uk
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Відкрити в Telegram

EEP Communication

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 533 підписників, посідаючи 8 338 місце в категорії Технології та додатки та 2 162 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 533 підписників.

За останніми даними від 29 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 6, а за останні 24 години на -1, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 25.10%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 16.85% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 901 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 2 619 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 8.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
EEP Communication

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 30 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Технології та додатки.

15 533
Підписники
-124 години
-167 днів
+630 день
Архів дописів
photo content
+3

በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ ለኬንያ በሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል  መጠን ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው .........////........ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የተከሰተው ድርቅ ለኬንያ በሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል  መጠን ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል በሚል የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ ካላት የኃይል ምርት ለጎረቤቶቿ በፍላጎታቸው መጠን እያቀረበች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ የተሻለ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ከፍተኛ የውሃ ሀብት ባለቤት የሆነችና ከውሃ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለማመንጨት ተስማሚ መልክዐ ምድር ያላት አገር መሆኗን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡   በሀገሪቱ ያለውን ከፍተኛ የውሃ ሀብት በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መቻሉ ለኢትዮጵያና ለጎረቤት ሀገሮች ትልቅ በረከት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህም በቀጠናው ያለውን አንድነትና ትብብር ለማጠናከር እንደሚያግዝ  ገልፀዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ኬንያ፣ ጅቡቲና ሱዳን የኃይል ፍላጎት መጠናቸው እያደገ በመምጣቱ በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎታቸውን ማሟላት የሚያስችል ሰፊ የኤሌክትሪክ ምርት አቅም አለ፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች በአብዛኛው በቂ ውሃ እንዲይዙ በመደረጉ ምንም ዓይነት የኃይል እጥረት አለመኖሩን ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡ ሚኒስትሩ እንደገለፁት ባለፉት ሁለት ዓመታት በዝናብ መዛባት የተነሳ ግድቦች በሚፈለገው መጠን ባይሞሉም በኃይል አቅርቦትና የሽያጭ ገቢ ላይ ግን ምንም ዓይነት ተፅዕኖ አላሳደረም፡፡ ስለሆነም በአፍሪካ ቀንድ ያለው የአየር መዛባት ኢትዮጵያ ለኬንያ በምታቀርበው ኃይል ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡ ሰሞኑን ኬንያ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የኃይል ማመንጫ ግድቦች የውሃ መጠን ክፉኛ በመቀነሱ ከኢትዮጵያ ማግኘት ከሚገባኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ግማሹ ብቻ እያገኘሁ ነው ስትል በሀገሪቱ የኃይል እና የነዳጅ ሚኒስትር ዴቪስ ቺርቺር በኩል መግለጫ መስጠቷን ቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ የተሰኘው ድረ-ገፅ ማስነበቡ ይታወሳል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

በማሰራጫ መስመር ላይ በተፈጠረ ችግር ምክንያት በአዲስ ሰፈር እና በወረገኑ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው ኃይል ተመልሷል .........////......... ከቃሊቲ አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል በሚቀበሉት የወረገኑ እና የአዲስ ሰፈር ማከፋፈያ ጣቢያዎች ተቋርጦ የነበረውን ኃይል ማገናኘት መቻሉን የቃሊቲ አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃላፊ ገለጹ፡፡ የጣቢያው ኃላፊ አቶ እጅጉ ማሬ እንደገለጹት በጣቢያዎቹ ላይ የተቋረጠው ኃይል በዝቅተኛ የማሰራጫ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት ነው፡፡ የኃይል መቋረጥ ችግሩ የተፈጠረው የኃይል ማሰራጫ መስመሩ ተበጥሶ ከቃሊቲ አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ አዲስ ሰፈር እና ሜክሲኮ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ ከተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጋር በመገናኘቱ ነው፡፡ ለንክኪው ምክንያት የነበረው የስርጭት መስመር ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ በተዘረጋበት መስመር አቅራቢያ የተዘረጋ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ በቃሊቲ አንድ- አዲስ ሰፈር ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ላይ የተፈጠረው ችግር ከቃሊቲ አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያገኘውን የወረገኑ ማከፋፈያ ጣቢያን ኃይል አቋርጦ እንደነበርም አቶ እጅጉ ተናግረዋል፡፡ ችግሩ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 5:57 ደቂቃ ላይ እንደተከሰተ ያነሱት የጣቢያው ኃላፊ በዚህም የአዲስ ሰፈር ማከፋፈያ ጣቢያ ለ17 ደቂቃ እንዲሁም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርበው የወረገኑ ማከፋፈያ ጣቢያ ደግሞ ለ23 ደቂዎች ያህል ኃይል ተቋርጦባቸው መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመቀናጀት የተቋረጠውን ኃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ ማገናኘት መቻሉንም አቶ እጅጉ ተናግረዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+2

ተቋሙ ባከናወነው የኮንትራት አስተዳደርና የቁጥጥር ሥራ የተገነባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ………...///……... ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃይል ማቅረብ የሚችል ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና የማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ የሱፐርቪዥን እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ግርማ ዘለቀ እንደገለፁት የተቋሙ የማማከር ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ መጥተዋል። ተቋሙ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ ለገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ ለደርባ ሲሚንቶ፣ ለለሚ ሲሚንቶ፣ ለሲ ኤንድ ኢ የብረት ማቅለጫ እና ለአባይ ሲሚንቶ የማማከር ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልፀዋል። ለአየር መንገዱ ለተገነባው የማከፋፈያ ጣቢያ የአዋጭነት ጥናት፣ ዲዛይን የማፅደቅ፣ የጨረታ ዝግጅት፣ የሳይት ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር ሥራዎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማከናወኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ አየር መንገዱ የራሱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እንዲኖረው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቀረበ ምክረ ሃሳብን ተከትሎ ነው ፕሮጀክቱ የተገነባው። አዲሱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ከቃሊቲ አንድ ወደ ኮተቤ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በሁለት በኩል ኤሌክትሪክ እንዲያገኝ ታስቦ የ7 ኪሎ ሜትር ግንባታ እንደተከናወነለት ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተደጋጋሚ ያጋጥሙት የነበሩትን የኃይል ማነስ እና የመቆራረጥ ችግሮች በዘላቂነት መፍታት እንደሚያስችለው ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር የኃይል ተጠቃሚ በመሆኑ ምክንያት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደንበኛ ሆኗልም ብለዋል። የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን የኦፕሬሽን እና የጥገና ሥራዎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያከናውን የገለፁት ዳይሬክተሩ ለዚህም የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ( Service Level Agreement) ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር መፈራሩሙን ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን፣ ለግንባታው 7 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በጀት ተይዞለት መከናወኑን ተናግረዋል። የፕሮጀክቱ የፋይናንስ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸፈነ ሲሆን ጀኔራል ኤሌክትሪክ እና ሲ.ሲ.ሲ.ኤስ የተባሉ ሥራ ተቋራጮች ግንባታውን በጋራ አከናውነዋል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+4

የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታ 35 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል ………..///…….... የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ የዲጂታላይዜሽን እና አቅም ማሻሻል ፕሮጀክት አንድ ሥራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ወ/ ጊዮርጊስ እንደተናገሩት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ 35 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል። በአሁኑ ወቅት በፕሮጀክቱ የሁለት የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከላት እና አንድ የመኖሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት አቶ በኃይሉ በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የፕሮጀክቱን ግንባታ 70 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ከሁሉም የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ወደ አንድ ማዕከል መሰብሰብ የሚያስችሉ የኮሙዩኒኬሽን እና የኔትወርክ መሳሪያዎች ፍብረካ መጀመሩንም ነው ሥራ አስኪያጁ የገለፁት። በመቆጣጠሪያ ማዕከላቱ ውስጥ የሚተከሉ ሰርቨሮች ፍብረካ መጠናቀቁን የጠቆሙት አቶ በኃይሉ የፍተሻና ሙከራ ሥራዎች ከተከናወኑ በኃላ ማጓጓዝ እንደሚጀመር ተናግረዋል። እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የኃይል ማመንጫና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን የመረጃ ልውውጥና የግሪድ ክትትል ሥርዓቱን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ሶፍትዌሮች እየበለፀጉ ይገኛሉ። ከሁሉም የኃይል ማመንጫዎች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት የሚላኩ መረጃዎችን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል የሚረዱ የደህንነት መሳሪያዎች እንደሚኖራቸውም ነው አቶ በኃይሉ ያስታወቁት። የብሔራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ፕሮጀክቱ በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ ከሚገኘው የመቆጣጠሪያ ማዕከል በተሻለ የኦፕሬሽን ሥራዎችን የሚያቀላጥፉ ዘመናዊ ሶፍትዌሮችና የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ይኖራቸዋል ብለዋል። ፕሮጀክቱ በሥራ ላይ ካሉት የኃይል ማመንጫዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች በተጨማሪ ወደፊት የሚገነቡትን የኃይል መሰረተልማቶች ታሳቢ በማድረግ እየተገነባ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የፕሮጀክቱን ግንባታ የፈረንሳዩ ጀኔራል ኤሌክትሪክ እና የቻይናው ሲኖ ሃይድሮ ኩባንያ በጋራ እያከናወኑ ሲሆን የማማከር ሥራውን ደግሞ ሒፋብ የተባለ የፊንላንድ ኩባንያ እያከናወነ ይገኛል። ፕሮጀክቱ 57 ነጥብ 67 ሚሊዮን ዩሮ እና ከ102 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል፡፡ የፕሮጀክቱ የፋይናንስ ወጪ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የሚሸፈን ነው። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content

ተቋሙ ያለአግባብ ሲከፈል የነበረ የኢንሹራንስ ክፍያ ማስቀረት ችሏል ---///--- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2015 በጀት ዓመት የመድን ዋስትና የማያስፈልጋቸውን ንብረቶች በመለየት ያለአግባብ ሲከፈል የነበረ የኢንሹራንስ ክፍያ ማስቀረቱን በተቋሙ የንብረት አስተዳደርና ጥገና መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የንብረት፣ ሪስክ እና ኢንሹራንስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሣህሌ ደግፍ እንዳስታወቁት በበጀት ዓመቱ ለኢንሹራንስ ሽፋን ሊከፈል የነበረ ንብረትን የሥጋት ደረጃ በመለየት ከ 59 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል፡፡ ተቋሙ ወጪውን ማዳን የቻለው በኮንትራክተሮችና አማካሪ ድርጅቶች ስም ለሚገኙ እንዲሁም በሰነድ አለመሟላት የተነሳ ጉዳት ቢደርስባቸው የካሳ ክፍያ ለመጠየቅ አስቸጋሪ ለሆኑ ተሸከርካሪዎችና የግንባታ ማሽነሪዎች የሚከፈለውን የኢንሹራንስ ክፍያ በማስቀረት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ለንብረት ኢንሹራንስ ሽፋን የሚከፈለውን ክፍያ ለመቀነስ በተከናወነው ሥራ በ2014 በጀት ዓመት ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታውሰዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጠቅላላ ውድመት ደርሶባቸዋል ተብለው የተለዩ ተሽከርካሪዎች አዋጭነታቸው ታይቶ በተቋሙ ጋራዥና በራሱ በመድን ድርጅት በኩል እንዲጠገኑ ተደርገዋል፡፡ በተያያዘ ዜና ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከተሸከርካሪዎች የጉዳት ኢንሹራንስ ሽፋንና ከኃይል ማመንጫና ማከፋፈያ ንብረቶች ጉዳት ተቋሙ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ማግኘቱን ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡ በኢንሹራንስ አሰራርና አፈፃፀም ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት በኩል ሥልጠና መሰጠቱንና ለተቋሙ ንብረቶች የስጋት ጥናት ለማከናወን የአማካሪ ቅጥር ለማከናወን እየተሰራ መሆኑንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+1

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሞግዚት (Child Caregivers) የሥራ መደብ ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ አውጥቶ የጽሁፍ ፈተና ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ከህዳር 03 ቀን 2016 ዓ.ም እሰከ ህዳር 05 ቀን 2016 ዓ.ም በወጣላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ በሚገኘው በተቋሙ ዋና መ/ቤት የሰው ኃይል ምደባ ቢሮ የቃል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ለቃል ፈተና ተዘጋጅታችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+2