uk
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Відкрити в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Показати більше
4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
#እንኳን_ከዘመነ_ሉቃስ_ወደ_ዘመነ_ዮሐንስ_በሰላምና_በጤና_አደረሰን_አደረሳችሁ!!! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻እንቁጣጣሽ🌻🌻🌻 🌻መልካም አዲስ አመት🌻 🌻🌻🌻@EOTC2921🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

🌻✞🕊 #ስርዓተ_በዓል_ወጾም_ዘኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተ_ክርስቲያን 🕊✞🌻 @EOTC2921 #እንኳን_አደረሰን!!! ❀✞ #ዓመተ_ምህረት፥ ፪ሺ፲፪ ❀✞ #ወንጌላዊ፥ ዮሐንስ ❀✞ #የዘመን_መለወጫ_ቀን፥ ሐሙስ ❀✞ #አበቅቴ፥ ፮ ❀✞ #መጥቅዕ፥ ፳፬ ❀✞ #ጾመ_ነነዌ፥ የካቲት ፪ ❀✞ #ዐብይ_ጾም፥ የካቲት ፲፮ ❀✞ #ደብረ_ዘይት፥ መጋቢት ፲፫ ❀✞ #ሆሳዕና፥ ሚያዝያ ፬ ❀✞ #ስቅለት፥ ሚያዝያ ፱ ❀✞ #ትንሣኤ፥ ሚያዝያ ፲፩ ❀✞ #ርክበ_ካህናት፥ ግንቦት ፭ ❀✞ #ዕርገት፥ ግንቦት ፳ ❀✞ #ጰራቅሊጦስ፥ ግንቦት ፴ ❀✞ #ጾመ_ሐዋርያት፥ ሰኔ ፩ ❀✞ #ጾመ_ድኅነት፥ ሰኔ ፫ @EOTC2921 #እንኳን_አደረሰን 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏

ቅዱስ ሩፋኤል @EOTC2921 መዝሙር.3gp9.57 KB

🌿🌿🌾ቅዱስ ሩፋኤል🌾🌿🌿 ✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ❖ ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3):: ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ፡- “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ መካነ ትጉሃን ዐጸዱ ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ” (ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ (ባሕርዩ) በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ) ይላል ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤ ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡- “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)፤ ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)። እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል፤ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም ስለነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሲገልጽ “ወኲሎሙ ሰራዊተ መላእክት እለ ይቀውሙ ቅድሜሁ ይጸርሑ ወይባርክዎ ለእግዚአብሔር…” (በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚኽ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና የሚዘምሩ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በኾነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ) በማለት የቅዱሳንን ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር በማዕጠንታቸው ለማሳረግ የተመረጡት መላእክት ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ መኾናቸውን አስተምሯል፡፡ ይኽ መልአክ ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይኽ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይኽ ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ፋንድያ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “አይቴ ውእቱ ምጽዋትከ ወጽድቅከ” (በጐነትኽ ምጽዋትኽ ያዳነኽ ወዴት ነው?) በማለት በተናገረችው ጊዜ ዐዝኖ ሞትን ተመኘ (ጦቢ ፪፥፲፬)፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ሩፋኤል ርሱንና ባሎቿ ስለሞቱባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ለማዳን ተልኮ በመምጣት አስቀድሞ በርሷ ላይ ዐድሮ ባሎቿን ይገድልባት የነበረውን ጋኔን አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፤ በዚኽም “ፈታሔ ማሕፀን” ተብሏል፡፡ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት “አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምነ ሰብዐቱ ቅዱሳን መላእክት” (ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ) ብሏቸው ተሰውሯል (ጦቢ ፲፪፥፲፭)፡፡የቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን✞✞✞ 🌻💐🌹 #Join us... 🌹💐🌻 #Share #Share #Share #Share ❀✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆✞✆❀ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👇 @EOTC2921 👇 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🌾🕊✞ #ይቅርታ ✞🕊🌾 @EOTC2921 ✍በእኛ በደካሞች አንደበት እንዳሰብነው ሳይሆን እርሱ ፩ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ በፈቃዱ እንዳሰበልን አኑሮናል ፤ ከዘመን ዘመን አድርሶናል ፤ መጪውንም ዘመን እርሱ ፈጣሪ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሮን ይሁን፡፡✞✞✞ ☞🕊ፈጣሪ ⛪️ይህቺን ጳጉሜ የይቅርታና የምስጋና ቀን አድርጎ ስለሰጠን በእውነቱ፦ ❣ሳናውቅ በስህተት❤ 💙እያወቅን በእህል💔 ❌🌷ያስቀየምነውን ❌🌷ያሳዘነውን ❌🌷ያስከፋነውን ⛪️ለሰው ብቻ ሳይሆን ለፈጣሪ ብለን 💜በንፁህ ህሊናችን 💙ከልብ ተፀፅተን 😍በፍቅር አይናችን 🌍ሁሉንም ፍጡር 💞ይ💕ይ 💞ቅ💕ቅ 💞ር💕ር 💞ታ💕ታ 🌺🌸🌼እንጠይቅ!!!🌼🌸🌸 🌺🌸🌼 እናድርግ!!!🌼🌸🌺 @EOTC2921

🌻✞ #የማህበረ_ቅዱሳን_ቴሌቪዥን ✞🌻 "የምናውቀውን እንናገራለን የአየነውን እንመሰክራለን" እንኳን ደስ አለን ማህበረ ቅዱሳን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን የሙከራ ስርጭቱን መስከረም ፩ ቀን በይፋ ሊጀምርልን ነው፤ ለተባበሩን ሁሉ አምላክ ይባርካችሁ፡፡ Channel Name: EOTCMK Frequency: 11555 MHz Symbol rate: 2500 KS/s Polarity: Vertical(V) Satellite: Nilesat FEC: 7/8 ሁሉም #Share ያድርግ፡፡

🍀🌾✞ #ጳጉሜ ✞🌾🍀 @EOTC2921 ☞✞ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባል ትታወቃች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ ☞✞በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ☞✞ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፡2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ ☞✞የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነው፡፡ ☞✞ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡ @EOTC2921 ❀✿ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✿❀ መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንልን፡፡

🌻🌿 #ፊደል 🌿🌻 @EOTC2921 ✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✞ ☞✞ፊደላት ነገረ እግዚአብሔርን የሚያስረዱ ናቸው፡፡ የፊደላትን ትርጉም በሁለት ከፍለን እንመለከታለን፦ የመጀመሪያ ወይም የጥንቱ የግዕዝ ፊደል ማለትም #አበገደ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የአማርኛው #ሀለሐመ ነው፡፡ ☞✞በዚህ እርሳችን የምንመለከተው የጥንቱን የግዕዝ ፊደላት ማለትም የ #አበገደ ን ሲሆን ይህ የፊደል ቁጥር ፳፪ ነው፡ ይህም የ፳፪ ሥነ ፍጥረት ምሳሌ ነው፡፡ እነዚህም ፊደላት የራሳቸው መጠሪያ ስም እና ትርጉም አላቸው፡፡ እነርሱም፦ @EOTC2921 #አ፦ አልፍ፡ አሌፍ ብሂል አብ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም፤ አ፣ አልፍ፣ አሌፍ አለምን ሁሉ የፈጠረ አብ ማለት ነው፡፡ #በ፦ ቤት፡ ብት ብሂል ባዕል እግዚአብሔር፤ በ፣ ቤት፡ ማለት ባለጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ገ፦ ጋሜል፡ ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር፤ ገ፡ ጋሜል ማለት የሚያስፈራ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ደ፦ ዳሌጥ፡ ዳሌጥ ብሂል ድልው እግዚአብሔር፤ ደ፡ ዳሌጥ ማለት ዝግጁ የሆነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ሀ፦ ሄ፡ ሄ ብሂል ህልው እግዚአብሔር፤ ሀ፡ ሄ ማለት እግዚአብሔር ህልው ዘላለማዊ ነው ማለት ነው፡፡ #ወ፦ ዋው፡ ዋው ብሂል ዋህድ እግዚአብሔር፤ ወ፡ዋው ማለት እግዚአብሔር አንድ ነው ማለት ነው፡፡ #ዘ፦ ዛይ፡ ዛይ ብሂል ዝኩር እግዚአብሔር፤ ዘ፡ ዛይ ማለት እግዚአብሔር አሳቢ ነው ማለት ነው፡፡ #ሐ፦ ሔት፡ ሔት ብሂል ህያው እግዚአብሔር፤ ሔ፡ ሔት ማለት ህያው፡ ዘላለማዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ጠ፦ ጤት፡ ጤት ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር፤ ጠ፡ ጤት ማለት ጠቢብ፡ ጥበበኛ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #የ፦ ዮድ፡ ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር፡ እደ እግዚአብሔር፤ የ፡ ዮድ ማለት የእግዚአብሔር ቀኝ፡ የእግዚአብሔር እጅ ማለት ነው፡፡ #ከ፦ ካፍ፡ ካፍ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር፤ ከ፡ ካፍ ማለት ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ለ፦ ላሜድ፡ ላሜድ ብሂል ልዑል እግዚአብሔር፤ ለ፡ ላሜድ ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው፡፡ #መ፦ ሜም፡ ሜም ብሂል ምዑዝ እግዚአብሔር፤ መ፡ ሜም ማለት ጣፋጭ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ነ፦ ኖን፡ ኖን ብሂል ንጉሥ እግዚአብሔር፤ ነ፡ ኖን ማለት እግዚአብሔር ንጉሥ ነው ማለት ነው፡፡ #ሠ፦ ሣምኬት፡ ሣምኬት ብሂል ሰፋኒ እግዚአብሔር፤ ሠ፡ ሣምኬት ማለት ገዥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ #ዐ፦ ዔ፡ ዔ ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር፤ ዐ፡ ዔ ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው፡፡ #ፈ፦ ፌ፡ ፌ ብሂል ፍቁር እግዚአብሔር፤ ፈ፡ ፌ ማለት እግዚአብሔር የሚወደድ ነው ማለት ነው፡፡ #ጸ፦ ጻዴ፡ ጻዴ ብሂል ጻድቅ እግዚአብሔር፤ ጸ፡ ጻዴ ማለት እግዚአብሔር እውነተኛ ነው ማለት ነው፡፡ #ቀ፦ ቆፍ፡ ቆፍ ብሂል ቅሩብ እግዚአብሔር፤ ቀ፡ ቆፍ ማለት እግዚአብሔር ቅርብ ነው ማለት ነው፡፡ #ረ፦ ሬስ፡ ሬስ ብሂል ርኡስ እግዚአብሔር፤ ረ፡ ሬስ ማለት እግዚአብሔር አለቃ ነው ማለት ነው፡፡ #ሰ፦ ሳን፡ ሳን ብሂል ስቡሕ እግዚአብሔር፤ ሰ፡ ሳን ማለት እግዚአብሔር ምስጉን ነው ማለት ነው፡፡ #ተ፦ ታው፡ ታው ብሂል ትጉህ እግዚአብሔር፤ ተ፡ ታው ማለት እግዚአብሔር ትጉህ ነው ማለት ነው፡፡ ☞✞ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፡ ኀ የሐ፤ እና ፀ የጸ ድርቦች ተደርገው የግዕዝ ፊደል በቁጥር ፳፪ እንደሆኑ፤ እንዲሁም ጰ እና ፐ ከጊዜ በኃላ እንደተጨመሩ ሲገልፅ፡ የተጨመሩበትም ምክንያት፦ ሁለቱ ፊደላት በጽርዕ፣ በቅብጥና በሮማይስጥ ያሉ ፊደሎች ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መጻሕፍት ደግሞ የተተረጎሙት ከነዚ ነውና መጻሕፍቱ ከተተረጎሙበት ቋንቋ ጋር ለማስማማት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ☞✞ ኀ የሐ፣ ፀ የጸ ድርቦች ናቸው እንጅ በትርጉም እና በዘረ ድምፆች ግን የተለያዩ ናቸው፡፡ #ሰረቀ፦ በእሳቱ "ሰ" እና በንጉሡ "ሠ" የትርጉም ልዩነት እንደሚያመጡ ሁሉ፡ ኀ እና ፀም የትርጉም ልዩነት ያመጣሉ፡፡ ለምሳሌ፦ ☞✞ #ፈፀመ በፀሐዩ "ፀ" ሲጻፍ፡ አሰረ፣ ለጎመ፡ የሚል ትርጉም ሲሰጥ፤ ☞✞ #ፈጸመ በጸሎቱ "ጸ" ሲጻፍ፡ ደግሞ ጨረሰ የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡ እንዲሁም፦ ☞✞ #ነስሐ በሐመሩ "ሐ" ሲጻፍ፡ ተጸጸተ ተመለሰ የሚል ትርጉም ሲሰጥ፤ ☞✞ #ነስኀ በብዙኃን "ኀ" ሲጻፍ ደግሞ ሸተተ፣ ከረፋ የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ስለዚህ በቋንቋ ሥርዓት አንድ ድምፅ የፍች (የትርጉም) ለውጥ ካመጣ ሞክሼ ወይም ዘር ድምፅ ሊባል አይችልም፡፡ በመሆኑም ራሳቸውን የቻሉ የግእዝ ድምፆች እንደሆኑ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ @EOTC2921 #በእውኑ_ኢትዮጵያዊ_መልኩን_ወይስ_ነብር_ዝንጕርጕርነትን_ይለውጥ_ዘንድ_ይችላልን? ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ፡ ፲፫፥፳፫ እግዚአብሔር አምላክ በሐይማኖታችን ጸንተን ቅዱሳን አባቶቻችን የተሰጡንን ቅርስ ጠብቀን እኛም ለተከታይ ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል፡፡ @EOTC2921 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏

ዓለመ፡፡ ✍ቸር እረኛ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ታዛዥ የሆነ ክርስቶስ ለአሕዛብ የመጣ፡፡ እሺ ብሎ ታዛዥ ሆኖ ዓለምን ይቤዥና ያድን ዘንድ ከሰማይ ወረደ፤ መጣ፡፡›› (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ገጽ)፡፡ በማለት ሁሉን የሚገዛ አምላክ ዓለሙን ሊቤዥና ሊያድን እሺ ብሎ በፈቃዱ መምጣቱን መሰከረ፡፡ ሁሉን የሚመግብ፣ የሕይወት እንጀራንና የሕይወት መጠጥን የሚሰጥ ጌታ ወደ ሰርግ ተጠራ፡፡ ለፍጥረቱ ማዕድን የሚያዘጋጅ ጌታ በፈሪሳዊው ስምዖን ቤት ለግብዣ ተጠራ፡፡ ዮሐ 2፤2፣ ሉቃ ፤36-37፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በፈሪሳዊው ማዕድ ላይ የቀረበው የጌታ ማዕድ በሚለው ስብከቱ ‹‹ ንስሓ ስለምትገባው ስለዚያች ኃጢአተኛ ሴት ሲል ከግብዣው ቤት ተገኘ፤ ጌታ ርሀቡ ሥጋዊው ምግብ ሳይሆን የዚያች ኃጢአተኛ እንባ እንጂ… ወደ ፈሪሳዊው ስምዖን ቤት የሄደው በምግብና በመጠጥ ለመዝናናት አልነበረም ሕይወት መድኃኒት የሆነውን ትምህርቱን በማዕዱ ለማቅረብ በመሻቱ ነበር እንጂ፡፡ … ክፉ የተባለው ሰይጣን በመብል ምክንያት አዳምና ሔዋንን ሞትን የሚያመጣ ምክርን እንደመከራቸው እንዲሁ ቸሩ ጌታችን ደግሞ በማዕድ ቦታ ተገኝቶ ሕይወት ሰጪ የሆነ ትምህርቱን ለአዳም ልጆች በማዕዱ አቀረበ፡፡ እርሱ ጌታችን የጠፉትን ነፍሳት ለማጥመድ አሳ አስጋሪ ነበር፡፡ ቀራጮችና አመንዝሮች ወደ ስካርና ሥርዐት አልበኝነት ሲፋጠኑ ተመለከታቸው፤ ሥጋንም ከሚያወፍር የማዕድ ቦታ እነርሱን በማስገር ነፍስን ወደሚያወፍር ጾም ሊያሻግራቸው የቃሉን መረብ በማዕዱ ውቅያኖስ ላይ ጣለው፡፡››በማለት ገለጸው፡፡"ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም" 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 #JOIN #JOIN #JOIN #JOIN 🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻 🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻 🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻

✍☞⛪️ ነገረ ክርስቶስ ⛪️☜✍ 🌼💓 @EOTC2921 💓🌼 ✍ብርህት፣ ንጽህት፣ ጽድልት፣ የሆነች ቤተክርስቲያናችን ከምታስተምራቸው ትምህርቶች አንዱና ዋነኛው ነገረ ክርስቶስ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ሲሆን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ ሲሆን በኋላኛ ዘመን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆነ፡፡ እንዲህ እናምናለን፤ እንዲህም እናስተምራለን፡፡(ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ)፡፡ ✍ነገረ ክርስቶስ ማለት ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምናምነውን እምነት የምናስተምረውን ትምህርት የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ስለ ጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚታመነው፣ የሚነገረው፣ የምንመራበት ምንድነው የሚለውን በሚገባ ለመረዳት በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በሊቃውንት፣ በትውፊት የተላለፈውን አስተምህሮ የምናቀርብበት ነው፡፡ አግዚአብሔር አምላካችን የሚታየውን ዓለም ከማስገኘቱ በፊት እስከ ዘላለም ድረስ በአንድነቱና በሦስትነቱ፣ በመለኮቱ፣ በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከሚንቀሳቀስ እንስሳ በፊት ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት፣ እግዚአብሔር በመንግስቱ ነበረ፡፡ አዳምን በእርሱ አምሳልና አርአያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዙንም ሳያፈርስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ ማርያም ሥግው ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ የተገኘ ባሕርይ፣ ከሕይወት የተገኘ አዳኝ ከመድኃኒት የተገኘ መድኅን፣ ከገዥ የተገኘ ገዢ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ህላዌ እንደሆነ እናምናለን (መዝገበ ሃይማኖት)፡፡ ከአብ መወለዱም በዚህ ዘመን፣ በዚህ ወቅት፣ በዚህ ሰዓት ተብሎ ዘመን አይቆጠርለትም፤ በሰውና በመላእክት አእምሮም ሊመረመር አይችልም፡፡ ሰውንም ስለማዳን በአባቱ ፈቃድ በእርሱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በድንግልና ተወለደ፡፡ ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠም፡፡ በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ሆነ፤ በሚያስደንቅ ዙፋኑ ለደቀመዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮች መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት ፍቅር የአሕዛብን እግረ ልቡና ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ መላእክት ደነገጡ (ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘስሩግ)፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግብ ጌታቸው በብብቷ (በክንዷ) ተቀምጦ ጡቷን ሲጠባ ባዩ ጊዜ በአርያም ፈለጉና በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞው ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት፡፡ የጌታን ትሕትና ባዩ ጊዜም ዓይኖቻቸውን ወደ ላይ ወደ አርያም ከፍ ከፍ አደረጉ ክንፋቸውንም ዘርግተው ለሁሉ ጌታ ለአንተ ምስጋና ይገባሃል እያሉ ጌታቸውን አመሰገኑ፡፡ (አንቀጸ ብርሃን) አዳምን ካልታረሰች መሬት የፈጠረው ሔዋንንም ከአዳም ያለእናት የፈጠራት እርሱ ከንጽሕት ድንግል ያለ ወንድ ዘር ተወለደ፡፡ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና ስለዚህ የአዳምን ብድራት ትከፍለው ዘንድ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደች ይህም ድንቅ በሚሆን አንድነት የፍጥረት ሁሉ እኩልነት ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ከአዳም አጥንት ጎድን ሲነሳ ምንም አካል እንዳልጎደለው እንዲሁ ከድንግል የምትናገር ነፍስን ሲነሳ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተለወጠም፡፡ አዳም የጎድን አጥንት ከእርሱ ከተነሳ በኋላ አካል ሳይጎድለው ፍጹም ሆኖ እንደኖረ እንዲሁ ድንግልም ሕጻን ክርስቶስ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ በድንግልና ጸንታ ኖረች›› አለ፡፡ ሕዝ 44፤1-3፣ መኃ 4፤12 ነቢያት ስለእርሱ ሰው መሆን ተነበዩ፡፡ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።›› በማለት ትንቢት ተናገረ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ›› አለ፡፡ (ኢሳ 14 ፣ 9፤6፣ 8፤4)፡፡ ጌታችን በመወለዱ በዲያብሎስ የተያዙትን ማርኳል፣ ሲኦልን በዝብዟልና ስሙ ‹‹ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ›› ተብሎ ተጠራ፡፡ የማይደፈር ግሩም ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን ትሑት ነው፡፡ የማይደረስበት ልዑል ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን የባርያውን መልክ ነሳ፡፡ የማይዳሰስ እሳት ነው፡፡ እኛ ግን አየነው፣ ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋር በላን ጠጣንም (ቅዳሴ ማርያም)፡፡ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረና ሁሉን ሚመግብ ሁሉ በእጁ የተያዘ መላእክት የሚታዘዙለትና የሚያገለግሉት፣ እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ አለ (ሉቃ 22፤27)፡፡ በአዳም ምክንያት የጨለመውን ልቡናችንን ለማብራትና በእርሱ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኖ የመጣ (ዮሐ 12፤16)፡፡ ጨለማን ያስወገደ ብርሃን የሃይማኖትና የጽድቅ ጣሪያዋ (ጠፈሯ)፣ ሃይማኖትም ወንጌልም፣ በብዙ ድካም እርሱን ደስ ያሰኙት የሚወርሱት፣ የሃይማኖት ገንዘብን ይዘው በሠርክ የሚገቡበት መንግስተ ሰማያት እርሱ ነው (ሉቃ 17፤21፣ መልክአ ኢየሱስ)፡፡ ክብርና ምስጋና ይግባውና የእኛን ሞት ሞቶ የእርሱን ሕይወት የሰጠን፡፡ ድዳ ለነበሩት ቃል፣ ለተሰበሩት ምርጉዝ፣ ለዕውራን ብርሃን፣ለሐንካሶች መሄጃ፣ ለለምጻሞች የሚያነጻቸው ሆነ፡፡ በዴዌ የተያዙትን አዳነ፣ ደንቆሮዎችን ፈወሰ፣ ሞትን ዘለፈው ጨለማንም አሰቃየው፡፡ ብርሃን ኅልፈት የሌለበት፣ ፀሐይ፣ የማይጠፋ ፋኖስ፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ፣ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ሁሉን የፈጠረ፣ ሰውን ለማዳን ለሁሉ የተገለጠ፣ ነፍሳችንን የመለሳት እርሱ ነው (ኪዳን ዘነግህ)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ምንስ እላለሁ ምንስ እናገራለሁ ከዘመን በፊት የነበረ እርሱ ትንሽ ሕጻን ሆኗልና ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ›› በማለት የጌታን ትሕትና አደነቀ፡፡ ነፋሳት የሚታዘዙለት፣ መላእክት የሚላላኩት እርሱ ለእናቱና ለዘመዶቹ እየታዘዘ አደገ፡፡ ሁሉን አዋቂ ሲሆን አልአዓዛርን የት ቀበራችሁት ብሎ ጠየቀ፤ እርሱ የሕይወት ውሃ ሲሆን ከሳምራዊት ሴት ውሃ ለመነ፡፡ ምራቅ ከጭቃ ጋር ለውሶ እውር ያበራ እርሱን አይሁድ ምራቅ ተፉበት፡፡ ጠባቂ አጥተው ለባዘኑት መልካም እረኛ ሆኖ መጣ ስለበጎቹም ነፍሱን ሰጠ፡፡ (ዮሐ 1፤11) ቅዱስ ያሬድ ‹‹ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ዘመጽአ ውስተ ዓለም ተአዛዚ ከዊኖ ክርስቶስ ለአሕዛብ፡፡ ኦሆ ብሂሎ ተአዛዚ ከዊኖ ወረደ ወመጽአ ለአድኅኖ… ከመ ይቤዙ ወያድኅን

#መልክዐ_እግዚአብሔር_አብ #እግዚአብሔር ባዕል ዘኢትነዲ ለግሙራ፡፡ኀሩመ ምንዳቤ ወተጽናስ ወግብረ መከራ፡ ትቤ ነፍስየ ዘአፈ ድፈደት ቃለ ገዓራ፡፡ ያብዕለኒ ተሣሀሎትከ መብዓሌ ንጉሥ ሐራ፡፡ ከመአብዓልኮሙ ቅድመ ለሄኖክ ወዕዝራ፡፡ #ኦ_ዘትቤሎ፡ለእስራኤል ቍልዔከ፡፡ ኦርኀብ አፉከ ወእመልዖ ለከ፡፡ ዓዲ፡ አበቍው አፉየ ወእመልዖ ለከ፡፡ ዓዲ አበቍው አፉየ ምላዕ ስብሐቲከ ከመእስብሕ አኰቴተከ፡፡እስመ አምላክ አንተ ዘኢኮንከ ድሩከ #ኦ_ከሣቴ፡ ራዕዩ ለዮሐንስ ነቢየ ፍጥሞ፡፡ ክሥትሊተ እግዚኦ ለአንብቦ መጽሐፍ  ወተርጕሞ፡፡ወወጢነ ግብር ሐዲስ ምላዕ ለፈጽሞ፡፡ከመ እንብብ ሕገዚኣከ በልሳነ ሐዲስ  አቅሞ፡፡ ዘአልቦ ጽርዓት ወአልቦ አርምሞ፡፡ #ሰላም_ለዝከረ ስምከ ስቡሕ ወዉ ዱስ ዘትሴባሕ ወትረ በአፈ ኵሉ ዘነፍስ፡፡#እግዚአብሔር_አብ እስመ አልብከ ተጽናስ፡እምቅድመ ዘመን ዘመናዊ ወድኀረ ዘመናት ሐዲስ፡፡እንዘ ለዘመናት አንተ ሕገ ዛሕን ወመርስ፡፡ #ሰላም_ለስእርተ፡ ርእስከ መ ድ ም መ ፅዕዳዌ ፅዕድቱ፡፡ ወለርእስከ ዓጺቢጸ ተባይጾ አልቦቱ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ አበ ኀሩያን ፪ቱ ፀሐየ ሥሉስ ዋህድ ሠርጎ ምልዓ ዓለም፡፡ የሐቱ፡፡ እስከነ ምዕራብ ወሠርቅ እምላዕሉ ወታሕቱ ፡፡ #ሰላም_ለገጽከ፡ ዘተሰብሐ ወተ መዝገነ፤ ዘምስለ ፪ኤ ገጻት እንዘ ያርኢ ብርሃነ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ ግጻዌ ኵልነ፡፡ ስንከ ስነ ተደሞ ምልዓ ስፍሐ ሰማያት ሰፈነ፡፡ብዕለ ስብሐቲከ ፈጺሞ ከደነ፡፡ #ሰላም_ለቀሪንብቲከ፡ ወለአዕይንቲከ ብሩሃት፡፡ ዘኢይትጋወሮን ጽልመት፡፡#እግዚአብሔር_አብ፡ አበ ብርሃናት አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት፡፡እስመ ለከ ኃይል ወለከ ስብሓት፡፡ #ሰላም_ለአዕዛኒከ፡ አጽማዕያነ ጸሎት ኵለሄ ፡፡ ወለማላትሒከ ዓዲ እለ ተአጽፋ ነደ ሱራሄ፡ #እግዚአብሔር፡ ዘትትዌከፍ ምልዓ ስባሔ፡፡ ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወብሂሎትየ ኤሎሄ፡፡ ወአውይዎትየ ከመ አርዌ ዘይሰመይግሔ፡፡ #ሰላም_ለአዕናፊከ፡ መሣክወ ጼናርኀው፡፡ ወለከናፍሪከ ዓዲ አናቅጸ ንባብ ፍትው፡፡ #እግዚአብሔር_አብ፡ ዘኢትመውት ሕያው፡፡ እግዚአብሔር፡ ሳን እግዚአብሔር ታው፡፡ በኵሉ ወበውስተ ኵሉ ዓለም ህልው ፡፡ #ሰላም_ለአፋከ፡ ከመ አፉሁ ለአዳም፡፡ወለአስናኒከ ዓዲ አስናነ መለኮት ግሩም ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ፡ ህልወ ትካት እምቅድመ፡፡ ዘትሄሉ ወትረ ድኀረ፡ይመጽእ፡ ዘመነ፡ ሐዲስ፡ ዓለም፡፡ ምልእተ፡ ጸጋከ፡ በስብሓት፡ ፍጹም፡፡ #ሰላም_ለልሳንከ፡ ኢነባቢ፡ በግዱድ፡፡ወለድምፀ፡ ቃልከ፡ ድምፀ፡ ነጎድጓድ፡፡#እግዚኣብሔር_አብ፡ አኀዜ፡ ዓለም፡ በእድ፡፡ ያስተናብበኒ፡ በልሳነ፡ ኵሉ ነገድ፡፡ጰራቅሊጦስ ነድ፡፡ #ሰላም_ለእስትንፋስከ፡ እስትንፋሰ፡ ሕይወት፡ ወጥዒና፡፡ ወለጉርዔከ፡ ዓዲ፡ኆኀተ፡ ለሆሳስ፡ ወዴዴ፡ ጉህና፡፡#እግዚአብሔር_አብ፡ መድምመ፡ ልዕልና፡፡ዘታበድር፡ ጽድቀ፡ ወይዋሄ፡ ወግብረ፡ኵሉ፡ ትሕትና፡፡ ትዕቢትስ፡ አውድቆ፡ለሳጥን፡፡ #ሰላም_ለጽሕምከ፡ ለዘኢይትረከብ፡አቅሙ፡፡ መንክር፡ ቆሙ፡ ወዕሙቅ፡ክበበ ግድሙ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ፡ለአሮን፡ ከመ፡ ጽሕሙ፡፡ አሠንዮ ለጽምሕየ፡ በጠለ፡ ረድኤት፡ ዝናሙ፡፡ወደመና፡ ሣህልከ ሉዓላዊ ዘልዑል ምስያሙ፡፡  #ሰላም_ለክሣድከ፡ ዕበየ ግርማ ዘየዐውዶ፡፡ ወለመትክፍትከ ዓዲ እለ ሕልዋን በተዋህዶ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ ክቡተ ኀቡእ ዘእምተግህዶ፡፡ ኀብአኒ በጽላሎትከ እንዘ ያስተናሥእ እጾ፡፡አመ ከመ እሳት ወልድከ ያዉዒ ክርዳዶ፡፡ #ሰላም_ለዘባንከ፡ ዘኢያገምሮ ኪሩ ብ ፡፡ ወለእንግድዓከ ዓዲ ምርፋቀ የውሃን አርባብ፡፡ ባሕረ ጥበባት እሙቅ #እግዚኣብሔር_አብ፡፡ ያጥብበኒ እምዕበድየ ለወልድከ ጠቢብ፡፡ እስመ ነገሩ መድምም ወኪኑ ዕፁብ፡፡ #_ሰላም_ለሕፅንከ፡ከላስስተ ጸጋ አተቦ ወለአእዳዊከዓዲ መግቦት ዓለም ምልዓ መግቦ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ ክብርከ ዕፁብ ለተናብቦ፡፡ መድምም ጥቀ ሰሚዖቱ ለተናብቦ፡፡ መድምም ጥቀ ሰሚዖቱ በኀበ እዝነ ልብ ዘቦ፡፡ ወለመንግሥትከ ፍፃሜ ዘአልቦ፡፡ #ሰላም_ዕብል ለመዛርዒከ መዋዕያዌ ወለኵርናዕከ ዓዲ በተሰናፅዎ ህላዌ፡፡#እግዚኣብሔር_ኣብ መፈውሰ ደዌ፡፡ ንድፍ፡ ደዌ፡ ዘኣየ፡ በሐፀ፡ ፈያት፡ አርዌ፡፡ወግብርከ፡ ያሕይወኒ፡ ዘኮነ፡ ማኀየዌ፡፡ #ሰላም_ለእመትከ፡ እመታት አምላክ፡ግሩም፡፡ ወለእራኅከ፡ ዓዲ፡ አኃዜ፡ ስፋሕ፡ዓለም፡፡ #እግዚአብሔር_አብ፡ ብሑተ፡ሥልጣን፡ እምቅድም፡፡ ዘህልው፡በልዕልና፡ ዲበ፡ መንበረ፡ ነድ፡ ወፍሕም፡፡ወለእለሂ፡ በየማን፡ ወጽግም፡፡ #ሰላም_ለኣጻብኢከ ሕሩም፡ ሐኬት፡ለፈጢር፡፡ ወለአጽፈሪከ፡ ዓዲ፡ እለ፡ ቀጸባሁ፡ ለግብር፡፡ #እግዚአብሔር_አብ፡ወላዴ፡ ኂሩት፡ ወፍቅር፡፡ ወምላዕ፡ ፆታ፡ኵሉ፡ እምዉስት፡ ሰማያት፡ ወምድር፡፡ ዘትሜግብ፡ አንተ፡ እስከ፡ የብስ፡ ወባሕር፡፡ #ሰላም_ለገቦከ መብረቅ፡ ስብሐት፡ልብሱ፡፡ ወለከርሥከ፡ ዓዲ፡ ኢውሱን፡ራህበ፡ መቅደሱ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ ወለወልድ፡ ቅዱስ መንፈሱ፡፡ #ኪሩቤል_ወሱራፌል፡ እለ፡ አክናፊሆሙ፡ ስሱ፡፡ ኪያከ፡ ወትረ፡ ይቄድሱ፡፡ #ሰላም_ለልብከ ጻድቅ፡ ወየዋህ ፡፡ ወ ለሕሊናከ ፡ ዓዲ ፡ ማዕምረ ፡ ዘመን ፡ ነዋህ ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ በአፈ፡ ኵሉ፡ ስቡሕ፡፡ እስመ፡ ሣህልከ፡ ወምሕረትከ፡ ብዙኀ፡፡ የማንከ፡ ለምሕሮ፡ ኵለሄ፡ስፋሕ፡፡ #ሰላም_ለሕንብርትከ ዘመድምም፡ ርእየቱ፡፡ ወለሐቌከ፡ ዓዲ፡ መንክር፡ ሠርጐ ቅናቱ፡፡ ንጉሠ፡ ነገስት፡ #እግዚአብሔር_አብ እንተ፡ እምላዕሉ፡ ወታሕቱ፡፡ ያቀንተኒ፡ ጋጋ፡ አርምሞ፡ እስመ፡ መዋዒ፡ ውእቱ፡፡ ለአርዌ፡ ዐመፃ፡ ፀርየ፡ ከመ፡ እማዕ፡ ቦቱ፡፡ #ሰላም_ለአቍያጺከ_አቍያጸ፡ መለኮት፡ክቡድ፡ ወለአብራኪከ፡ ዓዲ፡ ዘምስለ፡ሰጊድ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ ወላዴ፡ ዋህድ፡ ወልድ፡፡ ቀደሱከ፡ በኁባሬ፡ትጉሃነ፡ሰማይ፡ ነገደ፡ አመ፡ አመንበሩ፡ ተነጽሐ፡ዕድወ፡ ደም፡ ወአብድ፡፡ #ሰላም_ለአእጋሪከ፡ ዘያንቀለቅል፡ምድረ፡፡ ወለሰኰናከ፡ ዓዲ፡ ዘምስለ፡መከየድ፡ ኀብረ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ፡ዘእምቅድመ፡ ዓለም፡ ነበረ፡፡ ወፀንዐ፡በተዋህዶ እስከ አስተጋብአ ምድረ፡፡ወእም ቅድመ ገቢር በለብዎ ዘፈጸመ ግብረ፡፡ #ሰላመ_ለአጻብኢከ ወለአጽፋሪከ ፲ቱ፡፡ለተዋህዶ ሕላዌ እለ ልጹቃን እሙንቱ፡፡#እግዚአብሔር_አብ ለአዳም ጥንተ ሕይወቱ፡፡ ያሕይወኒ ሕያውናከ እሞተኃጢአት ከንቱ፡፡ እስመ ለሐይው ልብየ ይፈቱ፡፡ #ሰላም_ለአካለ ቆምከ ኢውሱን እምአቅመ፡፡ ወለመልክእከ ዓዲ ዘግርማ ራእይ መድምም #እግዚአብሔር_አብ አበ ብርሃናት ግሩም፡፡ ቃልከ ወሕይወትከ ግሩመ መልክእ ወቆም፡፡ ለመንግሥትከ ዘአልቦ ተፍጻም፡፡ ኦ አምላከ ኵሉ እንዘ አምላከ ጽድቅ ባሕቲትከ፡፡ ወኵሎ ገበርከ በፈቃድከ፡፡ #እግዚአብሔር_አብ እስመ ተጽናስ አልብከ፡፡ምርሐኒ ፍኖተ ጽድቅ ወአለብወኒ ሕገከ፡፡ወኵሉ ቅሩብ ወስሩዕ በኀቤከ፡፡ ስብሐት ለከ፡ #እግዚአብሔር_አብ በኍልቈ ዕለታት ወለያልይ፡፡ #ስብሐት_ለከ_እግዚአብሔር_አብ በኍልቈ ኵሉ ግናየ ክረምት ወሐጋይ፡፡ #ስብሐት_ለከ_እግዚአብሔር_አብ በኍልቈ ኵሉ መዋዕል ወለያልይ ፡፡#ስብሐት_ለከ_እግዚአብሔር_አብ በጕልቈ ኵሉ ዘኢይትረአይ፡፡ ስብሐተ ስብሐተ ቅድም ናከ ዘልፈ ይነግር ሰማይ፡፡#ኦ_እግዚአብሔር_አብ ዕቀበኒ ወአድኀነኒ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ሊተ ለ________ ©ከመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ  የተወሰደ፤ የአባታችን በረከት ይደርብን፤ አምላክ ከዚህ በላይ የሚያገለግልበትን እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡

ውዳሴ_ማርያም_ዘ፯_ቱ_ዕለታት_በንባብ_በቁጥር.m4a20.86 MB

✞ #ፀሐይ_ተወለደ ✞ "በብርሃን ሳለን፣ የብርሃን ልብስ ለብሰን፣ ድንገት ብንራቆት፣ ጉስቁልና አግኝቶን፣ ከብርሃንህ ሸሽተን፣ ጨለማ ከቦን፣ የጨለማው ኑሮ፣ መንገድ አደናብሮ፣ ወደ ጥልቁ ገደል፣ ሲጥለን ወርውሮ፣ አይኖቻችን ይዩ፣ መንገዱን እንዳንስት፣ ብርሃንህን ላክ፣ እንዳን ከጽልመት፡፡" እያሉ ቢጮሁ፣ ደጋግ ነቢያት፣ ጨረቃዋ ወጣች፣ የብርሃን እናት፣ በጨረቃ ልደት፣ በደስታ ስንቦርቅ፣ ተዓምር ተከሰተ፣ የሚያስብል እፁብ ድንቅ፣ ከዚያች ከጨረቃ፣ ፀሀይ ተወለደ፣ የኃጢአት ተራራ፣ ጨለማ ተናደ፣ በጨለማው ጥላ፣ መንገድ የጠፋበት፣ ይምጣ ይመላለስ፣ ብርሃኑ ሳለለት፣ ፀሀይ እድሜው ጠልቆ እንዳይጨልምበት። 🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🙏

ደ ማለት ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ መለኮቱ ማለት ነው፡፡ ዱ ማለት ፈዋሴ ዱያን ማለት ነው፡፡ ዲ ማለት ቃለ ዐዋዲ ማለት ነው፡፡ ዳ ማለት ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዴ ማለት ዐማዴ ሰማይ ወምድር ማለት ነው፡፡ ድ ማለት ወልድ ዋሕድ ማለት ነው፡፡ ዶ ማለት ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ ማለት ነው፡፡ ገ ማለት ገባሬ ሰማያት ወምድር ማለት ነው፡፡ ጉ ማለት ለአስካለ ሕይወት ሐረጉ ማለት ነው፡፡ ጊ ማለት ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጋ ማለት ጋሜል ግሩም እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጌ ማለት ጽጌ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡ ግ ማለት ሐጋጌ ሕግ ማለት ነው፡፡ ጐ ማለት ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ማለት ነው፡፡ ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡ ጒ ማለት ጒንደ ሐረገወይን ወልድ ማለት ነው፡፡ ጓ ማለት ዕጓለ እመሕያው ማለት ነው፡፡ ጔ ማለት ዝንጓጔ መስቀል ማለት ነው፡፡ ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡ ጠ ማለት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጡ ማለት ውስጡ ለሰብእ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጢ ማለት መያጢሆሙ ለኃጥአን ማለት ነው፡፡ ጣ ማለት የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ ማለትነው፡፡ ጤ ማለት ጤት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጥ ማለት ስሉጥ ወርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጦ ማለት ሦጦ ለመንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ ማለት ነው፡፡ ጰ ማለት ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጥድቅ ማለት ነው፡፡ ጱ ማለት ኮጱ መዓዛ ሰብእ ማለት ነው፡፡ ጲ ማለት ሠራጲሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡ ጳ ማለት ጳጳስ ወንጌል ማለት ነው፡፡ ጴ ማለት አክራጴ ኃጢአት ማለት ነው፡፡ ጵ ማለት ጵርስፎራ ማለት ነው፡፡ ጶ ማለት ጶሊስ ማለት ነው፡፡ ጸ ማለት ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ፀ ማለት ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ጹ ማለት ገጹ ለአብ ማለት ነው፡፡ ፁ ማለት ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት ማለት ነው፡፡ ጺ ማለት ሐዋጺ ነፍሰ ትሑታን ማለት ነው፡፡ ፂ ማለት መላፂ ዘክልኤ አፉሁ ማለት ነው፡፡ ጻ ማለት ጻዴ ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ፃ ማለት ፋፃ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ጼ ማለት አዕቃጼ ሰኮና ማለት ነው፡፡ ፄ ማለት ሕፄሁ ለዳዊት ማለት ነው፡፡ ጽ ማለት ጽንሁ ተስፋሁ ማለት ነው፡፡ ፅ ማለት ዕፅ አብርሃም ዘሰፀረ ለምስዋዕ ማለት ነው፡፡ ጾ ማለት ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ ማለትነው፡፡ ፆ ማለት ማዕፆ አፉሆሙ ለጻድቃን ማለት ነው፡፡ ፈ ማለት ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ ማለት ነው፡፡ ፉ ማለት ምዕራፉ ለዓለም ማለት ነው፡፡ ፊ ማለት ፊደለ ወንጌል ዘአባ ኀነፊ ማለት ነው፡፡ ፋ ማለት አልፋ ወኦ ማለት ነው፡፡ ፌ ማለት ኀዳፌ ነፍሳት ማለት ነው፡፡ ፍ ማለት ፍኖት ለኀበ አቡሁ ማለት ነው፡፡ ፎ ማለት ፎራ ኅብስተ ቍርባን ማለት ነው፡፡ ፐ ማለት ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ፑ ማለት ኖፑ አስካለ ወንጌል ማለት ነው፡፡ ፒ ማለት ፒላሳሁ ማለት ነው፡፡ ፓ ማለት ፓንዋማንጦን ማለት ነው፡፡ ፔ ማለት ፔ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ፕ ማለት ሮፕ ጽኑዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ፖ ማለት በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ ወበደኃሪ የኀልፎ ለዓለም ማለት ነው፡፡ "✞ወራዙት አፍቀሩ ልሳነ ግእዝ ይትማህሩ✞" <✞ወጣቶች የግእዝን ቋንቈ ይማሩ ዘንድ ወደዱ።✞> 🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🙏

✞ #የፊደላት_ትርጉም ✞ ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡ ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡ ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡ ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡ ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡ ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡ ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡ ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡ ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡ ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡ ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡ ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡ ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡ ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡ ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡ ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡ ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡ ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡ ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡ ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡ ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡ ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡ ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡ መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡ ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡ ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡ ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡ ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡ ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡ ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡ ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡ ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡ ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡ ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡ ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡ ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡ ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡ ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡ ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡ ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡ ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡ ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡ ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡ ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡ ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡ ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡ ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡ ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡ ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡ ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡ ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት ነው፡፡ በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡ ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡ ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡ ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡ ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡ ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡ ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት ድንግል ማለት ነው፡፡ ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡ ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡ ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡ ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡ ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡ ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡ ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡ ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡ ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት ነው፡፡ ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡ ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡ ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡ ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ ማለት ነው፡፡ ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡ ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡ ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡ ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡ ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡ ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡ ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡ ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት ነው፡፡ ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡ ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡ ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡ ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡ ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡ ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ በምዕር ማለት ነው፡፡ ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡ ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡ ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡ ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡ ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡ ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡ ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡ ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡ ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡ ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዜ ማለት አኃዜ ዓለም በእራኁ ማለት ነው፡፡ ዝ ማለት ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዞ ማለት አግአዞ ለአዳም ማለት ነው፡፡ የ ማለት የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ ማለት ነው፡፡ ዩ ማለት ዕበዩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ዪ ማለት መስተሥርዪ ማለት ነው፡፡ ያ ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው፡፡ ዬ ማለት ዐሣዬ ሕይወት ማለት ነው፡፡ ይ ማለት ሲሳይ ለርኁባን ማለት ነው፡፡ ዮ ማለት ዮድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡

#ጸሎተ_ሃይማኖት በመ/ር ኤርምያስ

በሰላመ ቅዱስ ..............ተና.ተጣይ ገብ #ር ኤል..................... ሰያፍተነሺ መላእክ .......................ተጣይ ኦ...................... ወዳቂ እግዝእትየ .......... ተነሺ ማርያም ...........ተጣይ ሰላም ...............ተጣይ ለ #ኪ ................ተነሺ ድንግል ............ተጣይ በኅሊናኪ ..............ተነሺ ወድንግል.............. ተነሺ በሥጋኪ ................ተነሺ እመ #እግዚአብሔር ...........ተነባቢ ተጣይ ጸባዖት .................. ተጣይ ሰላም ...................ተጣይ ለ #ኪ ......................ተነሺ ቡርክት ....................ተጣይ አንቲ ........................ተነሺ እም አንስት ...............ተጣይ ወቡሩክ ....................ተጣይ ፍሬ ከርሥኪ ...... ............ተነባቢ.ተነሺ ተፈሥሒ ........................ተነሺ ፍሥሕት .......................ተጣይ ኦ ....................... ወዳቂ ምልእተ ፀጋ ...............ተነባቢ #እግዚአብሔር .............ተጣይ ምስሌኪ ................ተነሺ ሰአሊ ...................ተነሺ ወጸልይ............... ተነሺ ምሕረተ .. ................. ተነሺ ኅበ ፍቁር .................... ተናባቢ.ተጣይ ወልድኪ ...................... ተነሺ ኢየሱስ ክርስቶ .................. ተጣይ ከመ ይስረይ ..................ተናባ.ሰያፍ ተነሺ ለነ .....................ተነሺ ኀጣውኢነ ................ተነሺ

በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል .mp33.94 KB

#አቡነ_ዘበሰማያት #አቡነ ....................ተነሺ #ዘበሰማያት .............ተጣይ ይትቀደስ.................. ሰያፍ ተነሺ ስምከ .....................ተነሺ ትምጻእ .................. ሰያፍ ተነሺ መንግሥትከ ................ተነሺ ወይኩን ..................ሰያፍ ተነሺ ፈቃድከ .................... ተነሺ በከመ በሰማይ ................ ተናባቢ ተጣይ ከማሁ ................ወዳቂ በምድር ....................ተጣይ ሲሳየ #ነ .................... ተነሺ ዘለለዕለት#ነ ................... ተነሺ ሀበነ ........................ ተነሺ ዮም ............................ተጣይ ኅድግ .................... ስያፍተነሺ ለ#ነ ..................... ተነሺ አበሳ#ነ ...................ተነሺ ወጌጋየነ ..................... ተነሺ ከመ ንሕነኒ .................ተናባ .ተነ ወዳ ንኅድግ ..................... ሰያፍ ተነሺ ለዘአበሰ ......................ተነሺ ለ#ነ .....................ተነሺ ኢታብአነ .................. ተነሺ እግዚኦ ................... ወዳቂ ውስተ መንሱት ............ተናባ.ተጣይ አላ ....................ወዳቂ አድኅነነ ...............ተነሺ ወባልሐ................ ነተነሺ እምኲሉ................ ወዳቂ እኲይ ...................ተጣይ እስመ ዚአከ ...............ተናባ.ተነሺ ይእቲ ...................ተነሺ መንግሥት ............. ተጣይ ኅይል ....................ተጣይ ወስብሐት................ ተጣይ ለዓለመ ዓለም ............. ተናባ.ተጣይ