HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
Відкрити в Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
Показати більше2 273
Підписники
+424 години
+127 днів
+2530 день
Архів дописів
በመምህር ተስፋዬና በሊቁ ስሙር አላምረው መካከል የተፈጠረው ምንድነው? አራት አይና ሆኜ አጋንንትን ማውጣት ለምን አቃተኝ? አጋንንትን ማስለፍለፍ በጣም ተራ ነገር እኮ ነው!!
https://youtu.be/DtCeoz1E03k?si=q8d7Onr1FARK6vDX
መምህር ተስፋዬ ለሶፎኒያስና ቤተሰቦቹ ያስተላለፈው ጥብቅ መልዕክት!! የሴት ዛር ዓይነጥላ ወንዶች ላይ ሲታድር 5 ምልክቶች ታሳያለች ይኼንን አስተውሉ!! #ንቁ https://youtu.be/sIr0MciCdus
ዛሬም ሌላ ትኩሳት! ወላጆች እባካችሁን ልጆቻችሁን ተከታተሉ ጠብቋቸው!! መፍትሔ ሥራይ ከ80 አሀዱ መጽሐፍት አንዱ ነው ተባለ!! #መተት #ጸሎት #አጋንንት https://youtu.be/pxmghQd-b0Y?si=4EIeX6MwFV47IV8r
++ ዐዲሲቷ አማናዊት መቅደስ ወደ ቤተ-መቅደስ ++
ዓመተ ኲነኔ [ዓመተ ፍዳ] ሊፈጸም፣ ዓመተ ምሕረት ሊተካ ፲፭ ዓመት ሲቀረው ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተራራ ተወለደች። ከእናት ከአባቷ ጋር አልከራረመችም። የስእለት ልጅ ናትና ኢያቄምና ሐና "ሆዷ ዘመድ ሳይወድ፥ አፏ ምግብ ሳይለምድ ወደ ቤተ መቅደስ እናስገባት" ተባብለው ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሲሆናት ቤተ መቅደስ አስገቧት። ለመለኮት ማኅደር ልትሆን የተገባት አማናዊቷ ቤተ መቅደስ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባች።
ክቡር ዳዊት አስቀድሞ፦ "ርሥዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ፤ እስመ ፈተወ ንጉሥ ሥነኪ - ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሽ። ንጉሥ ውበትሽን ወድዷልና። [መዝ ፵፬፥፲] ብሎ እንደተናገረላት የአባቷን ቤት ልትረሳ የተገባት ሆነ። ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት ምክንያት ልትሆን በአምላክ ኅሊና ታስባ የኖረች ድንግል ማርያም ታኅሣሥ ፫ ቀን መባዕ ሆና ተሰጠች። "እበውዕ ቤተከ ምስለ መባዕየ። ወእሁብ ብፅዓትየ ዘነበብኩ በአፉየ። ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ - መባዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ። በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርኩትን÷ በከንፈሮቼም ያልሁትን ስእለቴን ለአንተ እሰጣለሁ።" እንዲል [መዝ ፷፭፥፲፫]
በዚያ በቤተ መቅደስም መልአኩ ሰማያዊ ምግብ እየተመገበች ፲፪ ዓመት ኖረች። በዚህ ዕድሜዋ ከእናት ከአባቷ ፍቅር መለዬት ምን ዓይነት ድንቅ ነው። እንዴት ያለስ አሳዛኝ ነገር ነው። መልአኩ ሰማያዊ ምግብና ሰማያዊ ሲመግባት ደግሞ የደስታችን ጽዋዕ ይመላዋል።
"የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና፤
ወያሥተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልኅቀትኪ በቅድስና፤
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሤስየኪ መና፤
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና።" እንዲል (ማኅሌተ ጽጌ)
የሀገረ ብሕንሳው ሊቅ አባ ሕርያቆስ፦ «ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሳዶን። አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ፦ ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ።» ሲል ያደንቃል። (ቅዳሴ ማርያም)
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አማናዊት ቤተ መቅደስ መሆኗን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ «መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕለ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ።» (ውዳሴ ማርያም ዘእሑድ) የእመቤታችን የእመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ረድኤት በረከት አይለየን። ምልጃዋ አይራቀን። አሜን።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.facebook.com/hailegebrieltube2021
https://www.tiktok.com/@walkinaddistv
የቆሎ ተማሪው በተዋረሰው መንፈስና አጋንንት የተፈጠረውን ጉድ ተመልከቱ!! የአርቲስቱ ቤተሰብ ላይ የተፈጸመ አሳፋሪ ተግባር!! #አጋንንት #ተግባር #አሳፋሪ! https://youtu.be/OpTNlBy6lz4
ይኼንን ምስጢርና ጥበብ ስላልተረዳን ለብዙ ዘመናት ከስረናል ጠፍተናልም!! ሴቶች ይኼንን ጸጋችሁን ከተጠቀማችሁ የማትቀይሩት ነገር የለም!! #ሴቶች #ጸጋችሁን! https://youtu.be/mVH9F7LHsPY
ከምን ዓይነት ሰው መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ..?? ዝሙትን አቅልለህ እንድታየው ከሚያደርግህ ሰው..
በጣም በዝሙት ሕይወት ውስጥ ያለ ሰው ቢኖር ብትችል እንዲወጣ ንገረው ካልሆነ ግን አንተ ደግሞ እንዲህ ካለው ሰው ራቅ.. ቀስ በቀስ አንተም እየተላመድከው ትሄዳለህና.. አልያም አንተ ራስህን እንደ ንጹህ ማየትም ትጀምራለህና..
በወሬህ መሃል ዝሙትን እንደ ቀልድም ቢሆን ቀላል አድርገህ ብዙም አታውራበት.. ተጸየፈው.. ለሰይጣን እድል አትስጠው..
ቆነጃጅት ለእናንተም ነው👊😁
እግዚኦ! ታዋቂው ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ የገጠመው አስደንጋጭ ጉዳይ!! ወላጆች ከምንም ጊዜ በላይ ልጆቻችሁን መጠበቅ አለባችሁ!! ጎንደር ላይ የተከሰተው ምንድነው?? https://youtu.be/GJcqzlQTn24
ብቻዬን መቁረብ እችላለሁ ወይ ባለቤቴ ፍቃደኛ ስላልሆነ ምንስ ላድርግ? ከሰዎች ክፋትንና ተንኮልን የተማሩ መናፍስቶች! ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ምንም አልቀበልም ለምሉ ይድረስ!
https://youtu.be/Hgl8D5uAJpw?si=jNnBkLAkQ4bO9khI
መምህር ተስፋዬ ለድርሹ ዳና ጥያቄና ገጠመኟ የሰጠው አስገራሚ መልስ!! ምስቶች በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳብ ልትሰጡ ይገባል!! ጠንቋይ የሚገናኛቸው ሴቶችና መዘዙ!! https://youtu.be/MLJMu1n9sV8
ኅዳር ፳፱ /29/
በዚችም ዕለት የተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ (የሰማዕታት መጨረሻ) የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት። ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው። ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ጴጥሮስ" አለችው።
ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ። ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ጴጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት።
ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር᎓᎓ ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ᎓᎓
አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው። ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ። ብዙ ተአምራትንም ሠራ። በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ጵጵስናው ላይ አልተቀመጠም:: በኋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ።
ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ። በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ። ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ። ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ። ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
https://www.tiktok.com/@walkinaddistv
ዲያቆን ዮርዳኖስ ከ666 አባል የደረሰው አሳዛኝ መልእክት! አርትስት ሰሎሞን የመኪና ተሸላሚ ሆኑ! አንደበታችን በሰዎች ላይ የሚፈጥረው ጠባሳ! #666 #ጸሎት
https://youtu.be/mep8APaRQ9I?si=L6Dp7RDr0B-v0upj
ለረጅም ጊዜ ጸልዬ ሰግጄ ንስሐም ገብቼ አንዳች የሆነልኝ ነገር የለም!! እግዚአብሔር ረስቶኛል ዝምብዬ እደክማለሁ ለምንል!! ጸሎተን እግዚአብሔር አይሰማውም!!
https://youtu.be/hp1C6AgX1mI
መስገድ ስትጀምሩ የሚያደፍጡ መንፈሶችን እንድጋለጡ ለማድረግ!! ክፉ ትውልድ ቶሎ አይገባውም እኛም እንዲህ ሆነናል!! ውሃና እሳት ላይ የወደቀ ትውልድ! #ጸሎት https://youtu.be/wAFDQz82FwI
መምህር ተስፋዬ ማንም የማይነግራችሁን ምስጥር ይነግራችኋል አዳምጡት!! ኢቫን የእውነት ታማለች ጓደኞች ድረሱላት! ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ቤት ብቻ አይደለችም!
https://youtu.be/WCk-AzsnW34?si=8Oz1XdLLoUvZ3Zvi
ሞጣ ቀራኒያ ስለ መምህር ግርማ ወንድሙ የሰጠው አስገራሚው ምስክርነት!! ባሎችን አጥበቀው የሚጠሉ 3ቱ ክፉ መናፍስቶች!! ለአዶናይ የተላለፈ ወንድማዊ ምክር!! https://youtu.be/CdxcjeAqTiM
«ወንድምህን አትናቀው»
ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል። "እንዴት?" ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
