uk
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Відкрити в Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Показати більше
4 374
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
አቡነ ዘበሰማያት.mp34.97 KB

#ነአኩ_ተከ #ነአ ኩ #ተከ.....................ተነሺ #እግዚኦ ................. ወዳቂ ወንሴብሐከ ................ተነሺ ንባርከከ ... ................. ተነሺ እግዚኦ ....................ወዳቂ ወንትአመነከ ...................ተነሺ ንገኒ ........................ተነሺ ለከ ... .................. ተነሺ እግዚኦ ....................ወዳቂ ወንትቀነኝ................ ሰያፍ.ተነሺ ለስምከ ................. ተነሺ ቅዱስ ....................ተጣይ ንሰግድ ..................ሰያፍ ተነሺ ለ#ከ ...................ተነሺ ኦ ............................ ወዳቂ ዘለ#ከ .. .......................ተነሺ ይሰግድ .........................ሰያፍ ተነሺ ኩሉ..................................ወዳቂ ብርክ ...............................ተጣይ ወለ#ከ.............................ተነሺ ይትቀነይ .........................ሰያፍ ተነሺ ኩሉ....... ..........................ወዳቂ ልሳን................................ተጣይ አንተ................................ተነሺ ውእቱ .............................ተነሺ አምላከ አማልእክት ................ተናባ.ተጣይ ወእግዚአ አጋዕዝ ..................ተናባ.ተጣይ ወንጉሠ ነገሥት ....................ተናባ.ተጣ አምላክ ...........................ተጣይ አንተ .................................ተነሺ ለኵሉ................................ ወዳቂ ዘሥጋ ................................ወዳቂ ወለኵላ............................... ወዳቂ ዘ ነፍስ ................................ተጣይ ወንጼውዐከ ..........................ተነሺ በከመ መሐረነ .......................ተናባ.ተነሺ ቅዱስ ወልድከ............. ተነሺ እንዘይብል..............ተናባ.ተጣይ አንትሙሰ..................ተነሺወዳቂ ሶበትጼልዮ................ተናባ.ተነሺ ከመዝ ........................ወዳቂ በሉ ......................... ተነሺ

#ነአኩ ተከ #፩ ደቂቃ ከ፰ ሰከንደ ብቻ #የቦታ መጠን ፭ ፫ ፱ .፪ ኪሎ ባይት ብቻ #ለመስማት 0.35ሳንቲም ብቻ

#አአ ት #ብ .......... .ሰያፍ ተነሺ ገጽየ .............. .ተነሺ ወኩለንታየ ............... ተነሺ በትእ#ምርተ መስቀል............ ተናባ.ተነሽ #በስመ #አብ...................ተነባ.ተነሺ #ወወልድ ...................ተጣይ #ወመንፈስ #ቅዱስ .................ተጣይ አሐዱ ................ ወዳቂ አምላክ ................ ተጣይ በቅድስት .................ተጣይ #ሥ ላ #ሴ ...............ወዳቂ እንዘ አአምን............... ተና.ሰያ.ተነሺ ወእትመሐፀን ...............ሰያፍ ተነሽ እክደከ ....................... ተነሽ ሰይጣን .....................ተጣይ በቅድመ ዛቲ ..................ተናባ.ወዳቂ እምየ ................... ተነሽ ቅድስት ...................ተጣይ ቤተ ክርስቲያን .................ተናባ .ተጣይ እንተይ ይእቲ ...................ተናባ. ተነሽ ስምዕየ ................. .ተነሽ #ማርያም .....................ተጣይ ጽዮን ..................... ሰያፍ .ተነሽ ለዓለመ ዓለም .............. ተናባ.ተጣይ

🕊✞ #ማርያም_አርጋለች ✞🕊 ✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞ ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪) የሰማይ መላእክት እያረጋጒዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች #አዝ = = = = = = = ✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞ የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = = = = = ✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞ ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = = = = = ✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞ የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = = = = = ✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞ ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ አርጋለች ማርያም ተነስታለች #አዝ = = = = = = = ✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞🕊✞

ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ይታሰብባቸው ከነበሩ ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣ ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን፣ ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ኮትዲቭዋር፣ ማዳጋስካር እና ሌሎች በርካቶች የዓለም ሀገራት ይገኛሉ (Columbus World Travel Guide, 25th Edition, The Assumption of the Blessed Virgin Mary into Heaven, From Wikipedia, the free encyclopedia) ተመልከቱ፡፡ ★ ምንጭ፡- ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ፤ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተጻፈ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል አንድ መጽሐፍ፤ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተጻፈ መልክአ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተጻፈ፡፡ የእመቤታችን በረከት በዝቶ ተትረፍርፎ ይደርብን፡፡አሜን✞✞✞ ✍ @EOTC2921 ✍

በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡ ❖ በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 “ወአዘዞሙ እግዚእነ ለሰብአቱ ሊቃነ መላእክት ከመ ይጸውዕዋ ለምድር” (ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው) እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት” (ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ ያን ጊዜ በልጇ ሥልጣን የቅድስት ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ ነሐሴ 16 ዕለትም ከሞት ተነሣች፡፡ ❖ ያን ጊዜ “ወረዱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት” ይላል ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ” (ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች) እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው፡፡ ❖ ስለ አካላዊ ዕርገቷ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው በቊ ፹፪ ላይ፡- “አመ ነሥኡኪ እምኤዶም አዕላፈ ማሕሌት ጾታ (በበጾታ) እንዘ ይጼልሉኪ ድንግል በአክናፈ መባርቅት ከመ ወልታ ሰራዊተ ሰማይ ይቤሉ ለክብረ ፍልሰትኪ ግርማ ትርሲታ መኑ ይእቲ ዛቲ ዘገዳመ ጽጌ ዕጥነታ ወከመ ሠርጸ ጢስ ዘስኂን ይምዕዝ ዕጥነታ” (ድንግል ወገኖች አመስጋኞች መላእክት በየነገድ በየነገድ ኾነው በመባርቅት ክንፎች እንደ ጋሻ ጋርደው ከኤዶም ገነት በተቀበሉሽ ጊዜ የሚያስደንቅ ክብር ለተገለጸባት ለዕርገትሽ የሰማይ ሰራዊት አበባ ካለበት በረሓ የምትወጣ መዐዛዋም ከነጭ ዕጣን ይልቅ የሚሸትት አወጣጧም እንደ ጢስ አወጣጥ የኾነችይኽቺ ማናት? ይኽቺ ማን ናት ይላሉ (መሓ ፫፥፲፮)) በማለት በአስደናቂ መልኩ ዕርገቷን ገልጸዋል፡፡ ❖ ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ “ፈለሰት ማርያም በስብሐት ውስተ ሰማያት መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወረዱ ለተቀብሎታ” (እመቤታችን በምስጋና ወደዚያኛው ዓለም በተለየች ጊዜ ለአቀባበሏ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ወረዱ) ይለዋል፡፡ ❖ ያን ጊዜ በታላቅ ክብር በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡ ❖ ርሱም “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር” ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ይላል ተበጻብጾ ሊወድቅ ወደደ፤ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም አኹንም እመቤታችን ተነሣች ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለበረከት ሰበኗን ሰጠችው፡፡ ርሱም በደስታ ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤ እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ “ወነሥአ መክርየ” ይላል መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር ዠመር፤ ርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ በመስቀል ሥር የሰበኗ ምሳሌ የሚኾን ሰፊ ጨርቅ ታደርጋለች፡፡ ❖ ባመቱ ቶማስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሐዋርያት ሱባኤ ሲገቡ ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡ ❖ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ወደ ምጡቅ ሰማይ ስለተደረገው ዕርገቷ ፡- “እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ” (ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ) በማለት አስተምረዋል፡፡ ❖ በተመሳሳይ መልኩ ዳግመኛ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው በቊ፹፬ ላይ፡- “ትእምርተ ፍልሰትኪ እምድረ ጽጌ ድንግል በክልኤ በደመና ሰማይ አርአየ ዘሐዋርያት ጉባኤ ወእለ ሞቱ አንቅሐ እምከርሠ መቃብር ቀርነ ጽዋዔ ለነሰ እንዘ ይብሉ ሶበ ሰማዕነ ውዋዔ መሰለነ ዘበጽሐ ትንሣኤ” (በኹለት ወገን ድንግል የኾንሽ ማርያም ሆይ አበባ ካለበት ምድር ወደ ሰማይ የማረግሽ ተአምር በሰማይ ደመና የሐዋርያት ጉባኤን አሳየ፤ የሞቱትንም ከመቃብር ውስጥ በተአምር ነጋሪት ድምፅ አስነሣ፤ ለእኛስ የምስጋና ከፍተኛ ድምፅን በሰማን ጊዜ የሙታን መነሣት የደረሰ መሰለን እስኪሉ ድረስ) በማለት ሐዋርያትን ተሰብስበው ሳሉ ዕርገቷን እንዲያዩ እንዳደረጋቸው ጽፈዋል፡፡ ❖ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ስትኾን ክብር ይግባውና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች። ❖ ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡ ❖ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የ

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ነሐሴ 16 ✍ @EOTC2921 ✍ ነሐሴ 16 ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፤ የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡ ❖ በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ 72ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ 1፥14)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡ ከዚያም 64 ዓመት ሲመላት ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደ ጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፡፡ ❖ ጌታም እናቱን “እኔ ኹሉን መጋቢ የኾንኹትን ያጠቡ ጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይ ያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡ የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ” አላት፡፡ ❖ ይኽነንም ልጇ እያላት ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፡፡ ❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ይኽነን ይዞ በድጓው ላይ “ፃኢ እምሊባኖስ ሥነ ሕይወት ርቱዕ አፍቅሮትኪ ቡርክት አንቲ እምአንስት ማኅደረ መለኮት ሰላም ለኪ፤ ማርያም እመ አምላክ ወልድኪ ይጼውዐኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር” (የሕይወት ደም ግባት የአምላክ እናት ከሊባኖስ ውጪ፤ ፍቅርሽ የቀና ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ፤ የመለኮት ማደሪያ ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ የአምላክ እናት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወደ ዘላለማዊ ሕይወትና ወደ ክብር መንግሥት ይጠራሻል) በማለት አመስጥሮታል፡፡ ❖ ቅዱሳን ሐዋርያትም ሥጋዋን በክብር ገነዘዋል፤ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡- ╬ “ሐዋርያት አመድበሉ ሥጋ ድንግል ጠብለሉ በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ ልብሳ ተካፈሉ” (ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ) ╬ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት ወቀበርዋ ውስተ ገነት” (ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት) ╬ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ ገነዙ በክብር ወበስባሔ ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ” (ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ) ╬ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ ዳዊት ዘመራ በመሓልይ” (በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት፡፡) ╬“ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ በደመና ብርሃን ጸዐዳ ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ” (ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት) ╬ “ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት ብፁዓን ሐዋርያት ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ” (ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡ ❖ ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣ ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት እናቃጥላለን ብለው በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡ ❖ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡ ❖ ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን

☞❀በ69 ዓ.ም. ያረፈው ከ72ቱ አርድዕት የኾነው የአንጾኪያ የመጀመሪያው ጳጳስ ቅዱስ ኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር ፳፩ የኾነ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና በነሐሴ ፲፮ የተከናወነ በዓለ ዕርገቷን በዐይኖቹ የተመለከተውን “ድርሳን ዘደረሰ አባ ኢቮዲየስ ሊቀ ጳጳሳት ዘአንጾኪያ በእንተ ዕረፍታ ወፍልሰታ ለማርያም” (Evodius of Rome, Homily on the Dormition The falling asleep of Mary) በሚል ርዕስ ሲጽፍ የዚኽ መጽሐፍ ቅጂ በታችኛው ግብጽ ይነገር በነበረው በቦሃይሪክ ቅጅ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጻፈው ተገኝቷል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፍ ላይ ያንብቡ፨ ☞❀ቅዱስ ሚሊቶ በምዕራብ አናቶሊያ በሲሚርና አጠገብ በሳርዴስ ጳጳስ የነበረ ሲኾን በግሪክ (Μελίτων Σάρδεων Melíton Sárdeon) ሲባል ዕረፍቱም በ፻፹ (180) ዓ.ም ነው፤ ሊቁ ጀሮም የብሉይ ኪዳን ቀኖናን ሚሊቶ ሠርቶ እንደነበር መስክሮለታል፡፡ የጻፋቸውም መጻሕፍት ዝርዝር አውሳብዮስና ጀሮም ጽፈውት እናገኛለን፡፡ ብዙ መጻሕፍት ሲኖሩት በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ኅልፈተ ሕይወትና አካላዊ ዕርገት አስመልክቶ "የሳርዲሱ ቅዱስ ሚሊቶ የቡርክት ማርያም ኅልፈተ ሕይወት ትምህርት" The Passing of Blessed Mary) በሚል ርዕስ ርሱም እንደ ሐዋርያትና ሰባ አርድእት ጽፏል፡፡ ይኽም መጽሐፍ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ወደ ዐማርኛ ቋንቋ በነገረ ማርያም በሊቃውንት ተተርጉሟል። ☞❀በ380 ዓ.ም በኢየሩሳሌም ጳጳስ የነበረው ጢሞቴዎስ (Timothy of Jerusalem) ሲገልጽ “Wherefore the Virgin is immortal…” (ድንግል እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው) በማለት ሞት በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሳረጋት መኾኑን መስክሯል፡፡ ☞❀በተጨማሪም ከ70 ዓ.ም. ጀምሮ ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ በነበረው ስደት በክርስቲያኖች ዘንድ ዐፅመ ቅዱሳን ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ሲኾን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ እንደሚያስረዱን በዚያ የስደት ዘመን ክርስቲያኖች በድፍረትና ሐላፊነትን ተሸክመው በቈራጥነት የሰማዕታትን ሰውነት ከመግደያው ስፍራ በመውሰድ ዐፅማቸውን በክብር ይጠብቁ የነበረ ሲኾን ይኽነንም አጥብቀው በመጠበቃቸውና ለትውልድ በማስተላለፋቸው የከበረ ዐፅማቸው ባረፈበት ቦታ ላይ ዛሬ አብያተ ክርስቲያን ታንጸውበት እጅግ በርካቶች ጐብኚዎች እየጐበኙት ሲገኙ ለምሳሌ ያኽል የነቅዱስ ጴጥሮስ፣ የነቅዱስ ጳውሎስ፣ የነቅዱስ ቶማስ፣ የነያዕቆብ ወ.ዘ.ተ የከበረ ዐፅማቸው ስፍር ቊጥር በሌላቸው ሰዎች ከጥንት ዠምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲጐበኝና ሲታይ የቅድስት ድንግል ማርያምን አንድ የራሷን ጠጒርና የእጇን ጥፍር አገኘኊ የምትል ምንም ሀገርና ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ፈጽማ የለችም ምክንያቱም አምላካችን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ያደረባት የአምላክ ታቦት ክቡር ዳዊት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” ብሎ ትንቢት እንደተናገረላት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በዕረፍቱ ስፍራ አለችና ነው፡፡ ☞❀ይኸውም ሊታወቅ የዓለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን በ400 ዓ.ም አካባቢ ነግሦ የነበረው ንጉሡ ማርሲያን የኢየሩሳሌሙን ፓትሪያርክ የቅድስት ድንግል ማርያም ዐፅም ካለ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲያመጣለት ቢጠይቀው ርሱ ግን እመቤታችን እንዳረገችና ምንም ዐይነት የርሷ ቅሪት እንደሌለ አስረድቶ ስለ ዕርገቷ ጽፎለታል። ☞❀የሚገርመው ቅሪቶች ከፍተኛ ዋጋ ስላላቸው ብዙ ሰዎች ወደ ከተማቸው ጐብኚዎችን ለመሳብ ሲሉ አስመስለው ለመሥራት በመሞከራቸው ብዙዎች ተከሰው የነበረ ሲኾን ለምሳሌ አክሊለ ሦኩን መስቀሉን አስመስለው ለመሥራት ከበፊት ዠምሮ ቢሞክሩም ኾኖም ግን የቅድስት ድንግል ማርያም አካል አለን የሚልና የሚሞክር ከጥንት ዠምሮ እስከ ዛሬ በዓለም ላይ ለምን ጠፋ? ቢባል ማንም ሰው ይኽነን ሐሰት ስለማያምንና ከሐዋርያት ጊዜ ዠምሮ እስከ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እስከ አኹንም ድረስ የቅድስት ድንግል ማርያም አካል ፈጽሞ በምድር ላይ እንደሌለና ወደ ሰማይ በአካል እንዳረገች ስለሚታወቅ ነው፡፡ ☞❀በተጨማሪም ከመዠመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን-16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስም የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በቤተ ክርስቲያን፣ በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ኹሉ ሙሉ በሙሉ የታወቀ በመኾኑ በዕርገቷ ዙሪያ ምንም ዐይነት የጥርጥር ጥያቄን ያቀረበ ማንም የለም፡፡ ☞❀ዛሬ በጭፍኑ አንዳንዶች ከዕውቀት የራቁ መናፍቃን የካዱትን ይኽነን እውነታ የእምነቶቻቸው መሥራቾች እንኳን ደፍረው አልተናገሩትም ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሪፎርመር የኾነው ሄንሪች ቡሊነግር በ፲፭፻፴፱ (1539 ዓ.ም) ላይ ጣዖታትን ተቃውሞ በጻፈው መጽሐፉ ላይ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስለማረጓ ሲገልጽ፦ "Elijah was transported body and soul in a chariot of fire; ...he was not buried in any Church bearing his name,…It is for this reason, we believe, that the pure and immaculate embodiment of the Mother of God, the Virgin Mary, the Temple of the Holy Spirit, that is to say her saintly body, was carried up to heaven by the angel." (ኤልያስ በሥጋና በነፍስ ሳለ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ወጣ፤ በርሱ ስም በተሠየሙ ባንዳቸውም ቤተ ክርስቲያን አልተቀበረም፤ ይኽም ዘላለማዊነት እግዚአብሔር ለሚያምኑበት ለነቢያቱ ድንቅና ለማይነጻጸሩ ፍጡራኑ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀ ያሳውቀናል … በዚኽ ምክንያት የአምላክ እናት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ፣ አካሏ ንጹሕና ኀጢአት አልባ የኾነው የድንግል ማርያም ንጹሕ የተቀደሰ ሰውነቷ በመላእክት ታጅቦ ወደ ሰማይ እንዳረገ እናምናለን) በማለት ጽፏል (Heinrich Bullinger, cited in Thurian, page 89, 197, 198) ☞❀ዛሬ ደግሞ ጥቂቶች ይኽነን እውነት መቃወማቸው የእምነት መሪዎቻቸው እንኳን ያስተማሩትን ትምህርትና የጻፏቸውን መጻሕፍት እንዳላነበቡ ያጋልጥባቸዋል፡፡ ☞❀ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ከሚታሰብባቸው ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣ ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን፣ ካሜሩን፣ ጋቦን፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ኮትዲቭዋር፣ ማዳጋስካር እና ሌሎች በርካቶች የዓለም ሀገራት ይገኛሉ (Columbus World Travel Guide, 25th Edition) 🙏እመቤታችን ሆይ ከልጅሽ መንግሥት ለይቶ ሳጥናኤል ከሰራዊቱ ጋር ወደ ሚገባበት ዘላለማዊ እሳት ውስጥ ከሚያስጥል የሃይማኖት ክሕደት እኛ ልጆችሽን በምልጃሽ ጠብቂ አሜን🙏 [ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]

#የቅድስት_ድንግል_ማርያምን_እውነተኛ_ዕርገት_ክደው_ለሚያስክዱ_በዘመናችን_ለተነሡ_ሐሰተኞች_የተሰጠ_ምላሽ ☞❀ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ሥር በአደራ የተቀበለ ፲፭ ዓመት ከርሷ ጋር የኖረ በ፷፬ ዓመቷ የኾነ ዕረፍቷን፣ ፍልሰቷን፣ ትንሣኤዋን፣ ዕርገቷን በዐይኑ ያየው ቅዱስ ዮሐንስ አምላክን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ለመሸከም የበቃች የአምላክ ታቦት ካረገች በኋላም በሰማያት ያላትን ታላቅና ፍጹም ክብር በራእ ፲፩፥፲፱ ላይ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ከተናገረ በኋላ በተከታይነት አሕዛብንም ኹሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ የወለደች ርሷ በሰማይ ፀሓይን ተጐናጽፋ፣ ጨረቃን ተጫምታ፣ ከዋክብትን ደፍታ እንዳያት ጽፏል፡፡ ☞❀ዮሐንስ የአምላክ ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያምን በዕርገቷ በሰማያት ያላትን ክብር በዐይኑ ዐይቶ “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ” በማለት ሲጽፍልን፤ ሀብተ ትንቢት የተሰጠው ዳዊት ደግሞ አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት በመዝ ፻፴፩፥፰ ላይ “አቤቱ ወደ ዕረፍትኽ ተነሥ አንተና የመቅደስኽ ታቦት” በማለት ክብር ይግባውና ልጇ በሥልጣኑ አስቀድሞ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ለዐይን ቅጽበት እንኳን ወዳልተለየው ወደ ጌትነቱ ዙፋን ወደ ሰማይ እንዳረገ ኹሉ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችው ታቦቱ ቅድስት ድንግልም በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ እንደምታርግ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ ☞❀በዚኽ አማናዊ ምስክርነት በሰማይ ዮሐንስ ያያት ታቦት በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ያረገችው የአምላክ ታቦት ንግሥተ ሰማያት ወምድር ቅድስት ድንግል ናትና ኢትዮጵያዊዉ ቄርሎስ ዐምደ ሃይማኖት የተባለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በኆኅተ ብርሃን መጽሐፉ ላይ “ወታቦተ ራእየ ምስጢረ ኅቡአቲሁ ለዮሐንስ አቡቀለምሲስ ረኣዬ ኅቡአት” (የተሰወረ ነገርን የሚያይ የራእይ አባት የዮሐንስ የምስጢራቱ ምስጢር ራእይ ታቦት አንቺ ነሽ) በማለት በትክክል ገልጾታል፡፡ ☞❀ጌታችን እንኳን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመችውን በዠርባዋ ያዘለችውን በክንዶቿ የታቀፈችውን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የኾነው ታቦቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን ትቅርና ያገለገሉት ወዳጆቹን እንኳን ሞትን ሳያዩ ወደ ሰማይ እንደወሰዳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብብ፤ ለምሳሌ ሔኖክ ሞትን ሳያይ በሕይወቱ ሳለ እግዚአብሔር እንደወሰደው በዘፍ ፭፥፳፬ እና በዕብ ፲፩፥፭ ላይ ተጠቅሷል። ☞❀ነቢዩ ኤልያስም ሞትን ሳያይ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማይ እንደወጣ (፪ነገ ፪፥፲፩‐፲፪) ተጽፎልናል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከእግረ መስቀሉ ሥር በጌታ ሥልጣን ስለተነሡ ቅዱሳን ማቴዎስ ሲጽፍ “መቃብሮችም ተከፈቱ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” ይለናል (ማቴ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡ ☞❀ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና እንደምናገኘው በመቃብር ውስጥ መፍረስ መበስበስ የኀጢአት ውጤት ሲኾን ትእዛዝን የጣሰውን አዳምን “ዐፈር ነኽና ወደ ዐፈርም ትመለሳለኽና” በማለት ተረግሞ ነበር (ዘፍ ፫፥፲፱)፤ በዚኽም ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሥጋዊ ደማዊ የኾነው ኹሉ ወደ መቃብር ሲወድቅ፤ ርሷ ግን ከእናቷ ማሕፀን ዠምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፣ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ናትና በመቃብር ፈርሶ መቅረት አይስማማትም። ☞❀አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽነን ንጹሕ ሥጋዋንና ነፍሷን በመንሣት በተዋሐደው ሥጋ በመስቀል ተሰቅሎ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነሥቷልና እናቱም በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ዐርጋለች፤ ርሱን በመፅነስና በመውለድ ዕድፍ ጉድፍ ያላገኘው ያልተለወጠ ድንግልናዋ፤ የተሸከመው ማሕፀኗ፤ የታቀፉት ክንዶቿና፣ የዳሰሱት እጆቿ፤ የሳሙት ከንፈሮቿ ያሳደጉት ጡቶቿ፤ ከርሱ ጋር የተመላለሱ እግሮቿና፤ ያዘለው ጀርባዋ፤ ብሩሃት የሚኾኑ ዐይኖቿ በጎ መዐዛ ያላቸው አፍንጮቿ፤ ጸዐዶች የሚኾኑ ጥርሶቿ፤ በመልአኩ በገብርኤል ቃል ብሥራትን የሰሙ ዦሮቿ ፈጽመው በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት የለባቸውም፤ ከርሷ ሥሮችንና ጸጒርን፣ ደምንና ዐፅምን ነፍስንና ሥጋን ነሥቶ አባቶቻችን እንደ አስተማሩን ፈጽሞ ያለመለየትና ያለመለወጥ ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡ ☞❀የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አካላዊ ዕርገት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የነበረ አስተምህሮ ሲኾን ይኽን ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፈው በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ነው ብሎ መጻፍ የመጨረሻው የአለማወቅ ጥግ ነው ቢባል አያስከፋም፨ ☞❀ዮሐንስም የዕረፍቷንና የዕርገቷን ነገር በዐይኑ በማየቱ ስለአምላክ እናት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት የነባቤ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምስክርነት (The Account of St. John the Theologian of the Dormition of the Holy Mother of God) በሚል ርዕስ የጻፈው ሲኾን፤ ይኽም ጽሑፉ በእኛ በብራና በሚገኘው በነገረ ማርያም መጽሐፍ ላይና በመጽሐፈ ፍልሰታ ላይ በቀደምት መተርጒማኖቻችን የተተረጐመልን በመኾኑ ይኽነን የተቀደሰ ታሪክ ቀደምት የኾነችው ቤተ ክርስቲያናችን አስቀድማ አግኝታዋች፤ ይኽ በግሪክ ቋንቋ ተጽፎ የሚገኘው የዮሐንስ ምስክርነት አስቀድሞ በሱርስትና በዐረብኛ ቋንቋ የተተረጐመ ሲኾን በኋላም ወደ ተለያዩ የዓለም ቀደምት ቋንቋዎች ጽሑፉ ተተርጒሟል፤ በዚኹ ምዕራፍ በክፍል ኹለት ላይ ከጽርዕ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ተጽፎ ያለውን ሙሉውን ምስክርነት ነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ ተርጉሜዋለኹና ያንብቡ። ☞❀የአርማትያሱ ዮሴፍም ከጌታ ዕርገት በኋላ ከሐዋርያት ጋር ያልተለየና ዐብሯቸው የነበረ በመኾኑ የቅድስት ድንግል ማርያምና ዕረፍትና ዕርገት በዐይኖቹ በማየቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገትን ርሱም እንደ ዮሐንስ “ዮሴፍ ዘአርማትያስ የጻፈው የቡርክት ድንግል ማርያም ኅልፈት” (Joseph of Arimathea, The Passing of the Blessed Virgin Mary) በሚል ርዕስ ከእመቤታችን ዕርገት በኋላ የጻፈላት ሲኾን ይኽም አስቀድሞ በላቲንና በሱርስት ቋንቋዎች ተተርጒሞ ይገኛል፤ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጐመውና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሥራ (Ante-Nicean Fathers, Vol. 8.) በሙሉ በያዘው በክፍል ስምንት ላይ ያለውን የአርማትያሱ ዮሴፍን ሙሉውን ምስክርነት በነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ ላይ በአማርኛ ቋንቋ አስፍሬዋለኊ፡፡

ዝማሬ ዳዊት - ቡሄ በሉ id29416 16k.m4a7.32 KB

  🍀🍀🍀 #ቡሄ_በሉ 🍀🍀🍀 ቡሄ በሉ (2) ሆ ልጆች ሁሉ ሆ የኛማ ጌታ ሆ    የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባ ረቀው ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን (2) ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ       #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና (2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ       #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) በተዋህዶ ልጆች ሆ ወልድ የከበረው ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደ ማርያም ነው ሆ ቡሄ በሉ (2) የአዳም ልጆች ሆ ብረሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ #ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን ለኛ_መጣልን(2) አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ አጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ አክስቴም አለኝ ለከት ሆ ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ   #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2) ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ  ያላችሁ ሆ ባህላችሁን ሆ ያዙ ሆ አጥብቃችሁ ሆ ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ    #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)   አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ #ድምጽህን_ሰማና በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)     ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)  ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችን ይድረስ ሆ #ድምጽህን_ሰማና #በብህሩ_ደመና(2) #የቡሄው_ብርሃን #ለኛ_መጣልን(2)   ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና #በጋሽዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት  ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና #በእማምዬ_ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና       #እንዲሁ_እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ #ለዓመቱ_በሰላም በፍቅርያ ድርሳችሁ #ክርስቶስ_በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ #የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ #እንዲሁ_እንዳለን በፍቅር አይለየን #ለዓመቱ_በሰላም በፍቅር ያድርሰን #አማኑኤል_በቀኙ በፍቅር ያቁመን  #የመንግስቱ_ወራሽ በፍቅር ያድርገን የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት #በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት #በሁሉም_ቤት (2) ይግባ በረከት እንቁም በሃይማኖት ፀንተንበትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት #ባህላችንን_የአባቶች_ትውፊት (3) 🙏

ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን #ለደብረ_ታቦር በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን፡፡ እነሆ በዓሉን የሚመለከት ድንቅ ዝማሬ ቀርቦላችኃል፦ •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ☞ @EOTC2921 Channel ☞ @Ethio_Orthodox1 Group

🍀 #ደብረ_ታቦር_የታሪክ_ተራራ 🍀 ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ☞🕊 ደብረ ታቦር ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁለቱ ነቢያትና ለሶስቱ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ታሪካዊ ተራራ ነው። ጌታችንን መለኮታዊ ታሪክ የሰራባቸው ብዙ ታሪካዊ ተራራዎች አሉ። እነርሱም፦ #ደብረ_ሲና፦ ምሥጢረ ሥጋዌን የገለጠበት የምሥጢር ተራራ ነው #ደብረ_ቁስቋም፦ በስደቱ ጊዜ መላእክቱ ክንፋቸውን ዘርግተው ያመሰገኑበት የምስጋና ተራራ ነው። #ደብረ_ገዳመ_ቆሮንቶስ፦ ሶስቱ ፈተናዎችን እስከፈታኙ ድል ነስቶ አምላክነቱን የገለጠበት የድል ተራራ ነው። #ደብረ_ዘይት፦ ለሐዋርያቱ ወደሰማይ ሲያርግ ባርኳቸው ያረገበት የወይራ ተራራ ነው። #ደብረ_ታቦር፦ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት የለመለመ ተራራ ነው። ወደዚህ ተራራ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን ከሐዋርያት ዮሐንስን ያእቆብን እና ጴጥሮስን ይዞቸው ወጥቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦላቸዋል። ☞🕊ለምን_ከነቢያት_ሙሴና_ኤልያስን_መረጠ_ቢሉ? ነቢዩ ሙሴ በደብረ ሲና መልክህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ጠይቆት ነበረና ዛሬ መልኬን አታይም በሇላ ጀርባየን ታያለህ ብሎት ነበረና ጥያቄውን ለመመለስ ነው፤ በተራራ የተጠየቀውን በተራራ ለመመለስ ወደተራራው ወስዶታል። ኤልያስም ተአምር አድራጊ ነቢይ ስለሆነ ጌታችን ታምራቱን አይተው ኤልያስ ነው ብለውት ነበርና ኤልያስ እንዳልሆነ እና የኤልያስ አምላክ መሆንን ለማስመስከር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን አመጣ። ከሐዋርያት ዮሐንስ ያእቆብ ጴጥሮስ ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ? ጌታችን ወደተራራው ወጥቼ እነግሣለው ባለ ጊዜ የዮሐንስና የያእቆብ እናት ማርያም ልጆቼን በቀኝና በግራ አንግሥልኝ ብለው ነበረና የጠየቀችውን ጥያቄ ለመመለስ ያእቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወጥቷል ጴጥሮስን፤ ☞🕊ለምን_ይዞ_ወጣ_ቢሉ? ጌታችን ሰዎች ማን ይሉኛል ባለ ጊዜ? ጴጥሮስ አንተ የአብ የባህርይ ልጁ ኢየሱስ ነህ ብሎት ነበረና ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ አምላክነቱን ሊያስረደው ወደተራራው ወስዶታል። ☞🕊ሌሎችን_ሐዋርያት_ለምን_ተዋቸው_ቢሉ? "የሐትትዎ ለኀጥእ ከመ ኢይርዓይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል ኀጢአተኛውን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዳያይ ይከለክሉታል የተባለው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ይሁዳ ብረሃነ መለኮቱን እንዳያይ ነው። በሱ ምክንያት ስምንቱም በእግረ ደብር ቀርተዋል ለሶስቱ ሐዋርያት የተገለጠው ምሥጢር ለስምንቱ ሐዋርያት ተገልጦላቸዋል ። ይሁዳን ትቶ ሁሉን ይዞ እንዳይወጣ ከምሥጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት እንዳይል ነው። ከነቢያት ካገቡትም ካላገቡትም ከሐዋርያትም ካገቡትም ካላገቡትም ይዞ ወጥቷል። ☞🕊ከነቢያት ያገባው ሙሴ፤ ያላገባው ኤልያስ ነው። ከሐዋርያት ያገባው ጴጥሮስ ያላገቡት ያእቆብና ዮሐንስ ናቸው። የደናግል የሕጋዉያንም አምላክ እንደሆነ ለመግለፅ ህጋውያንን ደናግላንን ይዞ ወጥቷል፡፡ አንድም ደብረ ታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት መንግስተ ሰማያት የህጋውያንም የደናግልም እንደሆነች ለመግለጽ። ☞🕊አምስት መሆናቸው ስለምን ነው ቢሉ? ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት በቤተ ክርስቲያን የሚቀድሱ ካህናት አምስት እንዲሆኑ ስርዓት ለመስራት ነው አንድም በአምስቱ አእማደ ምሥጢር ምሳሌ ነው። ከሞቱት አንስቶ ካሉት ጠርቶ ለህያዋንም ለሙታንም ብርሃነ መለኮቱን የገለፀው የሙታንም የህያዋንም አምላክ መሆኑን ለመግለፅ ነው። ደብረ ታቦር ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን በዓላት አንዱ ነው፤ ይህ በአል መለኮታዊ አምላካዊ ላእላዊ ሰማያዊ በአል ነው። ☞🕊ደብረ ታቦር በእስራኤል ውስጥ የሚገኝ የለመለመ ተራራ ሲሆን በአሉ በተራረው ተሰይሞ ይከበራል። ከሌሎቹ ነቢያት ሙሴና ኤልያስን መርጦ ገልጦላቸዋል ምክንያቱም ሙሴ ፊትህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ሲጠይቀዉ "ገፅየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድህረሰ ትሬኢ ገፅየ" ዛሬ ፊቴን አታይም ኋላ ታያለህ ብሎት ነበርና ቃሉን ለመፈፀም ከመቃብር አምጥቶ ደብረ ታቦር ላይ ገለጠለት። ✔ሙሴ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢባል? በልጅነቱ ሙሴ በቤተ ፈርዖን ሲያድግ የፈርኦንን ግፍ አይቶ ንጉሡ ፈርዖንን በጥፊ ተማቶ የሞት ፍርድ ቢፈርድበት የንጉሡ አማካሪዎቹ ልጅ ነው ምን ያውቃል ብለው እሳት እና ፍትፍት ይቅረብለት እና እሳቱን ትቶ ፍትፍቱን ከበላ ይገደል ክፉና በጎን ያውቃል ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን ከጎረሰ ገና ስላላወቀ አይፈረድበት ብለው ፍትፍትና እሳት አቀረቡለት ፈትፍቱን ትቶ እሳቱን ጎርሶ ነበርና አፉ ተብታባ ነበር በዚህ ታውቋል አንድም ሙሴ ገና ሲወለድ ከፊቱ ላይ ብርሃን ተስሎበት ተወልዶ ነበርና በዚህ ታውቋል። ✔ኤልያስ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ? በጠጉሩ ኤልያስን ዘፀጓር ብእሲሁ ይለዋልና አንድም ኤልያስ ሲወለድ በእሳት ሰፋድል ተጠቅልሎ ነበር በዚህ ታውቃል ኤልያስን የመረጠበት ምክንያት ኤልያስ ሲያርግ ከኤልሳዕ በቀር ያየው አልነበረመና በህይወት ማረጉን ለመግለፅ ነው፡፡ ማቴ፡17፥1 ከመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ 🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን 🙏

ፍልሰታ.pdf2.56 KB

🌿🌾 #ይቺን_ዓመት_ተወኝ!🌾🌿 ✔ከዓመት እስከ ዓመት፦ ፍሬን ሳላፈራ፥ ደረቅ እንደሆንኩኝ፤ ✔በራድ ወይም ትኩስ፦ ሁለቱንም ሳልሆን፥ እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ፤ ✔አለሁኝ በቤትህ፦ ለሙ መሬትህን፥ እያጎሳቆልኩኝ፤ ✔አውቃለሁ አምላኬ፦ ፍሬዬን ለመልቀም፥ እንዳመላለስኩህ፤ ✔ዛሬም ሳላፈራ፦ እሾህን አብቅዬ፥ ደርቄ ጠበቅሁህ፤ ✔ያልተደረገልኝ፦ ያላፈሰሰክብኝ፥ ያልሰጠኸኝ የለም፤ ✔ነገር ግን ይህ ሁሉ፦ አላርምህ አለኝ፥ አልለየኝም ከዓለም፤ ✔የማትሰለቸኝ ሆይ፦ ተነሥቼ እስክቆም፥ እባክህ ታገሠኝ፤ ✔የእኔን ክፋት ተወው፦ መልአክህን ሰምተህ፥ ይህችን ዓመት ተወኝ፤ ✔አውቃለሁ ታውቃለህ፦ ቀጠሮን ሰጥቼ፥ እንደማላከብር፤ ✔ብዙ ጊዜ አቅጄ፦ ብዙ ጊዜ ዝቼ፥ በወሬ እንደምቀር፤ ✔ዘንድሮስ…! እንዳልኩኝ፦ አምና ይሄን ጊዜ፥ ሰምተኸኝ ነበረ፤ ✔ምንም ሳልለወጥ፦ ዘንድሮዬ› አልፎ፥ በአዲስ ተቀየረ፤ ✔ፍሬ የማይወጣኝ፦ እኔን በመኮትኮት፥ እጆችህ ደከሙ፤ ✔እኔ ግን አለሁኝ፦ ዛሬም አልበቃኝም፥ በኃጢአት መታመሙ፤ ✔የቃልህን ውኃ በድንጋይ ልጅህ ላይ፦ ሳታክት ስታፈስ፥ ዘመን ተቆጠረ፤ ✔ወደ ልቤ ሳይሰርግ፦ ሕይወቴን ሳይለውጥ፦ እንዲያው ፈስሶ ቀረ፤ ✔ቃልህን ጠግቤ፦ እያገሳሁት ነው፥ ሌሎች እስኪሰሙ፤ ✔በቃልህ መኖር ግን፦ አልያዝህ አለኝ፥ ከበደኝ ቀለሙ፤ ✔ብዙ ጥቅስ አገኘሁ፦ ከቅዱስ መጽሐፍህ፥ ገልጬ አይቼ፤ ✔ከራሴ ላይ ብቻ፦ አንድ ጥቅስ አጣሁኝ፥ በበደል ተኝቼ፤ ✔ውጤቴ ደካማ፦ ትምህርት የማይሠርጸኝ፥ ተማሪ ብሆንም፤ ✔ይህችን ዓመት ተወኝ፦ ደግሞ ትንሽ ልማር፥ ታገሠኝ አሁንም፤ ✔እባክህ አልቆረጥ፦ በቅዱስ መሬትህ፥ ልቆይ ፍቀድልኝ፤ ✔ያፈሩት ቅዱሳን፦ የፍሬያቸው ሽታ፥ መዓዛ እንዲደርሰኝ፤ ✔የተሸከምከኝ ሆይ፦ ዛሬም ተሸከመኝ፥ አትሰልቸኝ አደራ፤ ✔ማን ይታገሠኛል፦ ጠላት እየሆንኩት፥ አይሠሩ ስሠራ፤ ✔አታውጣኝ ከቤትህ፦ ብዙ ቦታ አልይዝም፥ ፍሬ ስለሌለኝ፤ ✔ስፍራ የማያሻኝ፦ ቤት የማላጣብብ፥ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ፤ ✔ቦታስ የሚይዙት፦ ባለ ምግባሮቹ፥ ቅዱሳንህ ናቸው፤ ✔ልክ እንደ ዘንባባ፦ የተንዠረገገ፥ ተጋድሎ ጽድቃቸው፤ ✔ከሊባኖስ ዝግባ፦ እጅጉን የበዛ፥ ገድል ትሩፋታቸው፤ ✔እኔ አይደለሁም፦ ቦታስ የምትይዘው፥ የአንተው እናት ናት፤ ✔ሥሮቿ በምድር፦ ጫፎቿ በሰማይ፥ ሲደርሱ ያየናት፤ ✔ይቺን ዓመት ተወኝ፦ ከሥርዋ እሆናለሁ፥ ባፈራ ምናልባት፤... ✔ይቺን ዓመት ተወኝ፦ እባክህ አምላኬ፥ አንድ ዓመት ምንህ ናት፤ ✔ሺህ ዓመት አንድ ቀን፦ አይደለም ወይ ለአንተ፥ ዓመት ኢምንት ናት!፤ ✔ይሄ ዓመት አልፎ፦ ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ›፥ እስከምልህ ድረስ፤ ✔እባክህን ጌታ፦ ይቺን ዓመት ተወኝ፥ የወጉን እንዳደርስ!። •••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ☞ @EOTC2921 Channel ☞ @Ethio_Orthodox1 Group

የቅዳሴ ተሰጥኦ መቀበያ.pdf1.50 MB

🌻ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ፡12፤🌻 1፤እንግዲህ፥ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችኹን፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡የሚያሠኝና፡ሕያው፡ቅዱስም፡መሥዋዕት፡ አድርጋችኹ፡ታቀርቡ፡ዘንድ በእግዚአብሔር፡ርኅራኄ እለምናችዃለኹ፥ርሱም፡ለአእምሮ፡የሚመች፡ አገልግሎታችኹ፡ነው። 2፤የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ርሱም፡በጎና፡ደስ፡የሚያሠኝ፡ፍጹምም፡የኾነው፡ነገር፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ፈትናችኹ፡ታውቁ፡ዘንድ፡በልባችኹ፡መታደስ፡ተለወጡ፡እንጂ፡ይህን፡ዓለም፡አትምሰሉ። 3፤እግዚአብሔር፡ለያንዳንዱ፡የእምነትን፡መጠን፡እንዳካፈለው፥እንደ፡ባላእምሮ፡እንዲያስብ፡እንጂ፡ማሰብ፡ከሚገ፟ባ፟ው፡ ዐልፎ፡በትዕቢት፡እንዳያስብ በመካከላችኹ፡ላለው፡ለያንዳንዱ፡በተሰጠኝ፡ጸጋ፡እናገራለኹ። 4፤ባንድ፡አካል፡ብዙ፡ብልቶች፡እንዳሉን የብልቶቹም፡ዅሉ፡ሥራ፡አንድ እንዳይደለ፥ 5፤እንዲሁ፡ብዙዎች፡ስንኾን፡በክርስቶስ፡አንድ፡አካል፡ነን፥ርስ፡በርሳችንም፡እያንዳንዳችን፡የሌላው፡ብልቶች፡ነን። 6፤እንደ፡ተሰጠንም፡ጸጋ፡ልዩ፡ልዩ፡ስጦታ፡አለን፤ትንቢት፡ቢኾን፡እንደ፡እምነታችን፡መጠን፡ትንቢት፡እንናገር፤አገልግሎት፡ ቢኾን፡በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም፡ቢኾን፡በማስተማሩ፡ይትጋ፤ 8፤የሚመክርም፡ቢኾን፡በመምከሩ፡ይትጋ፤የሚሰጥ፡በልግስና ይስጥ፤የሚገዛ ፡በትጋት፡ይግዛ፤የሚምር፡በደስታ፡ይማር። 9፤ፍቅራችኹ፡ያለግብዝነት፡ይኹን። ክፉውን፡ነገር፡ተጸየፉት፤ከበጎ፡ነገር፡ጋራ፡ተባበሩ፤ 10፤በወንድማማች፡መዋደድ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ተዋደዱ፤ርስ፡በርሳችኹ፡ተከባበሩ፤ 11፤ለሥራ፡ከመትጋት፡አትለግሙ፤ በመንፈስ፡የምትቃጠሉ፡ኹኑ፤ለጌታ፡ተገዙ፤ 12፤በተስፋ፡ደስ፡ይበላችኹ፤በመከራ፡ታገሡ፤በጸሎት፡ጽኑ፤ 13፤ቅዱሳንን፡በሚያስፈልጋቸው፡ርዱ፤እንግዳዎችን፡ለመቀበል፡ትጉ። 14፤የሚያሳድዷችኹን፡መርቁ፥መርቁ፡እንጂ፡አትርገሙ። 15፤ደስ፡ከሚላቸው፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችኹ፥ ከሚያለቅሱም፡ጋራ፡አልቅሱ። 16፤ርስ፡በርሳችኹ፡ባንድ፡ዐሳብ፡ተስማሙ፤የትዕቢትን፡ነገር፡አታስቡ፥ነገር፡ግን፥የትሕትናን፡ነገር፡ ለመሥራት፡ትጉ። ልባሞች፡የኾናችኹ፡አይምሰላችኹ። 17፤ለማንም፡ስለ፡ክፉ፡ፈንታ፡ክፉን፡አትመልሱ፤በሰው፡ዅሉ፡ፊት፡መልካም፡የኾነውን፡ዐስቡ። 18፤ቢቻላችኹስ፡በእናንተ፡በኩል፡ከሰው፡ዅሉ፡ጋራ፡በሰላም፡ኑሩ። 19፤ተወዳጆች፡ሆይ፥ራሳችኹ፡አትበቀሉ፥ለቍጣው፡ፈንታ፡ስጡ፡እንጂ፤በቀል፡የእኔ፡ነው፥እኔ፡ብድራቱን እመልሳለኹ፡ይላል፡ጌታ፡ተብሎ፡ተጽፏልና። 20፤ጠላትኽ፡ግን፡ቢራብ፡አብላው፤ ቢጠማ፡አጠጣው፤ይህን፡በማድረግኽ፡በራሱ፡ላይ፡የእሳት፡ፍም፡ትከምራለኽና። 21፤ክፉውን፡በመልካም፡አሸንፍ፡እንጂ፡በክፉ፡አትሸነፍ። 🙏✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞🙏

•✞✞✞ #እመቤቴ_ስልሽ ✞✞✞• እመቤቴ ስልሽ ነይልኝ ለልጅሽ፣ ቅረቢኝ በህይወቴ እናቴ ስጠራሽ፡፡/፪/ #አዝ••••••• ኑሮዬ ተዛብቶብኝ ደክሜኣለሁ እናቴ፣ እኔን ቅረቢኝና ልፅናና በህይወቴ፣ በደሳሳ ጎጆዬ በቤቴ ገብተሽልኝ፣ በኔ የነገሰውን ሀዘኔን ለውጪልኝ፡፡ #አዝ••••••• እሻለሁ ፍቅርሽን እናትነትሽን፣ ዘወትር ከጎንህ ነኝ ብለሽ አረጋጊኝ፣ ስምሽን ለዘላለም እጠራለሁኝ እኔ፣ ለመንገዴ መሪ ነሽ ለአይኔ ብርሃኔ፡፡ #አዝ••••••• በድቅድቁ ጨለማ እኔ እንዳልወድቅብሽ በቀኝ እና ከግራ ደግፊኝ እባክሽ፣ ኑሪ ከልጅሽ ጋራ እመአምላክ በዘመኔ፣ አደራ አትራቂኝ ጠበቃ ሁኝ ለኔ፡፡ #አዝ••••••• ከኔ ጋራ ስትሆኚ ድምፅሽም ያፅናናኛል፣ ከሀዘን ከትካዜ እናቴ ያስረሳኛል፣ በኖርሁበት ኑሪልኝ በምጓዝበት ሁሉ፣ የአንድዬ እናት ስጠራሽ ነይ ቤዛዊተ ኩሉ፡፡ #አዝ•••••••