uk
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Відкрити в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Показати більше
613
Підписники
Немає даних24 години
+27 днів
-930 днів
Архів дописів
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ ፰ (8) ቀን። ❤ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_በሁለት_ወገን #ድንግል_ለሆነች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል ማርያም ለታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ላለች #ለቤተ_ክርስቲያንዋ_ለቅዳሴ_ቤት ከእመቤታችን #ከሠላሳ_ሦስቱ_በዓል_አንዱ_ለሆነ_በዐል (እርሱም #ጌታችን ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ውሃ (ጠበል) ነው፣ ለርማኖስ እናት #ለቅድስት_ትምዳ_ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከአንድ ሽህ ሁለት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ ከቅዱሳን ከአትካሮንና ከአውሎጊስ ከበዓላቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤በዚች ቀን #አምላክን_የወለደች_በሁለት_ወገን #ድንግል_የሆነች_የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል #ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ #ክርስቲያንዋ_ለቅዳሴ_ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው። ❤ ይህም እንዲህ ነው ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት "ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ" አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ። ❤ ኄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት "ወደ እስራኤል አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ" አዘዘው። በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት እርሷም እስከ ዛሬ አለች ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ በዛሬዪቱ ሰኔ 8 ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ። ❤ እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 8 ስንክሳር።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ዕብል_ለቅዳሴ_ቤትኪ_ሕንፅት። ኀበ አንቅዐ ወሌድኪ ማየ በረከት። #ማርያም_ድንግል በስምከመ በቊዔት። እስመ ይትወሀብ ለዘጸለየ በኵሉ ዕለት። ሠናይ ሀብት ወፍጹም ፍት"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_8።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እፎ እስፋሕ ለከ ሥጋየ። በምድረ በድው ኀበ አልቦ ዕፅ ወማይ። ከመዝ በመቅደስከ አስተርአይኩከ"። መዝ 62፥1-2" ወይም መዝ 77፥15-16።  የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 4፥14-17።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወአስተዮሙ ከመ ዘእምቀላይ ብዙኅ። ወአውኃዘ ማየ ከመ ዘእምአፍላግ። ወአውጽአ ማየ እምዕብን"። መዝ 77፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥10-13 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-51። የሚነበበው ወንጌልን ዮሐ 4፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለሐዋርያት_ሰኔ_ጾም_ሁለተኛ_ሳምንት #ስለ_ዕርገቱና_ስለ_ጰራቅሊጦስ ለሚነገርበት ዕለተ ሰንበት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ሃሌ ሉያ በ፫ "#ዐረገ_እግዚአብሔር_በቃለ ቀርን #በይባቤ_ዐርገ ወበቃለ ቀርን ወነበረ በየማነ አቡሁ (ዐርገ) አዝ፣ #ዐርገ_በስብሐት_ውስተ_ሰማያት ተኰነኑ ሎቱ መላእክት (ዐርገ) አዝ፣ ተኰነኑ ሎቱ መላእክት ኵሉ ኃይል ወኵሉ ፍጥረት (ዐርገ) አዝ፣ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ ለንጉሥነ። ትርጉም፦ እግዚአብሔር በመለከት #ድምፅ_ዐረገ በዕልልታና #በመለከት_ድምፅ ዐረገ፤ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ፤ በክብር በምስጋና በጌትነት #ወደ_ሰማያት_ዐረገ፤ መላእክት ተገዙለት ኃይል ሁሉ ፍጥረት ሁሉ ተገዙለት፤ ለአምላካችንም ዘምሩ፤ አመስግኑ ለንጉሣችን ዘምሩ አመስግኑ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "ልበ ንጹሐ ፍጥር ሊተ እግዚኦ። መንፈሰ ርቱዓ ሐድስ ውስተ ከርሥየ። ኢትግድፈኒ እምቅድመ ገጽከ"። መዝ 50፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 12፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 2፥20-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 2፥14-22። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 14፥22-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ። መልካም ዕለተ ሰንበትና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ሰኔ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለድንግል_ማርያም_ቤተ ክርስቲያን_ለተከፈተበትና ለከበረችበት፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም ለሆነ #ለአባ_አበስኪሮን_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ መኰንን አርማንዮስ ካሠቃያቸው #ከአስራ_ስድስት_ሺህ_ሰማዕታት ከዕረፍታቸው መታሰቢያና ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           ✝️ ✝️ ✝️ #በዚች_ዕለት_አምላክን_የወለደች_የእመቤታችን_የድንግል_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን_የተከፈተበትና_የከበረችበት ነው። እርሷም ዌላ በሚባል አደባባይ ያለች ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ተዘግታ የኖረች ነበረች። ይኸውም በአንድ ሽህ ሃያ ዓመተ ሰማዕታት ነው። ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ሰው ለሆነ ሕይወትና መድኃኒት አድርጎ እርሷን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።                                                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_አበስኪሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዝ በደረሰችው ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት። ❤ መኰነንኑም ወደ አገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልደፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስና ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮስ ጋር ተስማሙ። በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ። ❤ የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ። ይህንም ሁሉ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር። ❤ ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ያም መሠርይ "የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ" ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ። ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን "የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለበት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አንተን ይቀጣሃል" አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ። በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ሰኔ 7 ቀን ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ❤ ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን እንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ክፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞተ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን በፈረስ ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም "ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ" አላቸው። እነርሱም "ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ" አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ። ❤ ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅዱሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት። የአገር ሰዎችም በጥዋት ነቅተው ወደ ውጭ በወጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በአባ በአበስኪሮን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 7 ስንክሳር።                        ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ዕብል_ለርኅወተ_ቤትኪ_ዮም። ከመ ኤልያስ አርኀወ ኆኅተ ዝናም። በስሱ አውራኅ ወበሠላስ ዓም። ማርያም ሥመሪ አርኅዎቶ ለሕሊናየ ሕቱም። ከመ ላዕሌሁ ይትከዐው ምስለ ጽድቅ ሰላም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 7።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #ሰኔ ፯ (7) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ከሾሟቸውና_በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው #ከ47ቱ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ማቴዎስ_ዘእንደርታ_ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዐልና ለታላቁ አባት #ለጻድቁ_ለሐዋርያም ለደራሲም ለመላእክት በዐል የሚቀደሰው ከ14_ቅዳሴ አንዱ የሆነ በስሙ የተሰየመው ቅዳሴ ለደረሰ ለተከራካሪ መምህርም #ለያዕቆብ_ዘሥሩግ_ለዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አቡነ_ማቴዎስ_ዘእንደርታ፦ እኚህ ጻድቅ ትውልድ አገራቸው እንደርታ ሲሆን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሾሟቸውና በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው ከ 47ቱ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ጻድቁ መላ ሰውነታቸው እንደ እሳት ያቃጥል ነበር። ወንጌልን በመስበክና በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ብዙ ያገለገሉ ታላቅ አባት ናቸው። መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት ላይ።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አቡነ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ፦ አገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት አገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ መካከል በምትገኝ ሥሩግ በምትባል አገር ስለሆነ ያዕቆብ ዘሥሩግ ተባለ። በ 3 ዓመቱ እናቱ ቤተ መቅደስ ስትወስደው መልአክ እጁን ይዞ በሊቀ ጳጳሱ እጅ እንዲቆርብ አድርጎታል። በዚህም ጊዜ ምሥጢራት ሁሉ ተገልጠውለታል። ገና በ 7 ዓመቱ ስለ ሦስት ነገሮች በእጅጉ ያለቅስ ነበር። "ነፍሴ ከሥጋዬ ተለይታ ስትወጣ ከጌታችን ጋር ስትገናኝና መጨረሻውን ፍርድ ስሰማ እነዚህን ሦስት ነገሮች በእጅጉ እፈራለሁ" እያለ ያለቅስ ነበር። ❤ በ 12 ዓመቱ ብሉይንና ሐዲስን አጠናቆ ተመምሮ ጨርሷል። ጸጋውን ዐውቀው 5 ቱ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው እጅ ነስተውት አዲስ ድርሰት ድረስልን ቢሉት እርሱም በፍጹም ትሕትና "በእናንተ ፊት እንኳን አዲስ ድርሰት ልደርስ ቀርቶ የተደረሰውንም መናገር አልችልም"። አላቸው። እርሱ በነበረበት ዘመን በሮማው መናፍቅ ልዮን አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለችበት ጊዜ ነበርና እነ ዲዮስቆሮስ "የውሾች ጉባኤ" ከተባለው ከኬልቄዶን ጉባኤ ተለይተው ሃይማኖትን ሲያጸኑ ልዮንንም ማውገዛቸውን ያዕቆብ ሲሰማ በዲዮስቆሮስ ጽናት በእጅጉ ተደስቶ ደብዳቤ ጽፎ አመስግኖታል። እነ ልዮንን ግን አውግዞ እረግሟቸዋል። ልዮንም ተከታይ ባገኘ ብሎ "እኔን ምሰል" በማለት ለያዕቆብ ደብዳቤ ጻፈለት። ያዕቆብም "ሳጥናኤል ከመላእክት ጋር ምን አንድ አደረገው? አንተ ርኩስ ነህ፤ የዲዮስቆሮስን ጥርስ አስወልቀህ፣ ጢሞን አስነጭተህ፣ ሃይማኖትህን የቀየርህ ከሁለት ዓለም ስደተኛ ጋር አልተባበርም፣ ይልቅስ ንስሓ ግባ፣ ንስሓ ባትገባ ግን አንተ ዲያብሎስ ነህ ተከታዮችህም አጋንንት ናቸው። በማለት መልሱን ጽፎለታል። እምቢ ብሎ በክህደቱ ቢጸናበትም አውግዞ እረግሞ ንጽሕናውን ቅድስናው እንደ መላእክት ነው የተባለለት ያዕቆብ ዘሥሩግ ጻድቅም ሐዋርያም ደራሲም ተከራካሪ መምህርም ነው። ሦስት ድርሰቶች ያሉት ሲሆን በስሙ የተጠራው ቅዳሴም አለው። ዕረፍቱ ሰኔ 7 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ያዕቆብ ዘሥሩግ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱም ይማረን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤              ❤ #ሰኔ ፮ (6) ቀን። ❤ እንኳን #ከእስክንድርያ_ከተማ_ለሆነ_ለመነኰስ #ሰኔ #ለአባ_ቴዎድሮስ_ሰማዕትነት_ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለቅዱሳን_ለአውሳብዮስ፣ #ታማን፣ #ሐርዋግና_ለባኮስ ለተባሉ #ለአገረ_እስና_ለአራት መኳንንት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከአገረ መርዩጥ #ከአርባ_ሰማዕታትና_ከሌሎች_አርባ_ሰማዕታት #ከመነኰስ_ገብረ_ክርስቶስም_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #መነኰስ_አባ_ቴዎድሮስ፦ ይህም የታመነና ንጹሕ ቅዱስ ተጋዳይ በእስክንድርያ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ በመልካም ገድል ተጠምዶ ኖረ። ታናሹ አርዮሳዊ ቈስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ አርዮሳዊ ጊዮርጊስ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አድርጎ ሾመው። ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስንም ከመንበሩ አሳደደው ይህ አርዮሳዊ ጊዮርጊስም በቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ሲቀመጥ ያን ጊዜ በአርዮሳውያንና በእስክንድርያ ምዕመናን መካከል ታላቅ መተላለቅ ሆነ ሃይማኖታቸው የቀና ብዙዎች ምዕመናንም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተገደለ። ❤ ከዚህም በኋላም ይህ አርዮሳዊ ጊዮርጊስ ስለ አባ ቴዎድሮስ እርሱ አርዮሳውያንን ተከራክሮ እንደሚአሸንፋቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ማስረጃ በማምጣትና በማስፈረድ ያሳፍራቸው ነበር ያን ጊዜ ይህን መነኰስ አባ ቴዎድሮስን ይዘው በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ❤ ከዚህ በኋላም ኃይለኞች ሩዋጮች በሆኑ ፈረሶች ላይ እግሮቹንና እጆቹን አሥረው በሰፊ ሜዳ ውስጥ እንዲአስሮጡአቸው አዘዘ ይህንንም በአደረጉ ጊዜ ሕዋሳቱ ሁሉ ተባጣጠሱ ራሱንም ተቆረጠች እንደ ዚህም ሁኖ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ሦስት አክላትንም ተቀዳጀ አንዱ ድንግልናውን ጠብቆ ስለ መመንኰሰ ሁሉተኛው ሃይማኖትን ስለ ማስተማሩና ተከራክሮ መናፍቃንን ስለመመለሱ ሦስትኛውም ስለ ቀናች ሃይማኖት ደሙን በማፍሰሱ ነው። ❤ ከዚህም በኋላ ምዕመናን የተቆረጡና የተበተኑ ሕዋሳቱን ሰብስበው በሣጥን ውስጥ አድረጓቸው በዚች ዕለትም ሰኔ 6 ቀን መታሰቢያ በዓሉን አደረጉ እንደ ሌሎቹ ቅዱሳን ሁሉ የምስጋና ድርሰትን በሮማይስጥ ቋንቋ ደረሱለት በጸሎት መጽሐፋቸውም ውስጥ ጻፉት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቴዎድሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የአገረ_እስና_አራቱ_መኳንንት፦ እሊህም ቅዱሳን ለእስና ምሰሶዎቿ ነበሩ ጸሐፊዎቿም ነበሩ ለብዙዎች ድኆችና ምስኪኖች ይመጸውቱ ነበር። ወደዚያች አገርም መኰንኑ አርያኖስ ዳግመኛ በተመለሰ ጊዜ እኛ ክርስቲያን ነን ክብር ይግባውና ሰማይና ምድር በጸኑበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን" በማለት በግልጥ በፊቱ እየጮኹ ተቀበሉት። ❤ አርያኖስም ሰምቶ በየራሱ በሆነ ሥቃይ አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ ቆረጠ የምስክርነታቸው አክሊል ሰኔ6 ቀን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ6 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#ሰላም_ለከቴዎድሮስ_መነኰስ። እሡረ አእጋር ወአእዳው በእግረ ፈረስ። እምኃይለ ሩጸቱ ፍሉሕ አምሳለ ነፋስ። እምአባልከ ተመቲራ ለእንተ ሠረረት ርእስ። እግዚአብሔር አስተቀጸላ በአክሊል ሠላስ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_6።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ። ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም። ወይትሌዓል ቀርኑ በክብር"። መዝ 111፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 9፥13-ፍ.ም፣ ያዕ 1፥12-19 እና የሐዋ ሥራ 5፥26-32። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥32-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ወይም የ­ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም በዐልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ ከዚህም በኋላ አንጾኪያ ከተማ አደረሱበት ወደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አቀረቡት እርሱም በእሳት በአፈሉት በወይን በሙጫ ድፍድፍ በማቃጠል አሠቃየው ከዚያም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አዳነው። ዳግመኛም በአንገቱ ከባድ ደንጊያ በሰንሰለት አሥረው ወደ ባሕርም አንከባለው ግማሽ ሥጋውን እንዲአሠጥሙ ግማሹን ግን እንዳያሠጥሙ አዘዘ እነርሱም በባሕሩ ዳር ታላቅ ምሰሶ ተከሉ በዚያም እንዳዘዛቸው አድርገው አሥረው ተዉት በዚህ ሥቃይም ከቀኑ እስከ ሰባት ሰዓት ዋለ ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ፈትቶ አወጣው እንደ ቀድሞውም ጤነኛ አደረገው ንጉሡም አይቶ አደነቀ ሰያፊውንም ፈጥኖ አንገቱን ሰኔ 5 ቀን ቆርጦ በባሕር ዳር ከምድር ላይ ጣለው ሥጋውንም አንሥቶ ከቊርበት በተሠራ ጋን ውስጥ ጨምረው ሥጋውም ከራሱ ጋራ ተገናኘና እንዳልተቆረጠ ሆነ ጋኑም በሃያ ቀን እስክንድርያ እስከሚደርስ ድረስ ሰው ሳይሸከመው ብቻውን የሚጓዝ ሆነ። ❤ የቦሀ አገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ መጡ ተሸክመውም በቦሀ አገር ከአለው ቤቱ ውስጥ አስገብተው ከወንድሙ አባ ጴጥሮስ ጋራ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባ ብሶይና በአባ ጴጥሮስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ቢፋሞን፦ ይህ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ የእናቱ ወንድም ልጅ ነበር ዮሐንስም ታሥሮ ሳለ ያገለግለው ነበር። ዮሐንስም ገድሉን በፈጸመ ጊዜ ሥጋውን ገነዘ በበድኑ ላይም እንዲህ ብሎ አለቀሰ "ከእግዚአብሔር የተለየሁ ሁኜ ብቻዬን እንዴት ትተወኛለህ" ከቅዱስ ዮሐንስ ሥጋም እንዲህ የሚል ቃል ወጣ ወዳጄ ቢፋሞን ከእኔ ጋራ መኖርን ከፈለግህ ፈጥነህ ወደ መኰንኑ ሔደህ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ታመን ነገም ወደ እኔ ትመጣለህ"። ይህንንም ሰምቶ የዮሐንስን ሥጋውን ቀበረ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሔደ። ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እየታመነ የረከሱ ጣዖታቱን ሰደበ። መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚህም በኋላ ራሱን ሰኔ 5 ቀን በሰይፍ ቆረጠ የምስክርነቱንም አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #መነኰሳዪት_ቅድስት_ማርታ፦ ይቺም ቅድስት ሃይማኖቷ የጸና ምግባርዋም የቀና ክርስቶስ ያደረባት ናት። በስደትም ዐረፈችና በተራራ ውስጥ ተቀበረች የመነኰሳዪት የቅድስት ማርታ በረከቷ ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 5 ስንክሳር።                                                      ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ይትነሥእ እግዚአብሔር ወይዘረዉ ፀሩ። ወይጒየዩ ጸላእቱ እምቅድመ ገጹ። ከመ የኀልቅ ጢስ ከማሁ የኀልቁ"። መዝ 67፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 2፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 3፥1-11 እ የሚነበበው የሐዋ ሥራ 16፥35-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥8-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ   ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ሰሞንና የጾም ጊዜ ይሁንልን። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለታማኛና ተጋዳይ ለሆነ ለምሥራቃዊው አባት #ለቅዱስ_ያዕቆብ ፣ ለተመረጠ ኃያል ተጋዳይ #ለአባ_ብሶይ_ለዕረፍታቸው_በዓል፣ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅል ለአጎት ልጅ #ለቅዱስ_ቢፋሞን ምስክር ለሆነበትና ሃይማኖቷ ለጸና ምግባርዋም ለቀና ክርስቶስ ላደረባት #ለመነኰሳዪት_ለቅድስት_ማርታ_ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ #ከቅዱሳን_ከመርቆሬዎስና #ከመቃርስ፣ #ከይስሐቅና_ከዕብሎን_ከዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ #ከአብላርዮስም ከምስክርነቱ መታሰቢያና በጌታችን ስም በባሕር ውስጥ በመስጠም ከዐረፈ #ከቅዱስ_መቃርስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ምሥራቃዊው_አባት ቅዱስ_ያዕቆብ፦ ይህም ቅዱስ ከምዕመን ዋልንጦስ ዘመን በኋላ የታላቁ ቈስጠንጢኖስ ልጅ በሆነ በታናሹ ቈስጠንጢኖስ ዘመንና በከሀዲው ሉልያኖስ ዘመን በምሥራቅ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም በገድል ተጠምዶ ኖረ። ዋልንጦስ ከተገደለ በኋላም በእርሱ ፈንታ ወንድሙ ነገሠ እርሱም አርዮሳዊ ነበር የጣዖት ቤቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሃይማኖታቸው የቀናውን የምዕመናንን አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲዘጉ አርዮሳውያንን አዘዛቸው ምዕመናን በግዳጅ እስቲገቡ ድረስ እንዲሁ አደረጉ። ይህም የንጉሡ ትእዛዝ በሚገዛው አገር ሁሉ ደረሰ። ❤ ይህም አባ ያዕቆብም ይሁን በሰማ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እሳትነት ልቡ ነደደ ያንጊዜም ተነሥቶ ወደ ቊስጥንጥንያ ሔደ በምዕራብ በኩል የተነሡበትን ጠላቶቹን ሒዶ ለመውጋት ሲወጣ ንጉሡን አገኘው። ይህ አባት ያዕቆብም በፊቱ ቆሞ "ንጉሥ ሆይ በጠላቶችህ ላይ እግዚአብሔር ይረዳህ ዘንድ ምዕመናን እንዲጸልዩልህ አብያተ ክርስቲያናቸውን ክፈትላቸው ብዬ እለምንሃለሁ ይህን ካላደረግህ ግን እግዚአብሔር ይጥልሃል ከጠላቶችህም ሸሽተህ በእሳት ቃጠሎ ትሞታለህ" አለው። ንጉሡም ይዞ ለሚጠብቀው ወታደር "በሰላምና በደኅንነት እስከምመለስ ጠብቀው" ብሎ ሰጠው። ቅዱስ ያዕቆብም "አንተ በደኅና ከተመለስክ በእኔ አንደበት እግዚአብሔር አልተናገረም ማለት ነዋ" አለው። ❤ ያንጊዜም ቅዱሱን ይዘው ደብድበው አሠሩት ንጉሡም ከሠራዊቱ ጋራ ወደ ጦርነቱ ሔደ በረከሰች ጸሎታቸው አርዮሳውያን ምንም ቢራዱት ክብር ይግባውና ጌታችን በጠላቶቹ አንጻር ጣለው እነርሱም ጠላቶቹ እየተከተሉት ሸሽቶ ከአንዲት ዐፀድ ውስጥ ገባ በዚያም በረከሰች ሃይማኖቱ ከሚያምን ወገኖቹ ጋር በእሳት አቃጠሉት። የቀሩትም ሠራዊት ሁሉ ሸሽተው ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሱ ይህንንም መልካም ዜና ሃይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን ተናገሩ የዚህም ጻድቅ አባት ያዕቆብም ትንቢቱ ተፈጸመ ከእሥር ቤትም በክብር አወጡት። ምዕመናንም ከሀድያንም በላዩ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ተረዱ ከአርዮሳውያንም ብዙዎቹ የአባቶቻችን ሐዋርያት ወደሆነች ቅን ሃይማኖት ተመለሱ በዚህ አባት እግር በታች ሰግደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ ታመነ። ❤ ከዚህም በኋላ ይህ አባት ወደ ቦታው ተመለሰ አርፎ የሕይወትና የሰማዕትነት አክሊልን እስከ ተቀበለ ድረስ እንደ ቀድሞው በገድል ተጠምዶ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ በቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #አባ_ብሶይ፦ የዚህ ቅዱስ አባቶቹ ክብር ይግባውና ጌታ ክርስቶስን የሚያመልኩና ትዕዛዙን የሚጠብቁ ክርስቲያን ነበሩ የአባቱም ስም ታግኅስጦስ ነው እርሱም ከአንጾኪያ የቃው ገዥ ነበር የእናቱም ስም ክሪስ ይባላል። እነርሱም ልጅ ሳይኖራቸው ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖሩ ስለዚህም እጅግ እያዘኑ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ይለምኑ ነበር። ከሌሊቶችም በአንዲቱ ለታግኅስጦስ ብርሃን የለበሰ ሰው ተገልጦለት እንዲህ አለው "የእግዚአብሔር ወዳጅ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቷል ሚስትህም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች ስሙንም ብሶይ ትለዋለህ እርሱም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ዕቃ ይሆናል እርሱም ደግሞ ክብር ይግባውና ለክርስቶስ ምስክ ይሆናልና ሥቃይና መከራም ተቀብሎ የሰማዕትነት አክሊልን ይቀዳጃል"። ከእንቅልፉ ነቅቶ ራእይ እንዳየ ለሚስቱ ነገራት። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ፀንሳ ይህን ቅዱስ ሚያዝያ አንድ ቀን ወለደችው ዕውቀትን ጥበብንና ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጉት። ❤ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ አክሚም ዮሴፍ ወደሚባል አንድ አረጋዊ መምህር ላኩት በዚያም እየተማረ ከወንድሙ ጴጥሮስ ጋር በጸሎትና በጾም ተጠምዶ ድንቆች ተአምራትን እያደረገ ኖረ። ከዚያም በኋላ ሃያ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ የስዒድ መኰንን ወዳለበት ወደ ቃው ከተማ መጣ እርሱም ክርስቲያኖችን እያሳደደ ከእርሳቸው ይገድል ነበር። ያን ጊዜም ክፉዎች ሰዎች ወደ መኰንኑ መጥተው "ለቃልህ የማይታዘዙና ለአማልክት መስገድንም እምቢ የሚሉ ሁለት ዲያቆናት አሉ" ብለው እኒህ የከበሩ አባ ብሶይንና አባ ጼጥሮስን ከሰሱአቸው። በዚያም ጊዜም እንዲአቀርቧቸው አዘዘና አቅርበው በፊቱ አቆሙአቸው ስለ ሥራቸውም መረመራቸው ክርስቲያን እንደ ሆኑም ከቃላቸው ሰምቶ እንዲአሥሩአቸው አዘዘ። ❤ ከሦስት ወር በኋላም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦላቸው "እኔ የምሥራች የምናገር ገብርኤል ረዳችሁና እነግራችሁ ዘንድ ወደእናንተ እግዚአብሔር ላከኝ ስም አጠራራችሁና መታሰቢያችሁ ለዘላለሙ ይኖር ዘንድ አለውና" አላቸው። "አንተም ወዳጄ ብሶይ ታላቅ ተጋድሎ አንተን ይጠብቅሃል ወደ እስክንድርያ ከተማ ሊሰዱህ አላቸው። ከዚያም ወደ አንጾኪያ ወስደውህ በዚያ የምስክርነትህ ገድል ይፈጸማል"። ❤ ከዚህ በኋላም መኰንኑ ከወህኒ ቤት አውጥቶ ለጣዖት እንዲሰግድ አስገደደው እምቢ ባለውም ጊዜ ከባላ ላይ አውጥተው በግንድ ውስጥ እጅግ እንዲጨምቁት ወታደሮቹን አዘዘ። በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወሪዶ ግንዱን ሰብሮ ቅዱስ ብሶይን በመዳሠሥ አዳነው። ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ጨምሩት በዚያም ብዙ በሽቶኞችን ፈወሳቸው። ዳግመኛም እንዲህ አዘዘ ከወህኒ ቤት አውጥተው በመርከብ ሆድ ውስጥ አስገብተው አንገቱን በብረት ማሠሪያ እንዲአሥሩት እንጀራና ውኃ እንዳይሰጡት አዘዘ እንደዚህም ኖረ ዐሥር ቀን ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ አውጥተው በፊቱ አቁሞ "ለአማልክቶቼ ስገድ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ከባላ ግንድ ላይ አውጥተው አጥብቀው እንዲጨምቁት ሁለተኛ አዘዘ። እንዲሁም በእርሱ ላይ አድርገው በወህኒ ቤት አሠሩት። የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ ተገለጠለትና "አይዞህ መልካም ገድልህን እስከምትፈጽም እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁና አትፍራ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወደ ቁልቁልያኖስ መኰንን ሰደዱት እርሱም ስለ ሥራው ሁሉ መረመረውና ሕዋሳቱ ተቆራርጦ እስቲወድቅ ድረስ ይደበድቡት ዘንድ አዘዘ። ሁለተኛም ዘይትን አፍልተው በጆሮው፣ በአፉና በደረቱ ላይ እንዲአፈስሱ ጐኖቹንም በእሳት ሠብራት እንዲአቃጥሉ አዘዘ ደግሞም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በዐይኖቹ ውስጥ አደረጓቸው። ሁለተኛም የእጆቹንና የእግሮቹን ሥሮች ሕዋሳቱንም ሁሉ እንዲነቅሉ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት በዚያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሕዋሳቱን ሁሉ ፈወሰው።

ክብር ይግባውና ክርስቶስ የምታመልክ ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ ታመነች። ❤ ዲዮቅልጥያኖስም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስ ስም በሰማ ጊዜ ቁጣን ተሞላ ወደ እርሱም እንዲያቀርቧት አዘዘ በቀረበችም ጊዜ "ለአጵሎን ስገጂ አላት "የሰው እጅ ለሰራው ለረከሱ አጋንትም ማደርያ ለሆነው እንዴት እሰግዳለሁ" አለችው ይህንንም ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከብረት በተሰራ ጅራፍም እንዲገርፏት አዘዘ ሁለተኛም አንገቷን ከባድ ደንጊያ አስረው ሥጋዋ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ በከተማው ጥጋጥግ እዲጎትቷት አዘዘ ይህን አድርገው ወደ ወሂኒ ቤት አስገቧት። በማግስቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ በመጣችም ጊዜ "በክፉ አሟሟት እንዳትሞቺ ለአጰሎን ሰዊ" አላት እርሷም "ክፉ ሞትስ ለአንተ ነው የእኔስ ከአንተ የሚገኘው ሞት በፈጣሪዬ ዘንድ ይሕወት ነው" አለችው። እርሱም "ከገደልኩሽ በኋላ ትነሽ ትነሻለሽን?" አላት "አንተ ሰነፍ የእኔን ተዋውና ለአንተም የደይን ትንሣኤ አለህ" አለችው። ይህንንም በሰማ ጊዜ አጥንቶቷ ሁሉም እስኪሰበሩ በብረት በትሮች እዲደበድቧት አዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉባት። ❤ ዳግመኛም በብረት አልጋ አስተኝተው ከበታቿ እሳት እንዲያነዱ አዘዘ ቀኑ በመሸም ጊዜ ወደ ወህኒ ቤት እንዲያስገቧት አዘዘ። በዚያችም ሌሊት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ገላዋን በመዳሰስ አጽናናት። በማግሥቱም ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ምን ሕማም እንዳላገኛት ሁና በእግራ መጣች ከመታጠቢያ ቤት ታጥባና ተቀብታ የመጣች ትመስል ነበር ንጉሡም ደኅንነቷን አይቶ አደነቀ፣ "የዚችን ክርሰቲያን ሴት የሥራይዋን ጽናት እዩ ትናንት በእሳት አሰቃይተናት ነበር ዛሬ ድናለች" አለ "ሥራይንስ አላውቀውቅም ነገር ግን ፈጣሪዬ ሥራይ የሚሽር ነው" አለችው። ❤ ከዚያም በኋላ እሺ ያሰኛት ዘንድ ሊሸነግላት ጀመረ እንቢ ባለችውም ጊዜ እራሷን በሰይፍ ሊቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ሊቆርጧት ይዘዋት ሲሆዱ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለፀላት ብዙ ቃል ኪዳኖችንም ሰጣት በማይታበል ቃሉም "መታሰቢያሽን የሚያደርገውን፣ ሁሉ በስምሽ የሚመጸውተውን፣ የገድልሽንም መጻሕፍ የሚጽፈው ሁሉ እቀበለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትን አወርሰዋለሁ" አለ። ከዚያም በኋላ አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ በጌታችንም ዘንድ የድል አክሊልን ተቀበለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በቅድስት ሶፍያ በጸሎቷ ይማረን በረከታም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ሳኑሲ፦ ይኽም ቅዱስ በልጅነቱ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ምሳውን ለጦም አዳሪዎች እየሰጠ እርሱ ግን እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር፡፡ በአንዲት ሌሊት የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት "የክብርን አክሊል ትቀበል ዘንድ ወደ መኰንኑ ሄደህ ስለ ፈጣሪህ ስለ ክርስቶስ መስክር" አለው፡፡ ቅዱስ ሳኑሲም ትእዛዙን በመቀበል እናቱን ተሰናብቶ ማርያ ከምትባል ደገኛ ሴት ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ወደ ከሃዲው ገዥ ወደ አርሳኖስ ዘንድ ሄዱ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ በከሃዲው ገዥ ፊት ቀርበው ክርስቲያን መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ገዥውም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰባቸው፡፡ ቅድስት ማርያ በስቃይ ውስጥ ሳለች ዐርፋ ሰማዕትነቷን ስትፈጽም ቅዱስ ሳኑሲ ግን በጌታችን ኃይል ታደሰ፡፡ መኰንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ እንዴናው ገዥ በግዞት ላከው፡፡ በዚያም እጅግ አድርገው አሠቃዩት፡፡ ተረከዙን ሰንጥቀው ገመድ አግብተው በከተማው ውስጥ ሲጎትቱት ዋሉ፡፡ ሥራየኛ ሰው አምጥተው ሥራየኛው ሰው በጽዋ የተመላ መርዝ እንዲጠጣ ቢሰጠው ቅዱስ ሳኑሲ በመስቀል ምልክት አማትቦ ቢጠጣው ምንም አልሆነም፡፡ እንዲያውም ምግብ ሆነው፡፡ ይህንን ታላቅ ተአምር ያየው ሥራየኛም "በቅዱስ ሳኑሲ አምላክ አምኛለሁ" ብሎ በመመስከር እርሱም ሰማዕት ሆነ፡፡ መኰንኑም ቅዱስ ሳኑሲን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን እንዲቆርጡት አዘዘና ሰኔ 4 ቀን የከበረች ራሱን በሰይፍ ቆርጠውት ሰማዕትነቱን በክብር ፈጽሞ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 4 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ "#አቄርብ_ለከ_አሞኒ_ሰላም። #ወሶፍያ_ምስሌከ ዘተሳተፈት ሕማመ። #በእንተ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥመሩ ፍጹመ። ከዊነክሙ ትሕፅኑ ኪያየ ደክታመ። ለሊከ አበ ወይእቲ እመ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሰኔ_4።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ቀስቶኒ ወተረ ወአስተዳለወ። ወአስተዳለወ ቦቱ ሕምዘ ዘይቀትል። ወአሕፃሁኒ እለ ይነዱ ገብረ"። መዝ 7፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 3፥9-18፣ 1ኛ ዮሐ 2፥12-20 እና የሐዋ ሥራ 12፥18_ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ወይም የ­ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                ❤ #ሰኔ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሐራቅሊ_ለዕረፍቱ በዓል፣ በኪም ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_ሳኑሲ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን አንገቷን በመቆረጥ ሰማዕትነት ለተቀበለች ተጋድይ ለሆነች #ለቅድስት_ሶፍያ ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከአርቃድዮስ፣ ከእህቱ #የዲሙናስና ከግብጻውያን ከንጉሥ ከዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮችም ከገድላቸው ፍጻሜ፣ #ከአባ_አሞንና ከሚናስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሐራቅሊ፦ የዚህም ቅዱስ አባት ስሙ ዘካርያስ ነው እርሱም የጳንጦስና የአብልያ አገሮች ገዢ ነበር የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም ይህን የተባረኩ ልጅ በተሰጡ ጊዜ ስሙን ዮሐንስ ብለው ጠሩት እርሱ ከአባቱና ከእናቱ ጀምሮ ከመጥምቀ አምላክ ዮሐንስ ጋር በስም አንድ ሁኗልና በተግሣጽና በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደጉት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ሂሣቦችንና ጥበቦችን ሁሉ አስተማሩት እናቱም በዘመኗ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ እንዳይወጣ ታማጽነው ነበር። አባቱም እንዲሁ ይመክረውና ያስተምረው ነበር። ❤ ከዚህም አባቱ ከሞተ በኋላ የሃያ ዓመት ልጅ ሲሆን መስፍን ሆነ የጳንጦስና የሐራቅሊ ሌሎችም አገሮች ሁሉ ተገዙለት። እንዲሁም እያለ በመልአክ አምሳል ሰይጣን ታየው እንዲህም አለው "አንተ ትነግሥ ዘንድ ወደ አንጾኪያ ሒደህ የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ አግባ ብሎ ጌታ አዝዞሃል" አለው ቅዱሱም "በውኑ ይህ መልአክ ነውን ግን አፉ የእግዚአብሔርን ስም ከሰማሁ አንጾኪያ እሔዳለሁ" አለ። ❤ ከዚህ በኋላም ወደ አንጾኪያ ከተማ ሔደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስንም ተገናኘው ንጉሡም በአየው ጊዜ አከበረው እጅግም ወደደው። በማግሥቱም በምሳ ላይ ከእርሱ ጋራ እያለ ከሃዲ ዲዮቅልጥያኖስ አጰሎንን ያመጡት ዘንድ አዘዘ ያንንም ጣዖት ባመጡት ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ አቃለለው ስለዚህም ሥራ ንጉሡን ረገመው ሰደበውም። ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገውን በአየ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ በእሥር ቤት አሠረው። በእሥር ቤትም ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን በብርሃን ሠረገላ ላይ ሁኖ ታየው ከእርሱ ጋራም መላእክት አሉ። ይዞም ሳመው ብዙዎች ቃል ኪዳኖችንም ሰጠው። ❤ በማግሥቱም ንጉሡ ልኮ ከእር ቤት አወጣው ወደ ርሱም አቀረበውና "ለአጰሎንና ለአርዳሚስ ስገድ" አለው ቅዱሱም "የሰው እጅ ለሠራው እንዴት እሰግዳለሁ" አለ ንጉሡ ግን ከእርሱ ጋራ መታረቅ ሽቶ ብዙ የሽንገላ ነገርን ተናገረው። ከዚህም በኋላ ግብርን ያስገብር ዘንድ ከሹመት ጋራ ወደ ግብጽ አገር ላከው ወደ ግብጽ ገዢ ወደ ስርያቆስም ስለ ርሱ እንዲህ ሲል ጽፎ ላከ "እንሆ ለዮሐንስ ዘሐራቅሊ ግብር በማስገበር የአማልክትንም ቤቶች አፍርሶ አዲስ እንዲአሠራ ከግብጽና ከኢየሩሳሌም እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ሥልጣን ሰጥቼለሁ። ቅዱሱም ይህን ምክንያት ይዞ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሶ ተዋቸው። ❤ በዚያም ወራት መኰንኑ ስርያቆስ የሰማዕታት ራስ መቆረጥን ሊያዝዝ በፍርድ አደባባይ ተቀምጦ በዚያን ጊዜ ከስዒድ፣ ዲዮስቆሮስ፣ ቢፋሞን፣ አሕራጋኖስ፣ ኪሮስ፣ ዮልዮስ እለእስክድሮስ፣ ዮሴፍ፣ ይስሐቅና እስጢፋኖስ የሚሉአቸው ሰዎች መጥተው እሊህ ሁሉም እኛ ክርስቲያኖች ነን እያሉ በግልጥ ጮኹ ያን ጊዜ መኰንኑ ይዞ ያለርኅራኄ ያሠቃያቸው ጀመር። ቅዱስ ዮሐንስ ይህን በአየ ጊዜ የሹመቱን ሥራ ትቶ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በግልጥ ጮኸ መኰንኑም ተቆጥቶ በእግር ብረት እንዲአሥሩትና ወደ እንዴና አገር ወደ መኰንኑ አርያኖስ እንዲወስዱት አዘዘ እርሱም ስለሆነው ሁሉ መረመረው ከቃሉ መልስም የተነሣ ተቆጣ በባላ እንጨት ላይ ሰቅለው በመንኰራኵር አጣበቀው እንዲጨምቁት ከዚያም ከባላው አውርደው ሥጋው እስኪቀልጥ ሆዱ ላይና ራሱ ላይ በቀጭኔ እንዲደበድቡት አዘዘ ምድሪቱም በደሙ ተመላች ከዚያም ወደ እሥር ቤት አስገቡት። ❤ ከጥቂት ቀኖች በኋላም በማረጃ ቢላዋ ቆዳውን ገፈው ቁስሉን በማቅ ያሹት ዘንድ ዳግመኛም አመድ ጐዝጊዘው በላዩ የእሳት ፍም ከጐኑ በታች አድርገው በላዩ እንዲአስተኙት አዘወ እንዲሁም አደረጉበት። ሁለተኛም በእሳት የጋሉ የብረት ችንካሮችን አምጥተው በፊቱ ላይ በጀሮዎቹም ላይ እንዲያኖሩዋቸው አዘዘ። እንዲህም አድርገው ከወህኒ ቤት ጨመሩት። በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ሰላምታ ሰጥቶ አጸናው። በማግሥቱም ከወህኒ ቤት አውጥተው በጋሉ ብረት ዘንጎች ደበደቡት። ከዚህም በኋላ በግንባሩን ወደ ምድር ደፍተው እጆቹንና እግሮቹን ከፈረስ ጭራ ላይ በገመድ አሠሩ። ❤ ከዚህም በኋላም ባለ ሰይፍ መጥቶ እግርቹንና እጆቹን ራሱንም ቆረጠ እንዲህም የምስክርነቱን ተጋድሎ ሰኔ 3 ቀን ፈጽሞ የድል አክሊል ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                         ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅድስት_ሶፍያ፦ የዚች ቅድስት ወላጆቿ ክርስቲያን ነበሩ በወለዱዋት ጊዜም በመልካም አስተዳደግ እግዚአብሔርን በመፍራት የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የአባቶቻችን ሐዋርያትንም ሥርዓት ሁሉ እያስተማሩ አሳደጓት። ❤ ከዚህም በኋላ በአደገች ጊዜ ወላጆቿ ለአንድ መስፍን ልጅ ሊአጋቧት ፈለጉ ቅድስቲቱም ይህን በመንፈስ ቅዱስ ዐውቃ ከተቀመጠችበት ተነሥታ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ መቶ ስግደትን ሰገደች ቆማም ረጂም ጸሎትን ጸለየች በጸሎቷም ውስጥ እንዲህ አለች "የክብር ባለቤት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወዳንተ የምደርስባት የከበረችና የቀናች መንገድህ ለእኔ ለባርያህ ለሶፍያ ምራኝ ወደ ጥፍት በሚወስድ በጠማማ መንገድ እንድንከራተት አትተወኝ የሚጠፍውንም ዓለም ያስብ ዘንድ ልቤን አትተወው ወላጆቼ በሚመክሩብኝም በረከሰ በሥጋ ፍትወት ውስጥ የኃጢአት ባርያ እንድሆን አቤቱ አትተወኝ የከበደ የዓለማዊ ፍላጐት ሸክምን ተሸካሚ አታድርገኝ ቀላልና ልዝብ የሆነ ቀንበርህን ይሸከም ዘንድ ትከሻዬ ዘንበል አድርገው እጂ"። ጸሎቷንም ከፈጸመች በኋላ በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች ጥቂትም ቆይታ እንዲህ የሚል ሃሳብ መጣባት "ተነስቼ በስውር ልውጣ ወደ ሩቅም ሔጄ ከበረሀ ውስጥ ገብቼ ለልዑል አምላክ ላገልግል"። ❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቿ የሰጣትን የምታገለግላት ብላቷናዋን ጠራች ወይን አምጥታ እንድታጠጣትም አዘዘቻት በአመጣችላትም ጊዜ እርሷ ጥቂት ቀምሳ ያመጣችው ወይን እስኪያልቅ ትጠጣ ዘንድ ብላቷናዋን አዘዘቻት ከስካርም የተነሣ ልባ በተሰለበ ጊዜ "ልብስሽ አንጪ የእኔንም ልብስ ውሰጂ" አላቻትና ሰጠቻት ወይኑ ስካር አእምሮዋን ነስቷታልና ተኚ አለቻት በላይዋም እንቅልፍ በከበዳት ጊዜ ማን ሳያያት ቅድስት ሶፍያ በስውር ወጣች ከወላጆቿም ማደርያ ነበርና። እርቃ በሄደችበት ጊዜ በተራራና በዋሻዎች ውስጥ ሊሰወሩ ፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ከከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ፊት የሚሸሹ ሰዎችን አገኘች "እናንተ ከወዴት ናችሁ?" ብላ ጠየቀቻቸው የእያንዳንዳቸውን አገራቸው ነገሯት ደግማ "ወዴት ትሔዳላችሁ?" አለቻቸው እነርሱም ስለ ሃይማኖት ከዲዮቅልጥያኖስ የሆነውን ሉሁ ነገሯት። "ይቺ መንገድ ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ታደርሰኛለችን" አለቻቸው "አዋ ታደርስሻለች" አሏት ከዚያም ጥቂ ተጉዛ ቁማ እረጅም ጸሎትን ጸለየች ወደ ዲዮቅልጥያኖስ ደርሳ

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #ሰኔ ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያ_ጻድቅ ለታላቁ አባት በደብረ ዳሞ ገዳም ለ37 ዓመታት ላገለገሉ 3 ታላላቅ ገዳማት በስማቸው ለተሰየመ #ለአቡነ_ሠምረ_አብ_ዘሳይንት_ወዘትግራይ ዓመታዊ ለልደት በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                                                              ✝️ ✝️ ✝️   ❤#አቡነ_ሠምረ_አብ ዘሳይንት ወዘትግራይ፦ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ሲሆኑ የትውልድ ሀገራቸው በወሎ አምሐራ ሳይንት ነው። አቡነ ሠምረ አብ የትውልድ ዕለታቸው ሰኔ 4 ቀን ነው። በብሕትውና ከተረጋገጠላቸውና ከ47ቱ ከታወቁት ሊቃውንት አንዱ ናቸው። ❤ አባ ሠምረ አብ ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ሄደው በዚያ 37 ዓመት ተቀምው፤በኋላም ወደ ገርዓልታ ሄደው በስማቸው የተሰራውን ታላቁን  ገዳም ቆረቆሩ። (ገርዓልታ አቡነ ሠምረ አብ ገዳም)፤በዚህም ምክንያት አቡነ ሠምረ አብ ዘትግራይ ይሏቸዋል። በተጨማሪም አስደናቂ የሆነ ገዳማቸው በጎንደር ደንቀዝ ውስጥ ይገኛል። ❤ በኢትዮጵያ ውስጥ በጻድቁ ስም 3 አብያተ-ክርስቲያናት ተሰርተዋል። የዕረፍት ቀናቸውም ጥር 4 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ሠምረ አብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!።  ምንጭ፦ ዜና ቅዱሳን።

❤ ቅዱስ ለውንትዮስም ለሥጋው መልካም ለሠራች ለመስፍኑ ሚስት መልካም ወጋዋን ሊከፍላት ሽቶ በዚያች ሌሊት በወህኒ ቤት ለባልዋ ተገለጠለት በወህኒ ቤቱም ብርሃን ወጣ ለመኰንኑም የራሱ የሆነውን በቤቱ ያለውን የሚያውቀውን የወርቅ ልብስ ለብሶ በጐልማሳ ፈረሰኛ አምሳል ተገለጠለት። ❤ ከዚህም በኋላ እንዲህ አለው "አትዘን አታልቅስም ዛሬ ከዚህ ወጥተህ ከንጉሥ ጋር በማዕዱ ትቀመጣለህና ከዚያም ወደ ቤትህ በሰላም ትሔዳለህ"። የታሠረው መስፍንም ይህን ጐልማሳ ፈረሰኛ ስለ አየው በላዩም ስለ ወጣው ብርሃን የወህኒ ቤቱም ደጅ እንደ ተዘጋና እንደ ተቆለፈ ወደ ርሱ ስለ መግባቱ ደግሞም የራሱ የሆነውን በቤቱ ውስጥ የተወውን የወርቅ ልብስ ለብሶ ስለ ማየቱ በዚህ ሁሉ ሥራ ያደንቅ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለውንትዮስ በዚያች ሰዓት ወደ ንጉሡ ሔደ በመኝታውም ተኝቶ ሳለ ረገጠው እጅግም ደነገጠ ለንጉሡም እንዲህ አለው "ንጋት በሆነ ጊዜ መስፍን ዕገሌን ከወህኒ ቤት አውጣው አክብረውም በክፉ አሟሟትም ሙተህ እንዳትጠፉ ወደ ቤቱ ይሔድ ዘንድ ተወው"። ንጉሡም ከግርማው የተነሣ እየተንቀጠቀጠ "እሺ ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብሎ መለሰለት። በነጋ ጊዜም ንጉሡ ወደ ወህኒ ቤት ልኮ መስፍኑን አወጣው ታላቅ ክብርንም አከበረው መልካም ልብሶችንም አልብሶ ከእርሱ ጋራ በማዕዱ አስቀመጠው። ፈረሰኛም እንደ ተገለጠለትና ይፈታው ዘንድ እንዳዘዘው ነገረው መስፍኑም አደነቀ። ንጉሡም የሥራይ ሥራ እንደሆነ አድርጎ አሰበ መስፍኑም "እኔ መጠበብንና ሥራይን አላውቅም ከእሊህ ከምትለኝም ነገሮች ማን እንደተገለጠልህ ምንም አላውቅም"። ንጉሥም ከተገለጠለት ራእይ ፍርሀት የተነሣ ክፉ ነገርን ሊናገው አልደፈረም ነገር ግን ወደ አገሩ በታላቅ ክብር ሰደደው። ❤ መስፍኑም በጎዳና ሲጓዝ ሁለተኛ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ወደ አገሩ ጠራብሎስም እስኪደርስ እያነጋገረው ያጽናናው ነበር ከዚህም በኋላ ተሠወረው። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ቤተሰቦቹን ሰላም አላቸው የእርሱን የወርቅ ልብስ የሚመስል ልብስ ለብሶ ፈረሰኛ ጐልማሳ እንደ ተገለጠለትም ነገራቸው ከወህኒ ቤትም እሥራት ያድነው ዘንድ ቃል እንደገባለት ነገራቸው። ሚስቱም ያዳነው ቅዱስ ለውንትዮስ እንደሆነ አውቃ "ብታየው ታውቀዋለህን" አለችው "አዎን" አላት ከዚያም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥዕል ወደ አለበት ቦታ አስገባችው አይቶም "የተገለጠልኝ በእውነት ይህ ነው" አለ። ❤ ሁለተኛም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥጋ ያለበትን ሣጥን ከፈተች ያንንም የርሱን የወርቅ ልብስ እንደለበሰ አየው። የፊቱንም መሸፈኛ ገለጠ የተገለጠለትና ከእሥራት ያዳነውም እርሱ እንደ ሆነ ተረዳ። መስፍኑም ማን እንደሆነ ስለ እርሱ ሚስቱን ጠየቃት እርሷም የቅዱስ ለውንትዮስን ገድል ነገረችው መስፍኑም ይህን መልካም ሥራ ስለ ሠራች ሚስቱን አመሰገናት መረቃትም የተመሰገነ እግዚአብሔርንም በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ሥራ ስለሚሠራ አመሰገነው። መብራትና ማዕጠንትም እንዳይለየው ሚስቱን አዘዛት ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስን ጌታችን እስከ አጠፋው ድረስ እንዲሁ የምትሠራ ሆነች። ❤ ከዚህም በኋላ መልካም ቤተ ክርስቲያን አንፀው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ በዚች ዕለትም ሰኔ 1 አከበሩዋት ከሥጋውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለውንትዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ #የሰኔ_1_ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እስመ ናሁ ዘእንተ ሠራዕከ እሙንቱ ነሠቱ። ወጻድቅሰ ምንተ ገብረ። እግዚአብሔር ውስተ ጽርሐ መቅደሱ። መዝ 10፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥42-ፍ.ም።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወሤሞ መልአከ አሕዛብ። ወረሰዮ እግዚአ ለቤቱ። ወአኰነኖ ላዕለ ኵሉ ጥሪቱ"። መዝ 104፥21-22። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥21-32፣ 1ኛ ጴጥ 4፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥9-23። የሚነበበው ወንጌል 24፥45-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የቅዱስ ዮሴፍና የሚስቱ የቅድስት አሰኔት የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ ዮሴፍ ከታሰረ ከሁለት ዓመት በኋላ ንጉሡ ፈርዖን ሕልም አየ፡፡ በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታውካ የግብፅን ሕልም ተርጓሚዎችና ጠቢባንን ሁሉ ሰብስቦ እንዲተረጉሙለት ሕልሙን በዝርዝር ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ሊተረጉሙለት አልቻሉም ነበር፡፡ የንጉሡም የጠጅ አሳላፊ አስቀድም ከዮሴፍ ጋር ታስሮ ሳለ እርሱ ያየውን ሕልም ዮሴፍ ተርጉሞለት እንደነገረው ሆኖለት ስለነበር በዚህ ጊዜ የጠጅ አሳላፈው ለንጉሡ ስለ የሴፍ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን አስመጥቶ ሕልሙን ነግሮት ተረጎመለት፡፡ በፈርዖንም ሕልም መሠረት ሰባት ዓመታት ጥጋብ እንደሚሆንና ከዚያም በኋላ ሰባት የርኃብ ዓመታት እንደሚመጡ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን "እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ" ብሎ በቤቱና በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው፡፡ ቀለበቱንም አውጥቶ አሰረለት፡፡ ይህም የሆነው በ30 ዘመኑ ነው፡፡ ዮሴፍ በእናት በባቱ ቤት 17 ዓመት፣ በጲጥፋራ ቤት 10 ዓመት፣ በእስር ቤት ሁለት ዓመት ተቀምጦ ባጠቃላይ ልክ 30 ዓመት ሲሆነው በፈርዖን ፊት ለሹመት ቆመ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በ30 ዘመኑ ለሹመት በፈርዖን ፊት እንደቆመ ሁሉ ጌታችን መድኃኔዓም ክርስቶስም በጲላጦስ ፊት ለፍርድ የቆመው በ30 ዘመኑ ነው፡፡ ❤ ዮሴፍም በግብፅ ምድር ዞሮ የሰባቱን ዓመት እጅግ ብዙ እህል ሰበሰበ፡፡ ሰባቱም የጥጋብ ዘመን ሲያልፍ ሰባቱ የርኃብ ዘመን በጀመረ ጊዜ በሀገሩ ሁሉ ታላቅ ርኃብ ሆነ ነገር ግን በግብፅ ምድር ብቻ እህል ነበር፡፡ ንጉሡም ከየሀገሩ ሁሉ ወደ እርሱ የሚመጡትን ወደ ዮሴፍ እየላካቸው ዮሴፍም እህል ከጎተራ እያወጣ ይሸጥላቸው ነበር፡፡ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በግብፅ እህል እንዳለ በሰማ ጊዜ ልጆቹን እህል እንዲሸምቱ ወደ ግብፅ ላካቸው፡፡ ነገር ግን ክፉ እንዳያገኘው ብሎ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ከእነርሱ ጋር አላከውም ነበር፡፡ ዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ ከሕዝቡ ጋር ገብተው ሲሰግዱለት አይቶ ዐወቃቸው፣ እነርሱ ግን የሰገዱለት የሀገሩ ገዥ ስለነበረ ነው እንጂ ወንድማቸው እንደሆነ ዐላወቁትም ነበር፡፡ ዮሴፍም በልጅነቱ ከእነርሱ ጋር ሳለ ያየውን ሕልም አሰበ፡፡ እነርሱም ስለራሳቸው በነገሩት ጊዜ "እቤት የቀረውን ወንድማችሁን አምጡ" ብሎ ለርኃባቸው እህሉን ሰጥቶ አንዱን (ስምዖንን) ለይቶ አስቀርቶ ዘጠኙን ስንቃቸውን ጭኑ ወደ አባታቸው ቤት ወደ ከነዓን ላካቸው፡፡ ሄደውም የሆነውን ለያዕቆብ ነገሩት፡፡ እርሱም ከወንድማቸው ጋር ድጋሚ ወደ ግብፅ ላካቸውና ድጋሚ በዮሴፍ ፊት ሰግደው ሰላምታ አቅርበው እጅ መንሻን አመጡለት፡፡ ዮሴፍም የእናቱን ልጅ ብንያምን ባየው ጊዜ ወደ ውስጥ ገብቶ አለቀሰ፡፡ ዮሴፍ ቆይቶ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ ያደረጉበትንም ነገራቸው፡፡ የርኃቡም ዘመን ገና 5 ዓመት ይቀረው ነበርና ዮሴፍ ወንድሞቹን "ስለሸጣችሁኝ አትዘኑ እነሆ ሕይወታችሁን ለማዳን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእናንተ በፊት ወደ ግብፅ ልኮኛል" አላቸው፡፡ አባቱንም ወደ እርሱ እንዲያመጡት ላካቸው፡፡ ያዕቆብም ከነቤተሰቡ ንብረቱንም ሁሉ ሰብስቦ ወደ ግብፅ ወረደ፡፡ ልጁን ዮሴፍንም ባየው ጊዜ እያለቀሰ አቅፎ ከሳመው በኋላ ሞቱን ተመኘ፡፡ ❤ በግብፅ የያዕቆብ የልጅ ልጆቹ ቁጥር 66 ሆነ፡፡ ከዮሴፍም ልጆች ጋር አንድ ላይ 70 ሆኑ፡፡ ያዕቆብም ፈርዖንን ገብቶ ከባረከው በኋላ በግብፅ ጌሤም ምድር 17 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ዘመኑም 140 በሆነ ጊዜ በሞት ማረፉን ዐውቆ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ በአባቶቹ መቃብር ቤት ውስዶ እንዲቀብረው ነገረው፡፡ የዮሴፍንም ሁለቱን ልጆች ምናሴንና ኤፍሬምን ባረካቸው፡፡ "አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፣ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ" ብሎ ባረካቸው፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ ወደፊት የሚሆነውን ሁሉ ይልቁንም የጌታችንን የመወለዱን ነገር በምሳሌ እያደረገ ነገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸውና በአብርሃምና በይስሐቅ ሣራም በተቀበረችበት መቃብር ወስደው እንዲቀብሩት ከነገራቸው በኋላ በ137 ዕድሜው እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ የግብፅ ሰዎችም 70 ቀን አለቀሱለት፡፡ ዮሴፍም አባቱን ባዘዘው ቦታ በእነ አብርሃም መቃብር ከቀበረው በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሰ፡፡ ❤ የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ "ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፣ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል" ብለው ፈርተው ወደ ዮሴፍ መልዕክት ልከው "አባትህ ገና ሳይሞት 'ዮሴፍን እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፣ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፤ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል' ብሎሃል" ብለው ላኩለት፡፡ ወንድሞቹም መጥው በፊቱም ሰግደው "እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን፣ በአባቶችህ አምላክ ባሮችህን ኃጢአታችንን ይቅር በለን" አሉት፡፡ ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ፡፡ እርሱም "ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ስለሆነ አይዟችሁ አትፍሩ" እያለ እንዳይፈሩ አጽናናቸው፤ ደስም አሰኛቸው፡፡ ዮሴፍም በግብፅ ተቀምጦ 110 ዓመት ኖረ፡፡ ❤ የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ካየ በኋላ ወንድሞቹን ጠርቶ "እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፣ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል፡፡ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት" ብሎ አማላቸው፡፡ ዮሴፍም በ110 ዕድሜው በሰላም በዚች ቀን ዐረፈ፡፡ በሽቱ አሽተው በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት፡፡ ዮሴፍም "እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት" ማለቱ አንድም ከግብፅ ምድር እንደሚወጡና የአባቶቻቸውን ርስት ከነዓንን እንደሚወርሱ ሲነግራቸው ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ግብፅ የመቃብር ከነዓን የትንሣኤ ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድም ግብፅ የገሃነም ከነዓን የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ያዕቆብም እንዲሁ ብሏልና ዮሴፍም እንዲህ ያለ ስለምን ነው ቢሉ አባቶቻችን እንዲህ ማለታቸው መውጣታችንን ቢያውቁ ነው ብለው እንዲነቁ፣ እንዲተጉ፣ አንድም ለማጸየፍ ነው፣ "አባቶቻችን አጥንታችን እንኳን ከዚህ አይቅር" ብለዋል ብለው እንውጣ እንዲሉ ነው፡፡ ከቅዱስ ዮሴፍ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎቱም ይማረን!። ምንጭ፦ አትሮንስ ሚድያ።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የቅዱስ_ለውንትዮስ_የቤተክርስቲያ_ቅዳሴ ቤት፦ ይኸውም ቅዱስ ለውንትዮስ በሐምሌ ወር በሃያ ሁለተኛው ቀን በሰማዕትነት በዐረፈ ጊዜ ከታላላቅ መኳንንቶች የአንዱ መኰንን ሚስት መጣች ለወታደሮቹም ብዙ ገንዘብ ሰጠች የቅዱሱንም ሥጋ ወሰደች በባሏም ልብስ ገነዘችው በሣጥንም አድርጋ በቤቷ ውስጥ አስቀመጠችው በቀንና በሌሊትም የሚያበራ መብራት በፊቱ አኖረች። እንሆም ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በመኰንኑ ባሏ ላይ በሆነ ሥራ ምክንያት ተቈጣ። በአንጾኪያም ከተማ በወህኒ ቤት አሠረው።

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤ ❤ #የተባረከ_የሰኔ_ወር_ቀኑ_ዐሥራ_አምስት_ሰዓት ነው። ከዚህም በኋላ ይጐድላል።                ❤ #ሰኔ ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን #እስራኤል_ለተባለው_ለያዕቆብ ልጅ #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ዮሴፍና_ለሚስቱ #ለቅድስት_አሰኔት_ለዕረፍት_ቀን_መታሰቢያ_በዓል፣ ከእርሱ ተአምራት ለተገለጡ #ለሶርያ_ሰው_ለሆነ #ለቅዱስ_ለውንትዮስ_ለቤተ_ክርስቲያኑ_ለቅዳሴ ቤቱ በዓልና ለመስተጋድል ለሰማዕት #ለቅዱስ_ቢፋሞን_ለዕረፍቱ_መታሰቢያና በስሙ ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት የመጀመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ ቤቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከላይኛው ግብፅ ከጣሀ አውራጃ ከሆኑ ከባልጀራሞች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ #ከሰማዕት_ቆዝሞስ_ከዕረፍቱ መታሰቢያና፣ #ከእስክድርያ_ከተማ_ሰማዕታትና #ከሊቀ_ጳጳሳት_ቶማስም_ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #ቅዱስ_ዮሴፍ፦ አባቱ ያዕቆብ እናቱ ራሄል ይባላሉ፡፡ ለአባቱ 11ኛ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ያዕቆብ የወንድሙን የኤሳውን በረከት ከአባቱ ከወሰደ በኋላ ከኤሳው ሸሽቶ ወደ አጎቱ ላባ ዘንድ ተሰዶ 14 ዓመት ለላባ ተገዝቶ ራሄልንና ርብቃን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወለደ፡፡ ሀብት ንብረትም ካፈራ ከ21 ዓመት በኋላ ወደ አባቱ አገር ተመልሶ ከወንድሙ ጋር ታረቀ፡፡ ያዕቆብም በምድረ በዳ አቅራቢያ ባለች አብርሃም ይቀመጥባት ከነበረ አገር ከአባቱ ከይስሐቅ ዘንድ ደረሰ፡፡ ይህችውም በከነዓን ያለችው ኬብሮን ናት፡፡ አባቱ ይስሐቅ አብርሃም ይቀመጥባት በነበረችው የወይራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅ አርጅቶ ዘመኑን ጨርሶ ሞተ፡፡ ያዕቆብም አባቱ ይስሐቅ ይኖርባት በነበረች አገር ኖረ፡፡ ያንጊዜም ልጁ ዮሴፍ 17 ዓመት ሆኖት ነበር፡፡ እርሱም ከአባቱ ከያዕቆብ ሚስቶች ከዘለፋ ልጆችና ከባላ ልጆች ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፡፡ ያዕቆብም በእርጅናው ዘመን ወልዶታልና አብልጦ ይወደው ነበር፡፡ ወንድሞቹም በዚህ ምክንያት ጠሉት፡፡ ዮሴፍም ሕልም አልሞ ሕልሙን ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ዮሴፍም ያየው ሕልም 11ዱ ወንድሞቹና አባቱም ጭምር ለዮሴፍ እንደሚገዙለትና እንደሚሰግዱለት የሚያሳይ ነበር፡፡ ይህንንም ሕልሙን ሲሰሙ ወንድሞቹ ይበልጥ ጠሉት፡፡ ❤ የዮሴፍም ወንድሞች የአባታቸውን በጎች ይዘው ወደ ሴኬም ጎዳና ሄዱ፡፡ አባቱም ዮሴፍን "ወንድሞችህን አይተሃቸው ና" ብሎ ስንቃቸውን ቋጥሮ ወደ ቆላው ላከው፡፡ ሴኬምም እንደደረሰ አንድ ሰው ወንድሞቹ ያሉበትን አሳይቶት ወደ ዶታይን ወረደ፤ በዶታይንም አገኛቸው፡፡ እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩትና ወደ እነርሱ ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡ "እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፡፡ ክፉ አውሬም በላው እንላለን" ብለው ሲመካከሩ ከእነርሱ ውስጥ ሮቤል ይህን ሲሰማ "ሕይወቱን አናጥፋ፣ ደም አታፍስሱ፤ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት፣ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት" አላቸው፡፡ ሮቤልም እንዲህ ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው፡፡ ❤ ዮሴፍንም ቀሚሱን ገፈው ወስደው ወደ ቀበሮ ጕድጓድ ጣሉት፡፡ ጉድጓዱንም በድንጋይ ገጥመው በላይ ተቀምጠው ዮሴፍ ያመጣላቸውን እንጀራ እየተመገቡ ሳለ የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ ሲመጡ አይተው በይሁዳ ምክር ወንድማቸውን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡት፤ እስማኤላውያንም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት፡፡ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው፡፡ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፡፡ ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ፡፡ ❤ ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን ስላገኘ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው፡፡ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው፤ የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ፡፡ ጲጥፋራም ያለውን ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ የጌታችን፣ ወንድሞቹ ደግሞ የአይሁድ ምሳሌ ናቸው፡፡ ዮሴፍ ምግባቸውን ይዞላቸው ቢሄድ ከበው እንደደበደቡት ሁሉ ጌታችንም "እኔ ግን እላችኋለሁ…›" እያለ የነፍሳቸውን ምግብ ቢያስተምራቸው አይሁድ ጠልተውት ገድለውታል፡፡ ዮሴፍ እንዲሸጥ ሀሳብ ያመጣው ይሁዳም ጌታችንን የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በግብፅ ሕያው በከነዓን ግን ምውት እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በትስብእቱ ግን ምውት ሆኗል፡፡ ❤ ወንድሞቹም የዮሴፍን ቀሚስ ወስደው የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነክረው ወደ አባታቸው ሄደው "ይህንን አገኘን፣ ይህ የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው" አሉት፡፡ ያቆዕብም "ይህ የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በልቶታል" ካለ በኋላ ልብሱን ቀዶ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ጊዜ አምርሮ ስላለቀሰ ዐይኑ ጠፋ፡፡ ❤ ዮሴፍም ጌታውን በቅንነት እያገለገለ ሲኖር የጌታው ሚስት ባሏ በሌለበት ጠብቃ በዮሴፍ ላይ የዝሙት ዐይኗን ጣለችበትና "ከእኔ ጋር ተኛ" አለችው፡፡ ዮሴፍም "እነሆ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፣ ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል፤ ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?" አላት፡፡ እርሷ ግን ስለዚህ ነገር በየጊዜው ትጨቀጭቀው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በቤት ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም ስላልነበረ ወደ እርሱ ገብታ ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሽቶ ወደ ውጭ ወጥቶ ሄደ፡፡ የጲጥፋራ ሚስት ግን የቤቷን ሰዎች ጠርታ "እዩ ዕብራዊው ሰው ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ፣ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ቢሰማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ" ብላ በሐሰት ከሰሰችው፡፡ ባሏም ሲመጣ እንዲሁ ብላ ነገረችው፡፡ ባሏም የእርሷን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፡፡ ዮሴፍን ይዞ እስር ቤት ጣለው፡፡ እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው፡፡ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር፡፡ ❤ የጲጥፋራ ሚስት የኃጢአት ምሳሌ ስትሆን ዮሴፍ የንጽሕና ምሳሌ ነው፡፡ ኃጢአት ደርሳ ሥሩኝ ሥሩኝ ስትላችሁ የንጽሕናን የቅድስናን ነገር አስባችሁ ፈጥናችሁ ከእርሷ ተለዩ ሲል ነው፡፡ ንጽሕናችሁን በኃጢአት አታቆሽሹ አለ፡፡ አንድም የጲጥፋራ ሚስት የዚህ ዓለም ዮሴፍ የመናንያን ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍን የጲጥፋራ ሚስት ሽንገላ ሳያታልለው ጥሏት እንደሸሸ ሁሉ መናንያንም የዚህ ዓለም ሀብት፣ ንብረት፣ ቤት፣ ልጅ፣ ባል፣ ሚስት… ሳያታልላቸው የዓለምን ጣዕም ሸሽተው ገዳም ይገባሉና ነው፡፡