታለች። ¹⁸ ንግድዋ መልካም እንደ ሆነ ትመለከታለች፤ መብራትዋ በሌሊት አይጠፋም። ¹⁹ እጅዋን ወደ አመልማሎ ትዘረጋለች፥ ጣቶችዋም እንዝርትን ይይዛሉ። ²⁰ እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች። ²¹ ለቤትዋ ሰዎች ከበረዶ ብርድ የተነሣ አትፈራም፥ የቤትዋ ሰዎች ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና። ²² ለራስዋም ግብረ መርፌ ስጋጃ ትሠራለች፤ ጥሩ በፍታና ቀይ ግምጃ ትለብሳለች። ²³ ባልዋ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ በበር የታወቀ ይሆናል። ²⁴ የበፍታ ቀሚስ እየሠራች ትሸጣለች፥ ለነጋዴም ድግ ትሸጣለች። ²⁵ ብርታትና ከበሬታ ልብስዋ ነው፤ በኋላም ዘመን ላይ ትስቃለች። ²⁶ አፍዋን በጥበብ ትከፍታለች፤ የርኅራኄም ሕግ በምላስዋ አለ። ²⁷ የቤትዋንም ሰዎች አካሄድ በደኅና ትመለከታለች፥ የሀኬትንም እንጀራ አትበላም። ²⁸ ልጆችዋ ይነሣሉ፥ ምስጋናዋንም ይናገራሉ፤ ባልዋ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፦ ²⁹ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፥ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ። ³⁰ ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ³¹ ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት፥ ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።
Показати все...
✝✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+ =>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል:: +ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው:: +መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል:: +ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16) +ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:- 1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው 2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር:: +ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች:: +ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል:: +ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል:: +በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:- "ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ: አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ:: +በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል:: +ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: +በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል:: +እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና:: =>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን:: =>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) 2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ) 3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን =>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† =>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: +በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት:: +ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች:: +ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች:: +የአምላክ እናቱ *እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: *ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: *የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: *የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: *የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: *እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች:: +ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: +አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: =>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ? 1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7) 2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: 3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1) 4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: 5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: 6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና 7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: =>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን:: =>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ 2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ 3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት 4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ) 3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም 5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) =>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
Показати все...
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖✝ ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ✝ቅዱስ እንድራኒቆስ +"+✝ =>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር ደምሮ አስተምሮታል:: +ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር:: ይሕ የተፈጸመ ገና መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20) +ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10 ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት ተቀብሏል:: እንደ ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን ሰብኳል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት አምላኩን አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ መልዕክቱ 16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው:: +ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ከቅዱስ ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል አብርተዋል:: እጅግ ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት ቤቶችን አፍርሰው አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል:: በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል:: +ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ በዚሕች ቀን አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር ገንዞ ቀብሮታል:: +"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+ =>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል:: +ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ (ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል:: በዚህም ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል:: ❖የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ ክብራቸውን ያድለን:: ❖ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት 2፡ ቅዱስ ደቅስዮስ 3፡ ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት 4፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 5፡ አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት 6፡ አባ ጳውሊ የዋህ ++"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ: ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
†✝†🌷 እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †✝†🌷 †✝†🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷†✝† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ✝✝✝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝✝✝ + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++ መጽሐፈ ስንክሳር፣ ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ +++መልካም ዕለተ ሰኞ መልካም ቀን። +++
Показати все...
ስንክሳር_ዘወርሃ_ግንቦት_ሃያ_አንድ_.mp33.05 MB
++"+ በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ:: አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ:: በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ:: ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ:: ይጠራኛል እመልስለትማለሁ:: በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ:: አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ:: ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ:: ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: +"+ (መዝ. 90:13-16) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.